“ሁሉም እርዳታ በአስቸኳይ ወደግንባር”
ይህ ከላይ የሚታየው የምስለኔ አስተዳደር፣ የተረኛውን የአንድ ብሄር የበላይነትን ለማረጋገጥ፣ በሁሉም ክልልሎች ተተግብሯል። በዚህ ወሳኝ ወቅት በሁሉም ክልልሎች የሚገኝ የኢትዮጵያ ሕዝብ ፋኖ መሆን ይኖርበታል።
የ31 ዓመታት የምስለኔ ሹመኞች፡ ትህነግ “የብሔር ብሄረሰብ” ተወካዮች ብሎ፣ ለአቅመ አዳም ያልደረሱትን የእንግዴ ልጆቹን ሰብስቦ፣ ሕገ መንግሥት ነድፎና አፅድቆ ሐገር መምራት የጀመረው የዛሬ 31 ዓመት ነበር። የአማራ ክልልም እንደሌሎቹ ኢትዮጵያ ውስጥ እንደተዋቀሩት ክልልሎች እነዚህን በመሰሉ የእንግዴ ልጅ ምስለኔዎች መተዳደር የጀመረው ከዚያን ጊዜ ጀምሮ ነው። እነዚህ አዲሱ ለገሰን፣ ዮሴፍ ረታንና አያሌው ጎበዜን የመሳሰሉት የትህነግ የአማራ ምስለኔዎች (ወደ ቀልቡ የተመለሰውን ገዱ እንዳርጋቸውን ሳይጨመር)፣ የአማራን ሕዝብ እንደ ጅብ ያስበሉና የበሉ፣ በሀይማኖቱና በባህሉ ያላገጡ፣ አፉን ሸብበው በደሉን እንዳይናገር ዱዳ ያደረጉ፣ በማንነቱ እንዲሰደብና እንዲገደል አስፈፃሚና ተላላኪ የነበሩ ዋነኛ ጠላቱ ነበሩ።
ገና ከጅምሩ፣ ትህነግ ጠ/ሚንስትር ብሎ በሾመው ታምራት ላይኔ በተባለ አማራዊ ምስለኔ ባራኪነት፣ በሺዎች የሚቆጠሩ የአማራ ተውላጆች በኦነግ ሰራዊት ጭዳ ሆኑ። እንደ በአርባጉጉና በደኖ በመሳሰሉት ቦታዎች በገፍ ታረዱ። ወደ ገደል ተጣሉ። በእሳት ተቃጠሉ። በገጀራ ተቆራረጡ። ዛሬ ይኅው አማራዊ የትህነግ ምስለኔ፣ በግራ እጁ ዳዊት ተሸክሞ፣ የቀኙን ደግሞ የፖለቲካ ደጅ መጥኚያ አድርጎታል። አልቀናውም እንጂ።
እንዴት አንድ ቋንቋን መሰረት ባደረገ በብሄር የተካለለ የፌዴራል አካል፣ በራሱ ሕገ መንግሥት የሚተዳደር ክልል፣ ለ31 ዓመታት በሞግዚትና በምስለኔ ይገዛል? በትክክል ቢቆጠር በሕዝብ ብዛት አብላጫውን የሚይዘው ይህ የአማራ ሕዝብ (ትህነግም ሆነ የኦህዴድ ብልፅግና ይህ ቁጥር እንዳይታወቅ ቢጥሩም፣ ለ31 ዓመታት እያሳደዱ ቢጨፈጭፉትም፣ በመርፌና በኪኒን እንዳይወልድ ቢያመክኑትም) እንዴት በዚህ አስከፊና ዘግናኝ ወጥመድ ውስጥ ከራሱ አብራክ በወጡ ምስለኔዎች መግቢያና መውጫው ተቆለፈበት? እንዴት ከስማቸው በፊት የዲግሪ ማዕረግ የለብዱ፣ “በወረቀት አዋቂዎች፣ በስነምግባርና በሞራል ደግሞ ብልሹዎች” የሆኑት “ቢቆጠሩ ሺዎች፣ ቢሰፈሩ ደግሞ ግለባዎች” የህዝባቸውን ሰቆቃ ለአሽከርነትና ለከርሳቸው ሸጡት? ፕሮፌሰር አል ማርያም፣ እኔ ልሙትልህ አንተን ማለቴ አይደለም። ፀጉርህ ግን የአልብርት አንስታይ ሎሌ ያስመስልሃልና ቁረጠው።
የደደቢት ባለቁምጣ አፍሮዎች። ከትግራይ ሕዝብ ማህፀን ሳይሆን፣ ከዲያብሎስ አፅም ፈልፍሎ ሳጥናኤል ህይወት የዘራበት ትህነግ፣ የአማራን ሕዝብ ህልውና፣ ባህል፣ ታሪክና ሀይማኖት ለማጥፍት በማኒፌስቶው ደረት ላይ የደረሰው ትርክት ከበቀለብት የደደቢት በረሃ ጀምሮ ነበር። የብሔር ብሄረሰብ ተወካዮች ለሚላቸው የእንግዴ ልጆቹም ይህንንው መርዘኛ ትርክት ለአቅመ አዳም እስኪደርሱ ግቷቸዋል።
ገና ወደ አዲስ አበባ የሚያስገባውን አውራ ጎዳና ሳያካትት፣ ደደቢት ላይ አልሞት የነበረውን የአማራን ህልውና የማጥፋት ዘመቻ በይፋ የጀመረው፣ የተከዜ ወንዝን ተሻግሮ ወልቃይት ፀገዴንና በምስራቅ በኩል ደግሞ የራያን አውራጃዎች ጠቅልሎ ወደትግራይ በማካለል ነው። ይህም ብቻ አልበቃውም። የአማራውን ግዛት ግማሹን ወደ ቢንሻንጉል፣ ሌላውን ደግሞ በልዩ አስተዳድር “ኦሮምያ ዞን” በማለት ከትውልድ ወደ ትውልድ የሚተላለፍ ቦንብ በህብረተሰቡ መካከል ቀብሯል። ይህን ሁሉ ሲያደርግ፣ የሾማቸው የአማራ ምስለኔዎች የት ሄደው ይሆን? የወልቃይትንና የራያን መንገዶች ከፊት ለፊት ሆነው እየመሩት ነበር።
የወያኔ ትህነግ፣ ሕገ መንግሥቱን ነድፎ ባፀደቀ ማግሥት ደግሞ፣ የአማራን ማንነት ለማሳንስና የትህነግ ተላላኪ እንደሆነ ለማሳየትም ብሎ ከራሱ የማይለያይ ሰንደቅ አላማ (ከየት እንደመጣ የማይታወቅ አንድ ኮከብ ያለበት ባለ ቢጫና ቀይ እራፊ ጨርቅ) በሾማቸው የአማራ ምስለኔዎች በኩል አማራ ክልል እንዲውለበለብ አድርጓል።
አዎን ይህ የ31 ዓመታት የትህነግና የኦህዴድ ብልፅግና የከረፋ ግፍ ነው፣ የዛሬውን የፋኖ “የአማራ ሕዝብንና የኢትዮጵያ ሕዝብን” አብዮት የወለደው። አዎን ይህ “የኔና ያንቺ” “ያንተና የኔ” ትግል ነው የአማራንና የኢትዮጵያን ድል የሚወልደው። እኔም ፋኖ፣ አንቺም ፋኖ፣ አንተም ፋኖ ነን። የሁላችንም ህልውና አደጋ ላይ ወድቋል። እኔ ስዋደቅ፣ አንቺ ስትዋደቂ፣ አንተ ስትዋደቅ፣ እጃችንን አጣጥፈን መቀመጥ የለብንም። ይህ የአማራ ሰቆቃ የወለደው ወሳኝ የትግል መእራፍ የሚያስፈልገው መስዋትነት ተክፍሎበት በድል መጠናቀቅ አለበት። የፋኖ ትግል ነው። የሕዝብ ትግል ነው።
የወያኔ ትህነግ፣ የአማራን ሕዝብ ብቻ ሳይሆን፣ መላውን የትግራይ ሕዝብ ለሃምሳ ዓመታት በረሃብ ያሰቃየ፣ የራሱን ልጆች ፈረንጅ ሐገር እያስተማረ፣ የደሃውን ልጆች በአስከፊና መጨረሻ በሌለው ጦርነት የማገደ፣ እሱ በሀገር ውስጥና በውጭ ሐገር ጮማ እየቆረጠ የትግራይን ሕዝብ ለ27 ዓመታት ተመፅዋች ያደረገ የፉርሽ ስብስብ ነው። ትናንትና፣ በሚልዮን የሚቆጠሩ የትግራይ ወጣትና አዛውንት፣ አዲስ አበባ የተከለውን ህንፃውን ለማስመለስ በለኮሰው ጦርነት መስዋእትነት ገብሮ፣ እድሜ በቁሙ ላገለገላት አሜሪካን፣ በምሮኮኝነት በአደባባይ ተሸልሞ ወደ ድሮው ቤቱ መገናኛና ቦሌ ብቅ ብሏል።
እራሱን ሰባተኛው ንጉሥ ብሎ የሰየመው የበሻሻው ፍሽስታዊ አምባገነን ወታደር
በቃልቻ፣ በጠንቋይና በወንጌል ሰባኪዎች ትንግርት ጭንቅላቱ ያበጠው፣ በእውን መሬት ላይ ሳይሆን በቅዠት አየር ላይ የተንሳፈፈው አብይ አህመድ፣ የኢትዮጵያን ሕዝብ እንዴት እንደናቀው መገመት ያዳግታል። ይህ ከበሻሻ ማህፀን ጊዜ ያበቀለው የሰው እንክርዳድ፣ ከሱ በስተቀር ከመላው 120 ሚልዮን የኢትዮጵያ ሕዝብ ውስጥ ሌላ እንክርዳድ አለ ብሎ አያምንም። እውነቱን ነው። ሌላ እንክርዳድ ቢኖርም በሱ ልክ ዲያብሎስ፣ ጨካኝ፣ አስመሳይ፣ ውሸታም፣ አላጋጭ፣ ከሃዲና ፋሽስታዊ አምባገነን ተፈልጎም አይገኝም።
አብይ አህመድ ወደ ስልጣን ከመጣ ጀምሮ በአሥር ሺህ የሚቆጠሩ አማራዎች በማንነታቸው ተጨፍጭፈዋል። የዜጎችን የሕግ ማስከበር እንደዋንኛ መርሆው የሚወስድ የሐገር መሪ “ለሞቱት ጥላ እንዲሆን እኛ ዛፍ እንተክላለን” በማለት በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በሺህ በሚቆጠሩ አማራዎች እልቂት አያላግጥም። ይህ ሰው፣ እውነትስ ከበሻሻ እናቱ የወጣ እውነተኛ ሽል ወይንስ በሰው አምሳል የተፅነሰ ዲያብሎስ ነው ያሰኛል።
አዎን ይህ በአምባገነናዊው ኮሎኔል አብይ አህመድና የኦህዴድ ብልፅግና የ5 ዓመት የከረፋ ግፍ ነው፣ የዛሬውን የፋኖ “የአማራ ሕዝብንና የኢትዮጵያ ሕዝብን” አብዮት የወለደው። አዎን ይህ “የኔና ያንቺ” “ያንተና የኔ” ትግል ነው የአማራንና የኢትዮጵያን ድል የሚወልደው። እኔም ፋኖ፣ አንቺም ፋኖ፣ አንተም ፋኖ ነን። የሁላችንም ህልውና አደጋ ላይ ወድቋል።
በኦሮሙማ “የኬኛ” ርዕዮተአለም ከአሥራ አራት ዓመቱ ጀምሮ ጡት እየጠባ ያደገውና አእምሮው ክፉኛ የተደበላለቀበት አብይ አህመድ፣ ለእሱም ለእራሱ አማራ ይሁን፣ ኦሮሞ ይሁን፣ እስላም ይሁን፣ ክርስትያን ይሁን ግራ ገብቶታል። አንድ ጊዜ እናቴ የኦርቶዶክስ አማራ ናት ይላል። ሌላ ጊዜ ደግሞ (የኦሮም አክቲቪስቶች አሃዳዊ አማራ ነው ሲሉት) ኦቢኤን ላይ ወጥቶ በኦሮምኛ አባቴም እናቴም ኦሮሞዎች ናቸው ይላል። በአማርኛና በኦሮምኛ የሚሰጣቸው መልዕክቶች ጭንቅላቱ ውስጥ እንዳለው ስእል የተዘበራረቁ ናቸው። በዚህ አስመሳይ በሆነው የፊት ገፁ አናት ላይ በተተከለው የተዘበራረቀ አንጎሉ ወስጥ በግልፅ ለአብይ አህመድ የሚታየው “እርካብና መንበሩ” ብቻ ነው። አዎን እርካቡን ለመርገጥ ለአመታት ድምፁን አጥፍቶ፣ እንደ እንሽላሊት ተለዋውጦ፣ ጊዜው ሲቀናው ደግሞ የሞት የሽረቱን ከለማ መገርሳ ተችሮት እርካቡ በአንድ እግሩ ላይ ጠልቆ፣ በሌላው እግሩ ደግሞ በደመቀ መኮንን ተጨክሎ፣ በመጨረሻም እድሜ ልኩን በቋመጣት መንበር ላይ ወጥቷል።
ከዚያ በኋላ፣ የዚህ ፍሽስታዊ አምባገነን መሪ ድርጊት ያደባብይ ሚስጥር ነው። ብዙም ሳይቆይ፣ “አስተማሪዬ” ያለውን ለማ መገርሳን ገፍትሮ፣ ከኤንጅነር ስመኘው ጀምሮ አምባቸው መኮንን፣ ጄነራል አሳምነው ፅጌን፣ ጄነራል ሳአረ መኮንን፣ ሃጫሉ ሁንዲሳንና ሌሎች የማናውቃቸውን “ለስልጣኔ አስጊ ናቸው” የሚላቸውን ሁሉ አስገድሏል።
አብይ አህመድ በ5 አመት ውስጥ አንድ የክልሉ ተወላጅና (ዶክተር አምባቸው መኮንን፣ የፋሽስታዊ ስርዐቱን አስከፊነት ቀድሞ በማውቁ ያስረሸነው)፤ አራት የኦህዴድ ብልፅግና ምስለኒዎችን የአማራ ክልልን እንዲመሩ ሾሟል። እንዚህ ምስለኔዎች በትህነግ እልፍኝ ከዳዴ ጀምሮ ያደጉ፣ በስማቸው “አማራ” በምግባራቸው ደግሞ “አድር ባይ ባንዳ” የተለጠፈባቸው የሕዝብ ጠላት ናቸው። ለትህነግ የመጣውን አውሎ ነፋስ እንደምንም አምልጠው፣ የአብይ አህመድ መንበር ሲረጋጋ ደግሞ ከትግሉ ፊት ለፊት ቀደም ቀደም ብለው በኦህዴድ ብልፅግና ለመታጨት የበቁ ናቸው። የአማራን ሕዝብ፣ በአንድ ብሄር መሪነት በተዋቀረው የአምባገነናዊው የአብይ አህመድ ጦርሰራዊት እንዲጨፈጨፍ ፈርመው የሰጡ፣ የደህንንነት መስሪያ ቤቱንና የፌዴራል ምክር ቤቱን የሚመሩ የታሪክ አተላዎች ናቸው።
የኦህዴድ ብልፅግና፣ የዳውድ ይብሳ ሸኔና የኦፌኮ ስብስብ በሙሉ በአንድ አንገት ላይ የተከሉ ጭንቅላቶች ናቸው። ሁሉም የተለያዩ ምላሶች ይኑራቸው እንጂ ግባቸው አንድ ነው። የኦሮም ብሄር ብቻ የሚመራው የኩሽ መንግሥት። አራት ኪሎ ያለው የኦህዴድ ብልፅግና፣ በየክልሎቹ በዘረጋውን የተላላኪ ካድሬዎች መዋቅር በኩል የያንዳንዱን ብሄር ብሄረሰብ ህልውና ጠፍንጎ ይዟል። በዳውድ ይብሳ የሚመራውና በኦህዴድ ብልፅግና ሰልጥኖ ምሪትና የዳቦ ሥም የሰጠው ኦንግ ሸኔ፣ አማራውንና ኦሮሞ ያልሆነውን ኢትዮጵያዊ ከኦሮምያ ምድር ያፀዳል። የነ መረራና የጀዋር ቡድን ደግሞ፣ ከሌሎቹ አንጋፋ የኦንግ መእኦዎች ጋር (ሌንጮ ለታ፣ ዲማ ነገዎ፣ አባ ዱላ ገመዳ) ከመሳሰሉት ትርክት በመፃፍና በማማከር ያገለግላሉ። በአንድ የአንገት ባላ ላይ የተከሉ ጭንቅላቶች ማለት ይሄ ነው።
የትህነግና የኦህዴድ ብልፅግና አዲሱ ፍቅር።
የኦህዴድ ብልፅግና፣ በኦሮሙማ የፖለቲካ ርዕዮተአለም የተዋቀረ፣ “ሴሜቲክ ጠል” ድርጅት ነው። የእንጀራ አባቱ ትህነግ “አማራ ጠል” ትርክት ከሜዳ ጀምሮ ቢግተውም ቅሉ፣ የሴሜቲክን ባህልና ታሪክ ከኢትዮጵያ ምድር አጥፍቶ፣ የኦሮሞ ብሄር ብቻ የሚመራው የኩሽ መንግሥት ከመመስረት ውጭ ሌላ አላማ የለውም።
ታድያ ይህ ባህር ዳር ላይ “አማራን ቁማር” በላሁ ያለው የኦህዴድ ብልፅግና፣ ዛሬ ደግሞ “መቀሌ ላይ ትህነግን ሱሪ አስወለኩት ቢል አይደንቅም። ለዚህም ማሰረጃው፣ ትህነግ 1ኛ) ኦህዴድ ክፉኛ የሚጠላውን የኢትዮጵያ ኦፊሲያል ቋንቋ አማርኛ በትግራይ እንዳይተገበር አድርጓል። 2ኛ) ለሺህ ዓመታት በቀኖናና በመንፈሳዊ ቃንጫ ተገምዶና ተቆላልፎ ከቆየው የኦርቶዶክስ ቤተክርስትያን እራሱን አግልሏል። ታድያ፣ የኦህዴድ ብልፅግና፣ አክርካሪውን በሰበረው የትህነግ ዋና ከተማ መቀሌ ላይ ያዙኝ ልቀቁኝ ብሎ ቢደነፋ፣ እነ ጌታቸው ረዳ ቀንና ማታ ወደ አዲስ አበባ እየተመላለሱ የጌቶቻቸውን ደጅ ቢጠኑ፣ ምን ያስደንቃል። አይ ትህነግ? ምርኮኛው ብርሃኑ ጁላ እንኳን አንተ ላይ የደረሰው “በዘራችሁ አይደረስ” ብሎ ጨርሶታል። ይህ ንግግሩ ደግሞ ወደራሱ እንደሚመጣ ገና ከጠንቋዮቹ አልተነገረውም።
አብይ አህመድ ፋሽስታዊ አምባገነን (Totalitarian Dictator) ለመሆኑ ከሚያሳዩት ምግባሮቹ በጥቂቱ።
ስልጣን። አብይ አህመድ ሁሉንም ቁልፍ የተባለ ሥልጣን በመዳፉ ሥት ይቆጣጠራል። የደህንነት ሹም፣ የወታደር ሹም፣ የፖሊስ ሹም፣ የባንክ ሹም፣ የከተማ ሹም በሙሉ በቁጥጥሩ ሥር ናቸው። ። ከደህንነት ሹሙ ይልቅ ማን ጠላት እንድሆነና ምን መደረግ እንደሚገባው ወሳኙ አሱ ነው። ሽመልስ አብዲሳን ደውሎ አማራን አዲስ አበባ እንዳያሰገባ የሚያዘው አብይ አህመድ ነው። ከንቲባዋ የት ፓርክ እንድምትሰራ፣ ለማን ኮንዶሚኒየም እንደምትሰጥ ትእዛዝ ሰጪም እሱው ነው።
አምባገነናዊና ፍሽስታዊ መሪዎች የመድረክ ተናጋሪ ናቸው። አይዲዎሎጂ መፈብረክ ይችላሉ (ለምሳሌ እርካብና መንበር፣ መደመርን ከሌላም ሀሳብ ገልብጦ ፈላስፋ ለመባል መጣር)። በድርጊት የማይተገበር ለሕዝብ ጆሮ ኝ የሚጥም ትርክት ደጋግመው ይናገራሉ (ስንኖር ኢትዮጵያዊ ስንሞት ደግሞ ኢትዮጵያ”። ሕዝብን ከህዝብ ለመለያየት ደግሞ “አከርካሪ ሰብረናል”፣ “በደማችን ያገኘንውን ድል” “ትምክህተኞች፣ ነፍጠኛ፣ ፅንፈኛ፣ ኦሮሞ ጠል፣ እኛ ዝሆን ነን ሚዳቆን እንገላለን” ወዘተ
አምባገነናዊና ፍሽስታዊ መሪዎች የመድረክ የወጣላቸው ውሸታሞች ናቸው። የአብይ አህመድ ውሸት ተቆጥሮ አያልቅም። ስለኢኮኖሚው የውሸት ቁጥር መፈብረክ። ታሪክንና እውነትን ማዛባት። ሕዝብ እየተራበ በከንቱ መመፃደቅ። የመግሥት ሥራ ማጋነን። ሐገር በሙሉ በተፈናቃይ ሞልቶ፣ ፍትህ ጠፍቶ፣ ሰው ከቦታ ቦታ መንቀሳቀስ አቅቶት እያለ፣ ሁሉም ሰላም እንደሆነ መስበክ። ሕዝብን ለማወናበድ የተለያየ ውሸትና አጀንዳ በየግዜው ይናገራል።
አምባገነናዊና ፍሽስታዊ መሪዎች ሽብርተኞች ናቸው። አብይ አህመድ በአሥር ሺህ የሚቆጠሩ አማራዎችን በጅምላ በማሰር፣ በሚልዮን የሚቆጠሩትን ደግሞ በማፈናቀልና በመግደልና የዘር ማፅዳት ወጀል ሰርቷል። የመናገርና የፕሬስ ነፃነት አፋኝ ነው (Propaganda & censorship)። እንደ አብይ አህመድ ያሉ አምባገነናዊና ፍሽስታዊ መሪዎች የሕዝብን ነፃነት ሙሉ በሙሉ በሚባል ደረጃ በማፈን በጋዜጣም፣ በሬዲዮም፣ በቴለቪዝንም ከራሱ በስተቀር ነፃ ሃስብ እንዲተላለፍ አይፈቅድም። ራዲዮም ሆነ ቴለቪዝን የአብይ አህመድን የቀን ተቀን ፕሮፖጋንዳና ውሸቶች ብቻ በመዘገብ በሕዝብ ላይ የሚቀልዱ ናቸው።
በሃይማኖትና በዘር እያመካኙ መወንጀል (Religious or Ethnic Persecution)። የአብይ አህመድ አምባገነናዊና ፍሽስታዊ አገዛዝ በሃይማኖትና በዘር እያማከኘ “የሐገር ጠላት” የሚል ሥም እየሰጠ ተፎካክሪና ድጋፍ ያልሰጡትን ዜጎች ማሰር፣ ማሰቃየትና መግደል ዋና ተግባሩ ነው። “ኦሮሞ ጠል”፣ “የአንድ ብሄር ሃይማኖት”፣ “አድሃሪ ሃይማኖት” “ቆሞ ቀር ሃይማኖት” ወዘተ።
ሁሉን አዋቂ “ከኔ በላይ ንፋስ”። ሚንስተሮቹም ሆነ ሌሎች የበላይ ሹማምንቶች (ከወታደር እስከ ዳኛ) በራሱ በአብይ አህመድ ችሮታና ፈቃድ እንጂ በችሎታቸው ብቻ ሥራውን እንዳላገኙት እንዲያምኑ ያደርጋል። ለዚህም ቢሰድባቸውም ጭጭ ብለው ይቀመጣሉ። ሁሉም ብሱ ቸርነት እንደሚገኝ ያሳምናል። ከተናገሩ ደግሞ ይባረሩና የያዙትን ሁሉ ያጣሉ። አምባገነናዊ መሪ ተበቃይ ነው። ይህን ስለሚፈሩ ሁሌም ጭራቸውን እየቆሉ “ሲጠሩ አቤት፣ ሲላኩ ደግሞ ወዴት” የሚሉ አደርባዮች ያደርጋቸዋል። ፋሽስታዊ መሪ ሚንስትሮቹንም ሆነ ሌሎች የምንግሥት የበላይ ሃለፊዎችን እንደበታች ይቆጥራል። እያንዳንዱን ሚንስቴር ለማስተማር ይሞክራል። እሱ ከሌለ (እሱ ከስልጣን ቢወርድ) ሁሉም ነገር እንደሚጠፋና እምደማይገኝ እንዲይምኑ ያደርጋል።
ይህ ከ31 ዓመታት በላይ የተመዘገበ የትህነግና የኦህዴድ ብልፅግና የከረፋ ግፍ ነው የዛሬውን የፋኖ “የአማራ ሕዝብንና የኢትዮጵያ ሕዝብን” አብዮት የወለደው። አዎን ይህ “የኔና ያንቺ” “ያንተና የኔ” ትግል ነው የአማራንና የኢትዮጵያን ድል የሚወልደው። እኔም ፋኖ፣ አንቺም ፋኖ፣ አንተም ፋኖ ነን። የሁላችንም ህልውና አደጋ ላይ ወድቋል። እኔ ስዋደቅ፣ አንቺ ስትዋደቂ፣ አንተ ስትዋደቅ፣ እጃችንን አጣጥፈን መቀመጥ የለብንም። ይህ የአማራ ሰቆቃ የወለደው ወሳኝ የትግል መእራፍ የሚያስፈልገው መስዋትነት ተክፍሎበት በድል መጠናቀቅ አለበት። የፋኖ ትግል ነው። የሕዝብ ትግል ነው።
ድል ለፍኖ። ድል ለኢትዮጵያ ሕዝብ። ሞት ለአምባገነናዊው አብይ አህመድና ለዘር ፖለቲካ ደቀመዛሙርት።
ነፃነታችንን በክንዳችን እናስከብራለን። መጪውን ትውልድ እናኮራለን።
ፋኖ ተሰማራ ፋኖ ተሰማራ፣
ልቡ ያበጠውን ጥጋበኛ ግራ።
አንድ ብሄር ለማንገስ ሌላውን እረግጦ፣
የመጣውን ጠላት ሊገዛህ ቆላምጦ፣
በደፈራት መሬት አስቀረው ተውጦ።
ደረጀ አያኖ
መስከረም 24 ቀን 2016 ዓ/ም