አቶ ታምራት በንግድ ተሰማሩ፤ ቢተው ስልጣን ያዙ
( ከኢየሩሳሌም አርአያ)
በአሜሪካ ዴንቨር ከተማ ከቤተሰባቸው ጋር የሚኖሩት አቶ ታምራት ላይኔ የጋዝ እስቴሽን በመክፈት በንግድ ስራ መሰማራታቸውን ምንጮች ገለፁ። በሙስና ወንጀል ተከሰው ለአስራ ሁለት አመት ታስረው የወጡት አቶ ታምራት ከተፈቱ በኋላ በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ ላይ ፥ አማኝ ሆነው እንደሚቀጥሉና ነገር ግን በማህበራዊና ፖለቲካዊ ጉዳዮች ዙሪያ ከማንም ፖለቲካ ድርጅት ጋር ሳይወግኑ ለአገር ይጠቅማል የሚሉትን ሃሳብ እንደሚያካፍሉ፣ መፅሃፍ እንደሚያዘጋጁ…ገልፀው እንደነበር ያስታወሱት እነዚህ ወገኖች፣ ታምራት ያንን ቢናገሩም በቃላቸው ግን እንዳልተገኙ አስረድተዋል። « የኢየሱስ አገልጋይ ሆኜ እኖራለሁ» ያሉት ታምራት አሁን ወደ ንግድ አለም መግባታቸው እንዳስገረማቸው ምንጮቹ ጠቁመዋል። ሌላው ቢቀር በስልጣን ላይ በነበሩበት ወቅት ለሰሩት ጥፋት ህዝብን ይቅርታ ያለመጠየቃቸው አስገራሚ ነው ያሉት እነዚህ ወገኖች፣ በይፋ አደባባይ ወጥተው ህዝብን ይቅርታ የጠየቁት ዶ/ር ነጋሶና አቶ ገብሩ ብቻ እንደሆኑ አስታውቀዋል። አቶ ታምራትና አቶ ስዬ ግን ይህን ለማድረግ ጨርሶ እንደማይፈልጉ ከያዙት አቋም በቀላሉ መረዳት ይቻላል ብለዋል።
በሌላም በኩል የሕወሐት ማ/ኮሚቴ አባል የነበሩትና ደቡብን በበላይነት ሲያሽከረክሩ ቆይተው በ1993ዓ.ም በሙስና ወንጀል ተከሰው የታሰሩት አቶ ቢተው በላይ ለስድስት አመት ታስረው ከተፈቱ በኋላ በአቶ መለስ ዜናዊ የአፋር ክልል አማካሪ ተደርገው ተሹመው እንደነበረ ምንጮች አጋለጡ። ከአቶ አባተ ኪሾ ጋር ተከሰው የነበሩትና ከሕወሐት ተገንጥሎ ከወጣው <አንጃ> ቡድን አንዱ የነበሩት አቶ ቢተው ተመልሰው የመለስ አገልጋይ መሆናቸው ብዙዎችን ግራ ያጋባ መሆኑን ምንጮቹ ጠቁመዋል። በአፋር ክልል አማካሪ ሆነው ለሶስት አመት የሰሩት ቢተው በአሁኑ ወቅት በመከላከያ ኢንጂነሪንግ ኮሎጅ ተዛውረው በመስራት ላይ እንደሚገኙ ምንጮቹ አረጋግጠዋል። የአቶ ቢተው ወንድም ኮ/ል ሲሳይ (በቅፅል ስሙ ሃመዴ) ጀግና ኢትዮጲያዊና አገሩን የሚወድ ታታሪ እንደነበርና በአሰብ ውጊያ ከነሂሊኮፕተሩ ጋይቶ ማለፉን ምንጮቹ አመልክተዋል። አንድም ቀን ስሙ በነመለስ ተነስቶ የማያውቀውና የጡረታ መብቱ እንኳ ሊከበርለት ያለቻለው ሟቹ ኮ/ል ሃመዴ ልጆቹ ያለአሳዳጊ ተበትነው መቅረታቸውን ምንጮቹ ሳይገልፁ አላለፉም።
አቶ ታምራት በንግድ ተሰማሩ፤ ቢተው ስልጣን ያዙ
Latest from Blog
ፋኖ ዝናቡ ልንገረው ለአገው ፈረሰኞች በዓል መልክት አስተላለፈ!
ፋኖ ዝናቡ ልንገረው ለአገው ፈረሰኞች በዓል መልክት አስተላለፈ!
ነገሩ እንዲህ ነው ባሳለፍነው ታህሳስ 15 በተካሄደው ብልጽግና ስራ አስፈፃሚ ስብሰባ ላይ የአማራ ክልል ፕሬዚዳንት አቶ አረጋ ከበደ እጃቸውን አውጥተው ተናገሩ እኔ አቅቶኛል የአማራ ክልል ቀውስ ማስተዳደር አልቻልኩም ብለው ተናገሩ በዚህ ጊዜ
“አንተን ለማኝ አደርጋለሁ” አቢይ አሕመድ ለአማራ ክልል ፕረዚዳንት ለአረጋ ከበደ የሰጠው ማስጠንቀቂያ
ከቴዎድሮስ ሃይሌ የምናከብራቸው ጀነራል ተፈራ ማሞ ሰሞኑን አደባባይ ወጥተው አድምጠናል:: የጀነራሉ ጤንነትና ደህንነት ሲያሳስበን ለቆየነው ወገኖች ሁሉ በጥሩ ቁመና ላይ ሆነው በማግኘታችን የሕሊና እረፍት ሰጥቶናል:: አሁንም ባሉበት ሰላሞት እንዲበዛ ምኞታችን ዳር የለውም::
እስክንድር ነጋ እና ጀነራል ተፈራ ማሞ ከድል ለዲሞክራሲ እስከ ፉኖ ተሰማራ!
በላይነህ አባተ (abatebelai@yahoo.com) ዛሬም እንደ ትናንቱ አያሌ ምሁራንና ታዋቂ ነን ባይዎች ስለብሔራዊ ሽምግልና እርቅ ይደሰኩራሉ፡፡ ያለምንም ሐፍረት ቅዱሱን ሽምግልናን ከምእራብ ከተሸመተው ኤፍሬም ይሳቃዊ ድርድር ጋር እያምታቱ የአያት የቅድመ አያቶቻችንን የተባረክ የሽምግልና ሐብት ያበላሻሉ፡፡ ሽምግልና በመለኮት
ፍትህ የሌለው ሽምግልናና እርቅ ሥራ እንደሌለው እምነት የሞተ ነው!
ፋኖ አገዛዙ ላይ ከባድ ጥቃት ፈፀመ /የመቀለ ውጥረትና ታጣቂዎች የፈፀሙት /በኦሮሚያ ተደራጅታችሁ ታጠቁ ተባለ