November 19, 2020
2 mins read

ተጠየቅ (ዘ-ጌርሣም)

115378255 mediaitem115379345

ተጠየቅ በህግ ፊት
ለፈፀምከው ክህደት
ቁምና ተሟገት
ሳይበየንብህ የዕድሜ ልክ እሥራት
ምስክር ከሌለህ
ዋቢም ካልቆመልህ
በወፍና ድንጋይ
ቀርበህ አደባባይ
እሰጥ አገባ በል
ከቻልክም አስተባብል
መሃላውን ፈፅም እውነቱን ተናገር
ህሊናህን ሞግት ያለ መደናገር
ተጠየቅ በህግ ፊት
ለፈፀምከው ክህደት
ቁምና ተሟገት
ሳይበየንብህ የዕድሜ ልክ እሥራት
ትናንት ሕዝብ በደልክ
የሀገር ጦር በተንክ
ከሥራም አባረርክ
ከሀገር አሰደድክ
የተፋለመህን እሥር ቤት ውስጥ አጎርክ
በጭካኔ በትር አካላት አጎደልክ
ወጣት አኮላሸህ
ጉብሏን አመከንህ
የእምነት ስዎች ደፍርክ
ሃይማኖት አረከስክ
ታሪክን
እምነትን
ባህልን
ሰብዕናን (ሰውነትን)
አቆሸሽክ
ተጠየቅ በህግ ፊት
ለፈፀምከው ክህደት
ቁምና ተሟገት
ሳይበየንብህ የዕድሜ ልክ እሥራት
ገበሬ እያሞገስክ
እሱኑ የበደልክ
መልሰህ የገደልክ
አምኖህ የኖረውን
አብሮህ የበላውን
አብሮህ የሞተውን
በቸገረህ ጌዜ አብሮህ የቆመውን
ደክሞት በተኛበት
በደረቁ ሌሊት
መከላክያውን
የሀገር መከታውን
ብሔር የሌለውን
ፖለቲካ ስልጣን የማይመኘውን
የዚያችን ድኃ ልጅ
የዚያን አፈር ገፊ የገበሬን ቀኝ እጅ
አንተን እያኖረ ለራሱ የማይበጅ
ሲያገኝ ፍርፋሪ
ሲያጣ ጦም አዳሪ
እሱ እየሞተ ሌላውን አኗሪ
በሆነው ወገን ላይ
በፈፀምከው በደል ባደረስከው ስቃይ
የጥይት እሩምታ እንዳዘነብክበት
የእጅህን አታጣም ቀኗ የመጣችለት
ተጠየቅ በህግ ፊት
ለፈፀምከው ክህደት
ቁምና ተሟገት
ሳይበየንብህ የዕድሜ ልክ እሥራት

2020-11-19

1 Comment

  1. አማራ እና ወልቃይት ጠገዴዎች አትቸኩሉ ነፃ ወጣን ብላችሁ ፈታ ለማለት። አዲስ አበቤዎችም ከዛሬ ሶስት አመት በፊት ትህነግ/ወያኔ አዲስ አበባን ለቃ ስትወጣ አዲስ አበባ ነፃ ወጣች ብለው ፈታ ማለት ጀምሮዋቸው ነበር። እያደር ነው የባሰባቸው ተረኞች መተካታቸው እና ከእስር የተፈቱት እነ እስክንድርንም ጨምሮ ነፃ አለመውጣታቸውን ወልቃይት እና ራያም ለውጥ እንዳላዩ አዲስ አበቤ የተገለጸለት።

    ስለዚህ ነፃ ወጣን ለማለት አንቸኩል ገና ብዙ ብዙ አደጋዎች በተለይ አማራ ላይ በያለበት ከአዳማ ፣ ከባህር ዳር ፣ ወለጋ ፣ አዲስ አበባ ፣ ደቡብ ጉራ ፈረዳ ፣ዳያስፖራ ሳይቀር እንኳን በማንነታችን አማራ ላይ ሞት ዙርያችንን ተጋርጦብናል። ለምን ይመስላችሁዋል የኦሮሚያ ልዩ ኃይልንም አስታጥቀው ከአማራ ልዩ ኃይል አጠገብ እብረው ያላሰለፉት?

    አንዘናጋ!

    ሁሉም ለአንዱ ፡ እንዱም ለሁሉም!!!

Leave a Reply

Your email address will not be published.

Previous Story

ሰይጣን ለወያኔ እጅ ሰጠ! – ይነጋል በላቸው

Next Story

” ኦሮማይ ! ”  በቋንቋ ና በዘር መቧደን አከተመ፡፡… – መኮንን ሻውል ወልደጊዮርጊስ

Latest from Blog

አስቸኳይ ህዝባዊ ጥሪ

July 24, 2024 ዓለማቀፍ ትብብር ለኢትዮጵያዊያን መብት Global alliance for the Rights of Ethiopians (GARE) በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ገዜ ጎፋ ወረዳ ኬንቾ ሳቻ ጎዝዲ ቀበሌ በደረሰው የመሬት መንሸራተት የብዙ ወገኖቻችንን ህይዎት ማለፉን
Go toTop