May 13, 2023
33 mins read

ኢት-ኢኮኖሚ /ET- ECONOMY የኦህዴድ ብልጽግና አንድ ቢሊዮን ዶላር ጦር መሣሪያ ሸምቷል!!! አንድ ትሪሊዮን ብር የቤተመንግሥት ግንባታ!!! የጦርነት ኢኮኖሚና የነፍስ ገበያ በኢትዮጵያ!!

eT 688699g 1 1

ክፍል  ሦስት                      ሚሊዮን ዘአማኑኤል (ኢት-ኢኮኖሚ)

ለዶክተር ዮናስ ብሩ ማኒፊስቶ ማጠናከሪያ የኢትዮጵያ ኢኮኖሚ ዳሰሳ መንግሥታዊ ዕዳ፣ የኢትዮጵያ የንግድ ሚዛን፣ የኢትዮጵያ የውጪ ንግድ ገቢ፣የኢትዮጵያ የገቢ ንግድ ወጪ በጥናቱ ተካተዋል፡፡

መንግሥት ዕዳ ከጠቅላላ የአገር ውስጥ ምርት (ጂዲፒ)

የኢትዮጵያ መንግሥት ዕዳ ከጠቅላላ የአገር ውስጥ ምርት (ጂዲፒ) በመቶኛ ጋር ሲነጻጸር በ2014 (30.90) በመቶ፣ በ2015 (33.80) በመቶ፣ በ2016 (42.60) በመቶ፣  በ2017  (46.30) በመቶ፣ በ2018 (49.70) በመቶ፣ በ2019 (47.68) በመቶ፣ በ2020 (50.69 )በመቶ፣ በ2021 (43.56) በመቶ ባር ግራፉ ያሳያል፡፡ (Ethiopia Government debt – data, chart | TheGlobalEconomy.com)

በኮነሬል አብይ አገዛዝ ዘመን  ከ2018 እስከ 2021 እኤአ ያለውን መንግሥታዊ እዳ መጨመሩን ያሳያል፣ በዚህም መሠረት የኢትዮጵያ ዕዳ ከሃምሳ እስከ ስልሳ ቢሊዮን ዶላር እንደሚደርስና እውነተኛውን መረጃ ማግኘት እንደማይቻል በተለይ ሃገራችን ከቻይና መንግሥት ጋር ያደረገችው ብድር በይፋ ስለማይገለፅ እንዲሁም የመንግሥታዊ ልማት ድርጅቶች ዕዳ ከመንግሥታዊ ዕዳ ጋር ስለማይደመር የእዳችን ነገር ቅጥ አንባሩ የጠፋ ሆኖል፡፡ እዳችንን ከጂዲፒ ጋር ሲነጸጸር የሚያሳየውን ከታችኛው ባር ግራፍ ያስተውሉ፡፡ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ገዥ አቶ ማሞ ምህረቱ ‹‹የዕዳ መጠናችን ከአጠቃላይ  የኢትዮጵያ ጂዲፒ አንፃር ሲለካ ገና 24 (ሃያ አራት) በመቶ ላይ ነው፡፡ ስለዚህ ያለብን የዕዳ መጠን በጣም ዝቅተኛ ነው፡፡›› ነገር ግን ዕዳውን ለመክፈል አሁን የአጭር ጊዜ የገንዘብ ችግር (የካሽ ፍሎ ችግር) ገጥሞናል፤›› ሲሉ ተናግረዋል፡፡ …………………………..………..(1)

ሆኖም የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ገዥ አቶ ማሞ ምህረቱ የዘነጉት የዋናውን ዕዳ ወለድ መክፈል አቅቶን ያን ለመክፈል አበዳሪ አገር አጥተኝ አገሪቱ የመበደር አቅሞ ተሞጦ ሲሲሲ ኔጌቲቨ ተርታ ተመድባ መሆኑን አቶ ማሞ ቀጥፈውናል የማያድግ ልጅ !!!

 

I-የኢትዮጵያ የንግድ ሚዛን (Ethiopia trade balance) የኢትዮጵያ የውጪ ንግድ ጉድስና ስርቪስ ሲቀነስ የገቢ ንግድ ጉድስና ስርቪስ ስሌት ነው፡፡ በዚህም መሠረት የኢትዮጵያ የንግድ ሚዛን በ2016እኤአ $-14.32B  (ኔጌቲቨ አስራአራት ነጥብ ሠላሳሁለት ቢሊዮን ዶላር)፣ በ2017እኤአ $-12.96B፣በ2018 እኤአ  $-12.18B፣ በ2019እኤአ $-12.41B፣ በ2020እኤአ $-10.50B፣ በ2021እኤአ $-10.09B (ኔጌቲቨ አስር ነጥብ ዚሮ ዘጠኝ ቢሊዮን ዶላር)ነበር፡፡  ኢትዮጵያ በውጪ ንግድ ባህር ማዶ አገሮች ከምትልከው ምርትና አገልግሎት የምታገኘው ገቢ ከሦስት እስከ አራት ቢሊዮን ዶላር ሲገመት ወደ አገር ውስጥ  የምታስገባው ምርትና አገልግሎት  ከአስር እስከ አስራሰባት ቢሊዮን ዶላር የሚገመት ስሆን የኢትዮጵያ የንግድ ሚዛን ኔጌቲቨ ቢሊዮን ዶላር መሆኑን ያመላክታለል፡፡ የላይኛውን ግራፍ ምስል ይመልከቱ::……………………………….………(3)

 

II-የኢትዮጵያ የውጪ ንግድ ገቢ (Export)

የኢትዮጵያ የውጪ ንግድ ገቢ (ኤክስፖርት)፡- በ2021 እኤአ የኢትዮጵያ የውጪ ንግድ ገቢ 4.41 (አራት ነጥብ አርባ አንድ) ቢሊዮን ዶላር ሲሆን ከዓለም የመቶ ሃያ ስድስተኛ ደረጃ ላይ ትገኝ ነበር፡፡  በኢትዮጵያ የውጪ ንግድ ገቢ ከፍተኛውን ደረጃ የያዘው ቡና $1.16B (አንድ ነጥብ አስራስድስት)ቢሊዮን ዶላር፣ ወርቅ $860M (ስምንት መቶ ስልሳ ) ሚሊዮን ዶላር፣ የቅባት እህሎች $337M (ሦስት መቶሠላሳ ሰባት)ሚሊዮን ዶላር፣ አትክልትና ፍራፍሬ  $272M (ሁለት መቶሰባ ሁለት)ሚሊዮን ዶላር፣ እንዲሁም የአበባ ምርት $235M (ሁለት መቶ ሠላሳአምስት)ሚሊዮን ዶላር ከውጭ ንግድ ገቢ ተገኝቶ ነበር፡፡ የኢትዮጵያ ኤክስፖርት ከምታደርግላቸው አገሮች መኃል ዩናይትድ አረብ ኢምራትስ ($1.05B), ዩናይትድ ስቴትስ ($495M), ሶማሊያ($361M), ሳውዲ አረቢያ ($248M),እና ጀርመኒ ($248M).

በ2022 እኤአ የኢትዮጵያ የውጪ ንግድ ገቢ 4.1 (አራት ነጥብ አንድ) ቢሊዮን ዶላር ሲሆን ከዓለም የመቶ ሃያ ስድስተኛ ደረጃ ላይ ትገኛለች፡፡  በኢትዮጵያ የውጪ ንግድ ገቢ ከፍተኛውን ደረጃ የያዘው ቡና $1.4 (አንድ ነጥብ አራት) ቢሊዮን ዶላር፣ ወርቅ $546M (አምስትመቶ አርባ ስድስት) ሚሊዮን ዶላር፣ እንዲሁም የአበባ ምርት $544M (አምስት መቶ አርባ አራት)ሚሊዮን ዶላር ከውጭ ንግድ ገቢ ተገኝቶ ነበር፡፡ ከአለፈው አመት ጋር ሲወዳደር የቡናና  የወርቅ፣ የውጪ ንግድ ሲቀንስ የአበባ ገቢ ጨምሮል፡፡

 

በ2023 እኤአ የኢትዮጵያ የውጪ ንግድ ገቢ ማሽቆልቆል

{1} የቡና ምርት የኤክስፖርት ገቢ ቀንሶል፡- የኢትዮጵያ በ2014ዓ/ም 300 ሽህ ቶን የቡና ምርት ኤክስፖርት አድርጋ አፈፃፀም 1.4 ቢሊዮን ዶላር ገቢ ተገኝቶ ነበር፡፡ በ2015ዓ/ም መጨረሻ 360 ሽህ ቶን የቡና ምርት ኤክስፖርት በማድረግ ሁለት ቢሊዮን ዶላር ለማግኘት ታቅዶ ነበር፡፡ ሆኖም የቡና ዋጋ 21.5 በመቶ በመቀነሱ (በአንድ ዶላር ሲሸጥ የነበረው 0.45 ኪሎ ግራም ቡና 70 ሣንቲም ቅናሽ) በማሳየቱ፣ የኢትዮጵያ በ2015ዓ/ም 143 ሽህ ቶን የቡና ምርት ኤክስፖርት አድርጋ 780 ቢሊዮን ዶላር ገቢ ተገኝቶል፡፡ በዓለም አቀፍ ገበያ የቡና፣የቅመማቅመም፣ የሻይ ፍላጎት በከፍተኛ ሁኔታ በመቀነሱ ዋጋቸው ወርዶል፡፡ በቡና ዋጋ መቀነስ ምክንያት 28 ሽህ ቶን ቡና ሽያጭ ሳይፈፀም መቅረቱ ተገልፆል፡፡  133 ሚሊዮን ዶላር ገቢ ያስገኝ ነበር፡፡ በተጨማሪም የባንክ ኤላሲ ተከፍቶ ሳይላኩ ቀሩ 334 ቶን ቡና የአገር ውስጥ መሸጫ ዋጋ ከዓለም አቀፍ የቡና መሸጫ ዋጋ ጋር ሲነፃፀር  በጣም ከፍተኛ በመሆኑ ወደ ዉጭ ሳይላክ ቀርቶል፡፡በአገሪቱ አንዳንድ የቡና አብቃይ አካባቢዎች በተፈጠረ የፀጥታ ችግር በተለይም ከምዕራብ ወለጋ ቡና ምርት ማቅረብ አልተቻለም፡፡ በእቅዱ ሁለት ቢሊዮን ዶላር ውስጥ እስካሁን የተገኘው 780 ሚሊዮን ዶላር ብቻ ነው፡፡……… (4)

 

{2} የወርቅ ምርት የኤክስፖርት ገቢ፡- በኢትዮጵያ የወርቀ ኃብት ለውጪ ንግድ ገቢ ከቡና ቀጥሎ በሁለተኛ ደረጃ ገቢ በማስገኘት ይታወቃል፡፡በ2018/19 እኤአ ሃያ ስምንት ሚሊዮን ዶላር ዝቅተኛ ገቢ አስመዝግቦ ነበር፡፡ በ2021 እኤአ 672 ሚሊዮን ዶላር የውጪ ምንዛሪ አስገኝቶ ነበር፡፡ በ2022እኤአ 546  ሚሊዮን ዶላር የውጪ ምንዛሪ አስገኝቶ ነበር፡፡ Mar 29, 2022 — Ethiopia’s income from gold export has been declining over the past few years generating all-time low of about $28 million in 2018/19. Gold, the second highest hard currency generator export commodity of Ethiopia, has generated $672 million last year concluded July 7, 2021. In recent years Ethiopia’s gold export earnings has been increasing and generated $546 million last year concluded July 7, 2022. One of Ethiopia’s major exports, gold, generated close to USD 117.4 million in exports during the first six months of the existing fiscal year, according to the Ministry of Mines.Jan 14, 2023በ2023እኤአ ስድስት ወራቶች ውስጥ 117.4 ሚሊዮን ዶላር የውጪ ምንዛሪ አስገኝቶል፡፡ ከተመሳሳይ አመቶች ጋር ሲነጻጸር ዝቅተኛ ገቢ መሆኑ ታውቆል፡፡ የሜድሮክ የወርቅ ልማት ገቢ በኦሮሚያ ክልላዊ መንግሥት የሮያሊቲ ግብር ጥያቄ በኃላ የወርቁን ኃብት ለእኩል ድርሻ የመካፈል ጥያቄ የተነሳ የወርቅ ምርት እንደቀነሰ የውስጥ አዋቂዎች ይናገራሉ፡፡ የኢትዮጵያ የወርቅ ኃብት የፌዴራል መንግሥቱ ኃብት ሳይሆኑ  የህወሓት ወያኔ የኢዛና የወርቅ ማዕድን እና የኦነግ ኦህዴድ የለገደንቢ የወርቅ ማዕድን በመቆጣተር የግል ሃብታቸው በማድረግ ተቀራምተውታለተ፡፡ በዚህም የተነሳ የሃገሪቱ የወርቅ ኃብት ከ ኦሮሚያ፣ ቤኒሻንጉል ጉሙዝ፣ ደቡብ ምስራቅ ኢትዮጵያ በኩል ወደ ኬንያ ፣ሱዳን ወዘተ በህገወጥ ንግድ ድንበር ጥሶ  እንደሚሸጥ ጣውቆል፡፡ በዚህም ጥገወጥ ንግድ ሽያጭ የቻይና ዜጎች ዋና ተሳታፊዎች እንደሆኑ ታውቆል፡፡ በዚህም የተነሳ ወደ ብሄራዊ ባንክ የሚገባውና የሚቀመጠው የወርቅ ኃብት መቀነሱን ባንኩ በተደጋጋሚ ማስታወቁ አይዘነጋም፡፡ በኢኖሚው መውደቅ የተነሳ የብር የመግዛት አቅም በመውደቁ የተነሳ ባለፀጋዎች ረብጣ ብር ከመያዝ ይልቅ፣ ዶላርና ወርቅ እንዲሁም ንብረት ቤትና መኪና በመግዛት  ላይ ይገኛሉ፡፡ በኢትዮጵያ የመገኙ ባንኮች ሁሉ አዲስ ዘመናይ ባንኮች የሚገነቡት በብር የመግዛት አቅምና ወደፊት ብር ዋጋ ስለሚረክስ ኪሳራቸውን ለመቀነስ ነው፡፡ Ethiopia police and army capture seven kilograms of gold and over one million dollars of hard currency from smugglers trying to take out of the country. The contraband gold and hard currency were captured before it leaves the country at the eastern part of the country Jigjiga customs branch. …….The latest report of the Customs shows that in the past six months the country has captured worth half a billion birr contraband goods. The goods are captured being smuggled into the country and out of Ethiopia to the neighboring countries…………………………………..….(5)

The Ministry of Mines of Ethiopia said foreign nationals mainly Chinese were found involved in smuggling of gold out of Ethiopia in collaboration with artisan miners. This is indicated by the Minister of Mines, Takele Uma, who briefed media on Friday. He indicated that the Ministry has conducted two weeks of operations to seize the foreign nationals involved in gold smuggling out of Ethiopia. The mining areas the foreign nationals were collaborating to smuggle the gold are found in Oromia, Benishangul Gumz, and South West regions of Ethiopia, according to the Minister.

{3} የአበባ ምርት የኤክስፖርት ገቢ፡- በኢትየጵያ የአበባ ምርት ዘርፍ የውጪ ንግድ ገቢ በ2001/2እኤአ መቶ ሃምሳ ሽህ ዶላር  ገቢ ያስገኝ የነበረ ሲሆን በ2011/12እኤአ 212.56 ሚሊዮን ዶላር በማስገኘት ገቢው እንዳደገ መረጃው ዘግቦል፡፡ by Y ABEBE · 2015 — As a result export earnings from cut flower sector jumped from USD 150 Thousand in 2001/ 02 to USD 212.56 Million in 2011/12 (Shaefer and. Abebe …

በ2021እኤአ ኢትዮጵያ የአበባ ምርት ኤክስፖርት ገቢ 235 ሚሊዮን ዶላር የአደገ ሲሆን ኒዘርላንድ ($5.17B) ሚሊዮን ዶላር፣ ሳውዲ አረቢያ($21.5M) ሚሊዮን ዶላር፣ ዩናይትድ ኪንግደም($9.53M) ሚሊዮን ዶላር፣ ኖርዌ($9.39M) ሚሊዮን ዶላር፣ እንዲሁም ሺሴልስ ($5.46M) ሚሊዮን ዶላር የአበባ ምርት ሸምተዋል፡፡

In 2021, Ethiopia exported $235M in Cut Flowers. The main destinations of Ethiopia exports on Cut Flowers were Netherlands ($157M), Saudi Arabia ($21.5M), United Kingdom ($9.53M), Norway ($9.39M), and Seychelles ($5.46M)

{4} የጫት ምርት የኤክስፖርት ገቢ፡-የጫት ንግድን ፖለቲሳይዝ ማድረግ(politicisation of the khat trade) በኢትዮጵያና በሱማሌላንድ የቆየው ድንበር ዘለል የጫት ንግድ  በኦነግ ኦህዴድ ብልፅግና መንግሥት በሱማሌና ኦሮሞ ተይዞ የነበረውን የጫት ንግድ በኦሮሞ ብቻ እንዲያዝ በማድረግና ከረዝም ጊዜ ጀምሮ አምስት ዶላር አንድ ኪሎ ግራም ጫት ይሸጥበት የነበረውን ዋጋ (The long-time fixed price of 5 USD/kg of khat) አስር ዶላር በኪሎግራም (10 USD/kg) በአፕሪል 2022 እኤአ  በማድረግ   የብልፅግና መንግስት የፖለቲካ ጣልቃ ገብነት የተነሳ የጫት ንግድ ተቀዛቅዞል፡፡ ኦነግ ኦህዴድ የብልፅግና መንግስት የጫት ንግድን በአንድ ዘር ብቻ ለማስያዝ ለኦህዴድ ፖለቲከኛ ነጋዴዎች የባንክ ብድርና የታክስ እፎይታ  እንዲያገኙ በማድረግ የአድሎ ሥራ በመስራት የሱማሌ ነጋዴዎችን የማግለል ስራ  በብልፅግና መንግሥት በመስራቱን ይቃወማሉ፡፡  Reacting to Ethiopia’s price rises, the Somaliland Khat Association announced on 29 June a ban of all khat imports from Ethiopia’s Oromia Regional State as of 6 July. በዚህም ምክንያት የሱማሌላንድ መንግስት ከኬንያና ከየመን መንግስት ጫት መግዛት ጀመረ፡፡…………………………….(7)

{5} የሠሊጥ ምርት (sesame ) የኤክስፖርት ገቢ፡- የኢትዮጵያ የሠሊጥ ምርት በ2017እኤአ ወደ ውጪ የተላከው  ሠሊጥ 388.6 (ሦስት መቶ ሰማንያ ስምንት ነጥብ ስድስት ) ዶላር ገቢ አስገኝቶ ነበር፡፡ የኢትዮጵያ የሠሊጥ ምርት በ2021እኤአ ወደ ውጪ የተላከው 173.94 ሜትሪክ ቶን ሠሊጥ 276.80 ዶላር ገቢ አስገኝቶ ነበር፡፡ The export value of Ethiopia was USD 276.80M, and the export volume was 173.94M metric ton in 2021. Export Value. in 2021. በኢትዮጵያ ነጩ ወርቅ በመባል የሚጣወቀው የሠሊጥ ምርት ወደ እስራኤል፣ ቻይናና ዩናይትድ አረብ ኢምሬትስ የሚላክ ሲሆን አስራአራት በመቶ የውጭ ንግድ ድርሻ ነበረው፡፡ ኢትዮጵያ ሁለት መቶ ሠላሳ ሽህ ሜትሪክ ቶን ሠሊጥ ለዓለም አቀፍ ንግድ ለማቅረብ ብታቅድም በወልቃይት በሁመራ አካባቢ ባለው ጦርነት ምክንያት የሠሊጥ እርሻ በመስተጎጎሉ የሠሊጥ ምርት መቀነሱ  አያጠያይቅም፡፡ ምንጭhttps://www.tridge.com › intelligences › export/https://www.fanabc.com › english › ethiopia-plans-to-…

With a 2017 monetary conversion of $388.6 million,/ https://www.selinawamucii.com › nuts-and-oil-seeds

 

{6} የቁም እንሰሳት (Liveanimal)፡-  በኢትዮጵያ የቁም እንሰሳት ኃብት ዘርፍ ከአስራሁለት  በመቶ ከአጠቃላይ  የሃገር ውስጥ ምርት (ጂዲፒ) ድርሻ  ሲኖረው እንዲሁም ሠላሣ ሦስት በመቶ ከግብርና ዘርፍ ገቢ ድርሻ ይዞ ይገኛል፡፡ የቁም እንሰሳ ኃብት ለስልሳ አምስት በመቶ ህዝብ መተዳደሪያ ገቢ ያስገኝለታል፡፡ በኢትዮጵያ የቁም እንሰሳት ኃብት ከአስራሁለት እስከ አስራአምስት በመቶ የውጪ ንግድ ገቢ ያስገኛል፡፡ በ2020 እኤአ ሀገሪቱ በቁም እንሰሳት ሽያጭ አርባ ሁለት ነጥብ አምስት ሚሊዮን ዶላር ገቢ ማግኘቶን የተባበሩት መንግስታት ኮምትሬድ  ዳታቤዝ የዓለም አቀፍ ንግድ መረጃ ዘግቦል፡፡  ከኢትዮጵያ በአመት አንድ ነጥብ አምስት ሚሊዮን የቁም እንሰሳት ወደ ጎረቤት ሃገሮች ድንበር አቆርጠው በህገወጥ መንገድ ይሸጣሉ፡፡ በዚህም ምክንያት የቁም እንሰሳት ኃብት ገቢ ቀንሶል፡፡  The livestock sector in Ethiopia contributes 12 and 33% of the total and agricultural Gross Domestic Product (GDP), respectively, and provides livelihood for 65% of the population. The sector also accounts for 12–15% of total export earnings, the second in order of importance. … Ethiopia Exports of live animals was US$42.5 Million during 2020, according to the United Nations COMTRADE database on international trade…..Over 1.5 million exportable livestock are smuggled out of Ethiopia to neighboring countries annually, through borders, according to assessments by the Ethiopian …

 

III-የኢትዮጵያ የገቢ ንግድ (ኢንፖርት) የኢትዮጵያ የገቢ ንግድ (ኢንፖርት) ወጪ በ2018 እኤአ $19.24B,(አስራ ዘጠኝ ነጥብ ሃያ አራት)  ቢሊዮን ዶላር፣ በ2019 እኤአ $20.02B,(ሃያ  ነጥብ ዜሮ ሁለት) ቢሊዮን ዶላር፣ በ2020 እኤአ $18.17B,(አስራ ስምንት  ነጥብ አስራሰባት)  ቢሊዮን ዶላር የገቢ ንግድ ወጪ ተመዝግቦል፡፡

የኢትዮጵያ ዋነኛዎቹ የገቢ ንግድ (ኢንፖርት) በ2021 እኤአ The top imports of Ethiopia፡- ዓይነቶችና ወጪ  መኃል ስንዴ ($927M), (ዘጠን መቶ ሃያ ሰባት)ሚሊዮን ዶላር፣ የተጣራ ነዳጂ ($782M), (ሰባት መቶ ሰማንያ ሁለት) ሚሊዮን ዶላር፣ጋዝ ተርባይንስ ($526M), (አምስት መቶ ሃያ ስድስት) ሚሊዮን ዶላር፣ መድኃኒቶችና  የህክምና መሳሪያዎች ($444M), (አራት መቶ አርባ አራት) ሚሊዮን ዶላር እንዲሁም የአይሮፕላንና ሂሊኮፕተር ($434M), (አራት መቶ ሠላሳ አራት)ሚሊዮን ዶላር በአመት ታወጣለች፡፡  ኢትዮጵያ ኢንፖርት ከምታደርግባቸው አገሮች መኃል ቻይና ($2.8B),ሁለት ነጥብ ስምንት ቢሊዮን ዶላር፣ ኢንዲያ ($1.09B),አንድ ነጥብ ዚሮ ዘጠኝ፣ ዩናይትድ ስቴትስ ($798M), ሰባት መቶ ዘጠና ስምንት ሚሊዮን ዶላር፣ ዩናይትድ አረብ ኢምሬትስ($794M),ሰባት መቶ ዘጠና አራት ሚሊዮን ዶላር፣ እና ዩክሬን ($595M).አምስት መቶ ዘጠና አምስት ሚሊዮን ዶላር ግዥ ያከናውናሉ፡፡

  • {1} ምግብና የምግብ ነክ ውጤቶች food products፡-የኢትዮጵያ በገቢ ንግድ በአመት ሁለት ቢሊዮን ዶላር የሚያወጣ የምግብ ነክ ውጤቶች ከባህር ማዶ አገራት እንደምታስገባ  ይፋዊ የንግድ መረጃዎች ይዘግባሉ፡፡  የአሜሪካ የንግድ ወኪል ዜና መሰረት አሜሪካ ሰባ ስድስት ሚሊዮን ዶላር የሚያወጣ የግብርና ውጤቶች ወደ ኢትዮጵያ በ2018 እኤአ ልካ እንደነበር ተዘግቦል፡፡ Official Ethiopian trade statistics indicate that Ethiopia imports nearly $2 billion worth of food products per annum. According to data from the U.S. Trade Representative (USTR), U.S. total exports of agricultural products to Ethiopia totaled $76 million in 2018.Jan 9, 2020
  • {2}ማሽነሪዎችና መለዋወጫ እቃዎች machinery ዋጋ 74 (አንድ ነጥብ ሰባ አራት) ቢሊዮን ዶላር በ2021 እኤአ ወደ ኢትዮጵያ ተገዝተው እንደገቡ በመረጃ ተረጋግጦል፡፡ Ethiopia: import value of machinery፡- Apr 4, 2023 — In 2021, an approximate value of 1.74 billion U.S. dollars of machinery and mechanical appliances was imported into Ethiopia.
  • {3} መኪናዎች Import value of vehicles into Ethiopia፡-በ2021 እኤአ ወደ ኢትዮጵያ የገቡ መኪናዎች ዋጋ 19 (አንድ ነጥብ አስራ ዘጠኝ) ቢሊዮን ዶላር የተገዙ መሆናቸው በመረጃ ተረጋግጦል፡፡  በ2018እኤአ 875 (ስምንት መቶ ሰባ አምስት  ሚሊዮን ዶላር መኪኖች ተገዝተው ነበር፡፡ ኢትጵያ በ2019 እኤአ 135457 (መቶ ሠላሳ አምስት ሽህ አራት መቶ ሃምሳ ሰባት)መኪኖች ወደ ሀገር ውስጥ አስገባታ ነበር፡፡ In 2021, vehicles (other than railway) in a value of approximately 1.19 billion U.S. dollars were imported into Ethiopia. This was an increase in value in comparison to 2018, when roughly 875 million U.S. dollars of the items were imported.Apr 5, 2023.

Aug 3, 2019 — The country has imported a total of 135, 457 vehicles during Ethiopia’s fiscal calendar ended July 7, 2019.……(8)

  • {4} መድኃኒቶችና የህክምና መገልገያ ቁሶችpharmaceutical products  ዋጋ 812 (ስምንት መቶ አስራ ሁለት ) ሚሊዮን ዶላር በ2021 እኤአ ወደ ኢትዮጵያ ተገዝተው በመረጃ ተረጋግጦል፡፡ In 2021, an approximate value of 812 million U.S. dollars of pharmaceutical products was imported into Ethiopia. This was a significant increase in value in comparison to 2018, when roughly 691 million U.S. dollars of the products were imported.
  • {5} የምግብዘይት ወጪ (Ethiopia edible oil):- የኮነሬል አብይ መንግሥት ለምግብ ዘይት ወጪ 48 (አርባ ስምንት) ሚሊዮን ዶላር በወር ወጪ እንደሚወጣና 2 ሚሊዮን ሊትር ዘይት በየወሩ እንደሚያስፈልግ  ታውቆል፡፡  የኢትዮጵያ የምግብ ዘይት አመታዊ ወጪ 576 (አምስት መቶ ሰባ ስድስት) ሚሊዮን ዶላር እንደሆነ የሀገሪቱ ጠቅላላ የውጭ ንግድ (ኢንፖርት) 15 (አስራአምስት) ቢሊዮን ዶላር  እንደነበረ በመረጃው ተዘግቦል፡፡
  • {6}ኢትዮጵያ  ወታደራዊ ወጪ ( Ethiopia Military expenditure-) ግሎባል ፋየር ፓወር (Global Fire Power)፡- እንደ ግሎባል ፋየር ፓወር መለኪያ መሠረት  የኢትዮጵያ ወታደራዊ ኃይል ደረጃ ከዓለም አርባ ዘጠነኛ ከመቶ አርባ አምስት አገሮች እንደተመደበች መረጃው ዘግቦል፡፡ Ethiopia Military Strength፡-For 2023, Ethiopia is ranked 49 of 145 out of the countries considered for the annual GFP review. The nation holds a PwrIndx* score of 7979 (a score of 0.0000 is considered ‘perfect’). This entry last reviewed on 01/05/2023……………….…(9)

እንደ ስቶክሆልም ኢንተርናሽናል ፒስ ሪሰርች  ኢንስቲቲውሽን ጥናት መሠረት፣  ዓለም አቀፍና የሃገራት  ወታደራዊ ወጪ አፕሪል  24 ቀን 2023  እኤአ ባወጣው መረጃ መሠረት ኢትዮጵያ  ወታደራዊ ወጪ አንድ ቢሊዮን ዶላር  (ሃምሳአራት ቢሊዮን ብር2022እኤአ እንደደረሰና ከአለፈው ዓመት ጋር ሲነፃፀር 88  (የሰማንያ ስምንትበመቶ እድገት  እንዳሳየ  ዘግበዋል፡፡  Addis Abeba – According to new data on global military spending published on Monday, 24 April, by the Stockholm International Peace Research Institute (SIPRI), Ethiopia spent 1 billion USD on military expenditures in 2022, showing an increase of 88 percent from the previous year.

ኢትዮጵያ  ወታደራዊ ወጪ ከሃያ አምስት ቢሊዮን ብር ወደ መቶ ቢሊዮን ብር በኮነሬል አብይ ዘመን ተመንድጎል፡፡  ኦህዴድ ብልፅግና መንግሥት በ2022 እኤአ የአንድ ቢሊዮን ደላር ወይም የሃምሳአራት ቢሊዮን ብር የጦር መሣሪያ ሸምቷል፡፡

  • {7}የኢትዮጵያየነዳጅ ወጪ (oil import)  አራት ቢሊዮን ዶላር ወይም (ሁለት መቶ አስራስድስት)ቢሊየን  ብር በአመት ወጪ ሲኖርባት፣ በሌላ በኩል ኢትዮጵያ 194 (አንድ መቶ ዘጠና አራት)  ቢሊዮን ብር የነዳጅ እዳ እንዳለባት ይታወቃል፡፡  ሱዳን ለኢትዩጵያ መንግስት  አራት ሚሊዮን ቶን የተጣራ ነዳጅ በመሸጥ $3.4 (ሦስት ነጥብ አራት) ቢሊዮን ዶላር የነዳጅ ፍጆታ ሺያጭ ወጪ ታወጣለች፡፡ ሱዳን ሦስት ነጥብ አምስት ቢሊዮን በርሜል የነዳጅ ክምችት ያላት አገር ስትሆን አሁን በተነሳው የሁለቱ ጀነራሎች የሱዳን ጦርነት የነዳጅ ክምችቱ አደጋ ላይ  ሲሆን ኢትዮጵያም ከሱዳን ነዳጅ ለማግኘት ያላት ተስፋ የተመናመነ ነው፡፡ በዚህም የተነሳ በአዲስ አበባ ከተማና በክልሎች ከተሞች የነዳጅ እጥረት ተከስቶል፡፡
  • {8}የማዳበሪያ ወጪ (fertilizer):-   ኢትዮጵያ ለግብርናው ዘርፍ ኢኮኖሚ ለማዳበሪያ ግዢ2 (አንድ ቢሊዮን ሁለት መቶ ሚሊዮን) ዶላር ወጪ ተዳርጋለች፡፡ ኢትዮጵያ በአለፈው አመት በዓለም አቀፍ ንግድ ገበያ የማዳበሪያ ዋጋ እጥፍ በመጨመሩ የተነሳ ከስድስት መቶ ሚሊዮን ዶላር ወደ አንድ ነጥብ ሁለት ቢሊዮን ዶላር ወጪ ተዳርጋለች፡፡ ኢትዮጵያ በጅቡቲ ወደብ በኩል አንድ ነጥብ ሁለት ሚሊዮን ሜትሪክ ቶን ፈርቲላይዘር ለማስገባት አቅዳላች፡፡ Ethiopia plans to import more than 1.2 million metric tons of fertilizer through Djibouti ports for the current farming season.Dec 28, 2022. የቢቢሲ አማርና ዜና መሠረት አንድ ኩንታል ማዳበሪያ ዋጋ አምና አንድ ሽህ ሰባት መቶ ብር የነበረ ሲሆን ከእጥፍ በላይ በመጨመር አራት ሽህ አምስት መቶ ብር በኩንታል በመሆኑ የተነሳ ገበሬዋች በማዳበሪያ ውድነት የተነሳ መሬት ጦሙን ያድራል ብለው ፈርተዋል፡፡
  • {9} ኮነሬል አብይ አህመድ ቤተ-መንግስታቸውን በ503 ሄክታር መሬት ላይ በማነጽ ላይ ይገኛሉ፡፡ የአዲስ አበባ መንገዶች ባለሥልጣን የ29 ኪሎሜትር የውስጥ ለውስጥ መንገድ ሠርቶል፡፡ የኢትዮጵያ ኮንስትራክሽን ሥራዎች የቤተመንግሥቱን ግንባታ እንዲያከናውን ውል ተሰጥቶታል፡፡ የቻይናው መንግሥታዊ የኮንስትራክሽን ኩባንያ ሲሲሲሲ ደግሞ ቅንጡ የሆቴል ግንባታዎች ‹ስካይ ቪው› ግንባታ ያከናውናል፡፡ የቻይና መንግሥትን ሃገሪቱን በዕዳ ነክሮ እያለ፣ ሰው ሰው ያልሸተተ ግንባታ የጫካው ፕሮጀክት እንዲያቆም ኢንባሲዎቹ በሚገኙበት ቦታ ሁሉ ማጋለጥ ያስፈልጋል፡፡  የጫካው ፕሮጀክት ሦስት ሰው ሰራሽ ሃይቆች በ ኢ ቶሎ ተቆራጭ በመገንባት ላይ ይገኛል፡፡ የጫካው ፕሮጀክት በምዕራቡ ዓለም የዲፕሎማቲክ ምንጮች 850 ቢሊዮን ብር የሚያወጣ ፕሮጀክት መሆኑን ሲገምቱ የውጪ ምንዛሪ የሚጠይቁ ከፍተኛ ወጪዎች እንዳሉበት ሙያተኞች ገልጸዋል፡፡ የኢትዮጵያ የገንዘብ ሚኒስቴር አህመድ ሸዴ፣  የኢትዮጵያየገንዘብ ሚንስትር እዮብ ተካልኝ ቶሊና፣ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ገዢ ማሞ ምህረቱ አድርባይ ምሁራን በጦርነቱ የተጎዱ መሠረተ-ልማታቸው የወደሙ የትግራይ ፣አማራና አፋር ህዝብ ችግሮችን መቅረፍ በተገባቸው ነበር እንላለን፡፡…………………..(10)

 ምንጭ (Reference)

(1) ኢትዮጵያ የገባችበት የውጭ ዕዳ ጫና አጣብቂኝና የአበዳሪ አገሮች ፖለቲካዊ   ፍልሚያ/ አፕሪል 16 ቀን 2023 እኤአ

(2) #ASDailyScoop: Ethiopia’s military spending in 2022 increased by 88% to $1 billion –research/April 24,2023

(3)  www.macrotrends.net/countries/ETH/ethiopia/trade-balance-deficit

(4) ቡና ላኪዎች በዓለም ገበያ መቀዛቀዝ ሳቢያ የገቡትን ውል እያፈረሱ በመሆኑ በገቢ ላይ ቅናሽ አምጥቶል ተባለ አፕሪል 9/ 2023

(5) Ethiopia captures 7 kg gold, $1.5 million dollar from smugglers/ February 6, 2019

(6) Ethiopia caught Chinese involved in gold smuggling/ September 3, 2022  NBE 

(7) Fixing the Price: The Politics of the Khat Trade Between Ethiopia and Somaliland – XCEPT (xcept-research.org)

(8) Ethiopia Begins Importing Fertilizer for 2023 Farming Season/ December 28, 2022

(9) 2023 Ethiopia Military Strength (globalfirepower.com)

(10)ጠቅላይ ሚንስትሩ የቤተመንግስት ፕሮጀክት ለሶስት ተቋራጮች ተሰጠ (ዋዜማ)/May 11, 2023

Leave a Reply

Your email address will not be published.

Latest from Blog

ከሃይለገብርኤል   አያሌው የኦቦ ሲራጅና የወይዘሮ ፉንታዬ ልጅ ጃዋር መሃመድ ትላንትን ዛሬንና ነጋችንን ሊያሳይ የሚችል መጽሃፍ አዘጋጅቶልናል:: በእውነቱ መጽሃፉ ሊነበብ በሚችል የሃሳብ ፍሰት ተቀንብቦ በአነጋጋሪነቱ ቀጥሏል:: ጃዋርን እና የቄሮን ትውልድ በቅጡ ለመረዳት መጽሃፉ ማንበብ

የጃዋር የፖለቲካ ጅዋጅዌ! “ድመት መንኩሳ አመሏን አትረሳ’’

ጥር 2 ቀን 2017 ዓ/ም   January 10, 2025  በኢትዮጵያዊነታችሁ፡ በኦርቶዶክሳዊ እምነታችሁ፡ በአማራነታችሁ፡ በአማረኛተናጋሪነታችሁ፡ በተሰነዘረባችሁ ብትር፡ ቤተ ሰብ፡ ወዳጅ ዘመዶቻችሁን ያጣችሁ: ልጆቻችሁን የቀበራችሁ፡ አካልችሁን ያጣችሁ፡ የተሰነዘረውን ብትር በመከላከል ላይ ያላችሁ፡ያለፈቃዳችሁ በመንግሥት ተጽእኖ ወደመግደልና

በኢትዮጵያዊነታችሁ፡ በኦርቶዶክሳዊ እምነታችሁ፡ በአማራነታችሁ፡ በአማረኛ ተናጋሪነታችሁ፡ በተሰነዘረባችሁ ብትር፡

January 10, 2025
መኮንን ሻውል ወልደጊዮርጊስ ¹⁵ የምድርም ነገሥታትና መኳንንት ሻለቃዎችም ባለ ጠጋዎችም ኃይለኛዎችም ባሪያዎችም ጌቶችም ሁሉ በዋሾችና በተራራዎች ዓለቶች ተሰወሩ ፥ ¹⁶ ተራራዎችንና   በላያችን ውደቁ በዙፋንም ከተቀመጠው ፊት ከበጉም ቍጣ ሰውሩን ፤ ¹⁷ ታላቁ የቁጣው ቀን  መጥቶአልና ፥ ማንስ ሊቆም ይችላል ? አሉአቸው ። ራእይ 6 ፤  15_17 ይኽ የመጽሐፍ ቅዱስ ቃል ። የኢየሱስን ልደት ሰናከብር የየሐንስ ራእይን ማንበብ ጠቃሚ ይመስለኛል ። ምክንያቱም በመጨረሻው ዘመን

ከኢየሱስ የፍርድ ቀን በፊት በህሊናችን ውስጥ ፍቅርን ለማንገስ እንጣር 

የምጣኔ ሀብታዊ ፍጥ፣ የፖለቲካ፣ የእውነትና የሰብአዊ መብት ታጋይ፣ የአመኑበትን ነገር ለመናገር እንደ ፖለቲከኛ በቃላት ሳያሽሞነሙኑ ቀጥታ የሚናገሩት የሀገሬ ኢትዮጵያ ታላቅ ሰው ነበሩ “ዘር ቆጠራውን ተዉት፤ የአባቶቻችሁን ሀገር ኢትዮጵያን አክብሩ!”  አቶ ቡልቻ ደመቅሳ

ሀገር ወዳዱ አቶ ቡልቻ ደመቅሳ ከዚህ አለም በሞት ተለዩ

January 6, 2025
ግን ይህ ሁሉ ወጣት የት ገባ? ግን ይህ ሁሉ ወጣት የት ገባ? ዛሬ፣ 2025 ዓ/ም ላይ ብንገኝም በዝንጋታ ገመድ ወደ ሞት እየተጎተትን እንደሆነ አናውቅም። (ሁል ጊዜ የሚሞተው የገነዝነው ይመስለናል። ) “ገብርዬ ነበረ

ግን ይህ ሁሉ ወጣት የት ገባ?

January 3, 2025
Go toTop