August 9, 2023
6 mins read

የአሜሪካ ጦር በጅቡቲና የአማራ ክልል ጦርነት ከመቶ አመት በፊት ከነበረው ክስተት ጋር ያለው ግጥምጥሞሽ!!! – በዳዊት ሳሙኤል

Screenshot 20230810 141032 Google 1 2ሰላምን አጥብቆ የሚወድ ለጦርነት በብርቱ ይዘጋጅ ይላል አንድ ፖብልየስ ፍላቪየስ የሚባል ጥንታዊ የጦር ስልት አዋቂ ሰው።  ዛሬ አለምን በጩልቅታ እምዳስስበትን የፌስቡክ መስኮቴን ስከፍት አንድ እሱ ባለው ጫኔ የሚባል ሰው በስሜት እና በወኔ ጅቡቲ ያለው የአሜሪካ ጦር በከፍተኛ የቴክኒዎሎጅ ድጋፍ ድሮንን ጨምሮ ለመንግስት በመስጠት በመከረኛው  በራያ እና በወልቃይት ህዝብ ላይ መጠነ ሰፊ የሶስት ቀን ጦርነት ለማድረግ እንዳሰበ ይገልጻል። እኔም ሶስት ነገሮች በፍጥነት ወደ አእምሮየ አመጣብኝ።
ሀሳብ አንድ፣
“” ”””””””””””
በዚህ ሳምንት የአሜሪካ ስቴት ድፖርትመንት ለጋዜጠኞች መግለጫ በሚሰጥበት ወቅት አንድ መስፍን የተባለ ጋዜጠኛ ስለ አማራ ክልል ወቅታዊ ሁኔታ ሲጠይቅ መላሹ ሲመልስ ስለ ትግራይ ክልል ነበር። ጋዜጠኛውም ደጋግሞ ጠየቀው። ይህ በዲፕሎማሲያዊ ቋንቋ አያገባኝም ማለት ነው።
ሀሳብ ሁለት፣
“””””””””””””
ከአራት ወራት በፊት ሀመር የተባለ ዲፕሎማት በቀጭን ትእዛዝ የአማራን ችግር ፍቱ ብሎ ለመንግስት ሲናገር እና ቀጥሎ ላለፉት አራት ወራት የሆነውን ስናይ ዲፕሎማሲያዊ ንግግር ቅኔ መሆኑን መረዳት ያስችላል።
ሀሳብ ሶስት፣
“””””””””””””
አእምሮ መቸም ረፍት የለውም በቀጥታ ተወርውሮ ወደ 1922 ዓም ወደተደረገው የአንችም ጦርነት ይዞኝ ሄደ።
ታሪኩ እንዲህ ነው። የታላቁን ንጉስ የዳግማዊ ሚኒሊክን ሞት ይጠባበቁ የነበሩት አውሮፖውያን ኢትዮጵያን ለሶስት ለመቀራመት ወስነው አድፍጠው ይጠብቁ ነበር። ነገር ግን ንጉሱ ሚኒስቴር መስሪያ ቤት አቋቁመው ሀገራችን እንድትቀጥል አደረጓት። ወራሻቸው ልጅ እያሱንም አደረጉ። ከኢያሱም ቀጥለው ልጃቸው ንግስተ ነገስታት ዘውዲቱ ተሾሙ። በዚህ ወቅት የንግስቲቱ ባል የነበሩት የአድዋው ጀግና የየጁ ስርወ ራስ ወራሽ እና የአሁኑ የበጌምድር ገዥ ራስ ጉግሳ ወሌ ሸዋ ላይ በተሰራ ሴራ የባለቤታቸው ስልጣን ሲሸረሸር አኩርፈው ባለበት የሸዋ መኳንንት የራያ ህዝብ አምጿልና ሂደህ ምታ አሏቸው። እሳቸውም ጦራቸውን ይዘው ሂደው ከወገኖቻቸው ጋር ተመካክረው ጦርነቱን በሰላም ይፈቱታል።  በዚህ ግዜ ከሸዋ በኩል ባስቸኳይ ትፈለጋለህ ና ሲባሉ አሁንም እንደገና ከበጌምድር ፣ ከየጁ እና ከራያ ህዝብ ጋር ምክር ተቀምጠው ህዝቡ አትሂድ እኛን አውራ አልባ ታደርገናለህ አላቸው። እሳቸውም አልመጣም አሉ።
በዚህ ወቅት ጣሊያን ከስድስት አመት በኋላ ኢትዮጵያን ለመውረር አቅዳ እየተዘጋጀች ያለችበት ወቅት ነበር። ታሪኩን ለማሳጠር ዛሬ ሰሜን ወሎ ጋሸና ከሚባለው አካባቢ ” አንችም” ሜዳ ላይ ከሸዋ በመጣው ጦርና በራስ ጉግሳ ጦር መካከል ከባድ ውጊያ ተቀሰቀሰ። ከዚህ ጦርነት በፊት የኢትዮጵያ ጦር መሪ የነበሩትን ራስ ብሩ ወልደ ገብርኤልን በሴራ እንዲወርዱ ተደርጎ ራስ ሙሉጌታ ይገዙ ተሹመዋል። የአንችምን ውጊያ የመሩት እሳቸው ናቸው። ይህ ሰው እጅግ ደካማ ሰው ነበሩ።
በዚህ ጦርነት ወቅት በአፍሪቃ የመጀመሪያው የተባለው የአውሮፕላን ቦምብ ድብደባ የተደረገው በዚህ ወቅት ነበር። ህዝቡ ከዚህ በፊት ከሰማይ የዚህ አይነት መአት አይቶ አያውቅም። የሰውና የበቅሎና የፈረስ ሬሳ ተነባበረ። ራስ ወሌም በዚህ ቦታ ላይ ተሰው።ዋናው ጭብጡ እዚህ ላይ ነው። አውሮፕላኖቹ የማን ነበሩ? ከየት ተነሱ? የሚለው ነው።
አውሮፕላኖቹ የተነሱት ዛሬ ጅቡቲ ከምንለው አገር ትዩዩ ኤደን ከሚባል ቦታ ነበር። ንብረትነታቸው የእንግሊዝ ሲሆኑ እንግሊዞቹ በተጠና ሁኔታ ቀድመው የሀገሪቱ ህዝብ  በደም እንዲቃባ አደረጉት። የበጌምድር ጦር በከሀዲው አያሌው ብሩ ምክንያት በጦርነቱ ሳይሳተፍ ቀረ። የየጁና የራያ ህዝብ አለቀ። ከስድስት አመት በኋላ ጣልያን ሲመጣ ራያ በዚህ በቀል ራስ ሙሉጌታ ይገዙን አምባራዶም ላይ ተፋልሞ ገደላቸው።
አንባቢ እንዳይሰለች ጽሁፉን እዚህ ላይ ላሳጥረውና ከላይ ከተቀመጡት ሶስት በፍጥነት ከተጅጎደጎዱብኝ ሀሳቦች አንጻር አሜሪካኖቹ አቶ እሱ ባለው ያለውን አይፈጽሙም ብሎ የሚጠራጠር ይኖራል?
ይቆየን።

Leave a Reply

Your email address will not be published.

Latest from Blog

ጥር 2 ቀን 2017 ዓ/ም   January 10, 2025  በኢትዮጵያዊነታችሁ፡ በኦርቶዶክሳዊ እምነታችሁ፡ በአማራነታችሁ፡ በአማረኛተናጋሪነታችሁ፡ በተሰነዘረባችሁ ብትር፡ ቤተ ሰብ፡ ወዳጅ ዘመዶቻችሁን ያጣችሁ: ልጆቻችሁን የቀበራችሁ፡ አካልችሁን ያጣችሁ፡ የተሰነዘረውን ብትር በመከላከል ላይ ያላችሁ፡ያለፈቃዳችሁ በመንግሥት ተጽእኖ ወደመግደልና

በኢትዮጵያዊነታችሁ፡ በኦርቶዶክሳዊ እምነታችሁ፡ በአማራነታችሁ፡ በአማረኛተናጋሪነታችሁ፡ በተሰነዘረባችሁ ብትር፡

January 10, 2025
መኮንን ሻውል ወልደጊዮርጊስ ¹⁵ የምድርም ነገሥታትና መኳንንት ሻለቃዎችም ባለ ጠጋዎችም ኃይለኛዎችም ባሪያዎችም ጌቶችም ሁሉ በዋሾችና በተራራዎች ዓለቶች ተሰወሩ ፥ ¹⁶ ተራራዎችንና   በላያችን ውደቁ በዙፋንም ከተቀመጠው ፊት ከበጉም ቍጣ ሰውሩን ፤ ¹⁷ ታላቁ የቁጣው ቀን  መጥቶአልና ፥ ማንስ ሊቆም ይችላል ? አሉአቸው ። ራእይ 6 ፤  15_17 ይኽ የመጽሐፍ ቅዱስ ቃል ። የኢየሱስን ልደት ሰናከብር የየሐንስ ራእይን ማንበብ ጠቃሚ ይመስለኛል ። ምክንያቱም በመጨረሻው ዘመን

ከኢየሱስ የፍርድ ቀን በፊት በህሊናችን ውስጥ ፍቅርን ለማንገስ እንጣር 

የምጣኔ ሀብታዊ ፍጥ፣ የፖለቲካ፣ የእውነትና የሰብአዊ መብት ታጋይ፣ የአመኑበትን ነገር ለመናገር እንደ ፖለቲከኛ በቃላት ሳያሽሞነሙኑ ቀጥታ የሚናገሩት የሀገሬ ኢትዮጵያ ታላቅ ሰው ነበሩ “ዘር ቆጠራውን ተዉት፤ የአባቶቻችሁን ሀገር ኢትዮጵያን አክብሩ!”  አቶ ቡልቻ ደመቅሳ

ሀገር ወዳዱ አቶ ቡልቻ ደመቅሳ ከዚህ አለም በሞት ተለዩ

January 6, 2025
ግን ይህ ሁሉ ወጣት የት ገባ? ግን ይህ ሁሉ ወጣት የት ገባ? ዛሬ፣ 2025 ዓ/ም ላይ ብንገኝም በዝንጋታ ገመድ ወደ ሞት እየተጎተትን እንደሆነ አናውቅም። (ሁል ጊዜ የሚሞተው የገነዝነው ይመስለናል። ) “ገብርዬ ነበረ

ግን ይህ ሁሉ ወጣት የት ገባ?

January 3, 2025
መኮንን ሻውል ወልደጊዮርጊስ ዛሬ እንደ አውሮፓዊያኑ አቆጣጠር ጥር 1ቀን 2025 ዓ/ም ነው ። አውሮፓውያኑ አዲስ ዓመትን “ሀ” ብለው ጀምረዋል ። አዲሱን ዓመት ሲጀምሩም ከልክ ባለፈ ፈንጠዚያ ነው ። ርቺቱ ፣ ምጉቡና መጠጡ

ዛሬ፣ 2025 ዓ/ም ላይ ብንገኝም በዝንጋታ ገመድ ወደ ሞት እየተጎተትን እንደሆነ አናውቅም። (ሁል ጊዜ የሚሞተው የገነዝነው ይመስለናል። )

Go toTop