በከንባታ ጠንባሮ ዞን ተቃውሞ ያነሱ ወገኖች ወደ አዲስ አበባ እና አርባ ምንጭ የሚወስደውን መንገድ ዘጉ

በደቡብ ክልል፤ ከከምባታ ጠምባሮ ዞን ወደ አዲስ አበባ የሚያቀናው መንገድ ዛሬ ዝግ ሆኖ ዋለ:: የደቡብ ብሔሮች ብሔረሰቦች ሕዝቦች ክልል መንግሥት ምክር ቤት ባለፈው ሳምንት ማገባደጃ ላይ በሐዋሳ ያከናወነው 8ኛ መደበኛ ጉባኤ ላይ የወረዳ ጥያቄ ተነስቶ፤ ለተወሰኑ ቦታዎች ሲፈቀድ ለ እኛ አልተፈቀደም በሚል ነዋሪዎቹ ተቃውሟቸውን እንደጀመሩ የአካባቢው የዜና ምንጮች ይገልጻሉ::

በከባታ ጠንባሮ ዞን ባሉት 7 ከተሞች ውስጥ ትናንት እና እና ከትናንት በስቲያ ተቃውሞ ሰልፎች ሲካሄዱ የቆዩ መሆኑን የገለጹት ምንጮች በተለይም በከምባታ ጠምባሮ ዞን የወረዳ ጥያቄ ያነሳችው አዲሎ ቀበሌ ትናንት፣ በጠምባሮ ወረዳ ደግሞ ከትናንት በስትያ ሰልፍ ነበር ያሉት የዜና ምንጮች በዛሬው ዕለት ተቃውሞው ወደ መንገድ መሸጋገሩን አስረድተዋል:

በመሆኑም ጠምባሮ ከተማ ጠምባሮ ከተማ አስተዳደር እንዲሆን ጥያቄ ያቀረቡት ነዋሪዎች በአዲሎ ቀበሌ መንገዶች መዝጋታቸው እና ወደ አዲስ አበባ የሚያቀናው መንገድ ይህ ዜና እስከተጠናቀረበት ጊዜ ድረስ አልተከፈተም:: ይህም ብቻም ሳይሆን ወደ አርባ ምንጭ የሚያሻግረው መንገድ ም በዛሬው ዕለት በተቃውሞ አቅራቢዎቹ ተዘግቷል::

ሦስተኛ ቀኑን በያዘው ተቃውሞ መንገዶች ቢዘጋጉም ምንም ዓይነት በሰውም ላይም ሆነ በንብረት ላይ የደረሰ ጉዳት እንደሌለ የሚገልጹት ምንጮች የፊታችን ቅዳሜ በመላው ከንባታና ጠንባሮ ዞን ከፍተኛ ተቃውሞ ሰልፍ ለማድረግ ቅስቀሳ እየተደረገ መሆኑን ነግረውናል::

በደቡብ ኢትዮጵያ ከምባታ ጠምባሮ ዞን በተለያዩ ጊዜያት ከከፍተኛ የትምህርት ተቋማት የተመረቁና ሥራ ያጡ ወገኖች ባለፈው ሳምንት በሰላማዊ ሰልፍ ጥያቄ ሲያቀርቡ በፖሊስ እንደተቀጠቀጡ ዘ-ሐበሻ ዘግቦ እንደነበር ይታወሳል::

https://www.youtube.com/watch?v=LCftg3owFj4&t=4s

ተጨማሪ ያንብቡ:  « ፀሎታችን በቤታችን » የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ እምነት ተከታዮች የፀሎት ቦታ እና የመቃብር ስፍራ ጥያቄ በሳውዲ አረቢያ ።
Share