October 13, 2013
28 mins read

ስለ ተስፋዬ ገ/አብ ስለተባለው እኔ የምለው “ከዲያቆኑ የጳጳሱ” – ከዳንኤል ገዛኸኝ (ጋዜጠኛ)

ከዳንኤል ገዛኽኝ አትላንታ

ቀደም ብሎ የብርሃኑ ዳምጤ አባ መላ…ለጥቆ የዳዊት ከበደ- አውራ አምባ ከዚያም የጅዋር መሃመድ “ ፈርስት ኦሮሞ” ጉዳይ ከመዘጋቱ የተስፋዬ ገ/አብ ጉዳይ መራገብ ከጀመረ እነሆ ቀናትን እያስቆጠረ ነው። ፌስቡከኛዎች…የፓልቶክ ጉዋዳዎች ነገሩን ይቀባበሉት ጀምረዋል። የሆነው ሆኖ ግን የጀዋርን ያህል ግን ሙሉ ለሙሉ ብዙዎቹ ከሹክሹክታ ባሻገር ፊትለፊት ሊሄዱበት አልከጀሉም። ነገርን ከስሩ እንዲሉ ጉዳዩን በአግባቡ ያልተመለከቱት እንዲሁ በስሜት ያሻቸውን ማለት ጀምረዋል በተስፋዬ ጉዳይ። የበግ ለምድ የለበሱ ተኩላዎች የወያኔ ደጋፊ የሆኑ ድረ-ገጾችም “የውሻ ጥል ለቀበሮ ሰርግዋ ነው” እንዲሉ ነገሩ ጥሩ አጋጣሚን የፈጠረላቸው ሆኖዋል። ከዚህ ባሻገር ጉዳዩን በተመለከተ በግልጽ ወደ አድማጭ በማምጣት ተዋንያኖቹን ለማነጋገር ከሞከሩት ውስጥ ህብር ሬድዮ ይጠቀሳል ምንም እንኩዋን ዘገባው ሙሉ እንዳይሆን ባለጉዳዮችን ማካተት ባይቻልም። ህብር ሬድዮ መሞከሩን አውቃለሁ ባይሳካለትም። ህብር ሬድዮ ከሁሉም ቀድሞ ጉዳዩን ሊሄድበት የቻለውም… “የሃገር ጉዳይ ይቀድማል…” ከሚል እሳቤ እንደሆነ የሬድዮው ፕሮዱውሰር ነግሮኛል። ለነገሩ ከላይ የጠቀስኩዋቸውን ለ አብነቱ ለመንደርደሪያ ያህል ላንሳ። አባ መላ የወያነ ደጋፊ ቁዋሚ ተከራካሪ ነበረ። ነገር ግን ወያኔን አውግዞ በቃህ እምቢ ለወያኔ ማለት ሲጀምር እሰየሁ ከማለት ይልቅ እንዳውም የጋበዘውን ሚዲያ ማጥላላት ተጀመረ። አስታውሳለሁ ዳዊት ከበደ አውራ-አምባ በሱ መድረክ ቢጋበዝ ወጅብኝ ወረደበት እኔ እንዳውም በጊዜው መድረክ የተነፈገው ዳዊት አባ መላ ዘንድ አይደለም አባ ገዳ ዘንድ ቢቀርብ ሃጢያቱ ምኑ ላይ ነው ብዬ ተከራከርኩ በጦማሬ። የሆነው ሆኖ የዴቭ አውራ አምባ ጉዳይ የተለየ ነገር ከወደሁዋላ አመጣ እንጂ ግን ግን እንደሚዲያ የግራ ቀኙን መዘገቡ ባይከፋም ያቺ የዶክተሩ የስልክ ሚስጥራዊ ንግግር ላይ ግን ዴቭ ጭቦ ሰራ። ያም ሆነ ይህ ዴቭ ወያኔ ከሃገር አባረረኝ ካለ ወደሃገሩ ይመለስ ዘንድ ትንሳኤውን ለማምጣት የሚታገልን ድርጅት የማሪያም ጠላት ማድረጉ አልተመቸኝም በዚህ አውግዤዋለሁ ግን ዴቭ ሃሳቡን የመግለጽ ነጻነቱን ባከብርም።

የሆነው ሆኖ ግን ከሰሞኑ በተስፋዬ ዙሪያ ጽሁፋቸውን ጀባ ያሉን ጸሃፊው የተከበሩ ዳኛ ወልደሚካኤል መሸሻ በመጸሃፍ መልክ ሊያወጡት አስበው በሁዋላም ለድረገጾች ሲሳይ ያደረጉት ጉዳይ በምን መመዘኛ ለመጸሃፍ ሊሆን እንደታሰበም ለኔ ፈጽሞ ሊገባኝ አልቻለም። እንዲያውም ጉዳዩ ተራ ግለሰባዊ ጉዳይ ሆኖ ሳለ ሃገራዊ አጀንዳ ያለው ጉዳይ እንደሆነ አድርጎ ደርዝ ለማስያዝ መሞከሩ አሳዝኖኛል። በበኩሌ የሃገር ጉዳይ ይቀድማል ትክክል ነው። ሆኖም ግን የግለሰቦችን ጉዳይ ወይንም በግልጽ ቁዋንቁዋ የግለሰቦችን ጸብ በሃገር ጉዳይ ስም ማንሳት ተገቢ አይደለም ባይ ነኝ። ባይሆን ዳኛው መጽሃፍ ሊወጣው የሚችል እርሳቸው በፍላጎት ይሁን ተገደው የሰሩዋቸው የዳኝነት ተግባሮች አሉ ከደርዘን በላይ።

ሲጀመር…

ዳኛ ወልደሚካኤል አስቀድመው በጽሁፋቸው መግቢያ ላይ ስለራሳቸው ስም እና የዳኝነት ዝና እየደረደሩ ጀብዳዊ ታሪካቸውን ሊንደረደሩበት ሞከሩ። በስተሁዋላም የደራሲ እና ጋዜጠኛ ተስፋዬ ገ/አብን ስብእና የሚነኩ ቃላቶች እና ግለሰባዊ ሚስጥሮችን በመደርደር የደራሲው ቀጣይ መጽሃፍ መነበብ እንደሌለበት ጥቁምታ የሚሰጥ መልዕክታቸውን አዥጎደጎዱት። ሁልጊዜም መቅደም የሚገባው ሃገራዊ አጀንዳ እና ጉዳይ እያለ ግለሰባዊ ተራ አተካሮ ውስጥ መግባት ለኔ ለዚህ ጽሑፍ አቅራቢ ፋይዳው አይታየኝም። በተለይ በተለይ በዳኝነት ታሪካቸው ብቻም ሳይሆን በአንድ በአጣሪ ኮምሽነነታቸው ጉዳይ ብቻ ህሊናቸው ሞግቶዋቸው ለ እውነት መቆምን መርጠው ሃገር…ኑሮ…ቤተሰብ ምቾት ሳይሉ በስደት ስለሃገራቸው ለመቆም ወስነው በቁርጥ ቀን የተገኙን ዳኛ ወልደሚካኤልን ቀርቶ እዚህ ግባ የማይባል ፋይዳ ያልፈየደን ሁሉ የትላንት ማነነቱን ሳንፈትሽ የዛሬን ሃገራዊ አቁዋሙን በማየት ማንንም ስናከብር እና ቦታ ስንሰጥ ኖረናል። በምን ምክንያት ቢሉ በይሉኝታ። ዳኛ ወልደሚካኤል የግለሰብን ማነነት በመፈተሽ ሃገራዊ ፋይዳ ያለው ነጥብ እንዳነሱ ሁሉ ተሰምቶዎት ከሆነ ይሄ ስህተት ነው። ይሉኝታው እየሸበበን እንጂ ጥቂት የፕሬስ ክሶችን…አንድ የቅንጅትንም የፍርድ ቤት ጉዳይ…ካስፈለገም ብሄራዊ ጀግናችን ብለን የምንጠራውን እውቁን የመምህራን ማህበር ፕረዚዳንት ዶ/ር ታዬ ወልደሰማያትንም የክስ ጉዳይ አንድ ነጥብ ከወያኔ እውቅ ሹመኛ ዳኛ ጎን በመቆም ስለተወሰነው ውሳኔ እና የህግ ሂደት ብሎም በቀኝ እጅነት በወያኔ ሙሉ አይን ይታዩ እና ይጠበቁ ከነበሩ ኢትዮጲያውያን ዳኛዎች የመጀመሪያው ረድፍ ላይ የሚገኙ ሰው እንደነበሩ ለማሳየት በመረጃ በተደገፈ ከላይ የዘረዘርኩዋቸውን ጉዳዮች ማንሳት ይቻላል።

ከዚህ መሰል ጉዳይ ይልቅ በርካታ እርስዎ የሚያውቁዋቸው ያልተሰሙ የወያኔ ዘመን የፍርደ-ገምድል የፍትህ ውሳኔዎችን ባስነበቡን ነበር። ከዚህ ቀደም በተለያዩ አጋጣሚዎች ያቀረቡልን እውነታዎች እንዳሉ ሆነው ማለት ነው። ግን ለኛ ለ ኢትዮጲያውያን ዳኛ ወልደሚካኤል “ሰው ማለት ሰው የሚሆን ነው ሰው የጠፋ እለት” እንዲሉ በቁርጥ ቀን ወደ ህሊናዎ ያዘነበሉ በመሆንዎ ወደ ሁዋላ መመለስ አያስፈልግም። ይመሰገናሉ ይከበራሉ ይደነቃሉ። ወደ ተስፋዬ ጉዳይ ስመጣ ታዲያ እንደ እርስዎ ያለ የተከበረ ታላቅ ዳኛ…የህግ ሰው…ህግ አዋቂ…ከግለሰብ እስከ አለም አቀፋዊ ህግ እና ስነ-ስርእት ጋር ጥብቅ ቁርኝት ያለው ሰው የግለሰብን ሚስጥር በማውጣት በዚህ መልኩ ለሚዲያ ማዋል ጉዳቱም ሆነ ጥቅሙ እንዲሁም መጥፎ ጎኑ ምን እንደሆነ ሳያስቡ ቀርተው ይህንን ማድረግዎ ብቻም አይደለም በአስቸጋሪ እና ፈታኝ ሁኔታ ውስጥ ላለነው ኢትዮጲያውያን ምን ፋይዳ ሊያበረክቱ አስበው እንደሆነ ሳስብ በጣም ተገርሜያለሁ። ምክንያቱም እኛ ኢትዮጲያውያን በሃገራዊ ጉዳይ እንዳንጠመድ እና የበኩላችንን ስራ እንዳንሰራ ከገዢዎቻችን አጀንዳ እየተመረጠ በዚያ እንድንወጠር ከምንደረግበት ሁኔታ የዘለለ ስላልሆነብኝ ነው ይህንን የምለው። እናም ለረጅም ጊዜም ጥብቅ ሚስጥር…ጥብቅ ሚስጥር ሲሉ ሲያዘግሙ ከመቆየትዎም አንጻር አርባውንም ገጽ አንድ በአንድ በመፈተሽ እጥብቁ ሚስጥር ላይ ለመድረስ እየጉዋጉዋሁ አንብቤ ምንም ውሃ የሚቁዋጥር ሚስጥር ሳላገኝ ቀርቻለሁ። ምንም እንኩዋን ተስፋዬ ከ ኤርትራ መንግስት ሰዎች ጋር ያደረገውን እና የሚያደርገውን ግንኙነት ሊጠቁሙ የሚችሉ የ እጅ ጽሁፎች ቢቀርቡም እንኩዋን። በሌላ በኩል የሚስጥሮቹ አቀባይ ማለትም የተስፋዬን ዶክመንቶች ኮፒ በማድረግ ለዳኛው ያቀበለው ግለሰብ ተስፋዬም ሆነ ወልደሚካኤል እኔም ሆንኩኝ ሌሎችም በሃገር ወዳድነቱ የምንወደው ወጣቱ አለማየሁ መሰለ በተራ የወዳጃሞች ጸብ እና አለመግባባት ሳቢያ የግለሰብን ሚስጥር ለሚዲያ ፍጆታ ከማብቃት ይልቅ አንድ ሁለት ብዬ የምዘረዝረው በአለማየሁ ላይ የተሰነዘረ በቂ ጉዳይ ነበረ ግን አለማየሁን በጠበቅኩት መንገድ ሳይሆን ባልጠበቅኩት አቅጣጫ አገኘሁት። ይህ በውስጠ-ታዋቂነት የማልፈውን ጉዳይ አለማየሁ ቢያነሳው ብዙ ሊያነጋግረን በጣት የሚቆጠሩ ግለሰቦች በሸንጎ እና በ አደባባይ…በሚዲያ እና በሌሎችም መድረኮች የተለዩ ሃገር ወዳድ የሃገር ተቆርቁዋሪ የሚመስሉንን ሰዎች ማነነት መፈተሽ እና መረዳት በቻልን ነበረ።

ይልቅም ከዚህ ይልቅ አለማየሁ አንድ ሁለት ጉዳይ ያልኩዋቸውን ነጥቦች በማንሳት አንድ በአንድ በመረጃ አስደግፎ ቢያቀርብልን ኢትዮጲያዊ ነን እያሉ በህዝብ ሚዲያ ላይ ፈላጭ ቆራጭ ሆነው የግል ጥቅማቸውን የሚያሳድዱ ግለሰቦችን መረዳት በቻልን ነበረ። ይህንን ሳስረግጥ… በሌላ በኩልም አለማየሁ መሰለ በምርጫ 97 በሱ እይታ ታይተው እና ተሰምተው የማያውቁ ግን ሌሎች ያልቃኙዋቸውን እውነታዎችንም ባስቃኘን ባስጎበኘን ነበረ።

ወደ ተስፋዬ ጉዳይ ስመለስ ከአመታት በሁዋላ ዛሬ እየተነሳ ያለው የቡርቃ ዝምታ ጉዳይ ነው። በቡርቃ ዝምታ መታተም ምክንያት በ ኦሮሞዎች እና በ አማራዎች መካከል በቀጥታ በታሪኩ አማካኝነት የተከሰተ እልቂት እና ግጭት አለ ? ይህንን የሚነግረኝ ካለ መልካም ነው። ምክንያቱም የቡርቃ ዝምታን ጦስ የመስቀል ጦርነት ልበለው የ እርስ በ እርስ ግጭት ማን ነው የሚያሳየኝ ? ይልቅስ ሃረርጌ አካባቢ በምትገኘው ጨለንቆ ከተማ በመገኘት በምኒልክ ዘመን “ሃርከ ሙራ…ሃርመ ሙራ” ብለው በሚጠሩት ዘመቻ ያኔ በዘመኑ ኢትዮጲያውያን ካልነበራቸው የህዝብ ብዛት ላይ ተበድረው መሞታቸውን እና መጨፍጨፋቸውን በማወጅ በመታሰቢያ ፕሮግራሞች ላይ አማራዎች የ ኦሮሞ ጠላት ተደርገው እንዲቆጠሩ ሲሰብኩ የነበሩ የመንግስት ባለስልጣን ዛሬ ምንም ሃጢያት እንዳልሰሩ በተቃዋሚነታቸው ብቻ ሲከበሩ ሲታፈሩ እናያለን። ትላንት ያንን አደረጉ ዛሬ ደግሞ ተጸጸቱ ይሁን። ደራሲ ተስፋዬ ገ/አብ ስዬ አብርሃን ደጋግሞ መተቸቱ እንደ ስህተት እና ለሻቢያ እንደመስራት እየተቆጠረ ከስዬ ጎን የሚሰለፉ ደጋፊዎች ማፍራት እንዲቻል ዘመቻ ከተከፈተ ከአንዳንድ ድረ ገጾች ያስተዋልነው ቢሆንም ዳኛውም ይህንኑ ጉዳይ በድጋሚ ተመላለሱበት። ስዬ አብርሃ ዛሬ ነው የፍትህ ሰው መሆኑ የታወቀው ? ወይንስ ያሳተመው መጽሃፍ ላይ ፍትህን የሚወክል ሚዛን ስለገሸረልን ? እርግጥ ነው ወያኔ በስዬ ላይ የፈጸመው የፍትህ ሂደት የሚተች ጉዳይ አለው። በአንድ ጀምበር የጸረ ሙስና ክስ ዋስ እንዲያስከለክል መቅረጹ ወያኔን እንድተቸው ያደርገኛል። ግን ስዬ በጊዜው ከነዘር ማንዘሩ እስከ አንገቱ ድረስ በሙስና ተዘፍቆ እንደነበረ እማኝ አያስፈልገውም። ሌላ…እርሱ የመከላከያ ሚኒስትር በነበረበት ዘምን አይደለም እንዴ በሃረርጌ ክፍለሃገር በደኖ እንቁፍቱ ገደል በርካታ አማራዎች ከነነፍሳቸው የተወረወሩት ብዙዎች ያለቁት ? በአርሲስ የተፈጸመውን እልቂት እንረስዋለን ? ስዬ በጊዜው የሰጠውንም ምላሽ በተለይ የነጻው ሚዲያ ልጆች ታውቁታላችሁ። ጎበዝ ልብ በሉ እኔ ሰዎች ተስፋዬ ላይ አገኘን የሚሉትን ሃጢያት እየሸፋፈንኩ አይደለም።
ተስፋዬ ገብረአብ ኢትዮጲያዊነኝ እያለ ሃገሪቱን የሚገዛው መንግስት የለም አይደለህም ብሎ ካበረረው ታዲያ የ ኤርትራን መታወቂያ መያዙ ለምን ያስገርመናል። በግድ ዜግነታችሁን ሳታጡ ገንዘብ ከፍላችሁ ለሰው ሃገር ልትሰሩ…ልትታመኑ…ቃላችሁን ልትጠብቁ እና ልታከብሩ መሃላ ገብታችሁ የሰው ሃገር ፓስፖርት ይዛችሁ እንደገና ኢትዮጲያ ኢትዮጲያ እያላችሁ የምታደነቁሩን ባለሁለት ቢላዎች አላችሁ አይደለ እንዴ ? በተጉዋዳኝ በምርጫ እጦት የሰው ሃገር ዜግነት ወስዳችሁ ከሃገር ሃገር እየተንከራተታችሁ ለ ኢትዮጲያ ቁዋሚ ጠበቃ የሆናችሁ ታማኝ ኢትዮጲያውያን እንዳላችሁ ግን ልመሰክር እፈልጋለሁ። ስለዚህ ግን አስገዳጅ ምክንያት ሳይገጥማችሁ ደግሞ የሰው ሃገር ዜግነትን የምትወስዱት ለመንቀሳቀስ ከሆነ ከነ የሚያስከፍለው ዋጋ ባላችሁበት ሃገር ትራቭል ዶክመንት ማግኘት ይቻላል። ለምን የተስፋዬ ኤርትራዊነት ይገርመናል ለምን ይደንቀናል። ተስፋዬ ቢሾፍቱን ስለተወለደባት ቀጠሮ ይዞዋል። የ እናት አባቱ ሃገር ደግሞ ኤርትራ መሆንዋን ገልጾ ቀይ አበቦችን ሊጽፍ አስቦዋል። እኔ በበኩሌ የኢትዮጲያ ተቃዋሚዎች በ ኤርትራ እየታገሉ ነው እንደግፋቸው እያላችሁ ስታበቁ ተስፋዬ የ ኤርትራ ሰላይ ነው ብላችሁ የምትነዙ ሰዎች ትገርሙኛላችሁ ከዚህ ይልቅ ልንንቀሳቀስበት እና ልንሰራበት የሚገባን ጉዳይ እያለ በግለሰባዊ ጉዳዮች እንደዚህ መሽቀዳደማችን ምን ያህል የገዢዎቻችንን እድሜ እንደሚያረዝመው ማን በነገረን። ለመሆኑ ኢትዮጲያ ውስጥ ያለው የዜግነት ህግ ምን ያህል እየተሰራበት እንደሆነ እና ዜግነት ሰጪው እና ነሺው ማን ሆኖ ነው ኢትዮጲያዊ ነኝ እያለ አታለለን ምናምን የሚል የቂላቂል አስተሳሰብ እያመጣን ለፖለቲካ ማጣፈጫ የምንጠቀምበት ምክንያቱ ምን ይሆን ?…።
ደግሞስ በአሃዳዊ የመንግስት ስልጣን ላይ ያሉ የመንግስት ባለስልጣናት በደም ለተወለዱባት ሃገረ-ኤርትራ በድብቅ ሲሰልሉ በተግባር ተገኝተው የነበሩበትን ሂደት ለማንሳት ለምን አልደፈርንም ?…።
ሲጨረስ…በመጨረሻም

(የዚህ ጽሑፍ አቅራቢ ጋዜጠኛ ዳንኤል ገዛኸኝ)
ስለ ተስፋዬ ገ/አብ ስለተባለው እኔ የምለው “ከዲያቆኑ የጳጳሱ” - ከዳንኤል ገዛኸኝ (ጋዜጠኛ) 1
ዳኛ ወልደሚካኤል የተስፋዬን የ ኤርትራን ሰላይነት መሰረት በማድረግ ቀጣዩ መጽሃፉ እንዳይነበብ እኛም ኢትዮጲያውያን እንዳናነብ ሲያስገነዝቡ በጽሁፋቸው ተመልክተዋል። ነገር ግን የ እሳቸውን የዋህነት ወይንም ሞኝነት ልበለው ያስገነዘበኝን አንድ ነጥብ እዚህ ላይ መጥቀስ ግድ ይለኛል። ለመሆኑ የተስፋየ ገ/አብ አዲስ መጽሃፍ የስደተኛው ማስታወሻ ነጻነት አሳታሚ የማን ነው ?…እርሳቸውስ በዚህ በስደት አለም በኔዘርላንድ ሲኖሩ የየትኛው የፖለቲካ ድርጅት አባል ናቸው ?…ለምታውቁ ሁሉ እና ለራሳቸው ለ ዳኛ ወልደሚካኤል እተወዋለሁ።/በ እርግጥ አሁን ነጻነት አሳታሚ እና ተስፋዬ ተፋርሰው ህትመቱ በነጻነት አሳታሚነት መታተሙ ቢቀርም/። እንዲሁም የተስፋዬን የግል መረጃዎች አሳልፎ ለዳኛ ወልደሚካኤል አቀበለ የተባለው ወጣቱ ትንታግ አለማየሁ መሰለ እርሳቸው አባል ከሆኑበት የፖለቲካ ድርጅት ጋር እና የዚሁ ድርጅት አቀንቃኝ ከሆኑ ጥቂት ጋዜጠኛ ተብዬዎች ጋር ምን እና ምንድነው ?…ይሄንንም ለ አለማየሁ እና ለራሳቸው ለዳኛ ወልደሚካኤል የምተወው ጉዳይ ይሆናል።

ማንኛውም ኢትዮጲያዊ ይህንን ጽሁፍ የሚያነቡ ሁሉ ለዚህ የጽሁፍ አቅራቢ ለ እኔ እንዲገነዘቡ እና እንዲረዱ የምፈልገው ነገር ግልጽ እና ግልጽ ነው…ይፋ እና ይፋዊም ነው። ማንም ለሃገሩ እንደሚቆረቆረው እኔም ለሃገሬ እቆረቆራለሁ በተመሳሳይ ሃገሬን እና ህዝብዋን የሚከፋፍሉ ዘረኛ ተግባራትን እቃወማለሁ። በዚሁ ልክ አስመሳይ እና ሰዎችን በግለሰባዊ ተግባራቸው ያለምንም ምክንያት የሚጠሉ እና የሚዲያ ግለሰቦችን አጥብቄ አወግዛለሁ። ይህ ብቻም አይደለም ለ ሃገር ተቆርቁዋሪ መስለው ህዝቡን ሃገር ወዳዱን ህብረተሰብ የሚያደናግሩትን የተቃዋሚ አይነት ካባ የለበሱ ግን ከወያኔ ምንዳ የሚወረወርላቸው ያሉትን ፕሬሶች እንደ መሰል የሙያ ባልደረባዎቼ በቸልታ …በትውውቅ የማልፍበት ምክንያት አይታየኝም። በቀጣይ በድፍረት ከነ ሚዲያዎቹ ስም እና ድብቅ ታሪካቸው ኦ ጋዜጠኛዎች በሚለው ጽሁፌ እመለስበታለሁ በሌላ ጽሁፍ ማለት ነው። መቼም የጀመርከው ጉዳይ ሌላ ወረድ ብለህ ያነሳሕው ሌላ የሚል ሃሳብ እንደሚሰነዘር አውቃለሁ ግን ምክንያት አለኝ።

እነ ዳኛ ወልደሚካኤል ያነሱት የተስፋዬ ጉዳይ በሃገር ላይ ችግር ያመጣል ተብሎ በግልጽ ከታመነበት እኔም የሃገር ጉዳይ ያገባኛል እና ሃሳቡን እደግፋለሁ ተስፋዬንም ሆነ ማንንም አወግዛለሁ። ቁም ነገሩ ከግለሰብ ጉዳይ እንውጣ አይነተኛ በሆነ መልኩ ለለውጥ የሚታገሉ ድርጅቶችንም ሆነ ግለሰቦችን አናግዝ። በዚሁ ልክ ኢሳት የተስፋዬን ጉዳይ አላራገበም ብለው ነገር የሚጎነጉኑ በፊትለፊት የ ኢሳት ደጋፊ መስለው ሚዲያውን የሚሠልሉ ዘረኛ የሚዲያ አካላትን እረፉ ኢሳት ስራውን ይስራበት ልንላቸው ይገባል። በበኩሌ እያስመሰሉ ዳር ዳሩን እየተራመዱ አንዳንዴም መሃል ሰፋሪ ተቆርቁዋሪ መስለው የሚንቀሳቀሱ “አዛኝ ቅቤ አንጉዋቾች” ስለ ኢሳት ለመናገር ከሚዳዱት ይልቅ እኔ ለ ኢሳት ቅርብ የሆንኩ ብተችም ምክንያት ያለኝ ኢትዮጲያዊ እንደሆንክሉ ይታወቅልኝ ስል…በቅዱስ መጽሃፍ እንደተጠቀሰቸው ከጻፎች እና ፈሪሳውያን ብሎም ከቀራጮች ይልቅ መቀነትዋን ፈትታ አስር ሳንቲም አስራት እንዳበረከተችው እኔም ከስደት ሃገር እንደመበለቲቱ የአቅሜን እያደረግኩ መሆኔን ስናገር ኢሳት እንዲስተካከል ካለው ይልቅ ይበልጥ እንዲሆን ስተች በባለቤትነት መንፈስ መሆኑን አስረግጨ በዚሁ ልገልጽ እወዳለሁ። ስለዚህ ሌሎቻችሁም ይህንን ልትገነዘቡ ይገባል። እውነት አለኝ የሚል ደግሞ ተደብቆ ሳይሆን በይፋ ሃሳቡን መሰንዘር ይኖርበታል ባይ ነኝ። በነገራችን ይህንን ጽሁፍ እነ ኢትዮ ሚዲያ እንደማያወጡት አውቃለሁ እና ወደዚያ አልሰደውም። ስለሆነም የ ኢትዮጲያ ጉዳይ ያገባኛል ብለው የሚቆረቆሩ አካላትን በ ኢጎ ስሜት የለም ዓያገባችሁም ውጡ የምንልበት ጥልፍልፍ አካሄድ መቅረት አለብት ልክ “ውጻዕ አይትበሎ ከምዝወጻዕ ግበሮ” እንዲሉ ብሂል መቅረት አለበት ባይ ነኝ። ሶማሌዎች እንደሚሉት “ነገር ቢበዛ በአህያ አይጫንም” አበቃሁ ሰላም።

Latest from Blog

ከሃይለገብርኤል   አያሌው የኦቦ ሲራጅና የወይዘሮ ፉንታዬ ልጅ ጃዋር መሃመድ ትላንትን ዛሬንና ነጋችንን ሊያሳይ የሚችል መጽሃፍ አዘጋጅቶልናል:: በእውነቱ መጽሃፉ ሊነበብ በሚችል የሃሳብ ፍሰት ተቀንብቦ በአነጋጋሪነቱ ቀጥሏል:: ጃዋርን እና የቄሮን ትውልድ በቅጡ ለመረዳት መጽሃፉ ማንበብ

የጃዋር የፖለቲካ ጅዋጅዌ! “ድመት መንኩሳ አመሏን አትረሳ’’

ጥር 2 ቀን 2017 ዓ/ም   January 10, 2025  በኢትዮጵያዊነታችሁ፡ በኦርቶዶክሳዊ እምነታችሁ፡ በአማራነታችሁ፡ በአማረኛተናጋሪነታችሁ፡ በተሰነዘረባችሁ ብትር፡ ቤተ ሰብ፡ ወዳጅ ዘመዶቻችሁን ያጣችሁ: ልጆቻችሁን የቀበራችሁ፡ አካልችሁን ያጣችሁ፡ የተሰነዘረውን ብትር በመከላከል ላይ ያላችሁ፡ያለፈቃዳችሁ በመንግሥት ተጽእኖ ወደመግደልና

በኢትዮጵያዊነታችሁ፡ በኦርቶዶክሳዊ እምነታችሁ፡ በአማራነታችሁ፡ በአማረኛ ተናጋሪነታችሁ፡ በተሰነዘረባችሁ ብትር፡

January 10, 2025
መኮንን ሻውል ወልደጊዮርጊስ ¹⁵ የምድርም ነገሥታትና መኳንንት ሻለቃዎችም ባለ ጠጋዎችም ኃይለኛዎችም ባሪያዎችም ጌቶችም ሁሉ በዋሾችና በተራራዎች ዓለቶች ተሰወሩ ፥ ¹⁶ ተራራዎችንና   በላያችን ውደቁ በዙፋንም ከተቀመጠው ፊት ከበጉም ቍጣ ሰውሩን ፤ ¹⁷ ታላቁ የቁጣው ቀን  መጥቶአልና ፥ ማንስ ሊቆም ይችላል ? አሉአቸው ። ራእይ 6 ፤  15_17 ይኽ የመጽሐፍ ቅዱስ ቃል ። የኢየሱስን ልደት ሰናከብር የየሐንስ ራእይን ማንበብ ጠቃሚ ይመስለኛል ። ምክንያቱም በመጨረሻው ዘመን

ከኢየሱስ የፍርድ ቀን በፊት በህሊናችን ውስጥ ፍቅርን ለማንገስ እንጣር 

የምጣኔ ሀብታዊ ፍጥ፣ የፖለቲካ፣ የእውነትና የሰብአዊ መብት ታጋይ፣ የአመኑበትን ነገር ለመናገር እንደ ፖለቲከኛ በቃላት ሳያሽሞነሙኑ ቀጥታ የሚናገሩት የሀገሬ ኢትዮጵያ ታላቅ ሰው ነበሩ “ዘር ቆጠራውን ተዉት፤ የአባቶቻችሁን ሀገር ኢትዮጵያን አክብሩ!”  አቶ ቡልቻ ደመቅሳ

ሀገር ወዳዱ አቶ ቡልቻ ደመቅሳ ከዚህ አለም በሞት ተለዩ

January 6, 2025
ግን ይህ ሁሉ ወጣት የት ገባ? ግን ይህ ሁሉ ወጣት የት ገባ? ዛሬ፣ 2025 ዓ/ም ላይ ብንገኝም በዝንጋታ ገመድ ወደ ሞት እየተጎተትን እንደሆነ አናውቅም። (ሁል ጊዜ የሚሞተው የገነዝነው ይመስለናል። ) “ገብርዬ ነበረ

ግን ይህ ሁሉ ወጣት የት ገባ?

January 3, 2025
Go toTop