August 14, 2023
3 mins read

ጎንደር ተደፈረች እብድ አግብታ #ዝናሸ (ጎንደሬው በጋሽው)

367441544 1931458527226145 7510044037883034699 n 1 1 1

ኧረ የጎንድር ሰው እትየ የዝና የኛይቱ የዝናሺ
ምን ክፉ ገጠመሺ ምን ጉደኛ አመጣሺ
ገዳዩ ጨፍጫፊው አውዳዊም ባልሺ
የሞተውወንድምሺ ያለቀውም ህዝብሺ

“ድርቡሽም ቢመጣ አልደረሰም ደጅሽ፤
ቱርክም ቢንደረደር አልመጣም ከበርሸ፤
ጣሊያን ቢገሰግስ አልገባም ከቅጥርሸ፤
የሀገር ጉልላቷ የፋሲል አዳራሸ፤
ጎንደር ተደፈረች እብድ አግብታ #ዝናሸ።

ወይ ብሬ ዘገየ ጉድህን አልሰማህ፤
አለመኖር ጥሩ በዓይን አለማየትህ፤
ቀኝ አዝማች ደጃዝማች የሾመህ ሀገርህ፤
ጎንደር ተደፈረ እብድ አግብታ ልጅህ።

“ሴት መውለድ ጉድ መውለድ” ይባል ነበር ድሮ፤
እውነት ነው ነገሩ ዓይኔ አየ ዘንድሮ፤
አርማጭሆ ስማ ወልቃይትም አድምጥ ዳንሻና ማሰሮ፤
ጎንደር ተነከሠ #ዝናሽ ባገባችው የጅማ ቀበሮ።

ያለ አቻ ጋብቻ የሀገሬ ወይዛዝርት፤
የአርማጭኾ ልጆች በደንብ የታወቁት፤
የደጃች ጎላ ልጅ የመለሰ ሚስት፤
የደጃች ብሬ ልጅ የዐቢይ እመቤት፤
እብድ እየጎተቱ እያመጡ ከቤት፤
ጎንደር ተቃጠለ ሙሉ ሠላሳ ዓመት።

በኢያሱ ዙፋን ላይ በምንትዋብ እልፍኝ፤
የመለሰ ቅኝት የወያኔ አቀንቃኝ፤
እህቴን ያገባ “አማች” በስለት አረደኝ፤
ጎንደርን አቃጥሎት በረመጥ ጠበሰኝ።

ወይ ሀገሬ ጎንደር ማማው ደብረታቦር፤
ባህል የሌለው ሰው ለማያውቅ ክብር፤
ያለ አቻ ጋብቻ ባልተገባ ነበር፤
#በዝናሽ አፈረች የፋሲል ከተማ የቴዎድሮስ ሀገር።

የደጅ አዝማቹ ሰው የብሬ ዘገየ፤
የአርማጭሆው መብረቅ በግንባር የታየ፤
በጣልያን ወረራ ነጩን ያበራየ፤
እብድ አግብታ ልጁ ጎንደር በሳት ጋየ።

አንባቸውን ሲገድል ታግሠን አልፈናል፤
ስመኘውን ሲገድል አልቅሰን ቀብረናል፤
ምግባሩንም ሲገድል አዝነን ተክዘናል፤
ወልቃይትን ሊሸጥ ከአሜሪካ መክሯል፤

መረረን ከበደን ከአቅም በላይ ሆኗል፤
ወይ እኛ እንኖራለን ወይ እሱ ይኖራል፤
#ዝናሽ ያገባሽው ጎንደርን አፍርሷል።”

Leave a Reply

Your email address will not be published.

Go toTop