October 3, 2013
10 mins read

ሕዝባዊ ጥያቄዎችን በማፈንና አደባባይ በመከልከል መገደብ በህግም በታሪክም ያስጠይቃል!! ሲሉ አንድነትና በ33ቱ ፓርቲዎች በጋራ ጋዜጣዊ መግለጫ ሰጡ

በአንድነትና በ33ቱ ፓርቲዎች በጋራ የተሠጠ ጋዜጣዊ መግለጫ

አንድነት ለዴሞክራሲና ለፍትህ ፓርቲ ለሶስት ወራት የሚቆይ ህዝባዊ ንቅናቄ በስትራቴጅው መሰረት በመጀመር፤ በመላው አገሪቱ የሚገኙ አባላቶቹንና ደጋፊዎቹን በማንቀሳቀስ ሕዝቡን ያሳተፈ ትግል በመላ ኢትዮጵያ በማካሄድ የተቃውሞ ሰልፎችንና ህዝባዊ ስብሰባዎችን በከፍተኛ ጫና ውስጥ ሆኖ በብቃት ማከናወን ችሏል፡፡

የመጀመሪያ ዙር የሆነውን ሕዝባዊ ንቅናቄ የሚሊዮኖች ድምጽ ለነፃነት በሚል መሪ ቃል ሰኔ 12 ቀን 2005 ዓ.ም ይፋ ስናደርግ በሰጠነው ጋዜጣዊ መግለጫ ላይ እንዳረጋገጥነው የዕቅዳችን ዋና አላማ ከጊዜ ወደ ጊዜ አምባገነንነትን እያስፋፋ፤  ዴሞክራሲዊና ሰብዓዊ መብትን እየገፈፈ፣ ዜጎችን በፍርሃት ተዘፍቀው በምንደኛነት እንዲኖሩ ያደረገውን ስርዓት ላይ ሕዝቡ ጫና ፈጥሮ መሰረታዊ መብቶች እንዲከበሩ፣ ስልጣን የህዝብ እንዲሆን፣ ግለሰቦች በፖለቲካ አመለካከታቸው፣ በዕምነታቸውና ሃሳባቸውን በነፃነት በመግለፃቸው የማይታሰሩባት ሃገር በመፍጠርና ፍትሃዊነትን ማስፈን ነው ብለን ነበር፡፡

ይህ እውን እንዲሆን ደግሞ የሚሊዮኖችን ድምፅ በመሰብሰብ ከህገ-መንግስቱ ጋር የሚጋጨውንና ገዥው ፓርቲ ተቀናቃኞችን ለማሸማቀቅ የሚጠቀምበትን የፀረ-ሽብርተኝነት አዋጅ እንዲሰረዝ ማድረግ፤ ሚሊዮኖች የፀረ ሽብር አዋጁን በመቃወም የሚፈርሙበት ሰነድም በማዘጋጀት ድጋፍ ማሰባበሰብና በአጠቃላይም ህዝቡ ከሚሊዮኖች አንዱ የሚሆንበትንና የሀገሬ ጉዳይ የእኔ ጉዳይ ነው የሚል ትውልድ መፍጠር ነው፡፡ ይህንን ከግብ ለማድረስም በአመራር ደረጃ፣ አባላትና ደጋፊዎች ዋጋ ለመክፈል ካሳዩት ቁርጠኝነት በተጨማሪ የመታሰር፣ የንብረት ማጣትና የሞራል መጎዳት ዋጋ የተከፈለበት ነው፡፡

አገሪቱን በማስተዳደር ላይ የሚገኘው ገዥ ሀይል ዴሞክራሲያዊ ባለመሆኑና ዴሚክራሲያዊ ባህሪ ስለሌለው በሰላማዊ ህዝባዊ ንቅናቄዎች ለሚነሱ ጥያቄዎች አፋጣኝ ምላሽ ከመስጠትና በተነሱ ጉዳዮች ዙሪያ ለመነጋገር በርን ከመክፈት ይልቅ ዙሪያ ጥምጥም በመሄድ ለጥያቄዎቹ አስተጋቢዎች የተለየ መልክ ለመፍጠር የሚያደርገው ሩጫ እንደተጠበቀ ሆኖ በህገ መንግስቱ በግልጽ የተቀመጡ ሰላማዊ ሰልፍ የማድረግ፣ የመሰብሰብና አቤቱታ የማቅረብ መብትን በአደባባይ እየጨፈለቀና እነዚህ መብቶች ይከበሩ ዘንድ የሚጠይቁ አባላቶቻችንን ከህግ አግባብ ውጪ በገፍ እያሰረም ቢሆን ህዝባችን ጋር ለመድረስና ተቃውሞ ድምፃችንን ከፍ አድርገን ለማሰማት ችለናል፡፡ ትግላችንንም የኢትዮጵያ ሕዝብ ለበርካታ ዓመታት ዋጋ የከፈለለት የነፃነቱ ባለቤት እስከሚሆንና የህግ የበላይነት እስከሚረጋገጥ ከዴሞክራሲያዊ ኃይሎች ጋር በመሆን የሚቀጥል እንደሆነ ለማረጋገጥ እንወዳለን

በሦስት ወር ህዝባዊ ንቅናቄያችን በጎንደር፣ በደሴ፣ በባህርዳር፣ በአርባምንጭ፣ በጅንካ፣ በአዳማ፣ በፍቼ አባሎቻችን ታስረውና ተደብድበውም ቢሆን በተሳካ ሁኔታ የተቃውሞ ሰልፎች የተካሄዱ ሲሆን በመቀሌና ባሌ ሮቤ በከፍተኛ ጫናና ህገ-ወጥነት ሳይካሄዱ ቀርተዋል፡፡ በወላይታ ሶዶና አዲስ አበባ ህዝባዊ ስብሰባዎች ተከናውነዋል፡፡ በአፋናና በጫና ያላካሄድንባቸው ቦታዎች ላይ ሕዝቡን የሚያስተዳድሩትን የስርዓቱ ሰዎችና ስርዓቱን ያጋለጥንበት፣ ሕዝቡም በቁጭት ከጎናችን እንዲቆም ያደረግንበትና ለቀጣይ የተደራጀ ትግል እንድንዘጋጅ ያነሳሳ ሁነት ነበር፡፡

አዲስ አበባን ጨምሮ ከላይ በጠቀስናቸው ከተሞች ሰላማዊ ሰልፎቹን ለማሰናከል ሃላፊዎቹ የየአካባቢዎቹን ሚሊሻዎች፣ የደንነት ሰዎች፣ ታጣቂዎችና ፖሊሶች በመጠቀም አባላቶቻችንን አስረዋል፣ አስፈራርተዋል፣ ደብድበዋል፣ አዋክበዋል፣ ሜጋ ፎኖች ተነጥቀዋል፡፡ በአዲስ አበባም  ከአንድ የመንግስት አካል በማይጠበቅ መልኩም አመራሮቻችንን አግተዋል፣ የቅስቀሳ መኪኖቻችንን እስከነ ሞንታርቦና ጀነሬተሮች ጠኋት አስሮ ማታ በመፍታት የተሳካ ቅስቀሳ እንዳናደርግ ተደርጓል፡፡ በራሪ ወረቀቶችን እንዳናሰራጭና ፖስተሮችን እንዳንለጥፍ በፖሊስ ተከልክለናል፣ ታስረናል፡፡ ከአዲስ አበባ ውጭ ደግሞ  የተለጠፉ የሰላማዊ ሰልፍ ጥሪ ወረቀቶችን እንዲቀደዱ በማድረግና ህዝቡ በሰልፎቹ እንዳይገኝ በካድሬዎች አማካኝነት የቤት ለቤት ቅስቀሳ ከማካሄዳቸው በተጨማሪ የትራንስፖርት እንቅስቃሴ እንዳይኖር በማድረግ ከየከተሞቹ አቅራቢያ ከሚገኙ ወረዳዎች ዜጎች ድምጻቸውን ለማሰማት እንዳይመጡ እንቅፋት ፈጥረዋል፡፡ በተንቀሳቀስንባቸው አካባቢዎች ሁሉ ገዢው ፓርቲ 99.6 ፐርሰንት እንዳሸነፈ ቢነግረንም በተግባር ያረጋገጥነው ከህዝብ የተነጠለ መሆኑንና ህዝቡን እየመራሁ ነው የሚለው ህዝብን በማሸማቀቅ እንደሆነ ነው፡፡

የመጀመሪው ዙር የሶስት ወር ሕዝባዊ ንቅናቄችን ከ33ቱ ፓርቲዎች ጋር በመሆን በአዲስ አበባ ለማጠናቀቅ የአዲስ አበባ ከተማ መስተዳድር የከንቲባው ጽ/ቤት መስከረም 3 ቀን 2ዐዐ6 ዓ.ም ሠላማዊ ሠልፉን በመስከረም 19 ቀን ማድረግ እንደምንችል  የሚገልፅ የዕውቅና ደብባቤ ቢሰጠንም   በእጅ አዙር ሠልፉን በመስቀል አደባባይ እንዳናደርግ ከመከልከሉም በላይ ከሕግ ውጨ በመከላከያ በፀጥታ ተቋማት አካባቢ እንድንሰለፍ ለማስገደድ በመሞከርና  ቅስቀሳ እንዳናደርግ በመከልከል ነው፡፡ ፖሊስም ህገ መንግስቱንና ህዝቡን መጠበቅ ሲገባው ለመቀስቀስ፣ ፖስተር ለመለጠፍ፣ በራሪ ወረቀቶችን ለማሰራጨት ፈቃድ ያስፈልጋል ትዕዘዝ አልደረሰንም በሚል ተልካሻ ምክንያት ህገ-መንግስታዊ መብታችንን በመጣስ የፓርቲያችንን ሊቀመንበር ጨምሮ በአጠቃላይ 101 (አንድ መቶ አንድ) አባላትን ከማክሰኞ እስከ እሁድ አስሮብናል፡፡ ፖሊስ ለህግ የበላይነት መቆም ሲገባው በድብቅ ለተሰጠው ትዕዛዝ ተገዥ በመሆኑ ከማዘናችንም በተጨማሪ ወደ ህግ በመሄድ የደረሰብንን ህገ-ወጥ የእስር መንገላታት፣ ካላግባብ ስለደረሰብን የንብረትና የገንዘብ ጉዳት እንዲሁም የሞራል ካሳ የአዲስ አበባ ፖሊስን፣ የአዲስ አበባ መስተዳድርን   በሕግ የምንጠይቅ  መሆኑን እንገልፃለን፡፡

ዘላለማዊ ክብር ለኢትዮጵያ!!!

የአንድነት ፓርቲና የ33ቱ ፓርቲዎች

መስከረም 23 ቀን 2006

አዲስ አበባ

Latest from Blog

ከሃይለገብርኤል   አያሌው የኦቦ ሲራጅና የወይዘሮ ፉንታዬ ልጅ ጃዋር መሃመድ ትላንትን ዛሬንና ነጋችንን ሊያሳይ የሚችል መጽሃፍ አዘጋጅቶልናል:: በእውነቱ መጽሃፉ ሊነበብ በሚችል የሃሳብ ፍሰት ተቀንብቦ በአነጋጋሪነቱ ቀጥሏል:: ጃዋርን እና የቄሮን ትውልድ በቅጡ ለመረዳት መጽሃፉ ማንበብ

የጃዋር የፖለቲካ ጅዋጅዌ! “ድመት መንኩሳ አመሏን አትረሳ’’

ጥር 2 ቀን 2017 ዓ/ም   January 10, 2025  በኢትዮጵያዊነታችሁ፡ በኦርቶዶክሳዊ እምነታችሁ፡ በአማራነታችሁ፡ በአማረኛተናጋሪነታችሁ፡ በተሰነዘረባችሁ ብትር፡ ቤተ ሰብ፡ ወዳጅ ዘመዶቻችሁን ያጣችሁ: ልጆቻችሁን የቀበራችሁ፡ አካልችሁን ያጣችሁ፡ የተሰነዘረውን ብትር በመከላከል ላይ ያላችሁ፡ያለፈቃዳችሁ በመንግሥት ተጽእኖ ወደመግደልና

በኢትዮጵያዊነታችሁ፡ በኦርቶዶክሳዊ እምነታችሁ፡ በአማራነታችሁ፡ በአማረኛ ተናጋሪነታችሁ፡ በተሰነዘረባችሁ ብትር፡

January 10, 2025
መኮንን ሻውል ወልደጊዮርጊስ ¹⁵ የምድርም ነገሥታትና መኳንንት ሻለቃዎችም ባለ ጠጋዎችም ኃይለኛዎችም ባሪያዎችም ጌቶችም ሁሉ በዋሾችና በተራራዎች ዓለቶች ተሰወሩ ፥ ¹⁶ ተራራዎችንና   በላያችን ውደቁ በዙፋንም ከተቀመጠው ፊት ከበጉም ቍጣ ሰውሩን ፤ ¹⁷ ታላቁ የቁጣው ቀን  መጥቶአልና ፥ ማንስ ሊቆም ይችላል ? አሉአቸው ። ራእይ 6 ፤  15_17 ይኽ የመጽሐፍ ቅዱስ ቃል ። የኢየሱስን ልደት ሰናከብር የየሐንስ ራእይን ማንበብ ጠቃሚ ይመስለኛል ። ምክንያቱም በመጨረሻው ዘመን

ከኢየሱስ የፍርድ ቀን በፊት በህሊናችን ውስጥ ፍቅርን ለማንገስ እንጣር 

የምጣኔ ሀብታዊ ፍጥ፣ የፖለቲካ፣ የእውነትና የሰብአዊ መብት ታጋይ፣ የአመኑበትን ነገር ለመናገር እንደ ፖለቲከኛ በቃላት ሳያሽሞነሙኑ ቀጥታ የሚናገሩት የሀገሬ ኢትዮጵያ ታላቅ ሰው ነበሩ “ዘር ቆጠራውን ተዉት፤ የአባቶቻችሁን ሀገር ኢትዮጵያን አክብሩ!”  አቶ ቡልቻ ደመቅሳ

ሀገር ወዳዱ አቶ ቡልቻ ደመቅሳ ከዚህ አለም በሞት ተለዩ

January 6, 2025
ግን ይህ ሁሉ ወጣት የት ገባ? ግን ይህ ሁሉ ወጣት የት ገባ? ዛሬ፣ 2025 ዓ/ም ላይ ብንገኝም በዝንጋታ ገመድ ወደ ሞት እየተጎተትን እንደሆነ አናውቅም። (ሁል ጊዜ የሚሞተው የገነዝነው ይመስለናል። ) “ገብርዬ ነበረ

ግን ይህ ሁሉ ወጣት የት ገባ?

January 3, 2025
Go toTop