አቶ ማሞ ምህረቱ የወቅቱ ኦሮሙማ መንግስት የብሄራዊ ባንክ ገዥ ተደርገው የተሾሙ የአብይ አህመድ የቅርብ ሰው ናቸው፡፡ አቶ ማሞ ጎበዝ ባለሙያ ሊሆኑ ይችላሉ፤ የኢትዮጵያን ብሄራዊ ባንክ በገዥነት ሊመሩት የሚችሉ ሰው ግን እንዳልሆኑ አብይ አህመድ ጎን ተሰልፈው በቆዩባቸው አመታት በሰሯቸው ስራወች ትዝብት ውስጥ ወድቀዋል፡፤ እርሳቸው ሳይሆኑ ስርአቱ እንዲያጎበድዱ አድርጓቸው ሊሆን ይችላል፡፡ይህ በአንዳንዶቻችን የዋሆች ዘንድ የብዙ ጎበዝ ባለሙያወች መጥፎ አጋጣሚ ተደርጎ ሊታሰብ ቢችልም ይህንን ተረኛ አገዛዝ በፈቃዳቸው ለማገልገል በመሰለፋቸው ሁሉም በሚባል ደረጃ ለአገሪቱ ምን እርባና ሰጡ ?? ምሳሌ የምርጫ ኮሚሽን ከሚሽነሯ ወ/ት ብርቱካን ሚደቅሳ፣ የስብአዊ መብት ኮሚሽን ኮሚሽነሩ ዳንኤል በቀለና ወዘተ …. መሰሎቻቸው፡፡
ኢትዮጵያ በታሪኳ አይታው የማታወቀው የፖለተካና የኢኮኖሚ ቀውስ ውስጥ ተዘፍቃለች፡፤ ፖለቲካው በለሆሳስ አቶ ማሞን አይመለከታቸውም ብለን እንለፈው፤ ኢኮኖሚው ግን ይመለከታቸዋል፡፤ ኢኮኖሚ ውስጥ ገንዘብ ትልቁ መሳሪያና ሞተር ነው፡፤ ማንም የራሷ መገበያያ ገንዘብ ያላት አገር የገንዘብ ስርአቷ የሚመራውና የሚተዳደረው በዚያችው አገር ማእከላዊ ባንክ በኩል ነው፡፡ ስለሆነም የአንዲት አገር ማእከላዊ ባንክ ለኢኮኖሚው ትልቅ ሀላፊነትና ሚና አለው፡፡ ይህ ማእከል እንደየአገሩ የተለያዩ መጠሪያወች አሉት፡፤ በአሜሪካ FEDERAL RESERVE በእንግሊዝ አገር BANK OF ENGLAND የሚባል ስም ያለው ሲሆን በኢትዮጵያም NATIONAL BANK OF ETHIOPIA የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ነው፡፡
የአንድ አገር ማእከላዊ ባንክ የዋጋ ንረትን ይቆጣጠራል፣ የኢኮኖሚመረጋጋቱን ይከታተላል፣ የአገሪቱን ገንዘብ ያትማል፡፡ ዝውውሩንና ህጋዊ ስርጭቱንም ይከታተላል፡፡ መንግስትን በኢኮኖሚ ፖሌሲ ያማክራል ሌሎች ባንኮችንም ይቆጣጠራል ወዘተ፡፡ በኢትዮጵያ ግን እነዚህ ድርጊቶች የሚፈጸሙት በብሄራዊ ባንኩ ሙያተኞች ታግዞ በባንኩ ነጻ እርምጃወች አይደለም፡፡ ታዲያ ጅብ ከሄደ ዉሻ ጮሀ እንዲሉ የአገሪቱ ኢኮኖሚ እምሽክ ድቅቅ ብሎ ክወደቀ በኋላ የአቶ ማሞ ምህረቱ የአርብ ሰኔ 5 ቀን 2013 ዓ/ም በቴሌቪዥን የተላለፈው የማይሆን ቅብጥርጥሮሽ ማንን ለማምታታት ነው፡፤
ስርአቱ ካልተቀየረ ኢኮኖሚው አያገግምም፡፡ አለቀ፡፡
ይህችን አጭር ጽሁፍ ለማቅረብም ያነሳሳኝ ብዙ የአብይ አህመድ ጀሌወች የባንኩን ገዥ ንግግር መሰረት አድርገው የኢትዮጵያ የኢኮኖሚ ችግሮች እንደተፈቱና በንግራቸውም መሰረት በቅርቡ እንደሚፈቱ የተሳሳተውንና ሆን ተብሎ የተዛባውን መረጃ በስፋት እያሰራጩት በመሆኑ ስለ ሁኔታው እውነታውን አስረግጦ መልስ መስጠት አስፈላጊ መስሎ ስለታየኝ ነው፡፡
የምርቶችና ሸቀጦችን ዋጋ ምን ያህል እንደናረ እዚህ ማንሳቱ ለቀባሪው አረዱት ነው፡፤አንዲት ምሳሌን ብቻ ላንሳላችሁ፡፡ አዲስ አበባ ጎዳና ላይ አንዲት ራስ በቆሎ 25 ብር ነው የምትሸጠው፡፤ በሌላ በኩል ደግሞ በይፋ የሚካሂደውን የውጭ ምንዛሬ የጥቁር ገበያ ቁማር በአጭሩ እንደሚከተለው በወፍ በረር ልጥቀስላችሁ፡፤
በአብይ አህመድና ሸሪኮቹ ገንዘብ አስተላላፊወች በኩል ወደ ኢትዮጵያ ከውጭ አገር ዶላር ሲላክ ክፍያው ለተላከለት ሰው የሚፈጸመው በባንክ በኩል በተላከለት ሰው ሂሳብ አማካይነት ነው፡፡ ይታያችሁ በጥቁር ገበያው ተላከ ወደ ኢትዮጵያ አካውንት ገባ ለተባለው ዶላር ነው አገር ቤት በባንክ ህጋዊ ተደርጎ ክፍያው የሚፈጽመው፡፡ ይህ የሚሆነው እንዴት ነው ብለን ብንጠይቅ አፈጻጸሙ በአጭሩ እንደሚከተለው ነው፡፡
በውጭ አገር በአብይ አህመድና ወይንም በሸሪኮቹ የሚታዘዝ የገንዘብ አስተላላፊ ቡድን አለ፡፡ በአገር ውስጥ ደግሞ ብሩን ወደ ተቀባዩ የባንክ ሂሳብ የሚያስገባ የተደራጀ ቡድን አለ፡፡ ሁለቱን ከላይ ሆኖ የሚመራው የጥቁር ገበያው ማእከል አለ፡፤ ይህ ማእከል ከፍተኛ የሆነ የመንግስት ጥበቃ የሚደረግለት ወይንም ራሱ መንግስት የሆነ አደገኛ ቡድን ነው፡፡
ገንዘብ አስተላላፊው አንድን ዶላር ለምስሌ በ110 ብር ሂሳብ ከዲያፖራው ይቀበላል፡፡ የሚላከው የዶላር መጠን አንድ ዶላርን በ110 ብር ተመን ተባዝቶ ለተላከለት ሰው በባንክ እንዲከፈል ለሚያደርገው ቡድን መልእክቱ ይተላለፍለታል፡፡የአገር ቤቱ ብር ከፋይ ቡድን ከገንዘብ አስተላላፊው የተነገረውን መረጃ ይዞ ብሩን ለተቀባዩ በባንክ ሂሳቡ ያስገባል፡፡ ይህ ዝውውር በበአላት ቀናት አካባቢወች ብዙ መቶ ሚሊዮን ብሮችም ሊደርስ ይቻላል፡፡ ይህን ያህል ገንዘብ ነው ያ ቡድን በቀን የሚያንቀሳቅሰው፡፡የውጭ ምንዛሬው ጥቁር ገበያው ሰንሰለት የተዘረጋው ከላይ ከከፍተኛ ባለስልጣናት ሚኒስትሮችንም ጨምሮ (ምናልባትም ከራሱ ከአብይና ከወ/ሮ አዜብ ሊጀምርም ይችላል) ወደታች እስከ ገንዘብ ከፋዩ ቡድን ድረስ ይወርዳል፡፡ የየእለት ኡደቱም ማለትም የዶላሩ ውጭና ገቢ በዚህ መልክ በየእለቱ ከተሰበስበ በኋላ ዶላሩ ወደ አገሪቱ ሂሳብ ሳይሆን ወደግለሰቦች ሂሳብ/ኪስ ውስጥ እንዲገባ ይደረግና በዚያው ሰምጦ ይቀራል፡፡ ታዲያ አንድ ዶላርን በብር 54 ሂሳብ እንዲመነዘር ያዘዘው ብሄራዊ ባንክ ይህንን ዘረፋ አያውቅም የሚል ሰው ካለ ሞኝ ብቻ ነው፡፡
ሌላውና እጅግ አሳፋሪ የሆነው ድርጊት ደግሞ የማንም አገር ገንዘብ ላይ ታትሞ ያለው ጽሁፍ እንደሚያስረዳው ማንም ሸቅጥም ሆነ አገልግሎት ስጪ ሰስጠው ሸቅጥም ይሁን ለሰጠው አገልግሎት ያንን ገንዘብ (ብር) አልቀበልም የማለት መብት የለውም፡፡ ይህ ጽሁፍ ላምሳሌ በብሩ ላይ “”ላምጭው እንዲከፈል ህግ ያስገድዳል-PAYABLE TO THE BEARER””ይላል፡፡በእሜሪካ ዶላር ላይ እንደዚሁ “THIS NOTE IS A LEGAL TENDER FOR ALL DEBTS PUBLIC AND PRIVATE “ ይላል፡፡
ይህ በኢትዮጵያ ውስጥ በአቶ ማሞ ምህረቱ ዘመን ተጥሷል፡፡ የትም ቦታ ኢትዮጵያ ውስጥ የትኛውም ነዳጅ ማደያና መሸጫ ቦታ ገዥው መደብ ለጥቅሙ ያዘጋጀውን ዲጂታል ካርድ ተጠቃሚው ካርዱን በብሩ ገዝቶ ጋዙን/ነዳጁን በካርድ እንዲገዛ ይገደዳል እንጅ ጋዝ/ ነዳጅ በብር መግዛት አይችልም፡፡
የኦሮሙማው መንግስት በህግ ይህንን ማድረግ እንደማይችል አያውቅም፡፡ ጠያቂም የለውም፡፡ይህ ህግንና ህዝብን ንቀት ነው ፤ መንግስት ተብየው ቡድን ይህንን ያደረገው ከዲጂታል ካርዱ ንግድ ድብቅ ጥቅም ስላለው ነው፡፡የተወሰኑ የገዥው መድብ ጅላንፎወች ድጅታል ካርድን መጠቀም የቴክኖሎጅ እድገትን ማስፋፋት ወይንም ስልጣኔን ማስረጽ ነው የሚሉ አሉ፡፡ እኔን!!! ተላለፍን አሉ እማማ ዝናሽ፡፡
ያም ሆነ ይህ ተረኛው የኦሮሙማ መንግስት ከገባበት የወቅቱ የውጭ ምንዛሬ ችግርና የተቆላለፈ የፖለቲካ አጣብቂኝ መውጫ ቀዳዳ ብሎ ያሰበው አቶ ማሞ ምህረቱን ማስለፍለፍ ነው፡፤ ማሞ ምህረቱ << … የዋጋ ንረቱ በ2016 በዚህ ያህል መጠን እንዲቀንስ እናደርጋለን፤ በ2017 ደግሞ ይህንንና ያንን እንደዚያ እናደጋለን….ወዘተ>>> እያሉ የሚቀባጥሩበት ዋናው ምክንያት ከኦሮሙሟው ቁንጮ ከአብይ አህመድ በተሰጣቸው ትእዛዝ መሰረት የአለም ባንክንና የአለምን ገንዝብ ድርጅትን በማማለል ብድርንና ርዳታን ለማግኘት ነው፡፡
የአለም ገንዘብ ድርጅትና የአለም ባንክ ከተጨባጭ እውነታው ውጭ በዚህ ቅጥፈት ይማልላሉ ወይ? የሚለውን የምናየው ይሆናል፡ ሁለቱም የገንዘብ ድርጅቶች በተወስኑ የምእራብዊያን አገሮች ተጽእኖ ስር የወደቁ ናቸውና ነገሩ ሊሆንም ላይሆንም ይችላል፤፡ አገሪቱም እንደዚሁ፡፡ ዋናው ነገር የኢትዮጵያ ህዝብ አገሩንና ነጻነቱን አሳልፎ ላለመስጠት ቆርጦ መነሳቱ ላይ ነው፡
በዚህ አጋጣሚ በሚሊዮኖች ታርዶና በሚሊዮኖች ተሰድዶ አላልቅ ያለውን የአማራን ህዝብ ህልውና ለማዳን ዘግይቶም ቢሆን የአማራ ህዝባዊ ግንባር አማራውን አስቀድሞ ነጻ የማውጣት ትግል ውስጥ ገብቶ በጥቂት ቀናቶች ትግል ብቻ አመርቂ ዉጤቶችን ማሳየቱን አደንቃለሁ፡፡ ቀጥሎም ወንድም ከሆነው ቀሪው የኢትዮጵያ ህዝብ ጋር ኢትዮጵያን ለማዳን የሚያደርገውን ግስጋሴና አራት ኪሎን የተጋድሎው መዳረሻው ያደረገውን ዉሳኔውን እደግፋለሁ፡፡ በመሰረቱ ኦሮሙማም ሆነ ብአዴን ወያኔ የተከላቸው መርዞች ናቸው፡፡ አማራው ሽምግልና ወዘተ የሚባሉትን የኦሮሙማ ማታለያወች መቀበል የለብትም፡፤ የሚያደርገው ተጋድሎ ነጻ ህዝብ የመሆን ወይንም ያለመሆን ትግል ነው፡፡ ወፍ ዘራሹ አብይ አህመድና መንጋው ኦሮሙማ የራሴ የሚለው የታሪክ አሻራ ስለሌለው ምቀኝነትም ጭምር ውስጥ ገብቷል፡፡ ስለሆነም የመከለክያ ዩኒፎምን አልብሶ ያሰለፈው ወራሪ የኦሮሞ ጦር በአማራክልል ከተሞች ያሉትን የታሪክ አሻራወቹች በመድፍና ታንክ እንድያወድሙበት ልክ እንደ አሁኑ ለጊዜውም ቢሆን ከከተማ ገሸሽ የማለት ስልትን እየለዋወጡ ወደ ድል የሚያደርሱ መሰል ስራቴጅወችን መከተል በሳል አመራር ነው፡፡
ከዚሁ ኑሮ ዉድነት ባለፈ የእርስ በስርስ ጦርነቱም አፍጥጦ እየመጣ ስለሆነ ህዝቡ ታሪክ የጣለበትን ሁኔታ በጥበብ ለማለፍ እውነትንና ሀቅን መሰረት አድርጎ የተረኞቹን የጠነባና የበስበሰ ስርአት ወደማይቀረው ቀብሩ አፋጥኖ መሸኘት አለበት፡፡ ሌላ አማራጭ የለም፤ ችግሩን ሲፈሩት ዉለው ሲፈሩት ቢያድሩ የሚቀየር ወይንም የሚሻሻል ወይንም ወደ በጎ የሚለወጥ ቅንጣት ነገር የለም፡፡ በዚህ መሀክል ያውም ባለቀ ሰአት የአቶ ማሞ ምህረቱ ይህን ሁሉ እንደማያውቁ ሆነው እንደ አለቃቸው አብይ አህመድ መበጥረቃቸው ፅብት ላይ ይጥላቸዋል እንጅ አይጠቅማቸውም፡፡
እውነቱንም የሚሆነውንም ቅንጣት አይቀይረውም፡፡