ኢትዮጵያዪ፤ ምነው እመብረሃን የስደት አገርሽን ተውሻት

 

ኢትዮጵያዪ

              ምነው እመብረሃን የስደት አገርሽን ተውሻት

              ዝም አልሻት እረሳሻት።

  • ኢትዮጵያየ ምነው ልጆችሽ ጨከኑብሽ

ለወዳጅ ጥላት ሊሰጡሽ አሰፍስፈው አሴሩብሽ።

ሰላምሽን ጠልተው ገፉት

ወተትሽን ንጠው ድፉት

ሥልጣን ሰጥተሻቸውም ሊጠሩሽ ጠሉሽ

በጎሳ ተከፋፍለው እርስ በእርሳቸው ተባሉልሽ

በአጎረስኩ ተነከስኩ ሆኑብሽ።

ግና አይዞሽ አሁንም ቢሆን ልጅ አለሽ

ብትገፊውም አርቀሽ

ነፍገሽም ቢሆን ሰስተሽ

ከማዕድሽ መቋደስ ባይችልም

ምን አረግሽልኝ ብሎ አይጠይቅም

ውርደትና መደፈርሽን አይፈልግም

ተነካሽ ሲሎት አይወድም።

  • ያለችውን ውድ ሕይወቱን ሊሰጥሽ

ውርድ ለሰማይ ለምድር ብሎ፣

ይዘምትልሻል ነፍጡን ያነሳል ሞቱን መርጦ

ከጠላት ሊታደግሽ ወድ ሕይወቱን ከፍሎ። 

            ምነው እመብረሃን የስደት አገርሽን ተውሻት

            በጎሳ ከፋፍለዋታል ሊአፈርሷት

           ዝም አልሻት አትርሻት።

 

  • እንዲህ አዝግመሽ ዘመናትን ያስቆጥረሽው

የአበው አባቶቻችን ጸሎትና ቡራኬ ቢደርሰን ነው።

ውሽትን ጠልተው ስርቆትን ተጠይፈው

በኢትዮጵያዊነታቸው ጥግ ዘልቀው ሁሉንም አካተው

መድሎን ኮንነው በማተባችው  ጸንተው

በአንች አማላጅነትና በልጅሽ አዳኝነት ተማምነው።

እንዲህ ነበር እኮ ያቆዮአት

3ሽህ ዘመን ያስቆጠሯት።

ግን እኮ እማማየ!! የአንችነትሽን ዲካ አሻራ

ታሪካዊነትሽን የሚአስጠራ

ከአገራት በፊት ቀደምትነት ያሰጠሽን

የዕምነት ሥረአትሽን  ባህልና ወግሽን

የአንችነት መገለጫዎች እኒያ እኒያ ትውፊታዊ ቅርሶችሽን

ቃል የዕምነት ዕዳ ሆኖበት አስጠብቆ ያቆየሽን

ለአንች ብለው የሞቱልሽን ድሮም ሆነ ዛሬ መች ፈለግሻቸው መች ከፈልሻቸው

አገር ባቀኑ ዕምነት ባጸኑ መታረድ  ሆነ እንጅ ትርፋቸው?

                          ክፍል ሁለት

  • አልሰሜን ግባ በለው አሉ

እንዴት እንዴት እንዲህ አልከኝ

መቸ አውከኝ ማንነቴን የት አይህኝ

አገር ማለት ምጥቅትና ስፋቱን መቸ አውቀህው

ተጨማሪ ያንብቡ:  አይ የሰው ነገር! የጥላቻ አጥር ክልል- በአልማዝ አሰፋ - ዘረ ሰው

አቅል ገዝተህ ምኑስ ገብቶህ መቸ ኖርከው ።

እንጅማ የዓለም አገራት ታላቅ ነን ከሚሉት ቀደም ብየ

         እታወቅ ነበር መንግሥት መስርቸ ሥረአት ጥየ

አውሮፓዎች ከእኔ በኋላ አገር ሁነው ሥልጣኔውን ቢአፋጥኑት

ከነሱ ተምረህ እንድ ጃፓን ቻይና መሽቀዳደም ሲገባህ

ጭራሽ አውቀህ ሙተህ ከዚያም ከዚያ በቃረምካት

አገርህን የብሔርስብ አስር ቤት ናት አልካት ።

ይህን እውቀት ብልህ

ከኢትዮጵያዊነት አሰባሳቢ ማንነትህ ወጥተህ

አንዲት ሰበዝ ብቻ መዘህ ቋንቋን መለኪያ አድርገህ

እንዲህ ነኝ ማለትህ

እውነት ይህ ብቻ  ሆኖ ነው የአንተ መገለጫ ማንነትህ?

አናማ  የወረደ ማንነት ፈለጋ ስትዳክር

የሳለፍከው ጊዜ ቢቆጠር

ለአገርና ለሕዝብ የሚጠቅም ስንት ቁም ነገር ትሠራበት ነበር።

  • አየ ኢትዮጵያየ!! ይህ ሁሉ ምን ያደርጋል የሚወዱሽ ልጆችሽ

በሕይወታቸው ተወራርደው የታደጉሽ

አሁንም  እኮ  እስር ሆነ የተረፋቸው

መሳደድ ሆነ ዕጣ ፈንታቸው።

አንዳንዶቹም እንግልቱን ተቋቁመው ሞትን ቢአሸንፉት

ከሃዲና ባንዳዎች ናቸው ሥልጣኑን የሚይዙት

ዋሸው እንዴ ኢትዮጵያየ አስቲ ንገሪኝ በእኔ ሙት!!!አልኳት

ምነው ወላዲት አምላክ ምልጃሽን ነፈግሻት

              የሰደት አገርሽን ዘነጋሻት ዝም አልሻት።

  • ይኽውና ሦስት አሥር አመታት አለፈን

በጎሳ ነገድ ተከፋፍለን ከተቧደን።

እርስ በእርሳችን እንዳንስማማ ተደርገን

የአንድ እናት ልጆች ሁነን አንዳላደግን

መደማመጥና መግባባት ተስኖን

አገር የሚአፈርስ  ሕግ አርቅቀን

ሆን ተብሎ እንደ ጠላት እንድንተያይ ከተደረገን።

እንዳይሻሻል በጎጤኞች እንቢተኝነት

በተረኞች እየተስፈራራን በመንጋ እየተዳኘን

አገር አልባ እኮ ሊአደርጉን ነው።

የዘር መጋኛ ተጠናውቶን ተጣግቶን

ክፍ አንዳላልን ወርደን ዘቅጠን

መወያየትና  መግባባት እኮ ተሳነን።

እኮ እረ እኛንስ ምን አስነኩን? ምን ተሻለን???

ተጨማሪ ያንብቡ:  ይክበር የአንች ቀን (ዘ-ጌርሣም)

እመብረሃን ምነው ዝም አልሽን

              ባዝን እኮ በዘር ልክፍት ጠመደውን

እረ እባክሽ ተለመኝን ከልጅሽ ከወዳጅሽ አማልጅን ።

  • ቀደመ አባቶቻችን ያስተማሩን

የምንታወቅበት ፍረሃ አግዚአብሔር ዕምነታችን

የወደቀ አንጀራ እንኳ ስናይ ጡሩን ፈርተን

ከመሬት ላይ አንስተን

ወደ ላይ ወደ ፈጣሪ አንጋጠን ስሙን ጠርተን

ይቅር እንዲለን ተማጽነን እንጎርሰ ነበር እፍ እፍ ብለን።

የአሳደገነውን ከበት ለመባረክ እጃችን አልጨክን ቢለን

እናስባርክ ነበር ከጎረቤት ሰው ጠርተን።

ሰውን በመንጋ ማጥቃትም የፈሪነት እንጅ የወንድነት ሙያ አልነበረም

ጠላት መሬት ሙጥኝ ካለም ጠያፍና ነውር ነው አይገደልም።

ይኽ ይኽ ሁሉ የጅግንነት ትውፊቱ ተረስቶ

አገር ለማዘመን የከፈለው መስዋአትነት ተሰርዞ ጠፍቶ

ሥልጣኑ  መንበሩ ላይ ባንዳው ተተክቶ

በእነ እንቶ ፈንቶ ፍርድ አማራው ታረደ ተበላ

ግፉ ጥግ ደረሰ  ቂም አርግዟል ሞልቶ።

ዋ !! ቤ ን ሻ ን ጉ ል የ ደ ም  ም ድ ር

የሚበላ እህል ሳይጎድል

ምነው የአማራ ስጋ አማረው ቤንሻጉል።

ታናሽና ታላቅ እያለ የውስጥ ዕቃ ያማረው

“የቀየ ሰው ደም” የጠማው

ቤንሻንጉልን ምን ነክቶት ነው ?

ለመሆኑ ቤንሻንጉልን እንዲህ ያጀገነው

ማን አይዞህ ቢለው ነው

ማን የልብ ልብ ቢሰጠው ነው??

እኛ ስናውቅ መተክል የጎጃም የአማራ ምድር  ነበር

አሁን ግን ጉምዝ፣ ወይጦውና ሽናሻው መዥንገር ሆነና ባላአገር

በቀስት በጎራዴ አማራው እየተለየ ይታረድና ይመተር ጀመር።

 

  • ኢትዮጵያዪን ባሉ የአገር አቅኒ ልጆች የነስሜ አይጠሬ

የእኒያ የእነ አጅሬ የነሞት አይፈሬ

ውጣልን ይሉታል ከአገር ከደንበሬ።

ወያኔም ከሄደ ጉድ እየስማን ነው ትናትና ዛሬ

ተጨማሪ ያንብቡ:  ““ነጻ”” ይወጣ ይሆን? ( ከአሁንገና ዓለማየሁ)

ይታረዳል አሉ ከቤት ከደጃፉ እንደሰንጋ በሬ።

ፍትሕ ተጓድሎበት ያም ያም ይገድለዋል

የአማረው ደም  ይጮሃል !!! የአማራው ደም ይጮሃል!!

ምነው እመብረሃን ዝም አልሻት

ቅድስት ሀገራችንን እንዳያፈርሷት

አባክሽ ከእንደነዚህ ያለ ብልሃስቦች ታደጊያት ።

  • መታሰቢያነቱ፤ በቤንሻንጉል ጎምዝ/ በመተከል፣ በኦሮሚያና በማይካድራ በአማራነታቸው ምክንያት ለታረዱና ለተጨፈጨፉ አማሮች ይሁንልኝ።

ኦ!!  ማ  ይ  ካ  ድ  ራ፤

  • የቅድስት አገር የኢትዮጵያ የአንድ እናት ልጆች መሆናችንን እረስተው

ደደቢት ላይ ከለከፋቸው ጋኔን ተጣብቀው

ሃይማኖታቸውን ክደው

ለፍቅረ ነዋይ ተገዝተው

ኢትዮጵያን አጨቀዩአት በደም ስክረው ዋጀተው።

ድሮ እንዲያ ትግራይን አጥግብልን ብለን ተማለደን እንልህ የነበር

በወያኔ እንዳየነው

እንዳለፈው 30 ዓመት መች እንደዚህ እንዲሆን ነው ።

አሁን ደግሞ ከ27ዓመት ወዲህ የተለየ የተለየ ጥጋብ ሆነ

ትንግርት ያለው ድግስ  ጠላና ጠጅ ተጣለ

በእያይነቱ ብልት በብልት ተደለደለ

አማራ አማረን ያስባለ

  • ማይካድራ ላይ ጉድ ተባለ ጉድ ያስባለ!!
  • መታሰቢያነቱ ማይካድራ ላይ በማንነታቸው ምክንያት በግፍ ለተጨፈጨፉ አማሮች ይሁንልኝ።

2 Comments

  1. Saint Mary, the mother of jusus, ignored Ethiopia because of the sin The Orthodox Tewahdo Church did evil against the Gojjamites violating the words of God.
    በጎጃም ሕዝብ ላይ በየገድላቱና ድርሳናቱ የተጻፉ የጥላቻ መልዕክቶች ፡
    ፨ ገድለ ተክለ ሃይማኖት፦ ጎጃሞች እንደ ጅብ የሰው ስጋ ይበላሉ
    ፨ ገድለ ክርስቶስ ሰምራ፦ ጎጃምን ቡዳ ነው ለማለት ነጭ ሽንኩርት በልቶ ቤተክርቲያን ስለገባ እመቤታችን እረገመችው
    ፨ ገድለ ገብረ መንፈስ ቅዱስ፦ ሌላውን ህዝብ ምሬልሃለሁ ጎጃምን ግን አልምርልህም
    ፨ ድርሳነ ራጉኤል፦ ከጎጃም ሀሰተኛ መሲሕ ይነሳል
    ፨ የነገስታቱ ዜና መዋዕል፦ ወደ ሰው በላው ሀገር ጎጃም እንዝመት
    1. አንድ ባለዛር ከ እምድረ ጎዣም ወእምድረ ዕብራቅይ ከጎጃም እና ከ ዕብራይቅ ተክለሃይማኖትን ለመግደል ብዙ መሰሪዎችን አመጣ እነዚህም ሂደው ” ፈረሶቻችን እሳት ልብሶቻችን እሳት ሲሆኑ ማን ይችለናል በመብረቅም እንመሰላለን አሉ….እኩሌቶቹ እሳት ካፋቸው ያናፋሉ እኩሌቶቹም እንደ ጅብ እንደ አንበሳ ይጮሃሉ ከነርሱም እንደ እባብ የሚያፏጩ እንደ ዝንጀሮ የሚጮሁ አሉ ።…” የሚል አስነዋሪ ጥላቻ ከስር የተለጠፈው ገድለ ተክለሃይማኖት በግእዝና አማርኛ ተስፋ ገብረስላሴ ዘብሄረ ቡልጋ ምእራፍ 53 ከ ቁ15 ጀምሮ ተፅፎ ይገኛል። እዚሁ ምእራፍ ላይ ወረድ ብሎ ቁ18ና 19 ላይ ”እንደጅብ ይጮሃሉ ያላቸውን ጎጃሜዎች ”ሊበሉን ሲመጡ ተክለሃይማኖት ሲያማትቡባቸው መሬት ተከፍታ ወደ ገደል ሰጠሙም” ይለናል። በነገራችን ላይ ”ጎጃሞች ሰጠሙበት” የተባለው ገደል እስከ ዛሬ ድረስ የደብረ ሊባኖስ ገዳም ለምእመኑ ያስጎበኘዋል።
    በሩዋንዳ ሁቱዎች ቱትሲዎችን በረሮዎችና እና እባቦች (cockroaches and snakes) እያሉ ከሰው ደረጃ በማሳነስ የዘር ፍጅት ቅስቀሳ እንዳደረጉባቸው ይህ በገድልና በሃይማኖት ስም የተፃፈ መፅሐፍ የጎጃምን ሕዝብ ከሰውነት ተራ አውጥቶ ወደ እንስሳነት (sub human) በመቀየር የጎጃም ሕዝብ ሰው እንደሚበላ አድርጎ በመፃፍ በጎጃም ሕዝብ ላይ ግልፅ የዘር ማጥፋት እንዲፈፀም ሲቀሰቅስ የኖረ እና አሁንም ድረስ እየታተመ የሚሰራጭ አደገኛ መፅሐፍ ነው። የዘር ማፅዳት (genocide) ዋናው አስኳል ከላይ በገድሉ ላይ ያየነው ሰውን ከሰውነት ደረጃ ማውጣት (dehumanization) መሆኑን ከአይሁዶች የመርዝ ፍጅት በሁዋላ በ1948 የጎሮጎሪያውያን አቆጣጠር የወጣው የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የዘር ማፅዳት ኮንቬንሽን (The Genocide Convention) በግልጽ ያስቀምጠዋል። በኢትዮጵያ በየዘመኑ ስልጣን ላይ የወጡት ነገስታት ”ወሖረ ሀገረ በላዕተ ሰብእ እምብሔረ ጎጃም (ወደ ሰው በላው የጎጃም ሀገር እንሂድ) ” እያሉ በጎጃም ላይ የዘመቱት እንደዚህ ባሉ በጎጃም ላይ የተነዙ የጥላቻ መፅሐፍ ተነሳስተው መሆኑን ለመገመት አያዳግትም።
    2. ጎጃሜን ቡዳ ነው ለማለት ነጭ ሽንኩርት በልቶ ቤተ ክርስቲያን ስለገባ እመቤታች ረገመችው የሚል የጥላቻ ንግግር የተክለሃይማኖት የስጋ ዘመድ ናት በተባለችው በክርስቶስ ሰምራ ገድልም ላይ ሰፍሮ ይገኛል። የሚገርመው አቡነ ተክለሃይማኖት ስጋ ለብሶ የመጣውን ሰይጣን አጥምቀው አመነኮሱት ተብሎ በተነገረበት በዚህ የገድል መፅሐፍ ላይ ጎጃሜዎችን ግን እንደ ጅብ እና እባብ ስለሆኑ መሬት ከፍታ እንድትውጣቸው አደረጉ መባሉ ምን ያህል ስር የሰደደ የጎጃም ጥላቻ እንዳለ ቁልጭ አድርጎ ያሳያል። በተመሳሳይ መልኩ በክርስቶስ ሰምራ ገድል ላይ ሰይጣንን ከ እግዚአብሔር ጋር ልታስታርቅ ሲኦል ድረስ ወረደች ተብሎ ቢፃፍም የጎጃምን ሕዝብ ሰይጣን ከሚሉትም በላይ ስለጠሉት ነጭ ሽንኩርት ስለበላ እመቤታችን ረገመችው የሚል የጥላቻ ንግግር ሰፍሮ እናገኛለን። ለሰይጣን ያዘኑ ለጎጃም እንዴት ማዘን ተሳናቸው??
    3. በገድለ ገብረ መንፈስ ቅዱስ”ወይቤሎ አቡነ ለእግዚእነ መሀሮሙ ለኩሎሙ ኢትዮጵያ ወኢትሌሊ አሐተ ወይቤሎ እግዚእነ እምህር ለከ ወሰና ለግዮን ለባህቲቶሙ ለኢትዮጵያ ወይቤሎ አቡነ ለምንት ትሌሊ ጎዣመ እለ ሀለው ማእከለ ግዮን ወኢትምህሮሙ ህቡረ ወይቤሎ ህቡረ ወይቤሎ እግዚእነ እወ እይምህር እስመ እሙንቱ እለ ሥራዬ ያበዝሁ
    ትርጉም አባታችን ገብረ መንፈስ ቅዱስ ጌታችንን ሁሉንም ኢትዮጵያውያንን ማራቸው አንድም አትለይ አለው ። ጌታችንም እስከ አባይ ወሰን ኢትዮጵያን ብቻ እምርልሃለሁ አለው። አባታችንም በአባይ ያሉ ጎጃሞችን ለምን ትለያቸዋለህ አብረህ አትምራቸውምን? አለው። ጌታችንም አዎ እነርሱ መድኃኒተኞች ስለሆኑ አልምራቸውም አለው ።” (ገድለ ገብረ መንፈስ ቅዱስ የእሁድ ንባብ ብራና ጠቅላይ ቤተክህነት ቤተ መጻህፍት)
    ይታያችሁ በኢየሱስ ክርስቶስ አዳኝነት አምኖ የተጠመቀን ክርስቲያን ሕዝብ አቡነ ገብረመንፈስ ቅዱስ ሁሉንም ማርልኝ ሲሉት ሁሉንም መውደድ የባህሪው የሆነ(omibenevalent ) “ፍቅር ሰሐቦ ለወልድ ኀያል እመንበሩ፤ ወአብጽሖ እስከ ለሞት— ፍቅር፣ ኀያል ወልድን ከዙፋኑ ሳበው፤ እስከ ሞትም አደረሰው” የተባለለት እግዚአብሔር ግን አይ ”ጎጃምን አልምርም” ብሏል ብሎ ሊያውም በሃይማኖት ስም መፃፍ ምን ይባላል ? እንዲህ ያለውን የጥላቻ ደረጃ በቃላት መግለፅ ይቻል ይሆን ? ወገኖቼ የጎጃም ሕዝብ በእንደዚህ ባሉ ፍፁም የተሳሳቱ የጥላቻ ትርክቶች ምክንያት ከፍተኛ በደል ሲደርስበት ኑሩዋል።
    4. በድርሳነ ራጉኤል ሁለተኛ ክፍል ፤ ዘሚያዚያ ቁ3 ላይ“ወበደኃሪ መዋዕል ውስተ ምድረ ጎዣም ይበዝኅ ትውልዶሙ ለሰብአ አፍርንጅ ሮማውያን ውሉደ ልዮን ካህናተ ሰይፈ አርዕድ ንጉሠ ከሐዲ
    ትርጉም- በኋላ ዘመን በጎጃም ምድር የልዮን ተከታዮች የከሐዲው ንጉሥ የሰይፈ አርዕድ ካህናት የሚሆኑ የሮማውያን ልጆች ይበዛሉ” የሚል የጎጃምን ሕዝብ በባእድነት ፈርጆ ከጎጃም ሀሳዊ መሲህ ይነሳል የሚል ክፉ ጽሁፍ ሰፍሮ ይገኛል ፡፡
    5. በ1976 ዓ.ም በአቡነ ጎርጎርዮስ 2ኛ የታተመው “የቤተ-ክርስቲያን ታሪክ” በሚለው መጽሐፍ“አልፎንሱ ሜንዴዝ የተባለ ካቶሊካዊ ቅብዓትን ለጎጃም አስተማረ” ተብሎ የተጻፈውን የውሸት አፈታሪክ መጥቀስ እንችላለን።
    በጠቅላላው ጎጃሜን መተተኛ ነው፣ ሰው ይበላል፣ ቡዳ ነው፣ ጅብ ይጋልባል የባእድ እምነት ይከተላል ወዘተረፈ የሚሉት የጥላቻ አባባሎች እና ትርክቶች ከላይ ካየናቸው መፅሐፍት የተቀዱ ናቸው።
    ዛሬስ ምን ደረጃ ላይ ነው ያለነው?
    በ1983 ትግራይና ኦሮሚያ የሚባሉ ክልላዊ መንግስታት ሲመሰረቱ ጎጃም ግማሽ ግዛቱን መተከል ተነጥቆ ገሚሱ ክፍል ብቻ በዞን ደረጃ አማራ የሚባል ክልል ውስጥ ተካተተ። ነገር ግን በኢትዮጵያ ውስጥ ከራያ እና ከባሌ ገበሬዎች አመፅ በፊት የዘውዱን ስርዓት የተቃወመውና ራሱን በራሱ የማስተዳደር ጥያቄ ያቀረበው የጎጃም ህዝብ ነበር። ከሃውዜን በፊት በኢትዮጵያ ታሪክ በራሱ መንግስት በአይሮፕላን በቦንብ የተደበደበውም ይህ አይበገሬ የጎጃም ህዝብ ነው። ለዘመናት ሲንከባለል የመጣው የጎጃም ህዝብ ጭቆና ዛሬ ላይ የግፉ ፅዋ መተከል ላይ ሞልቶ እየፈሰሰ ነው።

  2. መጽሀፍቅዱስ ውስጥ የሌለ ታሪክ በጎጃም ህዝብ ላይ መጻፍ ያሳዝናል። አማራ መጀመሪያ ራሱን ያጥራ። ስለአንድነት ከማውራቱ በፊት አንድ የሚያደርጉ ነገሮች ላይ መስራት አለበት። ስለዚህ ሁሉም አማራ በጎጃም ላይ የተጻፈውን ነውር አውግዞ በአንድ ላይ መቆም አለበት። ካለበለዚያ በአንድ በኩል እያዋረድከውና አስነዋሪ ስም እየሰጠከው እንተባበር ማለት አይቻልም። በኦርቶዶክስ ተዋህዶ በተክርስቲያን ላይ አዝኛለው። በተክርስቲያንዋም ማፈር አለባት።

Leave a Reply

Your email address will not be published.

Share