ኢትዮጵያ በግብፅ ላይ ተመጣጣኝ የኃይል እርምጃ ለመውሰድ 1ሺ 500 ኪሎ ሜትር የሚወነጨፍ ሚሳኤል መታጠቅ ብቻ ይበቃታል

June 12, 2013
በፋኑኤል ክንፉ
 
 የግብፅ ፕሬዝዳንት መሐመድ ሙርሲ የሕዳሴውን ሃይል ማመንጫ ግድብ ግንባታን በተመለከተ ሁሉም አማራጮች በጠረጴዛ ላይ ናቸው ማለታቸውን ተከትሎ፣ አንድ የቀድሞ መንግስት ከፍተኛ ወታደራዊ ኤክስፐርት የግብፅ መንግስት ላይ ተመጣጣኝ እርምጃ ለመውሰድ 1ሺ 500 ኪሎ ሜትር የሚወነጨፍ ሚሳኤል መታጠቅ ብቻ በቂ ነው ሲሉ በተለይ ለሰንደቅ ጋዜጣ ገለፁ።
ኤክስፐርቱ እንደገለፁት “ግብፅ የሕዳሴውን ኃይል ማመንጫ ግንባታ ግድብ በጦር መሣሪያ ለመምታት ካስቀመጠቻቸው አማራጮች አንዱ መሆኑን በመጠቆም ግብፅ የሕዳሴውን ኃይል ማመንጫ ግድብ ስትመታ ለኢትዮጵያ መንግስት ደግሞ በአፀፋው የአስዋን ግድብን እንዲመታ ሕጋዊ ፍቃድ መስጠቷን ልታውቅ ይገባል” ብለዋል።
አያይዘውም፤ “ግብፅ በወታደራዊ እቅዷ ከገፋችበት በኢትዮጵያ በኩል አማራጭ መንገዶችን መመልከት ተገቢ ነው። ለምሳሌ፤ ከሰሜን ኢትዮጵያ መነሻ አድርገህ ላቲቲውዱን በ14.3000 ዲግሪ እና ሎንግቲውዱን በ36.6167 ዲግሪ ብትወስደው እንዲሁም አስዋን የሚገኝበት ላቲቲውድ 23.9706 ዲግሪ እና ሎንግቲውዱን 32.8779 ዲግሪን አቀናጅተህ ብታሰላው በአየር ላይ ያለው ርቀት ከ1100 እስከ 1500 ኪሎ ሜትር የአየር ርቀት ነው ያለው። በዚህ ውጤት መነሻ የኢትዮጵያ መንግስት ከ1500 ኪሎ ሜትር የሚወነጨፍ የስከድ ሚሳኤሎችን መታጠቅ ብቻ በግብፅ አሰዋን ግድብ ላይ ተመጣጣኝ ሃይል ሊፈጥር ይችላል።”  ብለዋል።
ወታደራዊ የአየር ርቀቱን ለመለካት የተሄደበትን አሰራር ቢያብራሩት ተብለው ለቀረበላቸው ጥያቄ ሲመልሱ፤ “ይህ ሮኬት ሳይንስ አይደለም። http://www.movable-type.co.uk/scripts/latlong-gridref.html በሚለው ድረ ገጽ ዲግሪውን በመጠቀም ማስላት ይቻላል። ቁም ነገሩ ግን ወታደራዊ አማራጭ ሁለቱንም ወገኖች ተጠቃሚ አያደርግም። ብቸኛው አማራጭ በዲፕሎማሲ ደረጃ ለመፍታት መሞከር ነው” ሲሉ ኤክስፐርቱ አሳስበዋል።
በአሁን ሰዓት በዓለማችን ላይ ከ1ሺ 500 ኪሎ ሜትር እስከ 15ሺ ኪሎ ሜትር የሚወነጨፍ ሚሳኤል የታጠቁ ሀገሮች አሉ። ከእነዚህ ውስጥ ፈረንሳይ፣ ሕንድ፣ ኢራን፣ እስራኤል፣ ሰሜን ኮሪያ፣ ቻይና፣ ፓኪስታን፣ ሩሲያ፣ ሳዑዲአረቢያ እና አሜሪካ ይገኙበታል።n
ዶ/ር ቴዎድሮስ አድሃኖም
ግብፆች የያዙት የተሳሳተ መንገድ እንደማያዋጣቸው ገለፁ
በጋዜጣው ሪፖርተር
የኢትዮጵያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዶ/ር ቴዎድሮስ አድሃኖም ግብፃዊያን ከሰሞኑ በቴሌቭዥን ቀጥታ ስርጭት ላይ ኢትዮጵያንና የሕዳሴውን ግድብ በተመለከተ የሚናገሩት ነገር ትክክል አለመሆኑን እና እርሳቸውንም ጉዳዩ እንዳሳዘናቸው ተናገሩ። ግብፃዊያን እየተከተሉ ያሉት መንገድ እንደማያዋጣቸው ገልፀዋል።
ሚኒስትሩ ይህን የተናገሩት ከትናንት በስትያ በራዲሰን ብሉ ሆቴል የአፍሪካ ሕብረት 50ኛ ዓመት ክብረ-በዓልን በሚዘክረው “JUBILEE” በተሰኘው መፅሔት የምረቃ ስነ-ሥርዓት ላይ ባደረጉት ንግግር ነው። እንደ እርሳቸው ንግግር ከሆነ ግብፆች አሁን እያደረጉ ያሉት ነገር ትክክል አይደለም። በኢትዮጵያ ላይ የተለያዩ ነገሮችን ማወጅ እንደማያዋጣቸውና እንደማይጠቅማቸው ሚኒስትሩ ተናግረዋል።
ዶ/ር ቴዎድሮስ የቀድሞውን ጠቅላይ ሚኒስተር አቶ መለስ ዜናዊን ጠቅሰው እንዳወሱት፣ ኢትዮጵያ እና ግብፅ በአባይ ወንዝ ላይ ተጠቃሚዎች እንጂ አንዱ የበላይ ሌላው የበታች ሆኖ የሚኖርበት ዘመን ማብቃቱን ጠቁመዋል። ይልቅስ የተፋሰሱ ሀገሮች በጋራ የሚጠቀሙበትን አግባብ መኖር ነው ያለበት እንጂ ሁልጊዜ ግብፆች የበላይ ሌላው የበታች ሆኖ መቀጠል እንደማይቻል ከንግግራቸው መረዳት ይቻላል።
ከሰሞኑ በቀጥታ የቴሌቪዥን ሥርጭት ከግብፅ ሀገር የተላለፈው ዘገባ እንደሚያሳየው፣ ፕሬዚዳንት ሙርሲ ካቢኔዎቻቸውን ሰብስበው በማወያየት ኢትዮጵያ ላይ ጥቃት ለመፈፀም ታጥቀው መነሳታቸውን ያስረዳል። ከፕሬዝዳንት ሙርሲ ጋር የተሰባሰቡት የግብፅ ባለስልጣን እንደሚናገሩት ከሆነ ኢትዮጵያን በልዩ ልዩ ሁኔታዎች ማጥቃት እንደሚገባ አብዛኛዎቹ በሙሉ ስሜታቸው ሲናገሩ ታይተዋል። ኢትዮጵያን ማጥቃት መንገድ ብለው ከያዟቸው አቅጣጫዎች መካከል በተቃዋሚነት የሚንቀሳቀሱትን ኦነግን፣ የኦጋዴን ነፃ አውጭ ግንባርን መደገፍ፣ የኤርትራን መንግስትን መርዳት፣ ሱማሊያ ውስጥ ያለውን አልሸባብን ማስታጠቅ እና ሌሎም ተጠቅሰዋል።
ይህ የግብጻዊያን እብሪትና ትዕቢት ያናደዳቸው የኢትዮጵያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዶ/ር ቴዎድሮስ አድሃኖም ይህ የግብፃዊያን እስትራቴጂ ፈፅሞ ልክ ያልሆነ፣ የአንዲትን ሉአላዊ ሀገር መረጋጋት ለመረበሽ መጣር ለክፍለ አህጉሩ አለመረጋጋት የሚያጋልጥ አካሔድ መሆኑን ጠቁመዋል። ከዚህ ሌላም የእነዚህ የግብፃዊያን አካሔድ ወደ ተሳሳተ መንገድ የሚመራቸው በመሆኑ ሊመከሩ እንደሚገባም ጠቁመዋል።
ዶ/ር ቴዎድሮስ አድሃኖም በአዳራሹ ውስጥ ለታደሙት የኢትዮጵያ ምሁራን እና ለአፍሪካዊያንም መልዕክት አስተላልፈዋል። ምሁራኑም በዚህ በፀረ ኢትዮጵያዊ በሆነ መንገድ የሚጓዙን ግብጻዊያን የሚመክርና እውነታውን የሚያስረዱ ጥናቶችና የምርምር ስራዎችን እንዲሁም ፅሁፎችን እንዲያቀርቡ መክረዋል።n
ምንጭ ሰንደቅ ጋዜጣ የዛሬ ጁን 12፣ 2013 ዕትም

Latest from Blog

ነገሩ እንዲህ ነው ባሳለፍነው ታህሳስ 15 በተካሄደው ብልጽግና ስራ አስፈፃሚ ስብሰባ ላይ የአማራ ክልል ፕሬዚዳንት አቶ አረጋ ከበደ እጃቸውን አውጥተው ተናገሩ እኔ አቅቶኛል የአማራ ክልል ቀውስ ማስተዳደር አልቻልኩም ብለው ተናገሩ በዚህ ጊዜ

“አንተን ለማኝ አደርጋለሁ” አቢይ አሕመድ ለአማራ ክልል ፕረዚዳንት ለአረጋ ከበደ የሰጠው ማስጠንቀቂያ

January 31, 2025
ከቴዎድሮስ ሃይሌ የምናከብራቸው ጀነራል ተፈራ ማሞ ሰሞኑን አደባባይ ወጥተው አድምጠናል:: የጀነራሉ ጤንነትና ደህንነት ሲያሳስበን ለቆየነው ወገኖች ሁሉ በጥሩ ቁመና ላይ ሆነው በማግኘታችን የሕሊና እረፍት ሰጥቶናል:: አሁንም ባሉበት ሰላሞት እንዲበዛ ምኞታችን ዳር የለውም::

እስክንድር ነጋ እና ጀነራል ተፈራ ማሞ ከድል ለዲሞክራሲ እስከ ፉኖ ተሰማራ!

በላይነህ አባተ (abatebelai@yahoo.com) ዛሬም እንደ ትናንቱ አያሌ ምሁራንና ታዋቂ ነን ባይዎች ስለብሔራዊ ሽምግልና እርቅ ይደሰኩራሉ፡፡ ያለምንም ሐፍረት ቅዱሱን ሽምግልናን ከምእራብ ከተሸመተው ኤፍሬም ይሳቃዊ ድርድር ጋር እያምታቱ የአያት የቅድመ አያቶቻችንን የተባረክ የሽምግልና ሐብት ያበላሻሉ፡፡ ሽምግልና በመለኮት

ፍትህ የሌለው ሽምግልናና እርቅ ሥራ እንደሌለው እምነት የሞተ ነው!

Go toTop