August 17, 2024
23 mins read

የአማራ ፋኖ የሚታገለው በአንድ አና ለአንድ መርህ ነው! ሁለት መስመር እና ሁለት አላማ የለውም

Amhara Fnaos m456ዶ/ር መንግስቱ ሙሴ

በአንድነት ስም ግለሰብ ለማንገስ የፈለጉ የዲያስፖራ አንዳንድ ዩቲውበሮች እና የአገዛዙ የዲጅታል ሰራዊት በመቧደን በተለይ በጎጃም እና በጥቅል ደግሞ በአማራ ፋኖ ላይ እየተካሄደ ያለው የፕሮፖጋንዳ ዘመቻ ቀጥሏል። አገዛዙ በዋለበት የጦርሜዳ ውሎ ሁሉ ከሰው እስከ መሳሪያ ኃይሉ እያስረከበ በምትኩ በጦር ግንባር ሲቸነፍ በሰላማዊ ዜጎች ላይ እያካሄደ ያለው ወንጀል አንድም ዘር ተኮር በሌላም በኩል ለአቅመ አዳም እና ለአቅመ ህይዋን ያልደረሱ ህጻናት ደካማ እናቶች እና በእድሜ አቅም ያነሳቸው አዛውንቶችን በመግደል ላለፉት ሁለት ቀናት በመሸንቲ በቢኮሎ አባይ፤ በዱርቤቴ ባጠቃላይ በባህርዳር ዙሪያ ያካሄደው ሰላማዊ ዜጎችን መግደል ለአልም አቀፍ ተቋማት፤ የሰበአዊ መብት ተሟጋች ድርጅቶች እና ለተባበሩት መንግስታት የዚህ መንግስት ወንጀል ሊቀርብ ጉዳይ ሆኖ ሳለ የዲያስፖራው ሦስተኛ እረድርፈኖች እና የስርአቱ የፕሮፖጋንዳ ሰራዊት ትኩረት እንዲነፈገው አርገዋል።

ይህ በእንዲህ እንዳለ ሦስተኛ እረድፈኞች ያልናቸው ከአገዛዙ የዲጅታል ሰራዊት ጋር በመደባለቅ በፋኖ ላይ የሚያካሂዱት የፕሮፖጋንዳ ዘመቻ ይህ 360 የተባለውን የዩቲውብ ቻናልም ይጨምራል ከወዲሁ ወንጀል መሆኑን ሊገነዘቡት እና ከአፍራሽ ጸረ ፋኖ ጸረ የህልውና ተጋድሎው የፕሮፖጋንዳ ዘመቻቸው ሊታቀቡ ይገባል።

የዐማራን ሕዝብ የህልውና ትግል እና አንድነት መፍጠርን ባለቤቱ በመሬት ላይ ያለው እና አላማየ ብሎ ህይወቱን ለመስጠት በዚህ የህልውና ትግል መሳሪያ ያነሳው የአማራ ሕዝብ እና የፋኖ አርበኞች ስራ እና ሀላፊነት እንጅ በውጭ የሚኖሩ ትግሉን እንደግፋለን የሚሉ ግለሰቦችም ሆኑ ስብስቦች እኛ ያልነው ይፈጸም የሚልን ከንቱ እብሪት ሊያስቡበት የሚገባ ብርቱ ጉዳይ ነው። እናም ይህን ነውር አዙረው እንዲያዩ በተደጋጋሚ ቢነገራቸውም የትግሉ እና የትግልም መሪውን አንጋሽ፤ እና የሹምሽሩ አባወራወች አርገው እራሳቸውን በመቁጠር በትግሉ ላይ ጫና እየፈጠሩ እንደሆነ ሊገነዘቡት ይገባል።

በሰሞኑ ጋዜጠኛ ወግደረስ ጤናው ታፈነ በሚል ሲዟዟር የሰነበተውን የሦስተኛ እረድፈኞች ቱማታ እና የአገዛዙ የዲጅታል ሰራዊት ፕሮፖጋንዳ የሚያመክን እና ሀሰትነቱን አሳይ ፎቶግራፍ የጎጃም ፋኖ አሳይቷል።ያም ሆኖ ግን የነዚህ ጥንድ የትግል እንቅፋቶች ዘመቻ በጎጃም አማራ ፋኖ እና በግለሰብ አርበኛ መሪወቹ ላይ የአገዛዙ ዲጅታል ሰራዊት እና ህ ሦስተኛ እረድፈኛ ፕሮፖጋንዲስት ጥምረት አሁንም እንደቀጠለ ነው። አስገራሚ የሚያደርገው የህን የጥምረት የፕሮፖጋንዳ ዘመቻ ደግሞ ወግደረስ ጤናው መታሰር መታፈን ወይንም በሰላም እየተንቀሳቀሰ መሆን ሳይሆን አጀንዳቸው እንደሚያሳየው ጠንካራ መሰረት የያዘውን የጎጃም ፋኖ እዝ በግል እና የጠቅላላ የአማራ ፋኖን ትግል የአረመኔው ሰራዊት ያልሆነለትን በወሬ እና በቱማታ እንፈታዋለን ከሚል አስተሳሰብ የተነሳ ለመሆኑ ደግ ማሳያ ነው።

የሁለት አደረጃጀት አላስፈላጊነት

ታሪካችን እንደሚያሳየው ሁለት የተለያየ አላማ እና ግብ ያላቸው መሳሪያ የታጠቁ ድርጅቶች በአንድ ሕዝብ ውስጥ የሚንቀሳቀሱ ከሆነ የጋራ ጠላታቸውን ከማጥቃት ይልቅ እውሀ በቀጠነ እና ታጋዮቻቸው ባለፉ ባገደም ቋጥር ግጭቶች እንደሚደረጉ እና የእኔ እበልጥ እኔ እበልጥ ከምለው ሰላማዊ ውድድር ይለይልን ወደሚል አመጻዊ ፉክክር ተለውጦ ወደጦርነት መግባት እና ዋና ጠላትን ጨርሶ መርሳት በታሪካችን አየነው በመሆኑ በዚህ የፋኖ አደረጃጀት ትግል ውስጥ ያለው እና ትልቁ አላማ የአማራ ሕዝብ እህልውና ጥያቄ እንጅ የአይዲዮሎጅ ወይንም የፖለቲካል ኢኮኖሚ ባለመሆኑ የሁለት አደረጃጀት በዚህ ሕዝብ ውስጥ መኖር ጥቅም ሳይሆን ጉዳት ያተርፋል። ብሎም ትግልን እና አላማን በጠላት ግንባር ከማዋል ይልቅ የእርስ በእርስ መተናኮስ እና ለጠላት መገልገያ ወደመሆን ያስከትላል።

የአረመኔው ሰራዊት አላማ እና ስራ ተግባር እንደተጠበቀ ሆኖ ሦስተኛ እረድፈኛ በመሆን የአየር ላይ ታጋዮች ፕሮፖጋንዳ አሁንም ሊያውቀው የሚገባውን ጉዳይ የወሎ እዝ ዋና መሪ ታጋይ ምሬ ወዳጆ እና የጎጃም እዝ የፖለቲካ አመራር አስረስ ማረ እና ሻለቃ ዝናቡ ልንገርህ ግልጽ አድርገዋል። ታሪክም ሆነ እውነታው የሚያስተምረን አንድን መሰረታዊ እና ሁላዊ አላማ ስኬት እንዲያገኝ ከተፈለገ አንድ አደረጃጀት እና ወታደራዊ አመራር እንጅ ሁለት ወይንም ከዚያበላይ አደረጃጀቶች አፍራሽ መሆናቸውን ያሁን ወጣት አርበኞች ብቻ ሳይሆኑ በሐገራችን የቅርብ ግዜው ታሪካችን በደንብ ያስተምረናል እናም ጥንድ ወታደራዊ እአደረጃጀትን መፍቀድ ለችንፈት እና ድልን ለጠላት አሳልፎ መስጠት እንጅ ትግሉን አጠናክሮ ጠላትን ለማጥቃት ፈጽሞ የማይታሰብ እንደሆነ ከዚህ በታች በማሳያቸውን ሁነኛ የታዩ ታሪካዊ ተግባራት ልሞግት እችላለሁ።

ካታሪክ የታየው የጥንድ አደረጃጀት ጎጅ ታሪክ

በ1966 ዓም ገና ህወሓት በሻብያ ተደራጅታ ወደ ደደቢት በርሐ ከመግባቷ እና ጸረ ኢትዮጵያውን እና ጸረ አማራውን ግሏን ከመጀመሯ በፊት በትግራይ ሜዳ አሲምባ በሚባለው የአዲ ኢሮም አካባቢ ይንቀሳቀስ የነበረው ኢሕአፓ ነበር። በየካቲት 11 1967 ህወሓትን ያን ግዜ (ተሐት ትባል የነበረችውን) ድርጅት በሁአላ የድርጅቷ መሪወች የሆንትን ትቂት ግለሰቦች ሻብያ አስተምሮ ወደ ትግራይ ሜዳ ሲያስገባቸው በህወሓት እና ሻብያ በኩል ዋና ተግባር ሆኖ የተነሳው የኢሕአፓን ሰራዊት ከትጋይ ማስወጣት ነበር።እንደታሰበውም ብዙ ተሞክሮ እና በስምምነት ለመቀጠል ተደክሞ ሊሰራ ባለመቻሉ ሁለቱ ድርጅቶች ወደጦርነት ገቡ። በዚያም ሻብያም ይህን የህወሓትን አቋም ይደግፍ ስለነበር እና ስለኢትዮጳ የሚታገል ድርጅት በአቅራቢያው እንዲኖር ባለመፈለግ ኢሕአሰን በትብብር ወግተው ከትግራይ ሜዳ አስወጡ። በዚህ የማስወጣት ተጋድሎ ብዙ የኢሓፓ ሰአዊት አባላት መስዋእትነት ከፍለዋል።

የኤርትራ የመገንጠል ትግል እና ጥንዶች አደረጃጀቶችን እንደምሳሌ እንውሰድ። ሴምቴምበር 1961 እንደአውሮፓ አቆጣጠር በደቡብ ምእራብ ኤርትራ ክፍለሐገር የሽፍትነት ትግል ተጀመረ ብለው ታሪክ ይጽፋሉ። በዚህ 1961 እ ኤ አ በአቆርዳት በረሀ ሐሚድ እድሪስ አወቴ የተባለ የጣልያን ወታደር የነበረ የቆላ ኤርትርያ ተወላጅ በንጉሡ መንግስት እና በፈረሰው ፌደሬሽን ምክንያት ደስተኛ ባለመሆኑ ጫካ ገባ። እድሪስ አወቴ ከትቂት ወራት በኋላ የባርካ የምእራብ ኤርትርያ ተወላጆች ሁሉም በሚባል የእስልምና እምነት ተከታይ የነበሩት የእድሪስ አወቴን የመሳርያ ትግል ተቀላቀሉት በዚያው ሰሞንም የኤርትራ ነጻ አውጭ ድርጅት (ELF) ተመሰረተ። በዚህ ሳቢያ የኤርትራን ወደእናት ሀገሯ ኢትዮጵያ መቀላቀል አጥብቆ ይቃወም የነበረው የወልደአብ ወልደማርያም ተከታዮች ELF ን በገፍ ተቀላቀሉ።

በመጀመሪያወቹ የነጻ አውጭው ድርጅት ELF ምስረታ ተከትሎ በኤርትራ ሜዳ አንድ ድርጅት መንቀሳቀስ ጀመረ ይህ ብዙ ሳይቆይ በአንድ ሀይማኖት የበላይነት ስር የነበረውን ELF በመቃወም እነ ኢሳያስ አፈወርቂ ተገንጥለው ሌላ ድርጅት መሰረቱ እንደሚባለውም አሜሪካኖች ነገሩ ስላሳሰባቸው በ 1969 ዓም በረሀ እየሆነ የሄደውን የኤርትራ ምድር አረንጓዴ ማልበስ በሚል የስለላው ድርጅት አንዲስ መላ Richard / Miles Copeland የተባለ CIA ተወካይ ኢሳያስ አፈወርቂን መልምሎ ግንኙነት ፈጠረ።ከዚህ ግዜ በኋላ እነኢሳያስ EPLF የተባለ ድርጅት መስርተው መንቀሳቀስ ጀመሩ። ባብዛኛው በ 1960 ወቹ አጋማሽ በኋላ እስከ 1978 ትግሉ እና ጦርነቱ እርስ በእርስ የነበረ በመሆኑ ለደርግ መንግስት ብዙ እፎይታ ሰጥቶት ቆይቷል። ይህን ያወቀው አዲሱ የኢሳያስ ድርጅት ትኩረቱን ኢኤል ኤፍን ካላስወገዱ ትግላቸው እርባና ቢስ እንደሚሆን በመረዳት 1977-78 አምርረው ELF በመውጋት ከሜዳ አስወጡት። ከዚህ ግዜ በኋላ ነበር የመገንጠል ጦርነቱ መልክ ይዞ በ 1982 እ ኤ አ ደርጉ የቀይ ኮከብ ዘመቻ ብሎ ያወጀው በከፍተኛ ሦስት ግብረሀይሎች የታቀፈ ዘመቻ ያደረገው።

የኤርትራን መኢዳ ለብቻው የተቆጣጠረው ሻብያ ትኩረቱን ወደጦርነቱ በማዞር በአንድ ወር ያልቃል የተባለውን የቀይ ኮከብ ዘመቻ አፋቤት ላይ ከሰበረው በኋላ በኤርትራ በረሐ ብቸኛው ኃይል በመሆነ በአጭር ግዜ የመገንጠል ጥግሉን ማሳለጥ ብቻ አይደለም ህወሓትን አደራጅቶ እና አስታጥቆ የራሱን ሰራዊት መሪወችም ጭምር ልኮ ኢሕአሰን የኢሕአፓን ሰራዊት በትብብር ከትግራይ ለማስወጣት የቻሉት።

ባጭሩ በአንድ አላማ ስር ሁለት እና ከዚያ በላይ አደረጃጀቶች ለትግሉ ከሚሰጡት ጥቅም ይልቅ ለጠላት የሚሰጡት ግልጋሎት ከፍተኛ መሆኑን ከቅርቡ የትግራይ እና የኢ8እርትራ በረሀወች ለመማር እንችላለን። ሐገራችንን እዚህ ፍዳ ላይ ያስቀመጡት ሁለቱ የሰሜን ድርጅቶች ሌላ አደረጃጀቶችን ከሜዳው ተባብረው በማስወጣት ሜዳውን ለብቻ በመያዛቸው ኃይላቸውን አፈርጥመው ኢትዮጵያን የባህር በር ለማሳጣት ችለዋል።

የአማራ ፋኖ ትግል ብቸኛ ተስፋነት

የፋኖ አደረጃጀት ዋና አላማ የአማራን ሕዝብ የህልውና አደጋ ማስወገድ ነው። ይህ አላማ ሰፊ ተግዳሮት አለው። በተለይም ለአለፉት 50 አመታት በሐገራችን በዘር ተደራጅተው የተንቀሳቀሱት ሁለቱ ድርጅቶ ህወሓት እና ኦነግ ለትግል ጅማሮአቸው ዋና መሐከላዊ አላማ አማራን በመጥላት ላይ የተመሰረተ ሲሆን አማራ በሚኖርባት ኢትዮጵያ ከመኖር የየራሳችንን ሀገር ፈጥረን እንገነጠላለን የሚል መርህ ያዙ። ይህ የመገንጠል መርሐቸው ድርጅቶቹን ነጻ አውጭ ነን የሚል የተሳሳተ አላማ ሲያራምድ ግባቸው ኢትዮጵያ በውስጧ ያሉትን ብሔር እና ብሄረሰቦች ጨቁናለች በቅኝም ገዝታለች ከሚል ስህተት ወደ ዜጋን በሚናገረው ቋንቋ ለይቶ የጥላቻ ወታደራዊም የፕሮፖጋንዳም ዘመቻ መድረግ ነበር።

እናም የዚህ በመካሄድ ላይ ያለው የሕልውና ትግሉ ዋና አላማም አንድ ብቻ ሲሆን የአማራን ሕዝብ ደህንነት ማስጠበቅ እና በሰላም እንዲኖር መልክ ያለው ስርአት ማስያዝ ነው።ህን አላማ ተንተርሶ ወደትግል የገባው ፋኖ መዳረሻ ግቡ እንደሌሎች የብሄር ድርጅቶች ሐገርን መገንጠል እና ሌላ ሐገር የመመስረት አይደለም። ወንም አንድ ዘርን በደለኝ በሚል ቂም ትርክት ያነን ዘር የማጥፋት ወይንም በሐገሩ እንዳይኖር የማድረግ ሳይሆን በአማራ ሕዝብ ላይ በሰሜን እና በደቡብ የፖለቲካ ፕሮግራም ቀርጸው አማራን ከምድረ ኢትዮጵያ ማስወገድ ብቻ አማራጭ ነው ብለው የተነሱ ዘረኛ ድርጅቶችን አላማ ማምከን እና የአማራን ሕዝብ የህልውና ዋስትና መስጠት በመሆኑ ማንም ይህን አላማ የሚደግፍ ሁሉ ከልሂቅ እስከደቂቅ መሰለፍ ያለበት በአንድ እረድፍ እንጅ በተለያየ አደረጃጀት መሆን የለበትም።

ከላይ ለማሳየት እንደተሞከረው የኤርትራው የ ELF አላማ መገንጠል ከሆነ የ EPLF አላማ መገንጠል ነበር ግን ሁለቱ እርስ በእርስ የተዋጉበት ግዜ በጋራ ከቆሙበት ይበልጣል።አስገራሚው ሁለቱ የኤርትራ ድርጅቶች እርስ በእርስ ሲዋጉ የኢትዮጵያ ሰራዊት በኤርትራ መሬት የበላይነት ነበረው። ይህን ያወቀው እና በአሜሪካ የስለላ መረብ እና ምክር ውስጥ ያለው EPLF ጠንክሮ ELFን በመውጋት ከሜዳ ካጠፋው በኋላ ከአንድ ድል ወደሌላ ድል ተሸጋገር እጅግም ጥንክሮ ከኢትዮጵያ ሰራዊት ጋር ተገዳዳሪ ብቻ አይደለም አጥቂም እየሆነ ትግሉን ለመቋጨት ችሏል።የሁለት ኃይሎች በአንድ የትግል ሜዳ መቆም ያውም የታጠቁ ኃይሎች ለትግሉ ጎጅ መሆኑን አውቆ የተንቀሳቀሰው EPLF (ሻብያ) ELF ከኤርትራ ሜዳ ማስወጣቱ አላማውን በአንድ ገጽ እና በተሳካ ለማካሄድ እጅግ እንደጠቀመው ያለፈው የግንጠላው ትግል ታሪክ ያስተምረናል። በየትኛውም ቦታ ሆነ ግዜ ሁለት አይነት አደረጃጀቶች በአንድ ሰላማዊ ሆነው የቀጠሉበት ታሪክ ኖሮ አያውቅም የለም። ስለሆነም የአማራ ሕዝብ የህልውና ተጋድሎ ግቡን እንዲመታ የሚፈልግ ሁሉ መንትዮሽ አደረጃጀቶችን መቃወም እንጅ ማበረታታት የህዝባችንን መካራ ያራዝማል እንጅ አያሳጥርም ስለዚህ ይህ ሁለት አደረጃጀት ሊበረታታ ሳይሆን ሊገፋ እና እንዳይኖር ልናስወግደው የሚገባ ጉዳይ ነው።

የሁለት አደረጃጀቶች ምክንያቶች የአላማ መለያየት አይደለም። የልቅም ለዚህ አደረጃጀት ዋና ምክንያት የግለሰቦች የስልጣን ፍላጎት ይሆናል። በአማራ መሬት ያለው እውነታ እና ተጨባጭ ሁኔታ አንድ ነው ስለሆነ ግለሰቦች ስለእራሳቸው ስልጣን ሲሉ መጨነቅ እና የሕዝብን ትግል መከፋፈል አይገባም። የልቁን ስልጣን እንኳን ቢፈለግ እንኳን ለእነሱ ለሌሎች በትግሉ ውስጥ ላልነበሩም ጭምር የሚበቃ ይኖራል እናም ስልጣን የሚፈልግም ቢሆን በአንድነት መታገል ዋና የአላማው ማስፈጸሚያ እንጅ ጎጅ ሊሆን አይችልም።ከአለፍንባቸው ታሪኮቻችን እና ተመክሮ በመንሳት የምንሰጠው ምክር አንድነት፤ አብሮነት፤ መቻቻል ቀላል ተቃርኖወችን በውይይት ለመፍታት መዘጋጀት የትግሉ ዋና ፒላር ስለሆነ ለስልጣንም ለድል አድራጊነትም ቁልፉ አንድነት ነው። አንድነት ኃይል ነው! ልዩነት ማስፋት በሆነ ባልሆነው ለመለያየት መነሳሳት የሚታሰበውን ድል አድራጊነት አያመጣም። የስልጣን ፍላጎት ያለበት ሰው ቢሆን ልዩነት ያሰበውን ስቃይሆን ተቃራኒውን ያስከትላል። እናም ትብብር፤ በአንድነት መቆም፡ መተጋገዝ እና መከባበር የአጥቂነት ምሰሶ ነው።

ግለሰቦችን ስልጣን ላይ ማውጣት ወይንም መሪ እንዲሆኑ መመኘት በዚህ በህልውና ተጋድሎው ግዜ ሳይሆን በሰላሙ ግዜ በዴሞክራሲያዊ ውድድር እንዲመረጡ መትጋት እና ማስመረጥ ይቻላል። አሁን ያለንበት ግዜ ግን የስልጣን ውድድር ሳይሆን የአንድ ሕዝብን ህልውና የሚታደግ የሞት እና የሽረት ወይንም የታላቅ መስዋ’እትነት ግዜ ነው።ወደሰላማዊ ውድድር ለመድረስ አሁን መተባበር፤ በአንድ መቆም እና ለከባዱ ምስዋ’እትነት በአንድ መሰለፍ ነው።

ፈጣሪ ይህን ታጋይ ትውልድ የተቀደሰውን አላማ አንግቦ እየተሰዋ ላለው የምችል በጉልበት፤ የማይችል በጸሎት፤ እሩቅ ያለው በገንዘቡ እና በዲፕሎማሲ ተሳትፎው መትጋት ድልን ያቀርባል፤ ሕዝባችንን ከስጋት ያላቅቃል።

 

 

Leave a Reply

Your email address will not be published.

Go toTop