ክፍል ሁለት፣ ምዕራፍ ሁለት
አብርሃም ያየህ
“አቶ ኢሳያስ አፈወርቂና ሌሎች የህዝባዊ ግንባር ለፍትህና ለዲሞክራሲ መሪዎች በሁለቱ ሀገሮች [ኢትዮጵያና ኤርትራ] መካከል ያለው ወሰን ትርጉም የሌለው በመሆን ላይ ነው እስከማለት ደርሰው ነበር። ጥቂት የግንባሩ ከፍተኛ ካድሬዎች በመጨረሻ ኤርትራና ኢትዮጵያ በፌደሬሽን መሰረት ላይ የሚተባበሩበት [የሚተሳሰሩበት] ሁኔታ እስከሚፈጠር ድረስ የውህደትና የኮንፌደሬሽን መዋቅሮች እየተጠናከሩ መራመድ እንደሚኖራቸው ሃሳብ ሰጥተዋል”
(ዶ/ር ተስፋፅዮን “የህዝባዊ ግንባር ለፍትህና ለዲሞክራሲ” ሲሉ የጠቀሱት አሁን በሥልጣን ላይ ያለው የኤርትራ ገዢ ፓርቲን (ህግደፍ) ነው። የዶ/ር. ተስፋፅዮን ገለፃ የኤርትራ መንግሥት ለወያነ መንግሥት አቀረብኩት የሚለው የፌደሬሽን ሃሳብ ከግጭቱ በፊት ያቀረበ መሆኑን በሚገባ ይገልፀዋል።)
እንግዲህ፣ የዚህ ምዕራፍ የመጀመሪያውን ነጥብ ከማጠቃለላችን በፊት ጭብጦቻችንን ጨምቀን እንያቸው።
1. በዚህ በያዝነው “ክፍል ሁለት” በምዕራፍ አንድ ላይ እንደተመለከተው ባንድ በኩል ፕሬዚዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ ካሜሪካ ሬዲዮ ጋር ያደረገው ታሪካዊ ቃለመጠይቅና፣ የፕሬዚዳንት ኢሳያስ ቀኝ እጅና የፖለቲካ አማካሪ የሆነው አቶ የማነ ገብረአብ በዋሽንግተኑ ስብሰባችን ላይ የሰጠው ሰፊ ማብራሪያ በማያወላውል መንገድ ሁለት ጭብጦች አስጨብጦናል።
2. በዚህ ምዕራፍ ከላይ እንዳስቀመጥነው፣ የኤርትራው ገዢ ፓርቲ በጉባዔው ውሳኔ ተመስርቶ ያስተላለፈው ኦፊሴላዊ መግለጫና፣ ክቡር ወንድማችን ዶ/ር ተስፋፅዮን መድሓንየ በጦቢያ መጽሔት ላይ ባሰፈረው ሐቅ መሰረት ደግሞ ሌሎች ሁለት መጋቢ መረጃዎች ጨብጠናል።
Read Full Story in PDF