የእንባ ጠብታ – እኔንያየህተቀጣ

በፈረንጆች አቆጣጠር ኦክቶበር 8, 2018 ከምሽቱ ከምሽቱ አራት ሰዓት ሆኗል:: ከሁለት ወራት የአዲስ አበባ ቆይታ በሁዋላ ወደሰሜን አሜሪካ ለመመለስ ከአዲስ አበባ ቶሮንቶ ለመብረር በተዘጋጀው የኢትዮጵያ አየር መንገድ በረራ ቁጥር ET502 አውሮፕላን ውስጥ ቁጭ ብያለሁ:: በአዲስ አበባ ቆይታዬ ከቤተሰብ: ጉዋደኛ: እና ወዳጅ ዘመድ ጋር ያሳለፍኳቸውን ጊዜያት በማሰላሰል በሃሳብ ጭልጥ አልኩ:: አንድ ነገር በሃሳቤ ደጋግሞ ይመጣል: የትንሿ እህቴ ቤዛ ነገር:: ስለአሜሪካ ኑሮ የምትጠይቀኝ ጥያቄዎችና: ስለ አዲስ አበባ ከተማ ለውጥ የምታስረዳኝ ነገር ሁሉም ድቅን አሉብኝ:: ቤዛ ከጥቂት ዓመታት በፊት ታዳጊ ሕፃን ነበረች: አሁን ግን ከሶስት ወራት በሁዋላ ከጥቁር አንበሳ በዶክትሬት የምትመረቅ ሀኪም::

 

አንድ መንገደኛ ኤክስክዩዝ ሚ ማይ ሲት ነምበር ኢዝ 13ኬ ብሎ ከሃሳብ ከአነቃኝ:: ለማረጋገጥ የመቀመጫ ቁጥሬን አውጥቼ ተመለከትኩ: 13 ጄ አዎ መንገደኛው የሚቀመጠው በእኔና በአውሮፕላኑ መስኮት በኩል 13 ኤል በተቀመጠችው ሴት መሃከል ነው:: የመስማማት ፊት እያሳየሁ ተነስቼ አሳለፍኩት:: ሻንጣውን ማስቀመጫው ውስጥ ካስቀመጠ በሁዋላ ተቀመጠ:: ምንም ጊዜ ሳያባክን በእንግሊዘኛ ማርክ እባላለሁ አንተን ማን ልበል? አለኝ:: እኔም ዳሞታ እባላለሁ መልካም ትውውቅ አልኩኝ: ምክረአብ የሚለው ስሜ ብዙ ጊዜ ለውጫውያን ስለሚያስቸግር በአያቴ ስም ወይም በአጭሩ በመጀመሪያው ፊደል ዲ ብለው እንዲጠሩኝ አደርጋለሁ::

 

ከአውሮፕላ አስተናጋጆች አንዷ ክቡራትና ክቡራን መንገደኞቻችን: አውሮፕላኑ በረራ ሊጀምር ስለሆነ: የኤሌክትሮኒክስ መሳሪያዎቻችሁን በማጥፋት:መቀመጫችሁ ላይ በመቀመጥና የደህንነት ቀበቶአችሁን በመታጠቅ እንድትተባበሩን እንጠይቃለን ብላ በአማርኛ እና በእንግሊዝኛ ባስተላለፈችው መልዕክት አቁዋረጠችን::

 

አውሮፕላኑ ወደሁዋላ ከሄደና ከአኮበኮበ በሁዋላ በፍጥነት ተነሳ:: አዲስ አበባና አካባቢዋ ያሉ ከተሞች በፍጥነት ወደ ሩቅና ትንንሽ ዕይታዎች ሲቀየሩ ተመለከትን:: ያንን ተከትሎ ከአብራሪዎች አንዱ ክቡራትና ክቡራን ከአዲስ አበባ ቶሮንቶ ወደሚበረው የኢትዮጵያ አየር መንገድ በረራ ቁጥር ኢቲ 502 በደህና መጣችሁ:: በጉዞአችን መሃል ደብሊን አየርላንድ ላይ የ45 ደቂቃ ቆይታ ካደረግን በሁዋላ ወደቶሮንቶ የምናደርገውን ጉዞ እንቀጥላለን የሚል መልዕክት አስተላለፈ:: በመቀጠልም የበረራ አስተናጋጆች: አውሮፕላኑ የሚፈለገው ከፍታ ላይ ስለደረሰ የደህንነት ከበቶአችሁን መፍታት: ኤሌክትሮኒክስ መጠቀምና: መንቀሳቀስ ትችላላችሁ:: በጉዞአችን ላይ እራት: መቆያ እና: ቁርስ የምናቀርብ መሆናችንን እንገልፃለን የሚል መልዕክት ተላለፉ:: ማርክ ትከሻውን በመጠኑ ወደእኔ ዘወር ካደረገ በሁዋላ: አዲስ አበባ ላይ ትራንዚት እያደረክ ነው? በማለት ጠየቀኝ :: የለም የለም አዲስ አበባ ለሁለት ወር ቤተሰብ ጥየቃ መጥቼ እየተመለስኩ ነው ከአልኩት በሁዋላ: ምን አይነት ጥያቄ ነው ኢትዮጵያዊ አልመሰልኩትም እንዴ!? አልኩ በሆዴ:: ማርክ ጥያቄውን ቀጠለ: አዲስ አበባ ጥሩ ጊዜ አሳለፍክ? ከዳያስፖራ ሕይወት የተማርኩትን የውሸት ፈገግታ ካሳየሁ በሁዋላ: አዎ ለእረፍት ስትመጣ: በጠዋት አላርም አይቀሰቅህም: ስትነሳ ጥሩ ቁርስ ይቀርብልሃል: የእረፍት ቀናትና በዓላትን ከቤተሰብ: ጉዋደኛ: እና ወዳጆችጋ ሰብሰብ ብለህ ያሳልፋለህ: እያልኩ የጠየቀኝንና: ሊጠይቀኝ ይችላል: ያልኩትን ጥያቄ አንዴ ልመልስና እርፍ ልበል በሚል መለስኩለት:: የበረራ አስተናጋጆች በመንገደኞች ምርጫ እራት ማስተናገድ ጀምረዋል:: እኔ ቤተሰቦቼ የወጪ ብለው በጋበዙኝ ላይ ምንም ነገር ላለመጨመር አስተናጋጆቹን እቆያለሁ አልኳቸው:: መንገደኞች ሲመገቡና የቆርቆሮ ቢራና ወይን ጭምር እያዘዙ ሲጠጡ ዙሪያውን ከቃኘሁ በሁዋላ መታጠቢያ ቤት ደርሼ ተመለስኩ:: የመመገቢያ እቃዎች በአስተናጋጆች ከተሰበሰቡ በሁዋላ የአውሮፕላን ውስጥ መብራት ተቀንሶ ጭልምልም እንዲል ሆነ:: አብዛኞቹ መንገደኞች የአየር መንገዱን ፎጣ መሳይ ብርድልብስ በመከናነብ ተኙ:: ብቻዬን የቀረሁት መሰለኝ: እኔ እንኳን አውሮፕላን ላይ ከለመድኩት ቦታ ውጪ እንቅልፍ አይወስደኝም:: የጆሮ ማዳመጫውን ከሰካሁ በሁዋላ ከፊት ለፊቴ የሚገኝ ተንቀሳቃሽ ምስል ማሳያ ነክቼ የበረራ መረጃዎችን መከታተል ጀመርኩ::

ተጨማሪ ያንብቡ:  ውዝግብ በአዲስ አበባው ሲኖዶስ ውስጥ፡ ያሳዝናል! ቤተ ክርስቲያናችን እንዲህ ኹና አታውቅም፤ ይፋረደን!

 

በአየር ላይ የቆመ የሚመስለው የኢቲ 502 አውሮፕላን በሜድተራንያን ባህር ላይ 550 ማይል ወይንም 900 ኪ.ሜ በሰዓት ያህል እየከነፈ መሆኑን ያሳያል:: ትራንዚት የምናደርግበት የአውሮፓው ደብሊን ከተማ ለመድረስ የ 8 ሰዓታት ያህል በረራ ይቀረናል:: ተንቀሳቃሽ ምስሉ ላይ በአግራሞት እንዳፈጠጥኩ በአግራሞት ወንድማማቾቹን ኦሊቨር እና ዊልበርን ራይት ማሰብ ጀመርኩ:: ሁለቱ የአሜሪካው ኖርዝ-ካሮላይና ከተማ ነዋሪዎችና የበረራ ፈጠራ ባለሙያዎች:: ዓለም የአየር በረራዎችን እንደአሁኑ የሸረሪት ድር ከማስመሰሉ በፊት በዲሴምበር ወር 1903 ዓ.ም የመጀመሪያውን የሙከራ በረራ ከመሬት 120 ጫማ ከፍ በማለት ለ 12 ሰከንዶች ያህል በረዋል:: እኔ በአውሮፕላን እየተሻገርኩት ያለሁትን ሜዲተራንያን ባህር አቁዋርጠው አንዱ አውሮፓ ሀገር ለመድረስ በማሰብ ስንት ስደተኞች ህይወታቸውን አጥተው ይሆን ስል ራሴን ጠየኩ:: ኢትዮጵያውያንን ጨምሮ የተለያዩ የአፍሪካና አካባቢው ሃገራት ዜጎች ለምን ከሀገራቸው ይሰደዳሉ? ለምንስ ይሄንን የሞትና የሽረት ጉዞ መረጡ? መልስ ለማግኘት በመቸኮል ጉግል ማድረግ ጀመርኩ:: እንደ ዩናይትድ ኔሽን ዩኒቨርሲቲ http://unu.edu ዘገባ ሰዎችን ለስደት ከሚዳርጉ ምክንያቶች መካከል ድህነት: ጦርነትና: የአየር ንብረት ለውጥ ይገኙበታል:: ከአንዱ የመረጃ መረብ ወደሌላኛው የመረጃ መረብ በመለዋወጥ ተጨማሪ መረጃ ለማግኘት ጥረቴን ቀጠልኩ:: እንደ አለማቀፍ ስደተኞች ጉዳይ ማህበር አይ. ኦ. ኤም www.iom.com ዘገባ ከ2016-2019 ባሉ አራት ዓመታት ውስጥ ብቻ ሜዲተራንያን ባህርን ሲያቁዋርጡ ህይወታቸውን ያጡ ስደተኞች ቁጥር:-

2016-3,740
2017-3,139
2018-2,299
2019-1,283 ነው

ህይወታቸውን ከአደጋ ለማትረፍና: የተሻለ ኑሮ ፍለጋ ተስፋ ሰንቀው በማያውቁት መንገድ ወደማያውቁት ሀገር የሞት ሽረት ትግል በማድረግ ህይወታቸውን ያጡትንና: የት እንደደረሱ የማይታወቁትን ወንዶች: ሴቶችና: ሕፃናት እያሰብኩ የእንባ ዘለላዎች በጉንጮቼ ላይ ይወርዱ ጀመር :: እንባዬን ከፊቴ ላይ እየጠራረኩ ሳለቅስ መንገደኞች አለማየታቸውን ለማረጋገጥ ዘወር ዘወር አልኩኝ: ሁሉም ተኝተዋል:: ደብሊን ለመድረስ 6 ሰዓት ያህል በረራ ይቀረናል#እኔንያየህተቀጣ

ተጨማሪ ያንብቡ:  አቡሽ ዘለቀ (አውጡት ከፓርላማው) - New Ethiopian Music 2022

3 Comments

  1. ዳያስፖራዎች ብዙ ችግር ተሻግረን
    ኑሮ ከሚቀጭበት ደርሰን

    የሀገር ኢኮኖሚ ዋልታ ተብለን
    ዕውቀት ትምህርት ባይኖረንም ገንዘብ ልከን

    ተከብረን በቤተሰቦቻችን
    ሰሜን አሜሪካዊ ሆነን

    ትጉህ ሠራተኛ ህዝብ ለመባል እየተጋን
    የሽማግሌ እና የአሮጊት የቅዘን መጥረጊያ መሀረብ እያጠብን

    በኮሮና ሳንገታ የመኪና መንገድ በሀሩር ሙቀት እየወለወልን
    ለእንጀራችን ስንል በየመንገዱ የተጣለ ቆሻሻ ለቅመን

    ቤት መጦርያ ስናፈላልግ በሀገራችን
    ፈታ ብለን በሀገር ለመኖር የመጨረሻ እድሜዎቻችንን

    ሀገሪቷ በአለም አንደኛ የሀገር ውስጥ ተፈናቃይ ህዝብ ብዛት አስቆጠረችን

    መንከራተት መፈናቀል እየተደገሰልን፡ እንኳን ልንል ፈታ በኢትዮጵያ ውስጥ ልንኖር እየተጦርን

    ቤት አለን በኢትዮጵያ ሳይሆን
    ጀምረናል ማለት ቤት-መሳይ መቃብር አለን

    ከኖርንበት የምንታረድበት
    ልጅ የማንድርበት

    ተከበን በሰው በላ ጎረቤት
    የሚያጠና ያለንን ተመሳጥሮ ከባንክ ቤት

    ከሞከርን ልንኖር ከሀገሬው ተመሳስለን
    ባንክ ቤት ያሳብቃል በአራጅ ጎረቤት ሊያዘርፈን

    ተመላሽ ዳያስፖራ የውጭ ዜጋ ኢንቬስተር ከተባልን

    ለብልፅግና እርዳታ ባጀት ብድር ሲቋረጥ በሰሜን አሜሪካ ካለው መንግስታችን

    ብልፅግና እቅድዋል በተዘዋዋሪ ሊያገኘው አስዘርፎ ዳያስፖራን
    ብልፅግና ዳያስፖራን አኝኮ ሊተፋው እንደ ማስቲካ ፡ መጥምጦት ያለውን

    ዳያስፖራን ጠቅላዩ ሲያዝ ለእርዳታ ሰልፍ ወጥቶ ለብድር ሎቢ እንዲያደርግ ባለበት

    ስለ በትግራይ የተሙዋላ ሰላማዊ ኑሮ ለሰሜን አሜሪካ ባለበት እየመሰከረ እንዲወተውት

    ዳያስፖራ ጠቅላዩን ስላለው አሻፈረኝ አንድ ዶላር በቀን አልልክም
    ስለ ትግራይ ዘመቻም አላውቅልህም

    -ብልፅግና አቅድዋል አውጆ በስውር ፤ እያንዳንዱ ዳያስፖራ በግሉ ከሰሜን አሜሪካ ዌልፌር እንዲለምን-

    -ዳያስፖራ እንዲሰለፍ ከሰሜን አሜሪካ መንግስት እርዳታ ማስተባበርያ ሰልፍ ፤ በስተ እርጅና እንዲገፋው የምፅዋተኝነት ኑሮን-

    ዳያስፖራ እድል ነው ሀገር አለኝ በኢትዮጵያ
    የምፈናቀልበት የምታረድበት ያለኝን መዘረፍያ

    እስቲ የትኛው ከተማ የሰላም ኑሮ ይኖር ይህን
    መፈናቀል ያልተሰማበት አጋሮ ወይስ የበሻሻ ላይ ሰፈር ይሻል ይሆን?

    አለመፈናቀል ያለበትን የጃዋር ሳተላይትም አላየልን
    ኢሳትም ሆነ እስክንድር ነጋም አልጠቆሙን

  2. ሃገሩ ምንም ሳታረግለት ሃገሬ ሃገሬ እያለ እሳት ውስጥ ገብቶ የሞተ ህዝብ ቢኖር የሃበሻ ህዝብ ብቻ ነው። ለዚያውም እሱ ሞቶ ሌላው በወረፋ ሊጨቁነው፤ ሊጨፈልቀው። እናውቅላችሁአለን ያሉን፤ ነጻ እናወጣችሁ ብለው ጫካ ገብተው የከተማ አለቃ የሆኑት የወስላታ መንጋ ሁሉ ለራሱ እንጂ ለህዝብ አስቦ አያውቅም። 30 ዓመት ሙሉ በኤርትራ ነጻነት ሳቢያ የፈሰሰውን ደምና ዛሬ ኤርትራ ያለችበትን ሁኔታ ለተመለከተ ሃዘን ያስቀምጣል። ይበልጡ በምድሪቱ መኖርን ሳይሆን መሰደድን የመረጠበት ምድር፤ እልፎች በምድረበዳ የቀሩበት በውሃ የሰጠሙበት ያ የነጻነት ናፍቆት መልሶ ያመጣው ባርነትን ነው። ባንጻሩ የኢትዮጵያን ሁኔታ ለተመለከተ ደግሞ ከኤርትራ ችግር እጅግ የባሰ ነው። እድሜ ለወያኔ ሃገሪቱን በዘርና በቋንቋ ከፋፍሎ 27 ዓመት ቀጥቅጦ ገዝቶ ከስልጣን ሲገፋ ሸሽቶ ትግራይ በመወሸቅ የፈጠረውንና በመፍጠር ላይ ያለውን ሃበሳ እያየን ነው። አሁን ተራብን የኤርትራ ሰራዊት ወረረን የሚሉት ምግብና መድሃኒት የጫኑ መኪኖችን ልክ በፊት ያረጉ እንደነበሩት መንገድ ላይ ጠብቀው እያጋዪና ሾፌሮችን እየገደሉ እንደሆነ እንሰማለን። በጭራሽ አፍሪቃዊው ህይወት መራራ ነው። ለማንም አይጥምም። በናይጄሪያ፤ በካሜሩን፤ በደ/ሱዳን፤ በሱዳን እና በሌሎችም የአፍሪቃ ሃገሮች የምናየውና የምንሰማው ሞት፤ ረሃብ፤ የሰው ልጆች መብት መገፈፍን ነው።
    የአንተ በባህር ላይ ለቀሩት እንባ ማፍሰስህ ሰው መሆንህ ያሳያል። ወያኔ በሃገራችን ህዝቦች ላይ በተለይም በወልቃይትና ራያ ህዝብ ላይ ወያኔ ያደረሰውን ግፍ ስታይና ስትሰማ ናዚ ጀርመኒ በአይሁዶች ላይ ካደረሰው ጋር የነጻጸራል። የዘር ማጥፋት፤ የቋንቋ ማጥፋት፤ የመሬት ዘረፋ፤ ሌላው ቀርቶ በአምልኮ ስፍራዎች እንኳን አማርኛ እንዳይነገር የሚከለክል ህግ አውጥቶ ቄሳውስትን የገደለ ድርጅት ነው። በመጨረሻው ሰአትም ይህ ነው የማይባል ጭፍጨፋ በመፈጸም ወደ ሱዳን ተሻግሮ ከሱዳን ጦር ጎን ተሰልፎ ሃገርን እየወጋ ይገኛል። ይህንና ሌላውንም በአዲስ አበባና በሌሎች የሃገሪቱ ክፍሎች የሚሆነውን የፓለቲካ አሻጥርና የየቀን ዝርፊያና ቅሚያ አልፎ ተርፎም ግድያ ስትመለከት እልፈት የሌለባት ሃገር እንደሆነች ታያለህ። ስለሆነም ከጊዜ ወደ ጊዜ የክፋት ቋት እየሆነች ያለቸው የሃበሻ ምድር ጭራሽ ለሰው ልጆች አትመችም። ተማርክ አልተማርክ ዋጋ ቢስ ነው። ሰው በዘሩ፤ በቋንቋው የሚፈረጅበት ሃገር ላይ ሥራ ማግኘት ጭራሽ አይቻልም። ቢገኝም አያሰሩህም። የክልል ፓለቲካ ከደ/አፍሪቃው የነጮች አፓርታይድ ፓሊሲ ጋር ተመሳሳይ ነው። አሁን የትግራይ ጦርነት እንዳበቃ አድርገው ገደልን ያዝን ጠለፍን የሚሉን ወሬዎች ሁሉ ማቆሚያ የሌላቸው ድግግሞሽ ናቸው። ወያኔ በአንድም በሌላም መልክ ሃገር ማተራመሱን ይቀጥላል። ለዚህም ሌሎች የሃገርና የውጭ ሃይሎች ይተባበሩታል። የሙታን ፓለቲካ እንደዚህ ነው። ሁሌ ፈንጂ ማጥመድ፤ ጥይት መተኮስ፤ በመሬትና በክልል እያሳበቡ መገዳደል። በአሁኒቷ ኢትዮጵያ ህግ የለም። ዘራፊው በወረፋው ይዘርፋል፤ የሚገደለው ይገደላል፤ የሚታሰረው ይታሰራል፡ ጉቦ የሚሰጠውና ከበላይ አካል ጋር ትስስር ያለው አንድ ቀን ከሃዲ፤ ሰራዊቱን የከዳ ከውስጥ የወጋ ተብሎ በሚዲያ የተነገረባቸው ያለምንም ነገር ይለቀቃሉ። መለቀቅ የሚገባቸው ደግሞ ጨለማ ውስጥ ታጉረው ይገኛሉ። እነዚህ ነጻ ናችሁ ሂድ የተባሉት ሃይሎች ደግሞ እንደገና ተሰባጥረው ፈንጂ ቀባሪና ሰው ገዳይነታቸውን ይቀጥላሉ። ውጊያው ይቀጥላል፤ ለቅሶው ይቀጥላል፤ ለእኔ የሚታየኝ እይታ ጨለማ ነው። ኢትዪጵያ የሞተችው ደርግ ስልጣን ከወጣ በህዋላ ነው። በሰውነት ኑሮ ለሰው ሁሉ የሚያስብ እንባም በየጊዜው በሚያየውና በሚሰማው የተነሳ ከማዘንና እንባን ከማፍሰስ አይገታም። በቃኝ!

  3. በቅርቡ በአንድ ወር ከማይበልጥጊዜ ውስጥ ፤ በኢትዮጵያ መንግስት እገደላለሁ ፤ ስሞት ሬሳዬ ላይ እንዳትቆሙ ፤ አንድም ኢትዮጵያዊ ስሞት እንዳታዝኑልኝ ወይም እንዳትቀብሩኝ ሚስቴ ብቻ ትቅበረኝ ፤ በህይወቴ በቁሜ ያላዘናችሁኝ ኢትዮጵያኖች ስሞት ጠብቃችሁ ሬሳዬ አጠገብ ከደረሳችሁ የተረገማችሁ ሁኑ ፤ ስሞትም ስለ እኔ የአሙዋሙዋት ታሪክ የውሸት ወሬ አታውሩ የሚል መልዕክት ያዘለ ማስጠንቀቂያ በዛሬው ሰኞ ዕለት ከታላቅዋ ብሪታንያ ተላልፍዋል ከታዋቂው የዳያስፖራ መብት አስከባሪ አቶ ቶሎሳ ኢብሳ።

Leave a Reply

Your email address will not be published.

Share