ኢትዮጵያን ታደጋት – ሽመልስ ተሊላ

January 13, 2021

ሀያሉ ፈጣሪ አላህ ጎድ እግዚአብሔር
ኢትዮጵያን ታደጋት በረቂቁ ምስጢር።
ዘር ጎሳ ጎጥ ብሔር ዘውጌ ብሎ ነገር
የሀገር ካንሰር ነው በቁም ገዳይ እውር።
ማንም የማይችለን ሰዉ የማይበግረን
ጦርነት ባህላችን ወደርየለሽ የሆን
የጀግኖችም ጀግና ተራራ አንቀጥቅጥ ነን።
ከቶም እጅ አንሰጥም
ሽጉጥ መርዜን ግጥም።
ያሉት አቦይ ስብሃት
ገደል ውስጥ ተይዘው ሲጋራዋን ጠጡዋት።
የዘረኝነትን ግፍና ጭካኔ
ከጉድጓድ ተቀብሮ ሲገኝ አረመኔ
በካቴና ታሰሮ ሲሄድ ከድቶት ወኔ
አይተሀል ሰምተሀል…ተማር ከወያኔ።
ከሰውነት ባህሪይ በእጅጉ ማፈንገጥ
ሞቶ የአበቃለትን እሬሳ መቀጥቀጥ።
ከአዳምና ሔዋን ሰብዓዊ ተፈጥሮ
ከአንድ አብራክ ማህፀን በእትብት ተቋጥሮ።
የተወለደ ሰው
እሱነቱ ማን ነው?
ተጠየቅ ልጠየቅ
መልሱን በደንብ እወቅ።
ድል አድራጊው ጀግና መከላከያ ጦር
ገንጣይ ድባቅ መቶ ሕግ ሀገር ሲያከብር
የዘሩትን አጭደው ክምሩ ተወቃ
የዘረኞች ዘመን አከተመ በቃ።
ያ ሁሉ አጆሀ ያ ሁሉ ድንፋታ
እብሪቱ ተንፍሶ ቋጠሮው ተፈታ።
ሀያሉ ፈጣሪ አላህ ጎድ እግዚአብሔር
ኢትዮጵያን ታደጋት በረቂቁ ምስጢር።

ሽመልስ ተሊላ።

ተማር ከወያኔ

ሽመልስ ተሊላ
ሀያሉ ፈጣሪ አላህ ጎድ እግዚአብሔር
ኢትዮጵያን ታደጋት በረቂቁ ምስጢር።
ዘር ጎሳ ጎጥ ብሔር ዘውጌ ብሎ ነገር
የሀገር ካንሰር ነው በቁም ገዳይ እውር።
ማንም የማይችለን ሰዉ የማይበግረን
ጦርነት ባህላችን ወደርየለሽ የሆን
የጀግኖችም ጀግና ተራራ አንቀጥቅጥ ነን።
ከቶም እጅ አንሰጥም
ሽጉጥ መርዜን ግጥም።
ያሉት አቦይ ስብሃት
ገደል ውስጥ ተይዘው ሲጋራዋን ጠጡዋት።
የዘረኝነትን ግፍና ጭካኔ
ከጉድጓድ ተቀብሮ ሲገኝ አረመኔ
በካቴና ታሰሮ ሲሄድ ከድቶት ወኔ
አይተሀል ሰምተሀል…ተማር ከወያኔ
ዘረኛ ዘውገኛ በልና ነግ በኔ።
ከሰውነት ባህሪይ በእጅጉ ማፈንገጥ
ሞቶ የአበቃለትን እሬሳ መቀጥቀጥ።
ከአዳምና ሔዋን ሰብዓዊ ተፈጥሮ
ከአንድ አብራክ ማህፀን በእትብት ተቋጥሮ።
የተወለደ ሰው
እሱነቱ ማን ነው?
ተጠየቅ ልጠየቅ
መልሱን በደንብ እወቅ።
ድል አድራጊው ጀግና መከላከያ ጦር
ገንጣይ ድባቅ መቶ ሕግ ሀገር ሲያከብር
የዘሩትን አጭደው ክምሩ ተወቃ
የዘረኞች ዘመን አከተመ በቃ።
ያ ሁሉ አጆሀ ያ ሁሉ ድንፋታ
እብሪቱ ተንፍሶ ቋጠሮው ተፈታ።
ሀያሉ ፈጣሪ አላህ ጎድ እግዚአብሔር
ኢትዮጵያን ታደጋት በረቂቁ ምስጢር።

Leave a Reply

Your email address will not be published.

በመከላከያ ሰራዊትና በፌደራል የጸጥታ ተቋማት በቁጥጥር ስር የዋሉት የጁንታው አመራሮች አዲስ አበባ ሲገቡ
Previous Story

በመከላከያ ሰራዊትና በፌደራል የጸጥታ ተቋማት በቁጥጥር ስር የዋሉት የጁንታው አመራሮች አዲስ አበባ ሲገቡ የሚያሳይ ቪኢኦ

Next Story

መቆሚያ ያጣው በመተከል ያሉ ሰዎች እልቂት! – ኢሰመጉ

Latest from Blog

አትዮጵያ ያን ዕለት

ግም ሞት 20’ 1983 .ዓ.ም. ለህወሀት /ኢህአዴግ ልደት ለኢትዮጵያ እና ለብዙዉ ኢትዮጵያዉያን የዉድቀት ፣ጥልመት እና ሞት ዕለት መሆኑን ያ ለሁለት አሰርተ ዓመታት ከፍተኛ ዕልቂት እና ደም መፋሰስ የነበረበት ጦርነት አዲስ አበባ በደም
Go toTop