የሌለ ፓርቲ እንዴት ምረጡኝ ብሎ ይቀሰቅሳል? – ይነጋል በላቸው

ይነጋል በላቸው (yinegal3@gmail.com)

“አንበሣ ምን ይበላል?” ቢሉ “ተበድሮ” – “ምን ይከፍላል?” ቢሉ “ማን ጠይቆ!” የምትለዋን አባባል “እውን ደርግ አለ?” ከምትለዋ የኮሎኔል መንግሥቱ ኃ/ማርያም ታዋቂ ንግግር ጋር በቀብድነት ላስይዝና ህጋዊም ሆነ ሞራላዊ ሕይወት ሳይኖረው በድርቅና ብቻ… በጉልበት ብቻ … አንድ ሰውና ጥቂት አጋፋሪዎቹ ሁሉን ነገር ስለተቆጣጠሩ ብቻ ያለ መስሎት ሳይኖር ምረጡኝ ስለሚለው “ፓርቲ” ትንሽ ላውራችሁ፡፡ መንጌ መለዮኣቸውን ያወለቁ ደርጎችን እንደአዲስ ሰዎች ቆጥሮ ነበር “እውን ደርግ አለ?” ያለው፡፡ ለጠቅላላ ዕውቀታችን ያህል ደርግ ራሱ ነበር ሰደድን፣ ኢማሌድኅን፣ ኢሠፓአኮንና ኢሠፓን አልፎ ኢሕዲሪ የሆነው፡፡

ከህጋዊ አሠራር አኳያ እኔ እንዳለ የማልቆጥረው ራሱን “ብልጽግና” ብሎ የሚጠራው ፓርቲም ልክ እንደደርግ ነው፡፡

በነገራችን ላይ ደርግና ተተኪው ሕወሓት በማስመሰል ድራማ ብዙውን ጊዜ የተዋጣላቸው ነበሩ – “የተዋጣላቸው” የሚለው ገላጭ ቢከብድባቸውም ከነዚህ ጅሎች ጋር ሲወዳደሩ ግን በአንጻራዊነት ደህና ነበሩ ማለት ይቻላል፡፡ የነዚህን የአክራሪ ኦህዲድ ሸኔዎች የድንቁርና ደረጃ ለመግለጽ’ኮ ቃል የለኝም፡፡ ድርቅናቸው ፍጥጥ ያለና ምንም ወዝ የሌለው ነው፡፡ በጉልበት ማሰብን እያስተማሩ ያሉ ገልቱዎች ናቸው፡፡ መጪው ትውልድ ከነዚህ ተምሮ ሀገሪቱን እንዴት በጉልበት እያዳፋ መቀመቅ እንደሚከታት አንድዬ ይሁነን እንጂ መገመቱ አይከብድም፡፡ ማስመሰልን እንኳ አለመቻል ትልቅ የድድብናና የዕብሪት ምልክት ነው፡፡

ኢሕአዲግ ሲመሠረት በዐዋጅ ነበር፡፡ ትያትሩ የተሟላ ገቢርና ፆታ ነበረው፡፡ በመልክ በመልክም ነበር የሚተወነው፡፡ ተግባር ላይ እንጅ ድራማዊ ክንዋኔው ላይ የሚስተዋል ብዙም ህፀፅ አልነበረም፡፡ ከምሥረታው ጊዜ ጀምሮ በየጊዜው የጠቅላላ አባላት ጉባኤ ያካሂዳል፤ የማዕከላዊ ኮሚቴና ተለዋጭ የማ. ኮሚቴ አባላት ምርጫዎች ያደርጋል፤ ሊቀ መንበሩንና ምክትሎቹን፣ የኦዲት ኮሚሽን አባላትን፣ የፖሊት ቢሮ አባላት፣ የየክፍሎች ዋናና ምክትል ሊቃነ መናብርት ምርጫ፣ በየተወሰነ ጊዜ የማዕከላዊና የፖሊት ቢሮ ስብሰባዎች ወዘተ. እንደሚካሄዱና ለሕዝብም ይፋ እንደሚደረጉ አስታውሳለሁ፡፡ ትያትሩ ቅጥ ያለው ነበር ለማለት ነው፡፡

ተጨማሪ ያንብቡ:  አርበኞች ግንቦት 7 በአዲስ አበባ ዋና ዋና አደባባዮች ቅስቀሳ ሲያደርግ ውሏል

ብልጽግና ግን አንዴ ብቻ አዋሳ ላይ ይሁን አሰቦት ላይ ኮምሬድ(ጓድ) ናፖሊዮን (የእንስሳት ዕድር የተሰኘውን መጽሐፍ ያስታውሷል) ብልጽግናን መሠረትን አለ – ከዚያ በኋላ የአማራ የለ የኦሮሞ የለ  (በዱሮው አገላለጽ እንዳልጠቀም ከሳሽ ካለ ብዬ ነው) ሁሉም ዝም ዝም ሆነና መቼም ስም አይገዛም በደፈናው “ብልጽግና” በአንዳንድ ነገረኞች ደግሞ “ብልግና” እየተባለ ሕዝብና አባላት ተብዬዎቹን ማወናበዱን ቀጠለ፡፡ እንደማውቀው የዚህ “ፓርቲ” ጠቅላላ ስብስባ፣ የማዕከላዊ አባላት ማንነትና የሚያካሂዱት መደበኛም ይሁን ኢመደበኛ ስበስባ፣ የአባልነት ምልመላ፣ ዋናም ይሁን ምክትል የአመራሮች ምርጫ፣ አስቸኳይም ይሁን መደበኛ የአባላት ጠቅላላ ጉባኤ ምንትስ ቅብጥርስ አንድም የለም ወይም ተካሂዶም ከሆነ እኔ አላውቅም፡፡ ብቻ ብልጽግና ፓርቲ እየተባለ ሲጠራና ለምርጫ ሲዘጋጅ አያለሁ፡፡ “ሞኝ እንዴት ያሸንፋል?” ቢሉ “እምቢኝ ብሎ!” ይባላል፡፡ ህግ ቢኖር እነሱም የሉም ነበር፡፡

ሌላው ችግር ይሄው ፓርቲ ተብዬ መጪውን የግንቦት ወር 2013 “ምርጫ” በቁጥጥሩ ሥር ካደረገ በኋላ በካፈርኩ አይመልሰኝ የሚያካሂደው የምረጡኝ ዘመቻ ነው፡፡ ይህን ሁሉ ወጪ የሚከሰክሰው ለምንድን ነው? ከወዲሁ ያሸነፈውን ምርጫ ምረጡኝ ሲል አለማፈሩ የራሱ ጉዳይ ነው እንበልና ለዚህ ቅስቀሳ የሚረጨው ገንዘብ ስንትና ስንት ሀኪም ቤቶችንና ትምህርት ቤቶችን ማሳነጽና ማደስ ይችል አልነበረምን? ድሃ ሕዝብ ጫንቃ ላይ ፊጥ ብሎ በድሆች ገንዘብ መቀናጣት ወንጀልም ነውርም አይደለምን?

ከዚህ በተያያዘ በብዙ አሥራዎች የሚቆጠሩት እንደአሸን የፈሉት ሌሎቹ “ፓርቲዎች”ም በሀገራችን የሥራ አጥ ቁጥርን መብዛት ከመጠቆም ባሻገር አንድም ፋይዳ የላቸውም፡፡ በኢትዮጵያ የፓርቲ ጋጋታ የሚያሳየው ብቸኛ ቁም ነገር ሰዎች ሥራ ሲፈቱና መተዳደሪያ የሚሆን የገቢ ምንጭ ሲያጡ በቀላሉ  እንጀራ የሚያገኙት ፖለቲካ ውስጥ ሲገቡ መሆኑን ነው፡፡ የአሁኑ ፖለቲካ ደግሞ ለዚህ አመቺ ነው፡፡ ምክንያቱም ዕድሜ ለወያኔ ይህን የዘር ፖለቲካ አምጥቶ በተነው በዚያ ማዕቀፍ እየገቡ ሰማንያውን ነገድ በአራት እያባዙ ከ320 በላይ ፓርቲ በማቋቋም ሕዝብን ማራኮት እንደፋሽን ተወስዷል፡፡ የኢትዮጵያ ሕዝብ አድጎና በልጽጎ እነዚህን ሥራ አጦች አስቀምጦ በነፃም ቢሆን ደሞዝ ቢከፍልልን ትልቅ ግልግል ነበር፡፡ እንደሚታወቀው ገንዘብ ጠቃሚ የመሆኑን ያህል ጎጂም ነው፡፡ አፍቅሮተ ንዋይ የተጠናወተው ሰው በመጀመሪያ ኅሊናውን ባወጣ ይቀውረዋል፡፡ ከዚያ ገበያ አውጥቶ የማይቸበችበው ነገር የለም፡፡ ኅሊናቢስነት ደግሞ ሀገርንና ሕዝብን ብቻ ሣይሆን የገዛ ልጅንና ሚስትን፣ እናት አባትንና ወንድም እህትን ሳይቀር ያሸጣል፡፡ እንግዲህ በትምህርትም በዕውቀትም በልምድም ያልገፋ ምድረ የአእምሮ ድሃ ሁሉ ወደዚህ ክልክል የሌለበት ነፃ የፖለቲካ ቀጣና እየገባ ሀገራችንን የሚያምሳት የሆድ ጥያቄን ለመመለስ መሆኑን መረዳት ይኖርብናል፡፡ ሀገራችን ህጋዊና ሕዝባዊ መንግሥት ቢኖራት ኖሮ ቢያንስ እንደሌሎች ሀገራት በዘርና በሃይማኖት የመደራጀትንና ፓርቲ የመመሥረትን ጠንቀኛ አካሄድ በህግ ይከለክልልንና በዚህ አቅጣጫ የሚመጣብንን ከባድ አደጋ ያስወግድልን ነበር፡፡ እኛ ግን ለዚያ አልታደልንም፡፡ ከዚሁ መሪር እውነት ጋር በተያያዘም የዲያስፖራው ኑሮ ያንገሸገሸው አሰለጥና  ሞሽላቃ ሌባ እዚያ ያጣውን በጎሣና በሃይማኖት የመደራጀት መብት እዚህ እየመጣ ከጠማማው ህገ መንግሥት ይህን አስጠሊታ መብት ተብዬ ያገኝና ከላይ እስከታች ያምሰናል – አንዳች ነገር ያምሰውና፡፡

ተጨማሪ ያንብቡ:  Recruiting Assistant

 

2 Comments

  1. -ምርጫው በህዝባችን ጠንካራ አልበገሬነት እና በምርጫ ታዛቢዎች ያላሰለሰ ጥረት ሊሳካ ይችላል። ተስፋ የሚያስቆርጥ ቢመስልም ምርጫው ህዝቡ ቀን ከሌሊት በአቅራቢያው ያሉትን የምርጫ ጣቢያዎች ነቅቶ ከአጭበርባሪዎች ወይም ከደጋጋሚ መራጮች ከታደገ እና የምርጫ ታዛቢዎችን ሞራል አለንላችሁ በማለት ከደገፈ ሊሳካ ይችላል። ነገ ከቤት ንብረትህ እየተጎተትክ በቸርችል ጎዳና ፣ በመስቅል አደባባይ እና በቦሌ መንገድ የምትጣል አዲስ አበቤ ይህ ከመሆኑ በፊት የምርጫ ጣቢያዎችን ከበህ ከመጤ ሰርጎገቦች ተደጋጋሚ መራጮች ምርጫህን የሞት የሽረት ተጋድሎ አድርገህ ጠብቅ። ከአሁኑ ተስፋ አትቁረጥ ፤ ባልደራስ በፋራም በአራዳም ብለን እንነሳ። መታወቂያ ሲታደል የምትነግረን የወረዳ እና የቀበሌ ሠራተኞችን በሙሉ ከሥራ አባርረው አዲስ አበባን እንደ አጣዬ እንዳያጋይዋት ቀን ከሌሊት የምርጫ ጣቢያ መግቢያ መንገዶችን እንቆጣጠር።

    – ካልተቻለም የምርጫ ጣቢያዎች መግቢያ መንገዶችን በነቂስ ወጥተን እንዝጋቸው ። መግቢያ መውጫ ከታጣ ወደ ምርጫ ጣቢያዎች የሚያስገባ መንገድን በመዝጋት ህይወታችን ይተርፋል፤ የሽግግር መንግሥት ይቋቋማል።
    በየክልሉም የምርጫ ጣቢያዎች መንገዶች ከተዘጉ ፤ ሰላሳ አንድ ሚሊየን መራጭ የመዘገበው የብልፅግና መንግስት በቂ መራጭ ህዝብ ለምርጫ ስላልወጣ በሚል በፎርፌ እንደሚሸነፍ እና የሽግግር መንግስት ለማቋቋም እንደሚገደድ እወቁት። መንገድ ሲዘጋብን አመታት ስላሳለፍን አዘጋጉ አይጠፋብንም። ለመንገድ ዘጊዎች ሶስት አመታት መንገድ ሲያዘጉ ለከረሙት እኛም የኢትዮጵያ ህዝቦች በህዝባዊ ውሳኔ በየክልሉ በህዝባዊ እምቢተኝነት መንገድ መዝጋቱን እንደምንችልበት እናሳያቸው። በካርድ ብቻ ሳይሆን ምርጫችንን የምናሳውቅ ፤ መንገድ በመዝጋት እና ምርጫ ለመምረጥ ጨርሶ በአለመውጣት ሊሆንም ይችላል። በህዝበ ውሳኔ ብቻ!!

    በምርጫ ቀናት በኢትዮጵያ በሙሉ በየክልሉ የምርጫ ጣቢያ መንገድ ከተዘጋ አንድ ጥይት ሳይተኮስ ድል ለዲሞክራሲ!!

  2. ይነጋል እስቲ ነገሩን በዚህ በኩልም እናጢነው ሰሞኑን በመራራ ጉዲና አማካይነት ሾልኮ የውጣው አቤቱታ ለአሜሪካው አምባሳደር ግርምት የሚፈጥር ነው። ስር በስር የሚሰራውን የተገነዘብነው አልመሰለኝም። ማለቃችን ምንም የማይመስላቸው ለከፍተኛ እልቂት ዜጋን ያዘጋጁ እነ አቶ መራራ ጉዲናና አህመዲን ጀበል ኡስታዝ አቡብከርን የመሳሰሉ ብዙ ተከፋዮች ሰውነታቸው ከእኛ ጋር ሁኖ ልባቸው ወይ ግብጽ ወይ ጀርመን የሆኑ ሰዎች ስለበዙ ነገርን በጥንቃቄ ማየት መልካም ይመስላል።
    በድን ነው ብአዴን ስለሚሉት ልጽፍ ፈልጌ መልሼ ተውኩት እነ ሽመልስና ታየ ደንዳ በሚጋልቡት አገር አንዳንዴ ውሀ ማፍሰስም መልካም ነው። መቼም ካንተ በላይ አውቄ ሳይሆን ፍርሀት ቢገባኝ ነው። ከድር ሰተቴ የሚሰጥህን መልስ እጠብቃለሁ ሰላም ክረም።

Leave a Reply

Your email address will not be published.

Share