June 24, 2021
6 mins read

ምን ይባላል ? መንፏቀቅ ወይስ መንፈቅፈቅ !! -ማላጂ

ድመት መንኩሳ ዓመሏን አትረሳ እንዲሉ አበዉ ሰሞኑን የትህነግ እና ተባባሪ አገር አፍራሽ መሰሪ ቡድኖች የጎንደር እና ወሎ ግዛት  አካል የሆኑትን የትግራይ አዋሳኝ አካባቢዎች የይገባናል ጥያቄ እንዳገረሸባቸዉ እየተሰማ ነዉ ፡፡

በማንኛዉም መመዘኛ የሚጠቀሱት  የጎንደር (ወልቃይት) እና የወሎ (ራያ) የትግራይ ክፍል ካለመሆኑም በላይ በተፈጥሮ ፣ በሠዉ ሰራሽ  ድንበሮች ፣የወሰን ምልክቶች  ከሚገለጡበት በላይ የዉጭ ፀሃፍት ሳይቀሩ የዚህን ዕዉነታ በማያሻማ ሁኔታ ገልፀዉታል፡፡

ነገር ግን በዉስጥ እና በዉጭ ያሉ ቅጥረኛ ብሄራዊ ጠላቶች ለኢትዮጵያ እና ህዝቧ ካላቸዉ ስር የሰደደ ጥላቻ እና ንቀት ባነቀዘዉ የጥፋት መልዕክተኝነት በጎንደር እና ወሎ የሚገኙ ለግብርና ስራ ምቹ የሆኑትን የኢትዮጵያ ግዛት መሬቶች በጉልበት ተነጥቀዉ  ከሶስት አሰርተ ዓመታት በላይ በዘረፋ አስተዳደር መቆየታቸዉን እያወቁ አይናቸዉን በጨዉ የታጠቡ ከሀዲዎች ዛሬም እንደትናንቱ የአዞ ዕንባ የሚያነቡ መሆናቸዉ ያስተዛዝባል፡፡

ነባሩ እና የአገር ባለቤት የሆነዉ ኢትዮጵያዊዉ ከትዉልድ አገሩ በተለያየ ምክነያት ርቆ በፍርደ ገምደል የግፍ አስተዳደር ማንቱን እና ሰርቶ የመኖር መብቱን እንዲያጣ ለተደረገዉ ህዝብ ይቅርታ እና ከሳ ሲገባዉ ለዳግም ጥፋት ዳር ዳር ለሚሉት ኢትዮ-ጠል ጠላቶች  ምኞት  አፈር የነካ ስጋ እንደሆነ አለማወቃቸዉ አይገርምም ፡፡

የጥላቻ ገርሻት ባቀረሻቸዉ ቁጥር መንፏቀቅም ሆነ ዉሃ እንደፈጀ ንፍሮ መንፈቅፈቅ  እንዲያዉ  ሆድ ለበሰዉ ማጭድ አትስጠዉ የሚለዉን በሂል እነርሱ በህዝብ ላይ የትላቻ እና የበቀል አንክርዳድ መዝራታቸዉን ለማቆም አለመቻል ላልበላዉ ጭሬ ላጥፋዉ ከመሆን ዉጭ ከንቱ መታከት ነዉ ፡፡

የአገር አንድነት እና የህዝብ አብሮነት ሠላም የሚነሳቸዉ ታሪካዊ ጠላቶች በሚችሉት ሁሉ የኢትዮጵያን  የግዛት  ሉዓላዊነት ማዳከም ስለሆነ እና ይህም አብሯቸዉ የተፈጠረ ስለመሆኑ የዛሬዉ የጥፋት ሩጫቸዉ ማሳያ ሲሆን ምንም እንኳ ብዙ የተለያዩ ታሪካዊ ፣ነባር እና ወቅታዊ ማስረጃዎች ቢኖሩም እ.ኤ.አ. 2004 Matthew J. MacCracken

የተባለ የዉጭ አገር ፀሃፊ ስለ ጠላት ስግብግብነት እና የአገር ጠላትነት ከጻፈዉ እና በገፅ 185 ከሚታየዉ በጥቂቱ እንደሚከተለዉ ለማቅረብ ወደድኩ፡፡

ሁሉም ዓለም ዕዉነቱን እንዲያዉቅም ፈለኩ እነሆ ፡፡ እነርሱም ሆነ ተባባሪ አደናጋሪ  የዚህን ፅሁፍ ሙሉ ይዘት እንዲያዩት ስንጠይቅ  ስለማያዉቁት ሳይሆን ዕዉነታዉን  ከመካድ እንዲታቀቡ ይረዳቸዋል፡፡

ከዓለም በፊት የነበረች ጥንታዊት ሀገርን  የግዛት ወሰን ወርድ እና ቁመት ከእኛ ዉጭ ላሳር ለሚሉ ሰብሰብ በሉ ልንላቸዉ ይገባል ፡፡

ይህን የኢትዮጵያ  ጉዳይ በማንበብ ለሚያይ  እና ለሚረዳ በየትኛዉም የኢትዮጵያ ዘመነ መንግስት ያልተጻፈ ትልቅ ዕዉነታ ሆኖ“ በኢህዴግ ” ዘመነ መንግስት በራስ አገር መንግስት በአንድ ሉዓላዊት አገር ላይ የተፈፀመ የአገር ክህደት ድርጊት መሆኑን እና የሉዓላዊነት ዘረፋ የተከናወነበት ስርዓት መሆኑን ፀኀፊዉ ሲገልፅ ከየትኛዉ  የህብረተሰብ ክፍል(ብሄር) እንደሚመድቡት ግን አላዉቀም ….ምን አልባት ነጭ ትምክተኛ፣ ፀረ…..፣ነፍጠኛ…..ብቻ እንጃ የሆነ ነገር እንደሚሉት እገምታለሁ ፡፡ ክፉ በማድረግ  የሚደሰቱ  ስም ማክፋት ስለማይሳናቸዉ እና የዚህ ችግር ስሌለባቸዉ ይህን ፅሁፍ ለሚመለከቱ “ኢትዮ -ጠል  ” ፀሃፋን ምን እንደሚሉት እንጠብቃለን ፡፡ የለዉጥ ደጋፊ እንዳይሉት ……፡፡

“TPLF dominated EPRDF intentionally include article 39 in 1994 Ethiopian constitution so that Tigray region could loot Ethiopia’s resources using Ethiopian military to expand the boarder of Tigray and then secede from Ethiopia.”

It has been clearly cited on TPLF manifesto drafted in 1976 stating ‘The Republic of greater Tigray’.

The main purpose of this manifesto is planning of:-

  • Re demarking Tigray’s boarder expanding the region boarder in to Ethiopia and ,
  • Acquiring costal land with in Eritrea;
  • Seceding as independent nation.

“Tigray region was successfully annexed fertile lands from Wollo and Gondar with in Ethiopia.”

ምንጭ ፡ “Abusing self-determination & democracy: how TPLF is looting Ethiopia.”

Matthew J. MacCracken

ማላጂ

 

አንድነት ኃይል ነዉ !!

Unity is strength!

 

 

 

 

Leave a Reply

Your email address will not be published.

Go toTop