July 28, 2023
22 mins read

ኢትዮጵያ ሆይ በስምሽ ስንት ወንጀል ተሠራ?

Abiy Ahmed Killer 1ሐምሌ 20 ቀን 2015 ዓም(27-07-2023)

የሌላውን ዘመን ትተን እኛ ባዬነውና  እያለንበት ባለው ዘመን ኢትዮጵያ  በስሟ የተጠቀሙና በመጠቀምም ላይ ያሉ መሪና ተከታዮቻቸውን ተሸክማ ዘልቃለች።ሁሉም ጊዜ አመጣሽ እርስ በርሱ አንዱ ሌላውን እዬከሰሰና እዬወቀሰ ከዛም ባለፈ ሃይል ተጠቅሞ ያሶገደበት ትልቁ መሣሪያ ቢኖር ኢትዮጵያ የሚለው አንጀት የሚበላ ስሟ ነው።ኢትዮጵያ የሚለው መጠሪያ የሁሉንም ቀልብ የሚስብ፣የሚማርክና ልብን የሚሰልብ ትንግርተኛ ምድራዊ መለኮት ነው።ስለኢትዮጵያ የሞተውን፣በስምሽ የገደለውንና የዘረፈውን ለመቁጠር ያዳግታል።ስለአንች በንጹህ ልቦናና ፍቅር፣ዜጋዊ ግዳጁን ለመወጣት ሲል ሊያጠቁሽ ከመጡት የውጭ ጠላቶች ጋር ተናንቆ ፣የሕይወት ዋጋ ከፍሎና ደሙን አፍሶ ነጻነትሽንና አንድነትሽን ያስከበረ  የቁርጥ ቀን የሆነ ዜጋ የመኖሩን ያህል ከጠላቶች ጋር ተባብሮ፣የከዳሽ፣በውድቀትሽ የሚነግድና የሚጠቀም የናት ጡት ነካሽ የሆነም ባንዳና ሆዳም እንዲሁ በመሬትሽ ላይ በቅሏል።

ኢትዮጵያ ሆይ! ታዲያ እነዚህ አጥፊና ጠፊ የሆኑት ልጆችሽ የሚጠቀሙት ያንኑ የሚማርክ ስምሽንና እይታ የሚስብ ሰንደቅ ዓላማሽን በማውለብለብ ነው። ከብዙ በጥቂቱ ከሃምሳ ዓመት ወዲህ የመጡትንና የሄዱትን እስከአሁንም ድረስ በስልጣን ኮርቻ ላይ የተቀመጡትን ስንፈትሽ የሚከተለውን ይመስላሉ።

የአጼውን ዘመነ አገዛዝ ስንፈትሽ በባህላዊና በባላባታዊ ስነልቦና የሚመራ ሆኖም ግን ለኢትዮጵያ በነጻነት መኖር ያላሰለሰ ጥረት ማድረጉ፣አልፎ ተርፎም ለአፍሪካውያን ነጻነት ትልቅ ድርሻ  መክፈሉ አይካድም።ሆኖም ግን እያደገ ከመጣው የሕዝብ ቁጥርና አስተሳሰብ ጋር አብሮ መሄድ ስላልቻለና በነበረበት መቀጠል ስለፈለገ፣የሕዝቡን ጥያቄ ከመመለስ ይልቅ የሥርዓቱን ቁንጮዎች ጥቅምና ስልጣን ለማስጠበቅ ትኩረትና ቅድሚያ በመስጠቱ ፣ከዘመኑም የፖለቲካ አስተሳሰብ ጋር ሊራመድ ባለመቻሉ ከሕዝቡ ሊነጠልና ሊጠላ ከዚያም አልፎ ተርፎ በውጭ ሃይሎች የታገዘ ጸረ ኢትዮጵያ ሃይሎች እንደአሸን በመፍላታቸው የስልጣን ዘመኑ  ሊያጥር በቃ።

የሕዝቡን ብሶት መሰላል አድርጎ፣ባልተደራጀ ሕዝብ ትከሻ ላይ  የኢትዮጵያን ስም እዬጠራና ሰንደቋን አንግቦ ለሥልጣን የበቃው የወታደር አምባገነን ቡድንም ለአስራሰባት ዓመት የአረመኔና የጭካኔ አገዛዙን ሊያቆይ የቻለው  ኢትዮጵያ በሚለው ስምሽ እዬማለና እዬተገዘተ ነበር።ለሕዝብ ድጋፍ ኢትዮጵያ የሚለው ስምሽና አረንጓዴ ቢጫና ቀይ ሰንደቅ ዓላማሽ የስበት ትንግርት አለው የሚባለውም ለዚያ ነው።

ማንኛውም ነገር ይፈጠራል ያድጋል ያረጃል ይሞታል ።ይህ ሁለ-እንተናዊ የተፈጥሮ ሕግ ነው።ሥርዓትም እንዲሁ ይመጣል፣ይቆያል፣ ይሞታል።የደርግ ወታደራዊ የፋሽስት አገዛዝም ያንኑ የተፈጥሮ ግዳጅ ተከትሎ፣በሕዝቡ በቃኝ ባይነትና ልባዊ አመጽ ተገዶ እርዝራዡን በትኖ ዕድሜው ሊያጥር ችሏል። ያ ኢትዮጵያ እያለ ሥልጣን ላይ የወጣና ሲምል ሲገዘት የኖረ ቡድን በስምሽ ብዙ ግፍና ወንጀል ሠርቶ፤ኢትዮጵያን ለማፈራረስ በጫካ ለተደራጀ የጎሰኞች ተዋጊ ሃይል  አስረክቦ መሪው ሳይቀር ካዝናዋን አራቁቶ ፈረጠጠ።

በውጭ ሃይሎች እርዳታና በአገር ውስጥ ተባባሪዎቹ ሥልጣኑን  የነጠቀው ቡድን የሕዝቡን ስሜት ለመቆጣጠርና ለመደላደል ሲል ኢትዮጵያ የሚለውን ስም በተድበሰበሰ መልኩ የኢትዮጵያ ሕዝብ አብዮታዊ ዴሞክራሲ ግንባር (ኢሕአዴግ) በማለት የጎሳ ቅንብሩን ይዞና ሌላ ምልክት በመሃሉ ላይ  በተሸከመ አረንጓዴ ቢጫና ቀይ ሰንደቅ ዓላማ ሸፍኖ ብቅ አለ።በወጠነው አገር የማፈራረስ ዓላማ ይመቸው ዘንድ ሕዝቡን ብቻም ሳይሆን መሬቱን የጎሳ ማንነት ታርጋ እዬለጠፈ አንድነቱን አናጋው።ሥልጣኑን ከተቆጣጠረ በዃላ ምዝበራውን ሃ ብሎ ጀመረ። ሕዝቡን በተለይም አገር ወዳዱንና ለአገር አንድነት የሚቆመውን፣ውስጥ ውስጡን በመግደል፣በማሳደድና በማሰር፣ለማዳከም ሞከረ።በዚህ ዘዴ ለ27 ዓመት የዘለቀ ተዘርዝሮ የማያልቅ ወንጀል ከፈጸመ  በዃላ፣የሕዝቡ ኑሮ ከድጡ ወደማጡ እያቆለቆለ በመምጣቱ  ቁጣና ተቃውሞው  ከቁጥጥር ውጭ ሆነና በእራሱ ውስጥ በተነሳ የሥልጣን ሽኩቻ  ብትንትኑ ወጣ። የአገር አፍራሹ ቡድን አምበል የነበረው የወያኔ ቡድን ከተፈጠረበት የትግራይ ክፍለሃገር ተመልሶ መሸገ።በቦታው የራሱ ሎሌና አገልጋይ በሆነው በኦሮሞው አጋሩ ኦሕዴድ የተባለ ኦነጋዊ ሃይል የሚመራው የነባሩ ኢሕአዴግ ስብስብ ቦታውን ነጠቀው።ይህም የኦሕዴድ ቡድን የተደበቀ ኦነጋዊ አገር የማፍረስ ሴራ በወያኔ የስለላ ተቋም ውስጥ  በሃላፊነት ሲያገለግል የኖረውንና በብዙ የግድያ ወንጀሎች ተጠያቂ መሆን ያለበትን  ኮሎኔል አብይ አህመድን ከፊት አድርጎ  በኢትዮጵያዊነት ጭንብል ብዙዎችን ለማታለል ቻለ።

የኢትዮጵያን ስም ለመስማት ይናፍቅ የነበረው ብዙሃን በአብይ አህመድ የሰላ ምላስ ተጭበርብሮ አገሩንም፣ልቡንም ኪሱንም አሳልፎ ሰጠ።አብይ አህመድን ከሰማያት ሰማያት የወረደ መልአክ አድርጎ ሳለው።ሙሴና ነብዩ የሚሉ ቅጥያዎችም እያወጣለት ካንተ ወዲያ ላሳር ብሎ በእብሪት  ልቡን አሳበጠው። እንደ ግል ኳሱ በአገሪቱ ላይ ይጫወትባት ጀመር።አብይም ያንኑ የተለመደ የሕዝብ ማታለያ የሆነውን የኢትዮጵያን ስም እዬጠራ ውስጥ ውስጡን ኢትዮጵያ የምትፈርስበትን መንገድ ያስተካክል ጀመር።ጥቂቶች ገና ከጅምሩ ሂደቱንና የሰውዬውን ምንነት ቢገልጹም ሰሚ አላገኙም፤ ሁሉም በአብይ አህመድ ኢትዮጵያ በሚለው ባዶ ቃል  ደንዝዞ ዓይናችሁ ላፈር አላቸው። ግማሹ ለሥልጣን፣ግማሹ ለጥቅም ወገኑንም አገሩንም አሳልፎ ሸጠ፣ለአብይና ለሚመራው ሥርዓት ባሻጃግሬ ሆኖ ቆመ።ያባትህ ቤት ሲዘረፍ አብረህ ዝረፍ ብሎ የሌባ እጁን አሾለ።በዬአገሩ አብይ ወይም ሞት ብሎ ቆመ።ለቁራሽ መሬትና ለቤት ሲል የማይኖርባትን አገር ለማፍረስ ዶማ ጨብጦ አካኪ ዘራፍ አለ።አብይም ልሳኑን እዬቀያዬረ አገር የማፍረሱን ሂደት ተያያዘው።ኢትዮጵያ እናቴ፣እያለ በአንገቷ ላይ ገመድ ሸመቀቀባት።በጥቅም በተገዙ ሆዳደሮች እዬተደገፈ ለአገር አንድነትና ልዑላዊነት ይቆማሉ ያላቸውን ሁሉ ዘመተባቸው።ቤተእምነቶች ሳይቀሩ በከሃዲ አጋሮቹ ተጥለቅልቀው እንኳንስ ለሰማይ ለምድርም የማይበጁ ሆኑ።በሰይጣናውያን መንፈስ በከላቸው።ለግብረሰዶም መስፋፋት በዝምታ በራቸውን እንዲከፍቱ አደረጋቸው።ትምህርቱ፣ንግዱ፣ሥራው፣ሕክምናው እስፖርቱ ሳይቀር የአገር ፈረሳው አካል እንዲሆኑ አደረጋቸው።ኢትዮጵያና ኢትዮጵያዊነትን ለመዋጋት ኢትዮጵያ የሚለው ቃል የስበት ቃል አድርጎት በዬአደባባዩ አስተጋባ።ኢትዮጵያ የሚለውን ቃል የሚሰማ፣ሰንደቅ ዓላማዋን ሲውለበለብ ያዬ የዋህ እውነት መስሎት በኦነጋውያኑ በተዘጋጀ የተለያዩ ድግሶች ላይ ትከሻው እስኪነቀል ድረስ እስክስታ መደለቁን ተያያዘው።ያልተገነዘበው ቢኖር የመድረኩ አመቻችና አዘጋጆቹ እነዚያው በጥቅም የተገዙት ሆድ አደሮች መሆናቸውን ነው።

አብይ አህመድ “የሚፈልጉትን እያሳዬህ ወደምትፈልገው ንዳቸው” ያለውን በተግባር የሚገልጽበት መንገድ በኢትዮጵያና በኢትዮጵያዊነት ስም የሚዘጋጁትን በዓላትና ዝግጅቶችን በመጠቀም ነው።አያይዞ “በሬ ሆይ ሳሩን አይተህ ገደሉን ሳታይ የሚለውን አንስተህ ቀልድባቸው፤ሳቅባቸው” እንዳለው በዙፋኑ ላይ ተቀምጦ ይፈነድቃል። በአሳሳች ተላላኪዎቹ ሥራ ይመረቅናል።ለቀጣይ የጥፋት ተልእኮም እዬሸለመና እዬሾመ ያበረታታቸዋል።ደሃው አገር ወዳድ ግን ያልቃል።

ለዚህ ምሳሌ የሚሆነው ከብዙዎቹ መካከል አሁን ሰሞኑ በአመስተርዳም ከተማ የሚካሄደው በአውሮፓ የኢትዮጵያውያን የስፖርትና ባህል ዝግጅት በዓል(ፌስቲቫል)ነው።ይህ ዝግጅት በአውሮፓ ልዩልዩ ከተማዎች ለአስራሰባት ጊዜ ተካሂዷል።የአሁኑ 18ኛው መሆኑ ነው።የዘንድሮውን ዝግጅት ልዩ የሚያደርገው የኦነግ መራሹ መንግሥት በቀጥታ የተሳተፈበት መሆኑ ነው።ለዚያ ብዙ አመላካቾችን ታዝበናል።ከበዓሉም በፊት የደረሱን መረጃዎች ያረጋገጡት ይህንኑ ነው።

1 ለበዓሉ ዝግጅት የኢትዮጵያ መንግሥት ነኝ ባዩ የኦነጉ መራሹ የእስፖርትና የባሕል ሚኒስትር የሆነው  ቀጀላ መርዳሳ ኢትዮጵያ ውስጥ ገብቶ የውጩን የእስፖርት እንቅስቃሴ ከግብረአበሮቹ ጋር የሚያሽከረክረውን ክንፉ አሰፋ የተባለ ልማደኛ ሌባ አስተባባሪ በማድረግ ለዝግጅቱ የሚያስፈልገውን ወጭ ከኢትዮጵያ ንግድ ባንክና ከከበርቴዎች እንዲያገኝ ቀጭን ትእዛዝ ማስተላለፉ፣

2 የባለሥልጣናቱና ገንዘብ የከፈሉ ሃብታም ልጆችና ቤተሰቦች  በእስፖርት ስም በልዩ ልዩ የሥራ ድርሻ ከአገር እንዲወጡና ስደተኝነት ጠይቀው እንዲቀሩ የተመሳጠረ ወንጀለኛ ንግድ መካሄዱን፣ከአገር ቤት መጡ የተባሉትን ከፍተኛ ቁጥር ያላቸውን ማዬቱ ብቻ ይበቃል።

3 በአዲስ አበባ ከተማ ወጣቱን በመከፋፈልና ለከተማዋ አስተዳደር ተጠሪ ለአዳነች አበቤ ጠበቃ በመሆን ብዙ ወጣቶችን ለሞት፣ለመቁሰልና ለእስራት የዳረጉ ወንጀለኞች ከአዲስ አበባ የመጣውን የእግር ኳስ ቡድን በማጀብ፣ በእንግድነትና በተሳታፊነት ለመምጣታቸው፣ሌላው ማሳያ በአዳነች አበቤ ደጋፊነት የሚታወቀውና የከተማው ወጣት አንቅሮ የተፋው የሚታወቀው እጄ ቆራጣም አንዱ አጃቢ ሆኖ መምጣቱ ነው።

4 ዜጋ እንኳንስ ወደውጭ አገር ቀርቶ በአገሩ ምድር በተለይም በጋራ ከተማው በአዲስ አበባ የመግባትና የመውጣት መብቱን በተገፈፈበት ሁኔታ በእስፖርቱ ከለላ  በክንፉ አሰፋ የሚመራ ለዘፈንና ለንግድ በሚል ሽፋን የሥርዓቱን ገመና ለመሸፈን በውጭ ያለውን ተቃውሞ ለማዳከም ተልእኮ የያዘ ቡድን  መምጣቱ የመንግሥትን ይውንታና ድጋፍ ለመያዙ ሌላ ማስረጃ መፈለግ አያሻም።ፓስፖርትና ቪዛ ለማግኘት ምን ያህል አዳጋች እንደሚሆን እንኳንስ የደረሰበት ያልደረሰበት አብዛኛው ያውቀዋል።ለከተማ ነዋሪነት መታወቂያ ቁራጭ ደብተር ከአርባ ሽህ ብር በላይ በሚጠይቅ ስርዓት ውስጥ ሆኖ ለውጭ አገር ጉዞ የሚያስፈልግ ፓስፖርት ለማግኘት የሚከፈለውን ገንዘብና ድካም ሲያስቡት ቀላል አይደለም።ለደጋፊ ግን የቤት ውስጥ ሥራ ነው።

በዚህም በእስፖርት ስም የተሰባሰበው የመንግሥት ተላላኪ በአውሮፓ የሚኖረውን አገር ወዳድ ለማማለል የተጠቀመው የፈረደበትን የኢትዮጵያን ስምና ሰንደቅ ዓላማዋን ነው።በመክፈቻው ቀን  ስለሚሞቱት፣በእስር ስለሚማቅቁት፣ስለሚሳደዱት፣ቤታቸው እዬፈረሰ መንግድ ላይ ስለተጣሉት ወገኖቻችን ፣ስለ አገር ሰላምና አንድነት አደጋ፣ ስለመርዘኛው የጎሳ ፖለቲካና ስለሚፈጸመው መንግሥታዊና ቡድናዊ የሰብአዊ መብት ጥሰት የተባለ ነገር የለም።ከማን ላይ ነሽና ትሆኛለሽ ደህና  ብሎ ለማለፍ ህሊና ላለው ሰው ይከብዳል።ጤነኛ አይምሮ ያለው ሰው ሊያነሳው የሚገባ ጥያቄ ነው።

እንደ ሁሌዬውም የተገኘውን ጥቂት ታዳሚ ያማለሉበት አንዱ ስለኢትዮጵያና ኢትዮጵያዊነት የሚያሞግሰውን የጥላሁን ገሰሰን ዜማ በማሰማትና አረንጓዴ ቢጫና ቀይ ሰንደቅዓላማ በሜዳው ዳርቻና በመድረኩ  ላይ በማውለብለብ ነው። ለመሸወድ ቢሞከርም የአዘጋጆቹ  ያለፈና የአሁን ታሪካቸው ስለሚታወቅ ግን በንጹህ ልቦና፣በኢትዮጵያዊነትና በአገር ወዳድነት የተቀነባበረ ነው ለማለት ያዳግታል። እንደተለመደው የኢትዮጵያ ስምና ሰንደቅ ዓላማዋ የወንጀለኞች መጋረጃ ሆኗል።የኦነግንማ ጨርቅ ተሸክሞ ማን ቢቀርበው! የሚገርመው ግን የያገሩ ቡድን ተጫዋቾች የያዘት ብሔራዊ ሰንደቅ ዓላማ ጎልቶ አለመታዬቱ ነው።በተለይም ከኢትዮጵያ መጣ የተባለው ቡድን የአገሩን ሰንደቅ ዓላማ በመያዝ ግንባር ቀደም መሆን ይገባው ነበር። ለምን የሚለውን ጥያቄ እኔም ሌላውም ሊያነሳ ይገባዋል።የዚህ ክለብ ቀጣይ ሚና የሚቀጥለውን ጨዋታ በኢትዮጵያውስጥ ማዘጋጀት እንደሚሆን የቀደመ እቅድ መኖሩን የሚያውቁት ይናገራሉ።እንደ ሕጉማ ከሆነ በአውሮፓ በሚኖሩ ክለቦች የእስፖርት በዓል ላይ ከአውሮፓ ውጭ ያለ ክለብ ሊሳተፍ አይፈቀድለትም ነበር። አለያም የስፖርት ፌዴሬሽኑ ስም መቀዬር ይኖርበታል ማለት ነው።ነገሩ ሌላ ነው።

በቀጣዩ የምናዬው ነገር ቢኖር ከመጡት አብዛኛው በያገሩ የኢሚግሬሽን ቢሮዎች እዬቀረበ ስደተኝነት እንደሚጠይቅ ይሆናል።ስደተኝነት የነጋዴዎችና የወንጀለኞች መደበቂያ ዋሻ መሆኑን ከምናዬው ለመመስከር እንችላለን።አሁን ግን አገራችንን መዝብረው፣ወገናችንን ገለው፣እግሬ አውጭኝ የሚሉትን ወንጀለኞችና ቤተሰቦች የስደተኛነትን ትርጉም በመበከላቸውንና ለሌሎቹ እውነተኛ በደል ለደረሰባቸው ስደተኞች እንቅፋት መሆናቸውን ማጋለጥ ተገቢ ነው።አብዛኞቹ ባለሥልጣኖችና ቤተሰቦቻቸው በዘረፉት ገንዘብ ቤትና ንብረት እዬገዙ የተንደላቀቀ ኑሮ እንደሚኖሩም እዬታዘብን ነው።ይህ በዝምታ ማለፍ ግን ሊቆም ይገባዋል።በሕግ እንዲጠዬቁ ማድረግ የእውነተኛ ስደተኞችና አገር ወዳዶች ግዴታ ነው።  ኢትዮጵያ ስሟና ሰንደቅ ዓላማዋ ለወንጀለኞች መጠቀሚያ የሚሆንበትን ልማድ ተባብረን እናክሽፍ!

በዚህ አጋጣሚ በጨዋነትና በአገር ፍቅር አገር አቋርጦ የመጣው ታዳሚ የእስፖርት ዝግጅቱን በጥልቀት እንዲመረምረውና የዘራፊዎችና የወንጀለኛው ስርዓት መጠቀሚያ ላለመሆን የበኩሉን ጥንቃቄ እንዲያደርግ፣ብሎም ለኢትዮጵያ ሕዝብ ያለውን አጋርነት በእስፖርቱ ሜዳ ዙሪያ እንዲገልጽ ማሳሰብ እወዳለሁ።

ድል ለኢትዮጵያ ሕዝብ!!

አገሬ አዲስ

 

 

Leave a Reply

Your email address will not be published.

Latest from Blog

ጥር 2 ቀን 2017 ዓ/ም   January 10, 2025  በኢትዮጵያዊነታችሁ፡ በኦርቶዶክሳዊ እምነታችሁ፡ በአማራነታችሁ፡ በአማረኛተናጋሪነታችሁ፡ በተሰነዘረባችሁ ብትር፡ ቤተ ሰብ፡ ወዳጅ ዘመዶቻችሁን ያጣችሁ: ልጆቻችሁን የቀበራችሁ፡ አካልችሁን ያጣችሁ፡ የተሰነዘረውን ብትር በመከላከል ላይ ያላችሁ፡ያለፈቃዳችሁ በመንግሥት ተጽእኖ ወደመግደልና

በኢትዮጵያዊነታችሁ፡ በኦርቶዶክሳዊ እምነታችሁ፡ በአማራነታችሁ፡ በአማረኛ ተናጋሪነታችሁ፡ በተሰነዘረባችሁ ብትር፡

January 10, 2025
መኮንን ሻውል ወልደጊዮርጊስ ¹⁵ የምድርም ነገሥታትና መኳንንት ሻለቃዎችም ባለ ጠጋዎችም ኃይለኛዎችም ባሪያዎችም ጌቶችም ሁሉ በዋሾችና በተራራዎች ዓለቶች ተሰወሩ ፥ ¹⁶ ተራራዎችንና   በላያችን ውደቁ በዙፋንም ከተቀመጠው ፊት ከበጉም ቍጣ ሰውሩን ፤ ¹⁷ ታላቁ የቁጣው ቀን  መጥቶአልና ፥ ማንስ ሊቆም ይችላል ? አሉአቸው ። ራእይ 6 ፤  15_17 ይኽ የመጽሐፍ ቅዱስ ቃል ። የኢየሱስን ልደት ሰናከብር የየሐንስ ራእይን ማንበብ ጠቃሚ ይመስለኛል ። ምክንያቱም በመጨረሻው ዘመን

ከኢየሱስ የፍርድ ቀን በፊት በህሊናችን ውስጥ ፍቅርን ለማንገስ እንጣር 

የምጣኔ ሀብታዊ ፍጥ፣ የፖለቲካ፣ የእውነትና የሰብአዊ መብት ታጋይ፣ የአመኑበትን ነገር ለመናገር እንደ ፖለቲከኛ በቃላት ሳያሽሞነሙኑ ቀጥታ የሚናገሩት የሀገሬ ኢትዮጵያ ታላቅ ሰው ነበሩ “ዘር ቆጠራውን ተዉት፤ የአባቶቻችሁን ሀገር ኢትዮጵያን አክብሩ!”  አቶ ቡልቻ ደመቅሳ

ሀገር ወዳዱ አቶ ቡልቻ ደመቅሳ ከዚህ አለም በሞት ተለዩ

January 6, 2025
ግን ይህ ሁሉ ወጣት የት ገባ? ግን ይህ ሁሉ ወጣት የት ገባ? ዛሬ፣ 2025 ዓ/ም ላይ ብንገኝም በዝንጋታ ገመድ ወደ ሞት እየተጎተትን እንደሆነ አናውቅም። (ሁል ጊዜ የሚሞተው የገነዝነው ይመስለናል። ) “ገብርዬ ነበረ

ግን ይህ ሁሉ ወጣት የት ገባ?

January 3, 2025
መኮንን ሻውል ወልደጊዮርጊስ ዛሬ እንደ አውሮፓዊያኑ አቆጣጠር ጥር 1ቀን 2025 ዓ/ም ነው ። አውሮፓውያኑ አዲስ ዓመትን “ሀ” ብለው ጀምረዋል ። አዲሱን ዓመት ሲጀምሩም ከልክ ባለፈ ፈንጠዚያ ነው ። ርቺቱ ፣ ምጉቡና መጠጡ

ዛሬ፣ 2025 ዓ/ም ላይ ብንገኝም በዝንጋታ ገመድ ወደ ሞት እየተጎተትን እንደሆነ አናውቅም። (ሁል ጊዜ የሚሞተው የገነዝነው ይመስለናል። )

Go toTop