ሸዋ
በሸዋ ጠቅላይ ግዛት መርሀቤቴ አውራጃ በደራ ወረዳ ልዩ ስሙ ኮሉ በተባለ አካባቢ ላይ በሚገኙ የአማራ ተወላጆች ላይ አሸባሪው የሸኔ ቡድን ከኦሆዴዱ ጥምር ጦር ጋር ቅንጅት በመፈጠር መስከረም 22 ቀን 2017ዒ.ም ከለሊቱ 11:00 እስከ 12:00 ድረስ ከፍተኛ ጉደት አድርሷል።
አሸባሪው ሀይል ጨለማን ተገን በማድረግ በርካታ ንፁሀን ገድሏል፣ ቤቶችን አቃጥሏል፣ ንብረት ዘርፏል፣ በርካታ የቁም እንሰሳትን ሲወስድ ሰዎችን አግቶ ወስዷል።
ከ 500 በላይ የቁም የእንስሳት ከብቶችን ዘርፎ ወስዷል
ከ 6 በላይ ቤቶችን በእሳት አቃጥለዋል
7 ሰዎችን የገደሉ 3 ይታገቱና የወሰዱ ( 2 እናቶችን እና 1 ህፃን)
ጎጃም:
የአገዛዙ ጦር በጣለው ሞርታር አራት የአንድ ቤተሰብ አባላት ላይ ጉዳት ደርሷል::
የአገዛዙ ጦር ዛሬ መስከረም 23 ንፁሀንን አላማ አድርጎ በጣለው ሞርታር የአንድ ቤተሰብ አባል የሆኑ አራት ንፁሐን ላይ የአካል ጉዳት አድርሷል። ኮሶበር ሆኖ ወደ መኖሪያ መንደሮች በተጣለው ሞርተር ሳትማ ዳንጊያ በተባለ ስፍራ በንፁሀን ቤት ላይ በማረፉ የአንድ ቤተሠብ አባላት የሆኑ አራት ሰዎች ላይ ወላጅ እናትና ህፃን እንዲሁም እንስሳትን ጨምሮ የአካል ጉዳት ደርሷል።
ጉዳቱ የደረሰባቸው
1.መሠንበት ተስፋው 3. አቶ ተስፋው ጌታሁን(አባት)
2.ሙሉነህ ተስፋው 4. ወ/ሮ ቀኑ ፈቃዱ(እናት) የተባሉ የአንድ ቤተሰብ አባላት ናቸው።
በተመሳሳይ በአገዛዙ ሠራዊት በተፈፀመው ጥቃት አንድ ፈረስ እና 13 የቀንድ ከብቶች ተገለዋል።
የአገዛዙ ሠራዊት ከፋኖ የገጠመውን ደፈጣ መቋቋም ሲያቅተው የቡድን መሣሪያዎችን ወደ መኖሪያ መንደሮች እየተኮሰ ንፁሀንን እና የእንስሳ ከብቶችን እየገደለ ይገኛል::
ጅጋ ላይ ለ6ተኛ ጊዜ የሄሌኮፍተር ጥቃት ያደረሰ ሲሆን በሰውና በንብረት ላይም ጉዳት አድርሷል::
ሜጫ ወረዳ ዳጊ ጤና ጣቢያ የህክምና አገልግሎት በመስጠት ላይ እያለ የጤና ባለሙያዎች እና ታካሚ ህዝብን ጨፍጭፏል::
ወሎ
በደቡብ ወሎ ዞን ኩታበርና አንባሰል ድንበር ዚሃ በተባለ አካባቢ በሰብል ስብሰባ ላይ በነበሩ አርሶአደሮች በተተኮሰ ጥይት ስድስት (6) ንፁሀን አርሶአደሮችን ገድሏል::
ፋኖ በአካባቢው በሌለበት ቤትለቤት በመዞር ንፁሀንን እያንገላታና ወጣቶችን በማሰር ላይም ተጠምዷል::
ጎንደር
እብናት እና አካባቢው ከ4 ጊዜ በላይ የአየር ድብደባ ተካሂዷል:: በዚህም በርካታ ንፁሀን እየተጨፈጨፉ ነው::
ቋራ ወረዳ ሽንፋ ቀበሌ የድሮን ጥቃት በማድረስ 7 (ሰባት) ንፁሀንን ሲገድል ሰብሉንም አውድሟል::
በዚሁ በሽንፋ በቀን 23/01/2017 በገበያ ላይ በተጣለ የድሮን ጥቃት ከ16 ንፁሀን በላይ ወዲያውኑ ህይወታቸው ሲያልፍ ከ20 በላይ ቆስለዋል:: ቁጥሩ ያልታወቀ በርካታ ቤቶችም በዚሁ የድሮን ጥቃት ተፈፅሟል::
በአማራ ክልል ሰሜን ሸዋ፣ አዊ፣ ደቡብ ጎንደር፣ጎጃም ፣ ማዕከላዊ ጎንደር እና ምዕራብ ጎንደር ዞኖችን ጨምሮ በትንሹ 7 የዞን አስተዳደሮች ላይ የሰው አልባ አውሮፕላኖች ጥቃት ጨምሮ ጭፍጨፋ አካሂዷል::