October 7, 2024
20 mins read

የጨካኝ ገዥዎች እና የአድርባዮች የቤተ መንግሥት ፖለቲካ

Killer Abiy AhmedOctober 7, 2024

ጠገናው ጎሹ

“እነ ጥላሁን ገሠሠ፣ ቴዴ አፍሮ፣ አሊ ቢራ፣ ሙሃመድ አህመድ፣ … ድንቅ ድምፃዊያን መካከል ናቸው፤

 የሰው ልጅ ሆዱን ሲከፋው

ጊዜም እንደ ሰው ሲከዳው

መሄጃ መውጫ ሲጠፋው

ዝምታ ብቻ ነው ተስፋው” ይላል ሙሃመድ። ”ዝምታ ነው መልሴን” ሲያዜም ለአንድ ዓመት ሞከርኩት”

ይህንን ያስነበበችን (እወቁልኝ (ያለችን) ከወታደራዊው አገዛዝ ጀምሮ እና በተለይም  ለሩብ ምእተ ዓመት (1983 – 2010) እጅግ ሥር በሰደደ (ከባለሥልጣን አለቆቿ እግር ሥር በሚያንደፈድፍ የፖለቲካ አድርባይነትና የሞራል ዝቅጠት/ወራዳነት) ህወሃት/ኢህአዴግን  ያገለገለችውና  ከስድስት ዓመታት ወዲህ ደግሞ ያንኑ የጎሳ ደምና አጥንት ስሌት ፖለቲካ ሥርዓት እጅግ አስከፊ በሆነ ሁኔታ ያስቀጠሉትን ሸፍጠኛና ጨካኝ ገዥ ቡድኖች ቅብአተ ሹመት “በኩራት” ተቀብላ (ተቀብታ) በአሻንጉሊትነት እያገለገለች ያለችው እና ምናልባትም በቃሽ ካሏት ወይም በቃኝ ካለች ከጥሩ የጦረታ ጥቅማጥቅሟ ጋር ለመሰናበት በመጠበበቅ ላይ የምትገኘው ፕረዝደንት ሰሃለወርቅ ዘውዴ ነች ።

የዚህ ርካሽ የቤተ መንግሥት ፖለቲካ ተውኔት (ጭካኔና አድርባይነት) አካል የሆነችው “ርዕሰ ብሔር” የገዥውን ቡድን እኩይ አጀንዳና ፖሊሲ እጆቻቸውን እያወጡ ከማፅደቅና የመከረኛውን ህዝብ ደም ከመምጠት ያለፈ ምንም አይነት የፖለቲካና የሞራል ፋይዳ የሌላቸው የህዝብ ተወካዮች እና የፌደሬሽን ምክር ቤት ተብየዎች የጋራ ስብሰባ ላይ ከተለመደው የፕሮቶኮል ባህል ውጭ ንግግር ለማድረግ እንኳ ባልቻለችበት እጅግ አሳፋሪ ሁኔታ የአገር ሲምቦልነትን እንኳ በቅጡ ያልተወጣችበትን የብልፅግና “በረከተ ሹመት” ከእርሷ በእጅጉ ለባሰው የአድርባይነት ፈላስፋና ልክፍተኛ ለታየ አፅቀ ስላሴ አስረክባለች።

ለነገሩ ፕረዝደንት ተብየዋ በዚህ በሚጠበቀው የደንቆሮና ጨካኝ የኦህዴድ/ብልፅግና ፖለቲከኞች/ካድሬዎች ስብሰባብ ላይ ተናገረችም አልተናገረች፣ ዝምታን መረጠችም አልመረጠች ፣ የአዞ እንባ አነባችም አላነባች፣ በሌላ ጎምቱ አድርባ ተተካች አልተተካች ፣ ወዘተ  እርሷንና አያሌ መሰሎቿን በአሻንጉሊትነት ሲገለገልባቸው የኖረውና አሁንም የቀጠለው የጎሳ ደምና አጥንት ስሌት ፖለቲካ ቁማርተኞች ሥርዓት እንደ ሥርዓት ፅዕኑና ፈፅሞ ወደ ኋላ በማይመለስ የህልውና ፣የነፃነት ፣ የፍትህ፣ የእኩልነት፣ የሰላም (የዴሞክራሲ) ተጋድሎ እስካልተወገደ ድረስ የሚፈጠር አንዳችም የለውጥ ፍንጭ አይኖርም።

ለዚህም ነው በእንዲህ አይነ ዘመን ጠገብና እጅግ አስከፊ የቆሻሻ ግባ እና የቆሻሻ ውጣ (garbage in, garbage out ) የፖለቲካ ተውኔት በመዘናጋት  ወርቅማ የነፃነትና የፍትህ ጊዜን፣ እውቀትን፣ ገንዘብንና ማቴሪያልን ከማባከን መጠንቀቅ የሚኖርብን። ከፍተኛው መስዋእትነት መክፈል ያለበት ለዘመናት የበሰበሰውንና የከረፋውን  የፖለቲካ ቆሻሻ በማያዳግም ሁኔታ በማስወገድና ጤናማ ሆኖ ጤና የሚሰጥ ሥርዓትን  እውን በማድረግ ላይ እንጅ የቆሻሻ ጉልቻዎችን መተካካት እየተከተልን ከዚያኛው ይኸኛው ይሻላል በሚል የቂሎች ጨዋታ አይነት ላይ መሆን የለበትም ።

በሥልጣነ መንበር ላይ እየተፈራረቁ በህዝብ ላይ የመከራና የውርደት ዶፍ ከሚያወርዱ  እኩያን ገዥ ቡድኖች ጋር በመገለባበጥ ህሊናቸውን (ውስጠ ነፍሳቸውን) ለከርሳቸው ማርኪያነት አሳልፈው የሸጡና በመሸጥ ላይ የሚገኙ የአድርባይነት ደዌ ተሸካሚዎችን  (ልክፍተኞችን) ባህሪ ለዘመናት የለመድነው በመሆኑ ብዙም ላይገርመን ይችላል ። ይህ ማለት ማለት በቃ የምንልበት ጊዜና ሁኔታ ቢራዘም ሊያሳስበንና ሊገርመን አይገባም ማለት  አይደለም ።

ምንም እንኳ ከሥልጣንና ከተግባር አንፃር ብዙም ትርጉም ባይኖረውም ሲምቦልክ ለሆነው  ዕርሰ ብሔርነት (ፕረዝደንትነት -head of state )  እንኳ ፈፅሞ የማይመጥኑ አድርባዮች እና የፖለቲካና የሞራል ምንዱባን ግለሰቦች ዘፋኞች ራሳቸው የገጠማቸውን ተሞክሮ መነሻ አድርገው ያዜሙትን “የዝምታ ይሻለኛል ” ዜማ ዘመናትን ባስቆጠረው ፖለቲካ ወለድ ወንጀል አገሩ ምድረ ሲኦል ከሆነችበት መከረኛ ህዝብ  ጋር ማወዳደሪያና ማነፃፀሪያ በማድረግ “ዝምታ ነው መልሴ” በማለት “የምሬታቸውንና የትዕሥታቸውን እዮብነት” ሊያሳምኑን ሲሞክሩ በእጅጉ በዝቷልና በቃችሁ ማለት የግድ ነው።  የነፃነትና የፍትህ ሥርዓትን እውን መሆንን ከምርየምንፈልግና የምንናፍቅ ከሆነ።

ሌላው ይቅርና ሁኔታዎችን እየመረጡ መስሎ ለመታየት የሚደሰኮረውን ዲስኩር ለመደስኮር ባልተቻለበትና በማይቻልበት የፕረዝደንትነት (የርዕሰ ብሔርነት-head of state) አኗኗር  እየተምነሸነሹና   መንበር ላይ እየተሽከረከሩ “ዝምታ ነው ተሰፋውና ዝምታ ነው መልሴ’ የሚለው እንጉርጉሮ የእኔም ምንነትና እንዴትነት መገለጫ ነውና እወቁልኝ ማለት እጅግ  አስከፊ የሰብዕና ስብራትንና የሞራል ዝቅጠትን እንጅ እንዴት ኩራትንና አድናቆትን ሊያስገኝ ይችላል?  ፈፅሞ አያስገኝም! ኩራትንና አድናቆትን የሚያስገኘው ከተለከፉበት እጅግ አስከፊ የአድርባይነት (የመስሎና አስመስሎ አዳሪነት) ደዌ በመላቀቅ “የባለጌነትና የጨካኝነት ሥልጣንና ጥቅም ባፍንጫዬ ይውጣ” ብሎ ለፈፀሙት ከፉ ነገር ልባዊ ይቅርታ መጠየቅ እና ቢያንስ በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ የሥርዓቱ ሰለባ የሆኑትን በተለይም እናቶችን፣ ህፃናትንና አዛውንቶችን  ለመርዳት የሚደረገውን ሙከራ ማገዝ ነበር።

የአስከፊው የቤተ መንግሥት ፖለቲካ ተውኔት ተዋናይ አባል በመሆን ከመከረኛው ህዝብ እየተሰበሰበ በሚበጀት በጀት የመከረኛውን ህዝብ ሰቆቃና ውርደት እያራዘሙ “እንዳልተነፍስ ስለተደረግሁ  ዝምታን መርጫለሁና እወቁልኝ” ማለት የሚነግረን የወረድንበትንና እየወረድን ያለንበትን እጅግ መሪር አገራዊ/ማህበረሰባዊ ውድቀትና ውርደት ነውና ከምር ማጤንንና በአግባቡ ማስተናገድን ግድ ይለናል።

ፊደል መቁጠርን እና ረጅም የሥራና የህይወት ተሞክሮን ህዝብ ከፖለቲካ ወለድ መከራ ውርደት እንዲላቀቅ ዋነኛ የመፍትሄ መሣሪያ ( the means against catastrophe) ከማድረግ ይልቅ በሥልጣነ  መንበር ላይ ከሚፈራረቁ ሸፍጠኛና ጨካኝ ገዥ ቡድኖች ጋር እየተገለባበጡ የመከራውንና የውርደቱን ዘመን ካራዘሙ በኋላ የህዝብ በቃኝ አልገዛም ባይነት ሥጋት ሲያሳስድርባቸው የአዞ እንባ የሚያነቡ ወይም ብየ ነበር በሚል የሚመፃደቁ እንደ ፕረዝደንት ተብየዋ አይነት የፖለቲካና የሞራል ኮስማኖችን በቃችሁ ማለት የፖለቲካ ነውር ወይም ዝርጠጣ ፈፅሞ አይደለም ። ሊሆንም አይችልም። ነው እንጅ የሚል ወገን ካለም የእኔ መልስ ከሆነም እሰየው ( If so, so be it) ነው።

ይህ ማለት ግን ለተፈፀመ ፖለቲካ ወለድ ወንጀል በቀጥታ ወይም በተዘዋዋሪ ተጠያቂ ያልሆኑ ሁሉ መሠረታዊ መብቶቻቸው ይገደቡ ማለት አይደለም። ከትክክለኛ ፀፀት በሚመነጭ ይዘትና አቀራረብ ገንቢ የሆነ አስተዋፅኦ አደርጋለሁ  የሚልን ወገን  እሰየው ብሎ መቀበል ችግር የለውም። በሚደረገው መሠረታዊ የሥርዓት ለውጥ ተጋድሎ ሂደት ውስጥ እንደ መሪ ወይም እንደ ዋነኛ ተዋናይ የመሆን  ጉዳይ ግን በጥንቃቄ መስተናገድ አለበት ብሎ የመከራከር ጉዳይ ትክክለኝነት ግን የሚያወዛግበን መሆን ያለበት አይመስለኝም።

ውጠውትና ተስማምቷቸው የነበረውን ኢህአዴጋዊነት/ብልፅግናዊነት ሁኔታዎችን በማስላት አሟጠን ተፋነው ካሉ በኋላ ህዝባዊ ትግሉ የተዳከመና ለውጥ የማይመጣ ሲመስላቸው  መልሰው የሚልሱ (የሚውጡ) አሳዛኝ ባለሥልጣኖች፣ ፖለቲከኞችና  ካድሬዎች  ቁጥር ቀላል ባልሆነበት የፖለቲካ ባህልና አውድ ውስጥ ተገቢና ገንቢ የሆነ ጥንቃቄን ግምት ውስጥ የማያስገባ  የህልውና ፣ የነፃነት፣ የፍትህ፣ የእኩልነት፣ የሰላምና የጋራ እድገት ትግል ከውድቀት አዙሪት ሰለባነት የማምለጡ እድል ጠባብና አስቸጋሪ ነው።

አገር  ለስድስት ዓመታት እና አሁንም ለንፁሃን ልጆቿ (ዜጎቿ) ምድረ ሲኦል ስትሆን እንኳንስ ጦም አድራለሁ ብሎ የማያስብ እንደ ፕረዝደንት ተብየዋ አይነት ሰው ሌላም የሸፍጥና የሴራ ቤተ መንግሥት ፖለቲካ ባልደረባ  “በተንቀሳቃሽ ሥጋ ውስጥ የበሰበሰና የሚከረፋ ህሊና (ነፍስ) ተሸክሚ ሆኖ የተከበሩ ርዕሰ ብሔር ወይም የፓርላማ አባል ወይም ሚኒስትር ወይም የዚህ ወይም የዚያ ክልል መሪ ወይም … ከመባል ሁሉም ነገር ይቅርብኝ” የሚል ውሳኔ መወሰን ይኖርበታል። ይህንን የማድረግ የፖለቲካ አስተሳሰብና የሞራል ወኔ የሌለው ሰው ለራሱ ማታለያነት ይጠቅመኛል የሚለውን የሙዚቃና የፍልስፍና ጥቅስ እያጣቀሰ “ብሶቴንና የህዝብ አፍቃሪነቴን እወቁልኝ” ሲል ሰው ይሳሳታልና … የሚለውን እጅግ አጠቃላይ እውነት በግርድፉ በመውሰድ ያለ ምንም አይነት ሂሳዊና ገንቢ ጥያቄና ትችት ካልተቀበልነው የነፃነት ትግሉን አለመጥቀም ብቻ ሳይሆን ይጎዳልም የሚል ደምሳሳ አስተሳሰብ የትም አያደርስም።

እንደ ሰሃለ ወርቅ ዘውዴ (ፕሬዝደንት ተብየ) የመሰሉ ጊዜና ሁኔታ ፈፅሞ የማያስተምራቸውና የማይገታቸው  ሥር የሰደደ አድርባይነት ልክፍተኞች (victims of deeply chronic opportunism) በሥልጣነ መንበር ላይ እየተፈራረቁ በህዝብ ላይ የመከራና የውርደት ዶፍ ላወረዱና ለሚያወርዱ እኩያን ገዥ ቡድኖች ምቹ መሣሪያዎች (አሻንጉሊቶች) በመሆን በአገር ላይ የፈፀሙትንና እየፈፀሙት ያሉትን ታሪክ ይቅር የማይለው በደል ለመረዳት የሚሳነው ቅን፣ አስተዋይና ሚዛናዊ  ህሊና  ያለው የአገሬ ሰው የሚኖር አይመስለኝም።

ጠቅለል ባለ ትርጉሙ አድርባይነት ጊዜንና ሁኔታን ከትክክለኛ የአገር  ወይም የህዝብ ወይም የግል ወይም የቡድን ፍላጎትና ጥቅም ሳይሆን ትክክለኛ ካልሆነ የግል ወይም የቡድን  ፍላጎትና ጥቅም አንፃር እየተከታተሉና እያሰሉ የመራመድን እጅግ አደገኛ ሰብዕናን ወይም ባህሪን የሚገለፅ ፅንሰ ሃሳብ ነው።

ከአንድ ትውልድ አልፎ ለትውልደ ትውልድ የሚተርፍ የባለጌና ጨካኝ የጎሳ ደምና አጥንት ስሌት ፖለቲካ ሥርዓትን አስወግደን የግለሰብ (የዜጋ) እና የቡድን በጎ እሴቶች የሚረጋገጥበትና የሚከበርበት ዴሞክራሲያዊ ሥርዓት እውን እንዲሆን ለማድረግ ባለመቻላችን ይኸውና እንደ ሰሃለወርቅ ዘውዴ  አይነት የአድርባይነት  እንባ አንቢዎች  የእወቁልኝ ዲስኩር እና ተረትና ምሳሌ ማራገፊያዎች መሆናችንን እየመረረንም ቢሆን ለመቀበል ተገደናል።

ከዘመን  ጠገብና በእጅጉ አስከፊ  (terribly tragic)  ከሆነው የፖለቲካና የሞራል ቀውስ (ውድቀት) ሰብረን በመውጣት ትውልድ ተሻጋሪ የሆነ ዴሞክራሲያዊ ሥርዓትን እውን የማድረግ ታሪካዊ ተልእኮ  መወጣት ካለብን   ብቸኛው አማራጭ የጨካኞችንና የአድርባዮችን ሥርዓተ ፖለቲካ በዴሞክራሲያዊ አርበኝነት ተጋድሎ ወደ  መማሪያ የታሪክ መዘክርነት  መሸኘት ነው።

ለዚህ ደግሞ ወደድንም ጠላን በትግል ሂደት ውስጥ የሚያጋጥሙ  እጅግ ፈታኝ ሁኔታዎች እንደ ተጠበቁ ሆነው እስካሁን ከመጣንበት የውድቀት ፖለቲካ ባህል ታሪካችን (አስተሳሰብና አካሄድ)  አንፃር በእጅጉ አበረታች ሆኖ እየተካሄደ ያለውን የአማራ ፋኖ እና የሌሎች ነፃነትና ፍትህ ፈላጊ ወገኖች ተጋድሎን ሂሳዊ ፣ ተጨባጭና ገንቢ በሆነ አቋምና ቁመና መደገፍ/ማገዝ ዋነኛው ፍኖተ መፍትሄ ነውና ከምር ልንወስደው ይገባል ።

እኩያን ባለሥልጣናት ፣ ፖለቲከኞች ፣ ካድሬዎች እና  የአድርባይነት ልክፍተኞች የሁኔታዎችን ትኩሳት እየተከተሉ የሚያዋጣ ሲመስላቸው  የሚያነቡትን የአዞ እንባ   እና ራሳቸውን የማታለል እፎይታ ሲሰማቸው ደግሞ የሚያሰሙትን (የሚያላዝኑትን) አካኪ ዘራፍ ባይነት እእናም ልብ ያለው ልብ ይበል!የመለስንና እየመላለስን በማመንዠክ (በማንሳትና በመጣል) ፈፅሞ የትም አንደርስም!!!

እናም ልብ ያለው ልብ ይበል!

3 Comments

  1. “ኩራትንና አድናቆትን የሚያስገኘው ከተለከፉበት እጅግ አስከፊ የአድርባይነት (የመስሎና አስመስሎ አዳሪነት) ደዌ በመላቀቅ “የባለጌነትና የጨካኝነት ሥልጣንና ጥቅም ባፍንጫዬ ይውጣ” ብሎ ለፈፀሙት ከፉ ነገር ልባዊ ይቅርታ መጠየቅ እና ቢያንስ በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ የሥርዓቱ ሰለባ የሆኑትን በተለይም እናቶችን፣ ህፃናትንና አዛውንቶችን ለመርዳት የሚደረገውን ሙከራ ማገዝ ነበር።”
    Amen

    Professor Mesfin was wrong about Abiy Ahmed, but right on point about this despicable woman.

  2. ጠገናው በተመሳሳይ ሁኔታ ግርማ ሰይፉን፣ብርሀኑ ነጋን፣አረጋዊ በርሄን፣አገኘሁ ተሻገርን፣ተመስገን ጥሩነህ፣ በካልቾ ተመትተው የተባረሩትን ጠቅላላ የበድን አባላቶችን እነ ታገሰ ቀፎን ጨምረህ የጽሁፍህ ማጠናከሪያ ብታደርገው መልካም ነበር። እኝህስ በተከበሩበት ፓርላማ እንዳይናገሩ ቢከለከሉም የአማራ ተወካዮችን በጥፊ እየወለወሉ ከፓርላማው እንደሚያስወጧቸው ይታመናል። ክርስቲያን ታደለ የነዚህ ሰዎች የልጅ ልጅ ይሆናል ወደፊት ብዙ የመኖር እድል አለው የሱን ያህል ክብር እንዴት ሊያጡ ቻሉ?)

  3. ጠገናው እኝህ ሴት ወደ ስልጣን የመጡበት ወቅት ታማኝ በየነ የአብይን ጫማ ተደፍቶ የሳመበት ጊዜ ነበር አውሮፓ አሜሪካ በእሱ ፍቅር ያበደበት ጊዜ ነበር ሴትዮዋ ልጣኑን የተቀበሉት ምናልባት የለውጥ ጊዜ ነው ብለው አስበውም ይሆናል። እዛ ላይ ከተወጣ በሗላ ጥቅሙ ዝናው ይቅርብኝ ብሎ አሽቀንጥሮ ለመጣል ድፍረት ጥንካሬን ይጠይቃል እንኳን እሳቸው በመንፈሳዊ ህይወቱ የምናውቀው አቶ ዳንኤል ክብረት የሚሰራውን አታይም?በአንድ ፎቶ ላይ ዶር ብርሀኑ ጫማ ሊስም ሲያጎነብስ አብይ ለእሱ አፍሮ ቀና ሲያደርገው ተመልክተን በእጅጉ አዝነናል እንግዲህ ሰው እስክናገኝ ሰው መፈለግ ነው።

Leave a Reply

Your email address will not be published.

462285684 861253652803598 6644509506161987591 n
Previous Story

የፋሽስቱ አብይ አህመድ አሊ ኢትዮጵያ ውስጥ በአማራ ላይ እየተካሄደ ስለሚገኘው ጦርነት ከመስከረም 13 እስከ 27/2017 ዓ.ም በተለያዩ ቦታዎች ላይ የደረሰ የጉዳት !!!መረጃ:

7
Next Story

ናዝሬት ሞጆ መንገድ በፋኖ ተያዘ 7 ከፍተኛ ወታደራዊ አዛዦች ተሸኙ አሁን የደረሱን የድል መረጃዎች

Latest from Blog

blank

“መነሻችን እዚህ መዳረሻችን እዚያ” የሚለው የዲያስፖራ ከንቱ አታካራ! – ክፍል ሁለት

በላይነህ አባተ (abatebelai@yahoo.com) በአንዳንድ ስብሰባዎችና የሕዝብ መገናኛ መድረኮች የሚታየው የአንዳንድ ዲያስፖራዎች  “መነሻችን እዚህ መዳረሻችን እዚያ” የበከተ ከንቱ አታካራ በልጅነታችን ወላጆቻችን ትምህርት እንዲሆነን ይተርኩልን የነበረውን ከጫጉላ ወጥተው ጎጆ ለመመስረት የታከቱ ሁለት ያልበሰሉ ባልና ሚስትን ታሪክ
blank

መነሻችን አማራ መድረሻችን አማራ እና ወያኔያዊ መሠረቱ

የማይወጣ እንጀራ ከምጣዱ ያስታውቃል። የዛሬን አያድርገውና የትግሬ ልሂቆች “ትግራይ የጦቢያ መሠረት ናት ።  ጦቢያ ያለ ትግራይ፣ ትግራይ ያለ ጦቢያ ሊታሰቡ አይችሉም” በማለት ጦቢያዊ ከኛ ወዲያ ላሳር እያሉ አለቅጥ ይመጻደቁ፣ ይኩራሩ፣ ይታበዩ ነበር። ወያኔ
blank

ከ”ችርቻሮ” ድል አልፎ ለመሄድ የአንድነት አስፈላጊነት – ግርማ ካሳ

በአሁኑ ጊዜ ሁለት የፋኖ አሰላለፎች አሉ:: መኖር ያልነበረበት:: አንከር ሜዲያ ከሁለቱም አሰላለፎች፣ ሁለት ፋኖ መሪዎች ጋር ቃለ ምልልስ አድርጋለች፡፡ ሁለቱን አደመጥኩ፡፡ በሰማሁት ነገር ተደስቻለሁ:: ትልቅ ተስፋ እንድሰንቅም አድርጎኛል:: የአማራ ህዝባዊ ድርጅት የፖለቲካ
Go toTop