በልጅግ ዓሊ
እንደ አውሮፓውያን አቆጣጠር በሜይ 29/1993 በምዕራብ ጀርመን በሚገኝ ዞሊንግን (Solingen) በሚባል ከተማ አራት የናዚ ተከታዮች ቱርኮች ይኖሩበት የነበረውን ቤት አቃጥለው እንቅልፍ ላይ የነበሩትን 5 ሰዎችን ገድለው 15 አቁስለዋል። የዚህ አሰቃቂ ድርጊት ሃያ አመት መታሰቢያ ዝግጅት በቅርብ በጀርመን ውስጥ ተከታትየው ነበር። ይህ ድርጊት በዓለም ላይ ባስነሳው ተቃውሞና የጀርመን የስደተኛ ሕግ በመቀየሩ ምክንያት የስደተኛው ቁጥር በመቀነሱ በውጭ ሰዎች ላይ ይደርስ የነበረው አደጋ ሙሉ በሙሉ ጠፍቷል ባንልም ቀንሷል። ዛሬ እነዚህ ይህንን ወንጀል የፈጸሙ 4 ወጣቶች ከ10 ዓመት እስር በኋላ ነጻ ወጥተዋል። የተገደሉት እናትና አያት የሆኑት ባልቴት ባደረጉት ንግግር በሰላም አብሮ መኖር ጥቅሙን ካስረዱ በኋላ <<እኛም እናንተም እዚሁ ነን>> በሚል ንግግራቸውን ቋጭተዋል።
ሙሉውን በPDF ለማንበብ እዚህ ይጫኑ