October 5, 2023
13 mins read

በምድራችን እየሆነ ባለው ጉዳይ ህመሜ:-  (ያልታመመ ካለ ጤነኛ አይደለም) – ከአባይ ማዶ! ገሳ ለብሶ! እየቆዘመ!

Amhara cryአገሬን እወዳለሁ ካልን ለእውነት እንጂ ለብሄር ወይም ለዘር ፈጽሞ ጠበቃ አንሁን!
በቀድሞ ጊዜ ሁኔታዬ ደስ ያላለው አንድ የደርግ ካድሬ የነበረ ዘመዴ “ደም ከውኃ ይወፍራል” ይለኝ ነበር!  በደንብ አምኖበት አልነበረም ይህን የሚለኝ የኢሐፓን ማንነት እና  የአቁዋም ጽናት ጠንቅቆ ስለሚያውቅ ፈርቶና ሰግቶ ነበር ይህን ይለኝ የነበረው
ያደግንበት ማህበረሰብም እንዲህ ዓይነት አባባሎች ይጠቀም እንደነበር ትዝ ይለኛል! የትና መቼ እንደ ፈጸመው መረጃ ሳይኖር “ክርስቶስ ለሥጋው አደላ” እየተባለ ይነገር ነበር::
እነዚህና የመሳሰሉትን ወጎችና አባባሎች እየሰማ ያደገ ትውልድ ዋለልኝ አሻግሮ ሳያይ የጫረውን የብሄር ትርክት እና መለሰ ተግባራዊ ያደረገውን የዘር ፖለቲካ አሜን ብሎ በመቀበል ለማስተናገድ ጊዜ አልወሰደበትም::
ለዚህ ይመስለኛል ዛሬም የተገኘንበት ብሄር ስህተት ሲሠራ መቃወምና ሌላው ብሄር ጥሩ ሥራ ሲሠራ መደገፍ እንደ ክህደትና በደል የሚቆጠረው! ራሱን ሆኖ በራሱ መረዳት እውነትን እውነት! ውሸትን ውሸት የሚል ሰው እጅግ ይገዛኛል! ይማርከኛልም!
 የበለጠ የገረመኝና  ያሳዘነኝ ደግሞ ዶ/ሩ  ጴንጤ ስለሆነ ብቻ ዓይናቸውን ጨፍነው የሚደግፉ ጴንጤዎችና ጸረ-ማርያም ነው ብለው የሚቃወሙ ኦርቶዶክሶች ናቸው!
ያውም ዓለሙን አስደማሚ በሆነ ፍቅሩ የማረከውንና እየማረከ ያለውን የፍቅር ፈጣሪ እና
አይሁድን ከአሕዛብ የለየውን የጥል ግድግዳ አፍርሶ ከሁለቱ አንድ አዲስ ሰው የፈጠረውን አምላክ እናመልካለን እያሉ በዚህ መልኩ መውደድና መጥላት!
በመጨረሻም በአእምሮ ብስለት ብልጫ ሳይሆን በቁጥር ብዛታችሁ ላይ ተመስርታችሁ ሁሉን ነገር  ለመጠቅለል ሌት ከቀን ደፋ ቀና ለምትሉ ጠባብ ኦሮሞዎችና ጽንፈኛ አማራዎች  የምትሰሙና የምታርሙት ከሆነ በግል የታዘብኩትን ላካፍላችሁ:
1) አንዳንድ ጠባብ ኦሮሞዎችን እና ሸኔን በሚመለከት:
 >  በቂ መረጃ ሳይኖር (ቢኖርም አይጠቅምም) ዛሬን በትናንት የትርክት ሚዛን ለመመዘን ጥረት ማድረጋችሁ፣
> ጎረቢት ሆኖ አብሮአችሁ ይወጣ ይገባ የነበረውን (በተለይ አማራውን) ቅን ሕዝብ ማፈናቀላችሁ፣
> የሰውን ሕይወት እንደ ቅጠል በማርገፍና እንደ በግ በማረድ (ከበደኖ ገደል መጣል ጀምሮ) የአረመኔነት ጭካኔ ጥግ ማሳያታችሀ፣
> የኢትዮጵያ ብሄረሰቦች፣ የአፍሬካ መሪዎች እና የበርካታ ዓለም-አቀፍ ድርጅት መሪዎች መኖሪያ ከተማ የሆነቺውን አዲስ አበባ ከተማን የእኔ ብቻ (ኬኛ) በማለት ነውጥ እንዲፈጠርና ነፍስ እንዱጠፋ ማድረጋችሁ፣
> ከጥላቻ የተነሳ ለኦሮሞኛ ቁዋንቁዋ ባህር አቁዋርጣችሁ ፊደል መዋሳችሁና የጋራ አገራችን የታወቀችበትን የፊደልገበታ አጥብቃችሁ መጥላታችሁ፣
> የዶ/ር አቢይን እይታ ጠምዝዛችሁ ለጠባብ ዓላማችሁ ለማዋል የምታደርጉት ጥረት፣
> እንደ እቁብ ገንዘብ አገሪቱን ለመምራት ተረኞች ነን በማለት በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደርና የመንግሥት መስሪያ ቤቶች ውስጥ እያሳያችሁት ያለው ዓይን ያወጣ እንቅስቃሴ፣
                ወ  ዘ  ተ
ግልጽና ፍንትው ያሉ ስህተቶች ስለሆኑ እጅግ የሚያዋጣን በጋራ አገር ውስጥ በፍቅር በሰላምና በመተሳሰብ አብረን መኖር ነውና አብዛኛው ቅን ኦሮሞ በስምህ የሚነግዱትን ጥቂት ቀበሮችን ነቅተህ ጠብቅ! በፍቅር ወወጥመድ ቀስ ብለህ ይዘህ መልሳቸው ማለት እወዳለሁ!
2) አንዳንድ ጽንፈኛ አማራዎችና ነፍጥ ያነሳሃው ፋኖ:-
> በወይኔ ፊታውራሪነት በኦነግ የጭካኔ ተባባሪነት ገና ከጠዋቱ ጀምሮ በአማራው ላይ የደርሰውን በደል ለማወቅ የዓለም አቀፍና የአገር ውስጥ ሰባዊ መብት ድርጅቶችን ሪፖርት ማየት ይቻላል፣
(ይህ ሲሆን የት ነበራችሁ)
              ???
> በተለየ መልኩ አማራው ላይ የደረሰውንና እየደረሰ ያለውን በደል ለማወቅ ከተፈለገ በአገሪቱ ውስጥ በጊዜያዊነት የተሠሩትን መጠለያ ጣቢያዎች ማየት ይቻላል፣
(ለዚህ ሕዝብ በቅድሚያ
     ምን አደረጋችሁለት)
               ???
> ይህ ሁሉ በደልና ግፍ በዚህ ሕዝብ ላይ ሲፈጸም ግን  ያገሪቱን የፖለቲካ አካሄድ ከጅምሩ ተረድቶ ይህን ሕዝብ ከአንዣበበት የጥፋት ዳመና ለማትረፍ የተደራጀ የፖለቲካ ድርጅት ባለመኖሩ እረኛ እንደ ሌለው በግ ለቀበሮና ለተኩላ ተጋልጦ ሲበላ ቆይትዋል (የፕ/ር አሥራትን ጥረትና የሕይወት መስዋእትነትን ግን ታሪክ አይረሳውም
   (ለፕ/ሩ ምን አላችሁ)
              ???
> የሌሎች ብሄር ብልጥ ፖለቲከኞች ባልወከላቸው ሕዝብ ስም ተደራጅተው አቅማቸውን ሲያጠናክሩ እያየ የነበረው የአማራ ኤሊት ግን እስከ ቅርብ ጊዜ ድረስ ሌሎችን ጠባቦች በማለት እያወገዘና ኢትዮጵያ ኢትዮጵያ የሚል ዝማሬ እየዘመረ ሕዝቡን ካስበላ በሁዋላ ዛሬ ከረፈደ በሁዋላ ሌሎችን ባወገዘበት ተርታ ገብቶ ያለ መሪ ሲፋትር መታየቱ ጅብ ከሄደ…አያስብልም!
(ከጅምሩ አሻግሮ የሚያይ
  የነቃ ፕለቲከኛ እጦት)
              ???
> ከመከራ መላቀቅ ያልቻለው የአማራ ሕዝብ እንደ ዋና ጠላት ቆጥሮት ከደደቢት በርሓ ጀምሮ ሲገለውና ሲያስገድለው የነበረው ወያኔ በከፈተው አገራዊ ጦርነት ምክንያት የከፈለው  መስዋዕትነት ዋጋቢስ እዲቀር ማድረግ
አይሆንም???
> የወያኔ ጦርነት በቆመ ማግስት መንግሥት መደበኛና ኢመደበኛ በማለት ትጥቅ ለማስፈታት ባደረገው ሙከራ ፋኖ አልፈታም በማለቱ አሁንም ከመከላከያና ከክልሉ መንግሥት ጋር ጦርነት መገባቱ የት ያደርሳል???
> ልጅዋን አምጣ ወልዳ መልሳ እንደምትበላ እንስሳ ብርቅዬ የክልሉን ልጆች በጠራራ ጸሐይ የሚገል ቡድን በእውነት አማራን ይወክላል???
> እዚህ ላይ ፋኖ በአማራ መሬት ላይ ከመከላከያ ጋር ጦርነት ሲከፍት ከአማራው ሕዝብ ሙሉ ውክልና አግኝቶ ነው???
> ፋኖ መከላከያውን ለመመከት አቅም አለው? በቂ የሰውና የትጥቅ ኃይልስ አለው? ወዘተ ብሎ የሚጠይቅ ሰው በእውነት አማራ አጣ???
> አማራውን በሁለንተናዊ መልኩ እንደሚገባ አደራጅቶ፣ የፖለቲካ ንቃቱን አጎልብቶ፣ ማኒፌስቶ አውጥቶና ብቃት ያላቸው በሳል መሪዎች መርጦ በመዘጋጀት ስልጣንን በምርጫ መውሰድ ሳይሞከር በ21ኛው ክፍለ ዘመን በዚህ መልኩ በጉልበት መገለጥስ ያዋጣል???
*** በእውነት በእኔ እይታ ለዚህ መከራ ለበዛበት የዋህ ሕዝብ ፈጽሞ አለማሰብና አለማዘን ነው???
> በአጠቃላይ አማራውን “የአገር መከላከያ” ተብሎ በአገር ደረጃና ስም ከተመሰረተና እስከ አፍንጫው ከታጠቀ  የጦር ኃይል ጋርስ ማጋፈጥ ብሰለት ነው??
> ጦሩ ከሚወክላቸው ከ80 በላይ ከሆኑ ብሄረ ሰቦች ጋር ልክ እንደ (TPLF) ጦር መግጠም እንደሆነ የሚያስብ ፋኖ እንዴት ጠፋ???
> አዎ! እውነት ነው! አማራው ላይ በደል አለ! መንግሥትም ይህን እያየ ዝም ማለቱ የብዙዎቻችን ልብ በሃዘን እንዲዋጥ አድርጎናል:: ነገር ግን በዚህ ዝምታ ምክንያት በእልህና በስሜት ተዘሎ  ከአገር መከላከያ ጋር  በጦርነት እሳት ውስጥ መግባት አማራውን የበለጠ ከመጉዳቱም በላይ ከሞተላትና ዋጋ ከከፈለላት አገሩ ጋር ይህ ሕዝብ የታሪክ ገመዱን ማላላትና ለመበጠስ መሞከር አይደለምን??
***ለኢትዮጵያ የሞተ ሕዝብ ከኢትዮጵያ ጋር ጦር መግጠም ሆኖ አይሰማችሁም***???
           ትንሽ:
 ***የመፍትሄ ሃሳብ***
          ጥቆማ:-
ስህተትን በስህተት ማረም አይቻልም! የፖለቲካ ስንፍናንና ድካም በተሻለ እና በበለጠ የፖለቲካ ጥብብና ብስለት  ተደራጅቶ በአገሪቱ  እንደሚገባ አድጎ ባይጎለብትም ቅሉ በተጀመረው ነጻ ምርጫ በኩል አሸናፊ ሆኖ ለመውጣት ሳይሞከር እንዲሁ ድንገት ስልጣን በጠብ-መንጃ ኃይል ለመያዝ መሞከሩ ያለንበትን ዘመን ደህና አድርጎ አለመረዳት ነው የሆነብኝና ሰፊና የዋህ የሆነው የአማራና የኦሮሞ ሕዝብ በመካከሉ ያሉትን አዛኝ ቅቤ አንጉዋጆችን በማስተዋል ለይቶ በማውጣት አንድ ነገር እንዲላቸውና አገሪቱ ወያኔ ከቀደደቺው ዘር ተኮር የጥፋት አውራ ጎዳና ወጥታ ሰላም ታገኝ ዘንድ በያገባኛልና በጋራ መነሳት አለባችሁ ብዬ አምናለሁ?
ማስተዋል ለጎደለን ማስተዋል ይብዛልን!
               አሜን!
ከአባይ ማዶ! ገሳ ለብሶ! እየቆዘመ!

Leave a Reply

Your email address will not be published.

Latest from Blog

ጥር 2 ቀን 2017 ዓ/ም   January 10, 2025  በኢትዮጵያዊነታችሁ፡ በኦርቶዶክሳዊ እምነታችሁ፡ በአማራነታችሁ፡ በአማረኛተናጋሪነታችሁ፡ በተሰነዘረባችሁ ብትር፡ ቤተ ሰብ፡ ወዳጅ ዘመዶቻችሁን ያጣችሁ: ልጆቻችሁን የቀበራችሁ፡ አካልችሁን ያጣችሁ፡ የተሰነዘረውን ብትር በመከላከል ላይ ያላችሁ፡ያለፈቃዳችሁ በመንግሥት ተጽእኖ ወደመግደልና

በኢትዮጵያዊነታችሁ፡ በኦርቶዶክሳዊ እምነታችሁ፡ በአማራነታችሁ፡ በአማረኛተናጋሪነታችሁ፡ በተሰነዘረባችሁ ብትር፡

January 10, 2025
መኮንን ሻውል ወልደጊዮርጊስ ¹⁵ የምድርም ነገሥታትና መኳንንት ሻለቃዎችም ባለ ጠጋዎችም ኃይለኛዎችም ባሪያዎችም ጌቶችም ሁሉ በዋሾችና በተራራዎች ዓለቶች ተሰወሩ ፥ ¹⁶ ተራራዎችንና   በላያችን ውደቁ በዙፋንም ከተቀመጠው ፊት ከበጉም ቍጣ ሰውሩን ፤ ¹⁷ ታላቁ የቁጣው ቀን  መጥቶአልና ፥ ማንስ ሊቆም ይችላል ? አሉአቸው ። ራእይ 6 ፤  15_17 ይኽ የመጽሐፍ ቅዱስ ቃል ። የኢየሱስን ልደት ሰናከብር የየሐንስ ራእይን ማንበብ ጠቃሚ ይመስለኛል ። ምክንያቱም በመጨረሻው ዘመን

ከኢየሱስ የፍርድ ቀን በፊት በህሊናችን ውስጥ ፍቅርን ለማንገስ እንጣር 

የምጣኔ ሀብታዊ ፍጥ፣ የፖለቲካ፣ የእውነትና የሰብአዊ መብት ታጋይ፣ የአመኑበትን ነገር ለመናገር እንደ ፖለቲከኛ በቃላት ሳያሽሞነሙኑ ቀጥታ የሚናገሩት የሀገሬ ኢትዮጵያ ታላቅ ሰው ነበሩ “ዘር ቆጠራውን ተዉት፤ የአባቶቻችሁን ሀገር ኢትዮጵያን አክብሩ!”  አቶ ቡልቻ ደመቅሳ

ሀገር ወዳዱ አቶ ቡልቻ ደመቅሳ ከዚህ አለም በሞት ተለዩ

January 6, 2025
ግን ይህ ሁሉ ወጣት የት ገባ? ግን ይህ ሁሉ ወጣት የት ገባ? ዛሬ፣ 2025 ዓ/ም ላይ ብንገኝም በዝንጋታ ገመድ ወደ ሞት እየተጎተትን እንደሆነ አናውቅም። (ሁል ጊዜ የሚሞተው የገነዝነው ይመስለናል። ) “ገብርዬ ነበረ

ግን ይህ ሁሉ ወጣት የት ገባ?

January 3, 2025
መኮንን ሻውል ወልደጊዮርጊስ ዛሬ እንደ አውሮፓዊያኑ አቆጣጠር ጥር 1ቀን 2025 ዓ/ም ነው ። አውሮፓውያኑ አዲስ ዓመትን “ሀ” ብለው ጀምረዋል ። አዲሱን ዓመት ሲጀምሩም ከልክ ባለፈ ፈንጠዚያ ነው ። ርቺቱ ፣ ምጉቡና መጠጡ

ዛሬ፣ 2025 ዓ/ም ላይ ብንገኝም በዝንጋታ ገመድ ወደ ሞት እየተጎተትን እንደሆነ አናውቅም። (ሁል ጊዜ የሚሞተው የገነዝነው ይመስለናል። )

Go toTop