ለኢትዮጵያ ሕዝቦች የውይይት መድረክ – ጆቢር ሔይኢ ከሁስተን ቴክሳስ

የእግዚአብሔር ቃል፣”ሰላምን የሚያወርዱ ብፁዓን ናቸው የእግዚአብሔር ልጆች ተብለው ይጠራሉና።ምሕረትን የሚያደርጉ ብፁዓን ናቸው፣ምሕረትን ያገኛሉና”ይላል።ይህን የአምላካችንን ቃልና ፈቃድ ተከትለን እውነተኛ ዕርቅ ለመፈጸም፣እኛም እውነቱን በግልፅ መነጋገር ይገባናል።

ኢትዮጵያ አገራችን የብዙ ብሔር ብሔረሰቦች አገር ናት፡፡ የብሔር፣ የብሔረሰብና የሕዝቦችን መብት ደግሞ  በእኩልነት መከበር አለበት። ይህም የሰው ልጆች ሁሉ የእኩልነት መብት በተባበሩት መንግስታት ድርጅት ቻርተር የተደነገገ፣ በአባል አገሮች ፊርማ የጸደቀ ነው። በዚሁ ድንጋጌ መሠረት ነው፣በዙዎች አገሮች ከቅኝ ግዛት ነጻ የወጡት፡፡

አገራችን  ይህን ድንጋጌ ፈርማ የተቀበለች አገር ናት።ስለዚህ ሕዝባችን ከእንግዲህ ዴሞክራሲያዊ መብታቸውን ላማስከበር ሲሉ ትጥቅ አንግበው በረሓ ለበረሓ ሊንከራተቱ አይገባም።

እስከ እሁን በአገራችን  የሰፈነው ሁኔታ ሲታይ፣ ሁላችንም የምንወደው ራሳችንን፣ ቋንቋችንን፣ ባኅላችንን፣ ታሪካችንን፣ እምነታችንን ፣ጥቅማችንን በአጠቃላይም የኔ የሚንለውን ሁሉ ነው። ከሌላውም የምንሻውም  ሰው ሁሉ፣ዓይኑን ጨፍኖ፣ የራሱ የሆነውን ሁሉ ንቆ፣ ለእኛ ብቻ የሚጠቅመውን መርጦ፣በማድነቅ እንዲያጅበን ነው።

የፌድራሊዝም ሥርዓት ለአገራችን ያስፈለገውም፣ በሕዝቦች መካከል ሥር ሰዶ የቆየውን የብሔር ጭቆና በማስወገድ፤ በእኩልነት ላይ የተመሰረተ አንድነትና ሰላምን ለማስፈን ነበር።ይህ ነበር የቀደመው የኢሕአዴግ ዓላማ።ለወደፊቱም ቢሆን ከኢትዮጵያ ሕዝቦች መካከል ቅራኔዎች ተወግደው ፍቅር፣ ስላምና ኅብረት እንዲሰፍን ከፈለገን፣ከራስ ወዳድነት ተላቀን፣   የጭቆና ፈርጆችን ሁሉ በጋራ መታገል ይገባናል።

በዚህም ረገድ፣ ከንድ መቶ በላይ የሆኑ  የፖለቲካና የብሔር ድርጅቶች ተስባስበው በተወዳዳሪ ፓርቲነት ለመደራጀት ተዘጋጅተዋል። የኢሕአዴግ አባላትም ለሁለት ተከፍለው በሥልጣን ሽሚያ ውስጥ ገብተዋል።ከዚሁ የተነሳ ሕዝባችንም በሦስት ጎራ ተሰልፏል።ይህም  የመደመር ጎራ፣ የሕገ መንግሥትና የፌድራሊዝም ጎራና፤የአሐዳዊ መንግሥት ጎራ ናቸው።

በዚህ ላይ የብልፅግና ፓርቲ አንዳንዴ ከአሐዳዊያን ጋር  ሲደመር፣በሌላ ጊዜ የብሔር ጥያቄን በመመለስ ከፌድራል ኃይሎች ጎን  ሲቆም ይታያል።በምርጫ ረገድም አሁን ይደረግ በሚሉትና፣ የኮቪድ በሽታ ሥጋት ከተወገደ በኋላ ይደረግ በሚሉት መካከል ልዩነት ተከስቷል።ይህ የፖለቲካ ፓርቲዎች የሥልጣን ጥያቄ ነው።ምርጫው ዘግይቶም፣ድርጅታዊ አሠራር ቀርቶ ሕዝቡ የሚፈቅደውን ተወዳዳሪ በነጻነት ለመምርጥ ከቻለ እጅግ ጥሩ ነው።

ስለሆነም ይህንና መሰል ችግሮችን ለመቅረፍ ያለን ምርጫ አንድ ነው፣ይኸውም ከአሓዳዊያን ጎን በመሰለፍ የብሔር ጭቆና እንዲቀጥል መፍቀድ፤ ወይንም ደግሞ ከፌድራሊስት ኃይል ጋር በመቆም፣  የጭቆና ፈርጆችን ሁሉ ማስወገድ ይሆናል።

ለዚህም ጎራ በመለየትና  የጠራ አቋም ይኖረን ዘንድ፣ በቋንቋ አጠቃቀም ላይ ግልጽ ውይይት ማድረግ ይገባናል።     ይህም፦          ሀ/ የኢትዮጵያ ፌድራል ዴሞክራቲክ ሪፑብሊክ መንግሥት የትምሕርት፣ የምርምርና የሥራ ቋንቋ እንግሊዘኛ እንዲሆን በመፈቅድ የቋንቋ አድሎንና ልዩነትን ማስወገድ፣

ለ/ እንግሊዝኛ ቋንቋ ለማይችሉት፣ በአማርኛ፣ በአፋንኦሮሞ፣ በትግርኛ፣በፈረንሳይኛና በአረቢኛ የትርጉም አገልግሎት መስጠት፣   ሐ/ብሔራዊ መስተዳድሮች፣የክልል መስተዳድሮች፣ብሔራዊ ዞኖችና ብሔራዊ ወረዳዎች በክልላቸው በመረጡት ቋንቋ የመጠቀም  መብት ማረጋገጥ፣

መ/ ሰው ሁሉ በሕግ ፊት እኩል በመሆኑ፣ከብሔሩ፣ ከቋንቋው፣ ከጾታና ከእምነት የተነሳ ልዩነት እንዳይደረግበት ሕገ መንግሥዊ ጥበቃ  መስጠት፣

ሠ/ የየክልሉን ቋንቋ ለማያውቁ ነዋሪዎች፣በመንግሥታዊ ተቋሟት ሁሉ፣ነጻ የትርጉም አገልግሎት መስጠትን የሚያጠቃልል ሊሆን ይገባዋል።

መደበኛ ትምህርትን በሚመለከት፣የአንደኛና የሁለተኛ ደርጃ ትምሕርት ቤቶችና ኮሌጆች፣እንዲሁም የግል የትምሕርት ተቋሟት በሙሉ በክልል አስተዳደር ስር መዋል ይገባቸዋል። ከፍተኛ የትምሕርት ተቋሞች  ፈተና የማውጣትና ተማሪ የመመልመል፣ መብታቸው ሰፍቶ በትምሕርት ሚኒስቴር አስተዳደር ስር ሊውሉ ይገባል።

ሕገ መንግሥትን በሚመለከት፤ማንም ቢሆን  በአንድ ጊዜ የጠራ  ሕገ መንግሥት የቀረጸ አገር የለም።ነባራዊ ሁኔታ ሲለወጥ ሕግ መንግሥቱም ከሁነታው ጋር መጣጣም ይኖርበታል።ስለዚህም በቅድሚያ  ሕዝባችን በክልሉ የራሱን ሕገ መንግሥት አውጥቶና አጽድቆ ሊመራበት ይገባል። የፌድራል ሕገ መንግሥትም የክልሎቹን ሕገ መንግሥት መሠረት በማድረግ ሊሻሻልና በውሳኔ ሕዝብ ሊጸድቅ ይገባዋል።

በዚህ መልኩ የሕዝባችን ጥያቄዎች ቢፈቱ በሕገ መንግሥቱ ላይ የሚነሱ ጥያቄዎች ምላሽ ያገኛሉ። ከሕዝባችን መካከል ጥላቻ ይወጋዳል።መፈነቃቀሉ ያከትማል። መንግሥትም በሕዝቡ ላይ ፈላጭ ቈራጭ መሆኑ ይቀራል።የክልል ፓርቲዎችና የብሔር ድርጅቶችም  እስከ ምርጫው ወቅት ድረስ፣ሕገ መንግሥቱን በማሻሻል፣ ኅብርተሰቡን ለማገልገል ያስችላቸዋል።

የኢሕአዴግ የንብረት ክፍፍልን በሚመለከት፣እንደ እውነቱ ከሆነ ኢሕአዴግ የኢትዮጵያን  ሕዝብ ቢያንስ ለ27 አመታት አስተዳድሯል።በዚህ ጊዜ በውሳኔው አግሪቱን የባሕር በር አሳጥቷል፣በባድመን ጦርነትም የወንድማሞችን ደም አፋሷል። በልማት ረገድም አገሪቱን  ከኋላቀርነት አላቋል፣የትምሕርት፣የጤናና የትራንስፖት አገልግሎትን አስፋፍቷል፣ ከተሞችን አስውቧል። በዚህም ወቅት የተሰረቀና በጉልበት የተዘረፈ ሀብት ተጣርቶ፣ ከእዳ ነጻ የሆነውን  የግባሩን የወል ሀብት ሊከፋፈሉ ይገባል።

እንግዲህ ይህ  ያለመድሎ ፤በአገራችን የግለ ሰብ፣ የብሔረ ሰብና፣ የብሔር እኩልነትን  ለማስፍን የታቀደ በመሆኑ፣ትልቁም ሆነ ትንሹ ያለፈውን ጥላቻና ቅሬታውን  በይቅርታ በማለፍ፣ ከልብ  ሊተባበር ይገባል።ስለዚህም የሰላም አምላክ የሆነው እግዚአብሔር ከመለያየትና ከእርስ በርስ ጥላቻ አላቆ፤ በወንድማማች  ፍቅር አስማምቶ፣ በሰላም አብረን የምንኖርበትን ጸጋውን ያብዛልን።

ጆቢር ሔይኢ ከሁስተን ቴክሳስ፣

4 Comments

 1. እውነተኛ ዕርቅ ለመፈጸም፣እኛም እውነቱን በግልፅ መነጋገር ይገባናል።

 2. የባልደራስ ለእውነተኛ ዴሞክራሲ ፓርቲ በአዲስ አበባ የሚደረገውን የመሬት ቅርምት አወገዘ።

  የመሬት ዝርፊያ በአዲስ አበባ ነው!
  የመሬት ዝርፊያ በአዲስ አበባ !አዲስ አበቤ ንቃ!

  አዲስ አበቤ ንቃ!ንቃ!ንቃ!ንቃ!ንቃ!ንቃ!ንቃ!ንቃ!ንቃ!ንቃ!ንቃ!

  #አፓርታይዱ #ኦዴፓ #አዲስ #አበቤ #ለፍቶ #የቆጠበውን #ኮንዶሚኔም #ዘረፈው !!

  ከንቲባ ታከለ ኡማ ፍርድ ቤት እናቆመዋለን!! ፍትህ ለአዲስ አበባ ድሆች እንጠይቃለን በሪከርድ ይመዘገባል ነገ ሂሳብ ያወራርዳል።
  ///
  የአዲስ አበባ ነዋሪ አፈር ልሶ ቆጥቦ በሰራው ቤት ከዝዋይ አምቦ እና ባሌ የኦሮሚያ ክልል የመንግስት ሰራተኞች አደራጅተህ የሰዉ ቤት ማደል ከወንጀልም በላይ አደገኛ ዘረኝነት ነው። የተሰጡ የኮንዶሚኒዮም ቤቶች በአስቸኳይ ይታገድ በማለት በፍ/ቤት እንጠይቃለን ም/ከንቲባ ታከለ ኡማ በፍትህ አደባባይ እናቆመዋለን።
  በአዲስ አበባ ነዋሪ የተጫነ ሕገ ወጡ የከተማው አስተዳደር ም/ከ ታከለ ዑማ ያለ ህዝብ ምርጫና ይሁንታ በኦህዴድ ፍቃድ በከንቲባነት ከተቀመጡበት ዕለት አንስቶ በመመሪያ ለአንድ ብሔረሰብ አባላት ከዛም በታች ለፓርቲ ተቧዳኝ ግለሰቦች ያስተላለፏቸው የኮንዶሚኒዮም የጋራ መኖሪያ ቤቶች በፍትህ አደበባይ እንፋረደዋለን ሕግ ካለ የተሰጡት መኖሪያ ቤቶች በአስኳይ ይታገድ! ጥያቄ እናቀርባለን።

  አዲስ አበቤዎች ከዕለት ቀለባቸው ቀንሰው በቀን አንዴ አየበሉ ነገን የተሻለ ለማድረግ ያደረጉት የአንድ ጎረምሳ ዕድሜ ተስፋ ዛሬም በሕገወጡ ከንቲባ ታከለ ዑማ መሪነት ያለሃፍረት መንገዱን ስቷል ዘረኝነቱ ተባብሷል።

  እስካሁን ድረስ በሕገወጡ ከንቲባ ከ33 ሺህ በላይ በአዲስ አበቤዎች የቁጠባ ብር የተገነቡ የጋራ መኖሪያ ቤቶች ለተፈናቃይ #አርሶ አደሮችና #ለብልፅግና ፓርቲ ታማኝ ቅጥረኞች ያለሀፍረት ተስጥቷል።

  ዛሬም! ሕገ ወጡ ከንቲባ ታከለ ዑማ 10 ሺህ ብር ለዕጣ በማስከፈል ከ14ሺህ በላይ የጋራ መኖሪያ ቤቶች #ከቦሌ ፕሮጀክት 4 በቀን 16/10/2012( በትላንትናው ዕለት ) ከ 14 ሺ በላይ የጋራ መኖሪያ ቤቶች #ለኦሮምያ ቢሮ ሰራተኞች ባሳፋሪ ሁናቴ ተሰጥቷል።

  በመሪ ሳይት በቦሌ ቡልቡላ በሰንጋ ተራ (ሜክሲኮ) እንዲሁም በሌሎች ሳይቶች ገንዘብ ከፍለው ለዓመታት አየተጠባበቁ ያሉ የአዲስ አበባ ከተማ ኗሪዎችን በመናቅ ለተመረጡ የአንድ ብሔረሰብ አባላት ለመስጠት ዝግጅቱ እንደተጠናቀቀ መረጃው ደርሶናል።

  በመሆኑም የአገሪቱ ፍ/ቤቶች ይህንን ፍፁም ሕገ ወጥ ድርጊት ስለ ድሆች እንባ ሲል ባስቸኳይ የዕግድ ትዕዛዝ በማውጣት እንዲያስቆም እንጠይቃለን!!

  በዚህ የቅሬታ አቤቱታ ላይ የበኩልዎን ይወጡ
  ባልደራስ በአዲስ አበባ ውስጥ አምስት ቢሮዎች ያሉን ሲሆን ለእርስዎ በሚቀርብዎ ቢሮ በበምጣት መመዝገብ ይቻላል።

  1.ስድስት ኪሎ ቢሮ፡- መድሃኒአለም መስካይዙና አካባቢ ብራይት ኮሌጅ 3ኛ ፎቅ ስልክ፡- 09 05 00 25 25

  2.መገናኛ ቢሮ፡- ገነት ኮሜርሻል 6ኛ ፎቅ
  ስልክ ፡- 09 19 39 50 02

  3.ሜክሲኮ ቢሮ፡- ልደታ ባልቻ ሆ/ል አህመድ የገበያ አዳራሽ 3ኛ ፎቅ ስልክ፡- 09 62 72 52 84

  4.መርካቶ ቢሮ ፡- መሳለሚያ እህል በረንዳ ውልና ማስረጃ 2ኛ ፎቅ ስልክ ፡- 09 11 68 12 40

  5.አቃቂ ቃሊቲ ቢሮ፡- ወረዳ 8 ካፍደም 2ኛ ፎቅ ስልክ ፡- 09 68 05 38 43

  ለተጨማሪ መረጃ
  ስልክ: 09 05 00 25 25/0963159763 ይደውሉ።

  መልእክት
  አዲስ አበቤ ንቃ!ንቃ!ንቃ!ንቃ!ንቃ!ንቃ!ንቃ!
  ንቃ!ንቃ!ንቃ!ንቃ!ንቃ!ንቃ!ንቃ!ንቃ!ንቃ!ንቃ!

 3. መልስ ለአቶ ጆቢር ሔይኢ

  ከላይ በተጠቀስው ርእስ በጽሑፉ አቅራቢ የቀረበውን አስተያዬት በዘ/ሐበሻ ድረገጽ ወጥቶ አንበብኩኝ ስለሰላምና ምሕርት የእግዚአብሔርን ቃል ጠቅሰው እውነተኛ እርቅን ለማምጣት እውነቱን በግልጽ መነጋገር እንዳለብን መግለጻቸውን አደንቃለሁ ።
  አገራችን ኢትዮጵያ ጸሐፊው እንዳሉት የቋንቋ ፣ የባህል ፣ የእምነትና ወዘተ ብዝሀነት ያላቸው ( ከሰማኒያ በላይ ቋንቋዎችና ወደ መቶ ሃያ የሚሆኑ ዲያሌክቶች ያሉባት) ዜጎች አገር ነች ። የሰው ልጆች ሁሉ የእኩልነት መብት በተባበሩት መንግስታት ድርጅት ቻርተር በተደነገገው መሰረት መከበር አለበት ያሉትም ለጥያቄ የሚቀርብ አይደለም ። ይህንን እውን ለማድረግ በ21ኛው ክፍለዘምን መገዳደልም የለብንም በሰለጠነ መንገድ ለሁሉም የሚበጅ አማራጮች በኤሊቶች ቀርበው ሕዝቡ መክሮበት ቁመት ሳንለካካ ብዙኃኑም ሆነ አናሳው የሕብረተሰባችን አካል እንደ ግለሰብ ያልተሸራረፈ መብቱ በእኩል እንዲረጋገጥ መጣር ይኖርብናል ።
  ጸሐፊው ሀቅን ተናግረን እውነተኛ እርቅና ሰላምን እናውርድ ብለው ነበር ጽሑፋቸውን የጀመሩት ነገር ግን ከአንድ ሀረግ በላይ ሳይጽፉ በታሪክ አጋጣሚ የብሔረሰብ አባልነታቸው ተጽእኖ ሳያሳድርባቸው የቀደሙት ነገሥታት በሙሉ የቤተመንግሥት ቋንቋቸውን አማርኛ የማድረጋቸው ሳይንሳዊ አመክኒዮ መኖሩ እየታወቀ አማራ ገዛን በሚል የውሸት ትርክት ቋንቋው በሌሎች ላይ የተጫነና የብሔር ጭቆና እንደነበረ የሀሰት ትረካ ማቅረባቸው አስገራሚ ነው ።
  ሁሉም የሕብረተሰባችን አባል ቋንቋውን ፣ ባህሉን እምነቱንና ወጉን ለማሳደግ መጣሩ ተገቢ ነው ሊከበርለትም ይገባል ይህ መብት ማንም የሚቸረው ስጦታ ሳይሆነ ተፈጥሮአዊ ነው ። እነኝህና ሌሎችም ያልተዘረዘሩት ኢሴቶቻችን እንደ አንድ ሀገር ዜጋ የጋራ ታሪኮቻችን ፣ የጋራ ሀብትና ንብረቶቻችን እና የማንነት መገለጫዎቻችንም ጭምር ናቸው ።
  „የፌድራሊዝም ሥርዓት ለአገራችን ያስፈለገውም፣ በሕዝቦች መካከል ሥር ሰዶ የቆየውን የብሔር ጭቆና በማስወገድ፤ በእኩልነት ላይ የተመሰረተ አንድነትና ሰላምን ለማስፈን ነበር።ይህ ነበር የቀደመው የኢሕአዴግ ዓላማ“ ብለው ያሉት እጅግ በጣም የሚያሳዝንና በሰው ቁስል እንጨት እየሰደዱ የሚቀልዱ ነው ያስመሰለቦት ምክንያቱም በቀደመው ኢሕአዴግ ህይወታቸውን ያጡ ግለሰቦቹ በህይወት ባይኖሩም የቅርብ ዘመዶቻቸው አሉ ፤ አካለጎዶሎ ሆነው በህይወት ያሉ አሉ ፤ ተሰደው በባእድ አገር የሚንከራተቱ ወንድምና እህቶቻችንም ህያው ምስክሮች ሆነው እያሉ ፣ ከቄያቸው ተፈናቅለው ሜዳ ላይ የቀሩና በጎሣ ፖለቲካው ምክንያት የተላለቁ ዜጎች መኖራቸው እየታወቀ የኢሕአዴግ ዓላማ አንድነትና ሰላምን ለማስፈን ነው ማለትዎ ለምን አይነቱ አንባቢ እንደጻፉ አልገባኝም ።
  „ለወደፊቱም ቢሆን ከኢትዮጵያ ሕዝቦች መካከል ቅራኔዎች ተወግደው ፍቅር፣ ስላምና ኅብረት እንዲሰፍን ከፈለገን፣ከራስ ወዳድነት ተላቀን፣ የጭቆና ፈርጆችን ሁሉ በጋራ መታገል ይገባናል“ ። ትልቅ አባባል ነው ግን ውሸትን እውነት በማስመሰል ሳይሆን ለእውነት በእውነት በመቆም መሆን አለበት ። ከባለቤቱ ያወቀ ቡዳ ነው እንዲሉ የቀደመው ኢህአዴግ አሸባሪው ፣ ጸረ ሕዝብ፣ ወንጀለኛና ጸረ ዲሞክራሲው እኔ ነበርኩ ብሎ ባደባባይ ዶክተር አብይ ይቅርታ በጠየቁ በሁለት አመቱ ዓላማው ሰላምን ማስፈን ነበር ሲሉ የማስታወስ ችግር እንዳለቦት ካልሆነም የተገፉ የቀደመው የኢህአዴግ ባለስልጣን መሆንዎትን ያሳብቃል ።
  መሬት ላይ ያለውን ተጨባጭ ሁኔታ ለማመላከት በሚመስል ሁኔታ በአገራችን ተመስርተው ከሚገኙ ከመቶ በላይ ፓርቲዎች በተጨማሪ ሌላ ከንድ መቶ በላይ የሆኑ የፖለቲካና የብሔር ድርጅቶች ተስባስበው በተወዳዳሪ ፓርቲነት ለመደራጀት እንደተዘጋጁ ገልጸዋል መብታቸው ነው ይችላሉ። እህአዴጎች ለሁለት ተክፍለው የስልጣን ሽሚያ ውስጥ ገቡ የሚለው አባባልም እውነቱን ገላጭ አይደለም ምክንያቱም ለሁለት አልተከፈሉም የቀደመው ኢህአዴግ ከሕዝባዊ ማዕበል ለመሸሽ በአዋሳው ስብሰባ ውህደት ለመፍጠር ከተስማሙ በኋላ ህወሐት እንደለመደው በሪሞት ኮንትሮል የሚመራውን ግለሰብ ለማስቀመጥ ያደረገው ጥረት ሲከሽፍበት በውህደቱ ሳይስማማ ቀርቶ ቢቻውን ተገነጠለ እንጂ ኢህአዴግ ለሁለት አልተከፈለም ። የስልጣን ሽሚያው እንዳሉት አለ ያለውም በተገነጠለው በህወሀትና የዳቦ ስም ባወጣው ብልጽግና መካከል ነው።
  የኢትዮጵያን ሕዝብ በሶስት ጎራ ስለመክፈልዎ ፦
  የኢትዮጵያን ሕዝብ ባጠቃላይ ወስዶ ሶስት ከረጢት ውስጥ መክተቱ ትክክል አይስለኝም ነገር ግን ህዝቡን እንወክላለን ብለው ተቋቁመው የሚንቀሳቀሱ ድርጅቶች ይብዛም ይነስ የየራሳቸው ኮንስቲትውንሲ ስለሚኖራቸው በዚያ አስተካክዬ ልውሰደው። የመደመር ጎራ ያሉት አሁን ለውጡን እየመራሁ ነው የሚለውን ብልጽግና እንደሆነ ፣ የሕገ መንግሥትና የፌድራሊዝም ጎራ ያሉት ደግሞ በህወኃት መሪነት የቀድሞ ተለጣፊ ድርጅቶችና ጽንፈኛ ብሔርተኞች ሲሆኑ ፤ የአሐዳዊ መንግሥት ጎራ ናቸው ያሏቸው ግን እነማንን ለማለት እንደፈለጉ ግልጽ አይደለ ምክንያቱም ህብረብሔራዊ በሆነችው ሀገራችን ያሉትን ማህበራዊ ፣ ኢኮኖሚያዊና ፖለቲካዊ ችግሮቻችንን ለመፍታት የሚያስፈልገው መንግሥታዊ አወቃቀር ፌደራሊዝም አይደለም ብሎ ፕሮግራም ነድፎ የሚንቀሳቀስ የፖለቲካ ድርጅት እስካሁን አላየሁምና ነው ።
  ከሌሎች ተሞክሮ ብናይ ህብረብሄራዊ ሆነው በአሀዳዊ የመንግሥት አወቃቀር ጅግሮቻቸውን ፈተው ዲሞክራሲን ያሰፈኑ አገሮች አሉ በፌደራላዊ የመንግሥት አወቃቀር ዲሞክራሲያዊ ማህበረሰብ የገነቡ አገሮችም አሉ ወሰኙ በቅንነትና በቆራጥነት የሁሉንም መብት የሚያስከብር ዲሞክራሲያዊ ስርአት ለመገንባት የሚያስችለን ከሀገራችን ነባራዊ ሁኔታ አንጻር የቱ ነው ብለን መክረንና ዘክርን መሆን ያለበት ነው ።
  የሀገራችንን ነባራዊ ሁኔታ ግንዛቤ ውስጥ አስገብተን የትኛው የመንግሥት አወቃቀር ችግሮቻችንን ለመፍታት ያገለግለናል ካልን በእኔ እይታ የፌደራል አወቃቀር ቢሆን ይበጃል የሚል ነው ። ምክንያቱም እንደ ኢትዮጵያ ህብረ ብሔራዊ ለሆኑ አገሮች ዘርፈ ብዙ የሆኑ (የቋንቋ ፣ የባህልና ወዘተ) ልዩነቶች ላላቸው የህብረተስብ አካላት ልዩነታቸውን ዲሞክራሲያዊ በሆነ መንገድ ለማስተናገድ የሚያስችል መንግሥታዊ አወቃቀር በመሆኑ ነው ። ይህ ማለት ግን የህወኃት መንግሥ ሰፊውን የኢትዮጵያ ሕዝብ በጎጥ ከፋፍሎ ለመግዛት የመሰረተው በዓልም የለለ የጎሣ ፌደራሊዝም ማለት አይደለም ። ይህ የውሸት ፌደራሊዝም ለ27 ዓመታት የነበሩንን የጋራ ኢሴቶች አውድሞ ለጥላቻና ለመገዳደል ዳርጎናል ። ከጸሐፊው አቀራረብ ለመረዳት የቻልኩት እንደ ብሔርተኞቹ በጎሣ የተከፋፈለ ካልሆነ የአስተዳደር አመችነት ፣ ለእድገት መቹነት ፣ የጂኦግራፊ አቀማመጥና ወዘተ መስፈርቶችን ተጠቅሞ ፌደራል መንግሥት ማዋቀርን እንደ አሀዳዊ መንግሥት በመቁጠር ሕዝብን ውዥንብር ውስጥ ለመክተት ይሞክራሉ ። ይህም ያለምክንያት አይደለም እንደ ህወሐት የተደበቀ አጀንዳቸውን ለመተግበር ነው ።
  ከሁሉ በላይ የጸሐፊውን ማንነት ያጋለጠውና ለሕዝባችንም ሆነ ለአገራችን ጥቅም ያልቆመ የባእዳን ተላላኪ መሆኑን ያረጋገጠው ኩሩ የሆነው ሕዝባችን ያፈራው የራሱ ቋንቋ ፣ ባህልና ታሪክ እያለው እንደ ቂኝ ተገዢ የራሱን ቋንቋ ትቶ የትምሕርት፣ የምርምርና የሥራ ቋንቋ እንግሊዘኛ እንዲሆን በመፈቅድ የቋንቋ አድሎንና ልዩነት ይወገዳል ማለታቸው ነው ። ምናልባት የጻፉት ቴክሳስ ሆነው በመሆኑ ኢትዮጵያ ከቴክሳስ ጋር ተምታቶባቸው ይሆን ?

  ከድሉ ዘገዬ

 4. መልስ ለአቶ ጆቢር ሔይኢ

  ከዘገዬ ድሉ

ሀሃሳብ እና አስተያትዎን ይስጡ

Your email address will not be published.