September 10, 2013
7 mins read

እንኳን ለአዲሱ ዓመት አደረሰህ! – ከፕ/ር መስፍን ወልደ-ማርያም

የሰሞኑ መልካም ምኞች የሚመስል ስሜት የምንለዋወጠው “እንኳን አደረሰሽ (አደረሰህ)” በመባባል ነው። ከየት ተነስተን ወዴት እንደደረስን ግን አናውቅም። ምኞቱ የሚገልጸው ሁላችንም በአንድነት ወደተሻለ ደረጃ መሸጋገራችንን ይመስላል፤ እውነቱ ግን ሁላችንም በአንድነት ቁልቁል ወርደናል።
“… ጋሼ ማረኝ ማረኝ፤ ጋሼ ማረኝ ማረኝ
ዶሮ ብር አወጣች እኔን ሥጋ አማረኝ! …”
ተብሎ የተዘፈነበት ጊዜ መቶ ዓመት ሊሆነው ነው፤ ዛሬ እኛ ምን ብለን ልንዘፍን ይቃጣናል?
ለእኔ “ያለምንም ደም” የሚለው የደርግ መዝሙር ተስማሚ ሆኖልኛል። አንድ ዶሮ 200 ብር፣ አንድ ኪሎ ቅቤ 150 ብር፣ አንድ ኪሎ ሽንኩርት 15 ብር፣ አንድ እንጀራ 4 ብር ተኩል፣ አንድ እንቁላል 2 ከሃምሳ ሲሆን፣ የማገዶውንና የውሀውን ትተን (ውሀ ከዘይት መወዳደር ጀምሮአል፤ በአንድ ዓመት ያህል ጊዜ ውስጥ ወደ ሁለት ሺህ ስድስት መቶ ብር ግድም ከፍያለሁ!) አንድ ድስት የዶሮ ወጥ ምን ያህል ሊያወጣ ነው እንግዲህ እንኳን አደረሳችሁ ማለት መልካም ምኞት ነው ወይስ እርግማን? ብዙ ሰው ከ2005 ወደ 2006 የተላለፈው “ያለምንም ደም” ውሀውም ተወዶበት ነው። ለመሆኑ ለሚሌኒየም ግርግርና ከበሮ ምን ያህል ገንዘብ ወጥቶ ይሆን? ቂል አትበሉኝና የወጣው ገንዘብ ለእያንዳንዱ ገበሬ ለዓመት በዓሉ ሃምሳ ብር ቢታደል የሚያስፈልገው ወጪ 500,000,000 ብር ብቻ ነው። ጥድቁቀርቶ ሆነና …
የደላቸው ሰዎች በምድረ ኢትዮጵያ የሉም ማለት አይለም። እነሱ አዲሱን ዓመት ሲቀበሉ ግቢያቸውን ደም በደም አርጥበውታል፤ የዶሮውንም፣ የበጉንም፣ የፍየሉንም፣ የሰንጋውንም ደም ደሀው አላየም። ሀብታሞቹ ለርኩሳን መንፈሶች ገብረውልን የምሳቸውን ሰጥተው ባይገላግሉን በቅዥት እናልቅ ነበር! ሀብታሞች ርኩሳን መንፈሶችን መክተውልናል። ለአዲስ ዓመት ትልቁ ነገር ደም ማፍሰሱ ነው እንጂ ሥጋ መብላቱ አይደለም። ማን ነበር …
“… እኔ ስበላ አይተህ ደስ ይበልህ እንጂ
ያንተ መከጀልስ ለምንም አይበጅ፤ …” ያለው?
ዛሬ መከጀልም ቅንጦት እየሆነ ነው። “ደሀ በሕልሙ ቅቤ ባይጠጣ” ይባል ነበር – ዱሮ። ዛሬ ሕልም ማለም ቀርቷል፤ ዛሬ ሕልሙ ወደቅዠት ተለውጦአል። የዘንድሮው ቅዠት ክፋቱ እስቲተኙ አይጠብቅም፤ የሚያስለፈልፈው ደሀውን ብቻም አይደለም፤ በእውንም በጥጋብም ያቃዣል። ኢኮኖሚው እያደገ ነው፤ የህዝቡ ኑሮ እየተሻሻለ ነው እያሉ በጠኔ ለሚሰቃዩት መንገር ቅዠት አይደለም?
እኔ ከልጅነቴ ጀምሮ ለዕንቁጣጣሽ ዶሮ ማረድ ያልቻለ ደሀ አይቼ አላውቅም። በሠፈሬ የተካንሁት እኔ ብቻ ስለነበርሁ፣ ለዶሮ አራጅነት በየቤቱ እጠራ ነበርና በደንብ አውቃለሁ። ደሀው የሚቸገረው የዶሮውን መልክ መረጣ ላይ ነበር። ገብስማ፣ ጥቁር፣ ወይም ዛጎልማ ወይም ሌላ ነበር ትልቁ ችግር። ዛሬ ችግሩ ሌላ ሆነ፤ ዕንቁጣጣሽን የምንቀበለው ያለ ምንም ደም ሆነ።
ሃያኛውን ምዕተ-ዓመት ስንቀበል ደሀው ዶሮ ማረድ ይቻል እንደነበረ አትጠራጠሩ። ሃያ አንደኛውን ምዕተ-ዓመት ስንቀበል ዶሮ ማረድ ያለመቻላችን ዕድገት መሆኑ ነው? የመቶ ዓመት ዕድገት ለዕንቁጣጣሽ ዶሮ ማጣት!
ደሀነትን ማጥፋት ሲባል ግራ ይገባኝ ነበር፤ ለካስ ያውም ከተገኘ በአምስት ብር ደረቅ ሽሮ፣ የሦስት ብር እንጀራ ለእንቁጣጣሽ መብላት ነው! ማን ነው ይህንን ለደሀው የመረጠለት? ደሀነቱ እንኳን ደሀውን እኔንም ክፉኛ ተሰማኝ። ለዶሮ መግዣ እያልሁ ለዓመት በዓል ትንሽ ገንዘብ የምሰጣቸው ሰዎች ነበሩ። በአቅሜ ያስለመድኋቸው ገንዘብ ዛሬ የዶሮዋን አንድ ክንፍ አይገዛም። ታዲያ እኔ አልደኸየሁም? ዱሮ ለዶሮም፣ ለቅቤም የምሰጠው ዛሬ ለዶሮ ብቻ የሚበቃ ሲሆን አልደኸየሁም?
ተያይዘን ነው እየደኸየን ያለነው፤ በደርግ ዘመን አንድ ሰሞን የአምቦ ውሀና ክብሪት ጠፋና ህዝብ ተንጫጫ። በራዲዮና በቴሌቪዥን የተሰጠው መልስ አድኃርያን ለውስኪ መበረዣና፣ ለሲጃራ ማቀጣጠያ ቢቸግራቸው ሰማይ የተደፋባቸው መሰላቸው የሚል ነበር። ራዲዮኑንና ቴሌቭዥኑን ሲቆጣጠሩት ማሰብ ይቸግራል መሰለኝ።
እንዲያውም ሌላ ሃሳብ መጣብኝ። አድባሮቹ፣ ቆሌዎቹ፣ ምናምንቴዎቹ የሰው ደም ለምደው እንዳይሆን፤ ያለ ምንም ደም የሰውንም ደም ጨምሮ ከሆነ በዚሁ ይለፍልን፤ ሌላ ምን እንላለን።

Latest from Blog

ከሃይለገብርኤል   አያሌው የኦቦ ሲራጅና የወይዘሮ ፉንታዬ ልጅ ጃዋር መሃመድ ትላንትን ዛሬንና ነጋችንን ሊያሳይ የሚችል መጽሃፍ አዘጋጅቶልናል:: በእውነቱ መጽሃፉ ሊነበብ በሚችል የሃሳብ ፍሰት ተቀንብቦ በአነጋጋሪነቱ ቀጥሏል:: ጃዋርን እና የቄሮን ትውልድ በቅጡ ለመረዳት መጽሃፉ ማንበብ

የጃዋር የፖለቲካ ጅዋጅዌ! “ድመት መንኩሳ አመሏን አትረሳ’’

ጥር 2 ቀን 2017 ዓ/ም   January 10, 2025  በኢትዮጵያዊነታችሁ፡ በኦርቶዶክሳዊ እምነታችሁ፡ በአማራነታችሁ፡ በአማረኛተናጋሪነታችሁ፡ በተሰነዘረባችሁ ብትር፡ ቤተ ሰብ፡ ወዳጅ ዘመዶቻችሁን ያጣችሁ: ልጆቻችሁን የቀበራችሁ፡ አካልችሁን ያጣችሁ፡ የተሰነዘረውን ብትር በመከላከል ላይ ያላችሁ፡ያለፈቃዳችሁ በመንግሥት ተጽእኖ ወደመግደልና

በኢትዮጵያዊነታችሁ፡ በኦርቶዶክሳዊ እምነታችሁ፡ በአማራነታችሁ፡ በአማረኛ ተናጋሪነታችሁ፡ በተሰነዘረባችሁ ብትር፡

January 10, 2025
መኮንን ሻውል ወልደጊዮርጊስ ¹⁵ የምድርም ነገሥታትና መኳንንት ሻለቃዎችም ባለ ጠጋዎችም ኃይለኛዎችም ባሪያዎችም ጌቶችም ሁሉ በዋሾችና በተራራዎች ዓለቶች ተሰወሩ ፥ ¹⁶ ተራራዎችንና   በላያችን ውደቁ በዙፋንም ከተቀመጠው ፊት ከበጉም ቍጣ ሰውሩን ፤ ¹⁷ ታላቁ የቁጣው ቀን  መጥቶአልና ፥ ማንስ ሊቆም ይችላል ? አሉአቸው ። ራእይ 6 ፤  15_17 ይኽ የመጽሐፍ ቅዱስ ቃል ። የኢየሱስን ልደት ሰናከብር የየሐንስ ራእይን ማንበብ ጠቃሚ ይመስለኛል ። ምክንያቱም በመጨረሻው ዘመን

ከኢየሱስ የፍርድ ቀን በፊት በህሊናችን ውስጥ ፍቅርን ለማንገስ እንጣር 

የምጣኔ ሀብታዊ ፍጥ፣ የፖለቲካ፣ የእውነትና የሰብአዊ መብት ታጋይ፣ የአመኑበትን ነገር ለመናገር እንደ ፖለቲከኛ በቃላት ሳያሽሞነሙኑ ቀጥታ የሚናገሩት የሀገሬ ኢትዮጵያ ታላቅ ሰው ነበሩ “ዘር ቆጠራውን ተዉት፤ የአባቶቻችሁን ሀገር ኢትዮጵያን አክብሩ!”  አቶ ቡልቻ ደመቅሳ

ሀገር ወዳዱ አቶ ቡልቻ ደመቅሳ ከዚህ አለም በሞት ተለዩ

January 6, 2025
ግን ይህ ሁሉ ወጣት የት ገባ? ግን ይህ ሁሉ ወጣት የት ገባ? ዛሬ፣ 2025 ዓ/ም ላይ ብንገኝም በዝንጋታ ገመድ ወደ ሞት እየተጎተትን እንደሆነ አናውቅም። (ሁል ጊዜ የሚሞተው የገነዝነው ይመስለናል። ) “ገብርዬ ነበረ

ግን ይህ ሁሉ ወጣት የት ገባ?

January 3, 2025
Go toTop