May 8, 2023
31 mins read

ሽምግልናና ድርድር ብሎ ነገር የለም! ጦርነቱ የአሜሪካን ኢምፔሪያሊዝም ስራ-አስፈጻሚ የሆነውን የአቢይ አህመድ አገዛዝንና ግብረ-አበሮቹን በማስወገድ ፍጻሜ ማግኘት አለበት!

ፈቃዱ በቀለ (/)

ግንቦት 7 2023

ሰሞኑን በጥብቅ እንደምንከታተለው የአማራን ልዩ ኃይልና ፋኖዎችን ትጥቅ አስፈታለሁ በማለት በአማራው ወገናችን ላይ ጦርነት ያወጀው የአሜሪካን ኢምፔሪያሊዝም ቅምጥ የሆነው የአቢይ አህመድ አገዛዝ መጠነ-ሰፊ ጥቃት አድርሷል። ቁጥራቸው የማይታወቁ ሰዎች ከሁለቱም ወገን ህይወታቸው እንዲያጣ ተደርጓል። አርቆ-ማሰብ የጎደለውና መንፈሰ-አልባ የሆነው አቢይ አህመድ በአማራው ወገናችን ላይ የከፈተው ጦርነት የምርትና የንግድ እንቅስቃሴ እንዳይካሄድ ከፍተኛ መሰናክል ፈጥሯል። ማንኛውም ሰራተኛ የሆነና ላቡን እያንጠበጠበ ገቢ ለማግኘትና ቤተሰቡን ለመመገብ የሚሯሯጠው ሁሉ ከስራው እንዲተጓጎል ለመሆን በቅቷል።

አቢይ አህመድ በአሜሪካን ኢምፔሪያሊዝም በመደገፍና በመመከር ትጥቅ አስፈታለሁ በሚል ሰበብ በጠቅላላው በአማራው ህዝባችን ላይ ጦርነት ሲከፍት ሊያስከትል የሚችለውን ኢኮኖሚያዊ፣ ማህበራዊ፣ ስነ-ልቦናዊና የባህል ቀውስ ቆም ብሎ ሊያጤን በፍጹም አልቻለም። እንደ ኦሮምያ ክልል የመሳሰሉት እስከ አፍጢማቸው የሚደርስ መሳሪያ የታጠቁትንና ይህን ያህልም ለአደጋ ያልተጋለጡት መሳሪያቸውን ለመንግስት አስረከቡ ሳይባሉ የአማራው ክልል ልዩ ኃይልና ፋኖዎች ለምን ትጥቃቸውን መፍታት ወይም ለመንግስት ማስረከብ እንዳለባቸው አቢይ አህመድና ግብረ-አበሮች ግልጽ ሊያደርጉልን በፍጹም አልቻሉም። በሌላ ወገን ደግሞ ሁላችንም እንደምናውቀው በተለይም ባለፉት ሁለት ዓመታት በአሜሪካን አምፔሪያሊዝም በሚደገፈውና በሚታጠቀው በወያኔ ወንበዴዎች ከፍተኛ ጥቃት የደረሰበትና የሚደርስበት፣ እንዲሁም ለፍተኛ አደጋ የተጋለጠው የአማራው ክልልና በዚያ የሚኖረው ህዝብ ነው። እንደሚታወቀው ወያኔ  አመቺ ሁኔታ ተከፍቶለት እስከወሎና አፋር ድረስ፣ እንዲሁም ጎንደር በመዝለቅ በአማራው ኗሪ ህዝብ ላይ መጠነ-ሰፊ ጥቃትና ዘረፋ ሲያካሂድ የፌዴራሉ የመከላከያ ኃይል ሳይሆን፣ የክልሉ ልዩ ኃይልና ፋኖዎች ናቸው የወያኔን ወራሪ ኃይል መክተው የመለሱትና ሊያዳክሙት የቻሉት። ወያኔ ከሁለት ዓመት ተኩል በፊት፣ በህዳር ወር 2020 ዓ.ም ትግሬ ውስጥ በሰፈረው የሰሜን ዕዝ በመባል በሚታወቀው የአገሪቱ  የመከላከያ አካል ላይ በተኙበት ሲገድላቸው፣ የወያኔን ፋሺሽታዊ የታጠቀ ቡድን እየመከቱና እየተከታተሉ  ሊያንኮታኩቱት የቻሉት የአማራው ልዩ ኃይልና ፋኖዎች ናቸው። ታዲያ ይህ ሁሉ ግልጽ ከሆነና ወያኔም ሙሉ በሙሉ ትጥቁን ባልፈታበት ጊዜና፣ ይባስ ብሎ ለአራተኛ ጊዜ  በአማራው ህዝባችን ላይ ጦርነት ለማካሄድ ዝግጅት በሚያደርግበት ጊዜ በምን ምክንያት ነው የአማራው ልዩ ኃይልና ፋኖዎች ትጥቃቸውን እንዲፈቱ ሩጫ የተያዘውና፣ ይባስ ብሎ አሁን ደግሞ ጦርነት´ የተከፈተባቸው?

ሚስጥሩ ለሁላችንም የሚታወቅ ነው። የአማራው ልዩ ኃይልና ፋኖዎች ትጥቃቸውን ሲፈቱ ብቻ ነው በአሜሪካን ኢምፔሪያሊዝም የበላይ ተጠባባቂነት በአቢይ አገዛዝና በወያኔ ወንበዴዎች የሰላም ስምምነት ተደረሰበት የተባለበት ጉዳይና፣ በተለይም ወልቃይትና ጠገዴን ለህወሃት አሳልፎ መስጠት የሚቻለው። በመሰረቱ ወያኔ ባለፉት ሁለት ዓመታት ብቻ ሳይሆን፣ ስልጣን ላይ በነበረበት ጊዜ በህዝባችን ላይ ያደረሰው መጠነ-ሰፊ ግፍ ሲቆጠር የኢትዮጵያን ህዝብ እወክላለሁ የሚል አገዛዝ ከእንደዚህ ዐይነቱ በውጭ ኃይል በሚደገፍና በህዝባችን ላይ ጦርነትን አውጆ ስንትና ስንት ግፍ ከፈጸመ ጋር ተቀምጦ የስላም ድርድር ማድረግ አስፈላጊ አልነበረም። በተለይም ደግሞ ወያኔ በማቴሪያልም ሆነ በሰው ኃይል በተዳከመበትና፣ ያስታጠቀውን ኃይል በተከታታይ ስንቅ እያቀበለ ሊቀልበው በማይችልበት ወቅት ከእንደዚህ ዐይነቱ ፋሺሽታዊ ቡድን ጋር ተቀምጦ ስለሰላም ወይም ስለዕርቅ ማውራት አስፈላጊ አልነበረም። ሌላው ጉዳይ ደግሞ ይህ ጉዳይ ህዝብን እንወክላለን በሚሉት የህዝብ ተወካዮች ምክርቤትና በህዝቡ ዘንድ በቂና ሳይንሳዊ ውይይት አልተካሄደበትም። ይህም ማለት አቢይ አህመድ በአሜሪካን ኢምፔሪያሊዝም ተገፋፍቶ “የሰላም ድርድር” ሲያካሄድ ከህዝብ ዕውቅና ውጭ የሆነና በህገ-መንግስት የተደገፈ አይደለም። ምክንያቱም እንደወያኔ የመሰለ በውጭ ወራሪ ኃይል የሚደገፍ ቡድን በህዝብና በአገር ላይ ስንትና ስንት ጉዳት ካደረሰ በኋላ ተቀምጠን ስለሰላም እንነጋገር ማለት በከፍተኛ ደረጃ ብሄራዊ ነፃነትን ማስደፈር ብቻ ሳይሆን፣ ሰፊውን የኢትዮጵያን ህዝብም መናቅ ነው። እንደሚታወቀው የአንድ አገዛዝ መሰረታዊና ዋና ተግባር ከውስጥ ስላም የሚሰፍንበትን ሁኔታ ማመቻቸት ብቻ ሳይሆን፣ እንደወያኔ የመሳሰሉ በውጭ ኃይል የሚደገፉ ፋሺሽታዊ ቡድኖች ጦርነት በሚከፍቱበት ጊዜ በተባበረ ኃይል ጠራርጎ ማስወጣትና የተያዙትን ወንበዴዎች ደግሞ በቂ ቅጣት በመስጠት እንደዚህ ዐይነት ሁኔታ እንዳይደገም ለሌላውም ተስፈንጣሪና ሰላም ነሺ ኃይል ምሳሌ እንዲሆን ማስተማር ነበር። ለማንኛውም ኢትዮጵያዊ ነኝ ለሚል ግለሰብም ሆነ የዚኸኛው ወይም የዚያኛው ብሄረሰብ አካል ነኝ የሚል ግልጽ መሆን ያለበት ጉዳይ አንድ አገር መፈንጫ መድረክ አይደለችም። ነፃነት ሊገኝ የሚችለው በስራና ከአጉል ትረካ ውጭ የሆነ ሳይንስዊ ጥናትና ውይይት ሲካሄድ ብቻ ነው። እያንዳንዱ ግለሰብ ከዚኸኛው ወይም ከዚያኛው ብሄረሰብ ይምጣ ይህንን መሰረተ ሃሳብ በጭንቅላቱ መቋጠር አለበት። የስልጣኔም መለኪያው ይህ ብቻ ነው።

ይሁንና ግን አቢይ አህመድ ራሱ የአሜሪካን ኢምፔሪያሊዝም ቅምጥ አገዛዝ በመሆኑ በአገር ውስጥ ሰላምን ማስፈንና ብሄራዊ ነፃነትን ማስጠበቅ ሳይሆን ዋናው ተግባሩ አድርጎ የያዘው ከአማራው ህዝብና ከኦርቶዶክስ ኃይማኖት ጋር እልክ ውስጥ በመግባት የታሪክና የአገር ምሰሶዎች የሆኑትን ኃይሎችና ተቋማት ማዳከምና ኃይላቸውን መበታተን ነው። በተለይም አሜሪካን ኢምፔሪያሊዝምና ግብረ-አበሮች ጠቅላላው የዓለም ህዝብ እነሱ በሚፈልጉት አንድ ዐይነት ህግና ደንብ( Rules-Based World Order) መተዳደር አለበት በማለት በሚጣደፉበት ዘመን ይህንን ከህብረተሰብና ከተፈጥሮ ህግ ጋር የሚፃረረውን ህልማቸውንና ራሳቸው የፈጠሩትን ደንብ ዓለም አቀፋዊ ለማድረግ ወይም የዓለም ህዝብ ሁሉ እንዲቀበለው ለማድረግ በየአገሮች ያሉ ለብዙ መቶ ዓመታት ከትውልድ ትውልድ የተላለፉ ባህሎች፣ የአኗኗር ስልቶችና፣ ህብረተሰብአዊና ማህበራዊ ግኑኝነቶችና ኖርሞች፣ እንዲሁም ሃማኖትም ጭምር መወገድ አለባቸው። በሌላ አነጋገር፣  እያንዳንዱ አገርና ህዝብ  በራሱ እሴትና ደንብ መተዳደር ያለበት ሳይሆን አሜሪካና ግብረ-አበሮቹ በነደፉለትና በሚፈልጉት ብቻ ነው። እያንዳንዱ አገርና በእያንዳንዱ አገር የሚኖር ዜጋ በነፃ የማሰብ መብት የለውም። ይህ ዐይነቱ አስተሳሰብ ደግሞ እንዳለ የማዕከለኛው ክፍለ-ዘመን አስተሳሰብና ዲስፖታዊ አመላከት ብቻ ሳይሆነ በራሱ የሊበራል አስተሳሰብን የሚጻረር ነው። ምናልባት አብዛኛዎቻቸን የምናውቅ ከሆነ በማዕከለኛው ክፍለ-ዘመን በአውሮፓ ምድር ውስጥ የካቶሊክ ሃይማኖት ብቻ ነበር ተቀባይነት የነበረው  ሃይማኖት። በጊዜው የካቶሊክ ሃይማኖት መሪዎች ከሚያስቡትና ከሚሰብኩት ሃይማኖት ውጭ ማስተማርና ማመን በጥብቅ የተከለከለ ነበር። ስለሆነም ሳይንሳዊ ግኝቶችና አስተሳሰቦች በሙሉ የካቶሊክ ሃይማኖትን ዶክትሪንን የሚፃረሩ ሆነው በመታየታቸው፣ ትክክልም ቢሆኑም የሳይንስ ተመራማሪዎች እንደ ጋሊሌዬና ቡሩኖ ጋርዳይኖስ የመሳሰሉት ይታሰሩና ይሳደዱ ነበር። ቡሩኖ ጋርዲያኖስ ደግሞ እስከነ ነፍሱ እንዲቃጠል ለመደረግ በቅቷል። የዲስፖታዊ አገዛዞችም የሊበራል አተሰሳሰብ የነበራቸውንና መቻቻልን የሚያስተምሩትን እንደነ ሬኔ ዴካ የመሳሰሉትን በማሳደድ ከአገራቸው እንዲወጡ ያስገደዱበት ጊዜ ነበር። እንደሆላንድ የመሳሰሉት የነፃ አስተሳሰብ በሚፈቀድበት አገር ውስጥ ጥገኝነትን በመጠየቅ ነው ሳይንሳዊ ምርምራቸውን ማካሄድ የቻሉትና ለሰው ልጅ የተረፈ የቴክኖሎጂ ፈለግ ጥለውልን ለማለፍ የቻሉት። ስለሆነም የኋላ ኋላ ዲስፖቲያዊ አገዛዝን በመቃወም የተነሱት እንደነ ጆን ሎክና፣ የኋላ ኋላ ደግሞ እንደነካንት የመሳሰሉት ፈላስፋዎችና ሳይንቲስቶች የህግን የበላይነት በማርቀቅና በማስተማር ነው ማንኛውም ሰው፣ ራሳቸው የፍጹም ሞናርኪዎችም እንዲቀበሉት ለማድረግ የበቁትና፣ ቀሰ በቀስ የካፒታሊስት ስርዓትና ካፒታሊዝም ሊያድጉና ሊስፋፉ የቻሉት። ሳይንስና ቴክኖሎጂም ሊዳብሩ የቻሉትና ዓለም አቀፍ ባህርይ ለመውሰድ የቻሉት አገዛዞች የህግን የበላይነትን ከተቀበሉና ነፃ አስተሳሰብን የማይታለፍና ለህብረተሰብ ዕድገት አስፈላጊ መሆኑን እየተረዱ ከመጡ በኋላ ነው።

ወደ አሜሪካኖቹ አስተሳሰብና ድንጋጌ ስንመጣ፣  በዓለም አቀፍ ላይ አንድ ዐይነት ደንብ መስፈን አለበት፣ ማንኛውም መንግስት ተግባራዊ ማድረግ አለበት ብለው ሲነሱ ይህንን ዐይነቱን ከላይ የተነተንኩትን የካቶሊክ ሃይማኖት መሪዎችን ጭፍን አስተሳሰብና የዲስፖታዊ አገዛዞችን እጅግ ኋላ የቀረ አመለካከት ነው የሚያስታውሰኝ። ሰለሆነም እያንዳንዱ አገር የአሜሪካን ኢምፔሪያሊዝምና ግብረ-አበሮቹ ብቻ በሚፈልጉት ደንብ እንዲሰራ የሚገደድ ከሆነ በነፃ የማደግና ህብረተሰቡን በስነ-ስርዓት የመገንባት ዕድል አይኖረውም። ከዚህም በላይ ይህ ዐይነቱ አንድ ዐይነት ደንብ ለዘረፋ እንዲያመች ተብሎ የረቀቀ በመሆኑ፣ እንደኛ ባለው መንፈሰ ደካማ አገዛዝ ባለበት አገር ተግባራዊ በሚደረግበት ጊዜ እንዳለ ኢኮኖሚያዊ፣ ማህበራዊ፣ ባህላዊ፣ ስነ-ልቦናዊና የኢኮሎጂ ቀውሶችን ነው የሚያስከትለው። ለዚህ ደግሞ ዋናው የመስበኪያና አገሮችን በአንድ የዓለም አቀፍ አገዛዝ ጥላ ስር ማምጫ ዘዴ እያንዳንዱ አገር የዓለም የገንዘብ ድርጅትና(IMF) የዓለም ባንክ የነደፉትንና የደነገጉትን የነፃ ገበያ የኢኮኖሚ ፖሊሲ ብለው የሚጠሩትን ተግባራዊ ማድረግ አለበት። የነፃ ገበያ የሚባለውም የኢኮኖሚ ፖሊሲ በመሰረቱ በመጀመሪያ ደረጃ የእያንዳንዱን ግለሰብ መሰረታዊ ፍላጎት(Basic Needs) ማሟላት ሳይሆን፣ የየአገሩን ገበያ ለዓለም አቀፍ ኩባንያዎች ክፍት በማድረግ ለጥሬ-ሀብት ዘረፋ አመቺ ሁኔታዎችን መፍጠር ነው።  ወያኔ 27 ዓመታትት ያህል ስልጣን ላይ በቆየበት ዘመን ይህንን ህግና ደንብ ተገን በማድረግ ነው በነፃ ገበያ ስም ተግባራዊ ያደረገው የኢኮኖሚ ፖሊሲ ከፍተኛ ዘረፋና መመሰቃቀልን ሊያስከትል የቻለው። ወያኔም ወደ ዘራፊ አገዛዝ(Predatory State) ሊቀየር የቻለው የኒዎ-ሊበራል ኢኮኖሚክ ፖሊስን ተግባራዊ በማድረጉ ነው።

ወደዋናው ቁም ነገር ስንመጣ፣ እነ አቢይ አህመድ ባለፉት ሶስት ዓመታት በተከታታይነት በአማራው ህዝባችንና በኦርቶዶክስ ሃይማኖት ላይ የከፈቱት ጦርነትና፣ ወያኔ ተግባራዊ ያደረገውን የኢኮኖሚ ፖሊሲና የብልግና ኢንዱስትሪ ማስፋፋት በዚያው የቀጠሉበት ምክንያት የአሜሪካንን ፍላጎት ፍጻሜ ለማድረስና አገራችንን ድምጥማጧን ለማጥፋት ነው። እንደሚታወቀው አንድ ህዝብ ከትውልድ ትውልድ ሲተላለፍ የኖረበት ባህሉና የአኗኗር ልምዱ ሲደመሰስበት፣ ወይም በተዘበራረቀ መልክ ሌላ ሲካተትበት አቅጣጫው ሁሉ ይጠፋበታል። ሰው መሆኑን ይዘነጋል። ጥያቄ ለመጠየቅ በፍጹም አይችልም። ሁኔታዎች በተዘበራረቀ መልክ ሲለዋወጡና ሲባላሹ ለምን እንደዚህ ሆኑ ብሎ የሚጠይቅ ስለማይኖር በዚያው እየተደናበረና ለመብቱ ሳይታገል በሌሎች ጉልበተኛ ኃይሎች እየተሰቃየና እየተናቀ እንዲኖር ይገደዳል፟። በዚያው መጠንም እግዚያብሄር የለገሰውን የማስብ ኃይሉን እንዳይጠቀም ይገደዳል። በአገሩ ባይተዋር ዜጋ በመሆን፣ የመስራት ዕድል ከሌለው ወደ ሌላ አገር እንዲሰደድ ይደረጋል።

ከዚህ ሀቅ ስንነሳ እነ አቢይ አህመድ የአማራውን ልዩ ኃይልና ፋኖዎችን መሳሪያዎቻቸውን እናስፈታለን ብለው የከፈቱት ጦርነት የኦሮሙማን የበላይነት ለማስፈን የሚመስል ቢሆንም፣ ዋናው ዓላማው ኢትዮጵያን በአሜሪካን ኢምፔሪያሊዝምና በግብረ-አበሮቿ ቁጥጥር ስር በማድረግ የጥሬ-ሀብቷን መዝረፍ ነው። በዚህም አማካይነት ህዝቡን በጎሳና በሃይማኖት በመከፋፈል፣ በተለይም ደግሞ አማራውንና የኦርቶዶክስ ሃይማኖትን እንደጨቋኝ ነገሮች በማየትና በህዝባችን ዘንድ አለመተማመን በመፍጠር ወደ ውስጥ ያተኮረ በሳይንስና በቴክኖሎጂ ላይ የተመሰረተ ጠቅላላውን ህዝብ የሚጠቅም ሰፋ ያለ የገበያ ኢኮኖሚ እንዳይገነባ እንቅፋት መፍጠር ነው። ህዝባችን ከድህነት እንዳይላቀቅ በማድረግ ለዝንተ-ዓለም ለማኝ ሆኖ እንዲቀር ማድረግ ነው። ደሀና ያልተማረ ህዝብ ደግሞ እየመላለሰ ለውጭ ኃይሎች ስለሚጋለጥና ለውጭ ወራሪ ኃይሎች ስለሚያመች በቀላሉ ብሄራዊ ነፃነቱ ይገፈፋል፤ እየተናቀም እንዲኖር ይገደዳል ማለት ነው። በተጨባጭ ሲታይ እነ አቢይ አህመድ በዓለም አቀፍ ደረጃ ከተንሰራፋው ስርዓት ጋር በማበርና ትዕዛዝ በመቀበል የህዝባችንን ሰቆቃ ማርዘም ብቻ ሳይሆን፣ ብሩህ የሆነውንም በሳይንስና በቴክኖሎጅ የሚደገፈውን ኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ ዕድገት ተግባራዊ እንዳይሆን እንቅፋት መፍጠር ነው። አንድ ህዝብና አንድ አገር በጦርነት ሲያዝ የማሰብና የመፍጠር ኃይሉ ስለሚዳከም ጦርነትን እንደባህል አድርጎ መቀበል አለበት። የህይወቱ አካል አድርጎ መኖር አለበት። አንደኛው ሌላውን እየፈራና ጉልበተኛው ደካማውን እያስፈራራ የሚኖሩበት አገር ይፈጠራል ማለት ነው። በአጭሩ አንድ አገር ታሪክና ባህል የሚሰራባቸውና የሚዳብርባቸው ሳይሆኑ የወንበዴዎች አገር ይሆናል ማለት ነው። አቢይ አህመድና ግብረ-አበሮቹ፣ ወያኔም ጭምር ለጊዜው በአማራውና በኦርቶዶክስ ሃይማኖት ላይ ጦርነት የከፈቱ ቢሆንም፣ ከረጅም ጊዜ አንፃር አካሄዳቸው በጠቅላላው ህዝብ ላይ ጦርነትን ያወጁና በዚያውም የሚገፉበት ናቸው። ስልጣንም ላይ ለረጅም ጊዜ ተደላድለው ሊቆዩ የሚችሉት የህዝቡን መንፈስ በጦርነት ሲይዙትና ጦረነትን በየቦታው ሲፈለፍሉ ብቻ ነው። ጦርነቱ ደግሞ በግልጽና ግልጽ ባልሆነ መንገድ የሚካሄድ ሲሆን፣ ማንኛውንም ብሄረሰብ የሚጎዳና አቀጭጮት የሚያስቀረው ነው። ባጭሩ ሰፊው የኢትዮጵያ ሁዝብ የኑሮን ትርጉም እንዳያውቅ በማድረግ እየተደናበረና እርስ በርሱ እየተጋጨ እንዲኖር የሚያደርግ ነው።

አቢይ አህመድ ግርማ የሺጥላን አስገድሎ ልክ ፋኖዎች እንዳስገደሉት በማስመሰል አሳቦ የከፈተው ጦርነት ብቻውን ያቀነባበረው ሳይሆን የውጭ እጅም አለበት። በጠቅላላው የአማራውን ክልል የጦር ቀጠና ለማድረግና ሰፊውን የአማራ ህዝብ ለማዋከብና ለማድከም፣ እንዲያም ሲል በቁጥር ለመቀነስ ቀደም ብሎ የተቀነባበረ ዕቅድ ነው። ከመቅጽበት የመጣ አይደለም። በሌላ ወገን ደግሞ ቀኝ-እጁ የነበረውንና ፋኖዎችን ያሳድድ የነበረውን ግርማ የሺጥላን ማስገደሉ የሚያረጋግጠው የአቢይ አህመድን መንፈስ-አልባነት ወይም አረመኔያዊነት ነው። ለማንኛውም አቢይ አህመድና ብርሃኑ ጁላ እንዳሰቡት ፋኖዎችንና የአማራውን ልዩ ኃይል ትጥቃቸውን በቀላሉ ለማስፈታትና ለማንበርከክም አልቻሉም። እንዲያውም የተወሰነው የፌዴራሉ መከላከያ ኃይል፣ አይ ከነትጥቁ ወደ ኤርትራ በመግባት፣ አንዳንዱ ደግሞ ከፋኖዎችና ከአማራው ልዩ ኃይል ጋር በመሰለፍና በመተባበር የአቢይ አህመድንና የብርሃኑን የኦነግ ሸኔ የታጠቀ ኃይል መግቢያና መውጫ እያሳጧቸው ነው። ቁጥሩ የማይታወቅም ኃይል ተግድሏል፤ ከእነ ትጥቁም የተማረከ አለ። ሰፈው የአማራ ህዝብም ከፋኖዎችና ከክልሉ ኃይል ጎን በመሰለፍና ማንኛውንም ድጋፍ በመስጠት የአቢይን ወራሪ የኦነግ ሽኔ ኃይልን እያዳከመውና እየበታተነው ይገኛል። ይህንን የተረዳው አቢይ አህመድ እንሸመጋገል እያለ የማታለያ ዘዴ በመፈለግ ፋኖዎችንና ልዩ ኃይሉን በማዘናጋት ላይ ይገኛል። በሌላው ወገን ደግሞ በ21ኛው ክፍለ-ዘመን በሃሳብ ዙሪያ ነው መወያየት ያለብን በማለት፣ እዚያው በዚያው ደግሞ ጦርነቱን በስፋት ለማካሄድ ተጨማሪ የጦር ኃይል በመላክ ላይ ይገኛል። ሰለጠንኩኝ የሚለው፣ በሃሳብ ዙሪያ እንወያይ የሚለው አቢይ አህመድ በሃሳብ ዙሪያ እንወያይ ሲል ራሱ ብቻ በመታጠቅና በመውረር ሌሎች ትጥቃቸውን እንዲፈቱለት ማለቱ ነው። በመሰረቱ አቢይ አህመድና ግብረ-አበሮች በውጭ ኃይል የሚጠመዘዙ ስለሆነ የራሳቸው ነፃ አስተሳሰብ የላቸውም። ስለሆነም በአቢይ አህመድ ሎጂክ በሌለው አነጋገርና የማታለያ አባባል መዘናጋት የለብንም። መታወቅ ያለበት ጉዳይ አቢይ አህመድና ግብረ-አበሮች የኢትዮጵያን ህዝብ የሚወክሉ አይደሉም። የሚያካሂዱትም የወረራና የውክልና ጦርነት ሊቆም የሚችለው አቢይ አህመድና ግብረ-አበሮቹ ብቻ ሳይሆኑ፣ ወያኔና ሌሎችም ከኢትዮጵያ ምድር ተጠራርገው ሲጠፉ ብቻ ነው። በኢትዮጵያ ምድር ዘላቂ ሰላም ሊሰፍን የሚችለው እንደነዚህ ያሉ የውጭ ቅምጥ አገዛዞችና እዚህና እዚያ የሚሯሯጡ፣ ይህንን ወይም ያኛውን ብሄረሰብ እንወክላለን የሚሉ የተወናበዱ ኃይሎች ሲወገዱ ብቻ ነው። ዘላቂ ሰላም ባልሰፈነበት አገርና፣ ህዝቡ የራሱን የጥሬ-ሀብት በማይቆጣጠርበት አገር የተሟላና ሰፊውን ህዝብ የሚጠቅም ዕድገት ተግባራዊ ማድረግ ስለማይቻል እንደነ አቢይ አህመድና ወያኔ የመሳሰሉት ኃይሎች ለአንዴም ለመጨረሻም ጊዜ ከኢትዮጵያ ምድር ተጠራርገው መጥፋት አለባቸው። እነዚህ ኃይሎች ብቻ ሳይሆኑ፣ የአሜሪካን ኢምፔሪያሊዝም ናፋቂዎች ሁሉ እንደነቀርሳ በሽታ የሚታዩ በመሆናቸው እነዚህ ሲወገዱ ብቻ ነው አገራችንና ህዝባችን ብሄራዊ ነፃነታቸውን አስከብረው እያንዳንዱ ዜጋ እንደ ነፃ ዜጋ ሊኖር የሚችለው። ከዚህ ስንነሳ ማንኛውም የአቢይ አህመድን አገዛዝና ወያኔን የሚቃወም ሁሉ ያሁኑን ሁኔታ በመጠቀም በአሜሪካኖች ተደግፎ ስልጣን ላይ ቁጥጥ ለማለት የሚያደርገውን መሯሯጥ ማቆም አለበት። የኢትዮጵያ ህዝብ የተሟላ ሰላሙን ለማግኘትና እፎይ ብሎ ለመኖር የሚችለው ከአሜሪካን ኢምፔሪያሊዝም ቁጥጥር ውጭ የሆነ አገዛዝና በነፃ የሚያስብና በራሱ ዕውቀት የሚመራ ብሄረተኛ ኃይል ስልጣንን ሲጨብጥ ብቻ ነው። ስለሆነም በጦር ሜዳ ላይ ህይወታቸውን የሚሰዉት እህቶቻችንና ወንድሞቻችን ህልማቸው ዕውን እንዲሆን ከፈለግን በቀና መንፈስ ልናግዛቸው ያስፈልጋል። ድልና የተሟላ ነፃነት ለሰፊው የኢትዮጵያ ህዝብ። መልካም ግንዛቤ!!

  [email protected]

 www.fekadubekele.com

Leave a Reply

Your email address will not be published.

Latest from Blog

ከሃይለገብርኤል   አያሌው የኦቦ ሲራጅና የወይዘሮ ፉንታዬ ልጅ ጃዋር መሃመድ ትላንትን ዛሬንና ነጋችንን ሊያሳይ የሚችል መጽሃፍ አዘጋጅቶልናል:: በእውነቱ መጽሃፉ ሊነበብ በሚችል የሃሳብ ፍሰት ተቀንብቦ በአነጋጋሪነቱ ቀጥሏል:: ጃዋርን እና የቄሮን ትውልድ በቅጡ ለመረዳት መጽሃፉ ማንበብ

የጃዋር የፖለቲካ ጅዋጅዌ! “ድመት መንኩሳ አመሏን አትረሳ’’

ጥር 2 ቀን 2017 ዓ/ም   January 10, 2025  በኢትዮጵያዊነታችሁ፡ በኦርቶዶክሳዊ እምነታችሁ፡ በአማራነታችሁ፡ በአማረኛተናጋሪነታችሁ፡ በተሰነዘረባችሁ ብትር፡ ቤተ ሰብ፡ ወዳጅ ዘመዶቻችሁን ያጣችሁ: ልጆቻችሁን የቀበራችሁ፡ አካልችሁን ያጣችሁ፡ የተሰነዘረውን ብትር በመከላከል ላይ ያላችሁ፡ያለፈቃዳችሁ በመንግሥት ተጽእኖ ወደመግደልና

በኢትዮጵያዊነታችሁ፡ በኦርቶዶክሳዊ እምነታችሁ፡ በአማራነታችሁ፡ በአማረኛ ተናጋሪነታችሁ፡ በተሰነዘረባችሁ ብትር፡

January 10, 2025
መኮንን ሻውል ወልደጊዮርጊስ ¹⁵ የምድርም ነገሥታትና መኳንንት ሻለቃዎችም ባለ ጠጋዎችም ኃይለኛዎችም ባሪያዎችም ጌቶችም ሁሉ በዋሾችና በተራራዎች ዓለቶች ተሰወሩ ፥ ¹⁶ ተራራዎችንና   በላያችን ውደቁ በዙፋንም ከተቀመጠው ፊት ከበጉም ቍጣ ሰውሩን ፤ ¹⁷ ታላቁ የቁጣው ቀን  መጥቶአልና ፥ ማንስ ሊቆም ይችላል ? አሉአቸው ። ራእይ 6 ፤  15_17 ይኽ የመጽሐፍ ቅዱስ ቃል ። የኢየሱስን ልደት ሰናከብር የየሐንስ ራእይን ማንበብ ጠቃሚ ይመስለኛል ። ምክንያቱም በመጨረሻው ዘመን

ከኢየሱስ የፍርድ ቀን በፊት በህሊናችን ውስጥ ፍቅርን ለማንገስ እንጣር 

የምጣኔ ሀብታዊ ፍጥ፣ የፖለቲካ፣ የእውነትና የሰብአዊ መብት ታጋይ፣ የአመኑበትን ነገር ለመናገር እንደ ፖለቲከኛ በቃላት ሳያሽሞነሙኑ ቀጥታ የሚናገሩት የሀገሬ ኢትዮጵያ ታላቅ ሰው ነበሩ “ዘር ቆጠራውን ተዉት፤ የአባቶቻችሁን ሀገር ኢትዮጵያን አክብሩ!”  አቶ ቡልቻ ደመቅሳ

ሀገር ወዳዱ አቶ ቡልቻ ደመቅሳ ከዚህ አለም በሞት ተለዩ

January 6, 2025
ግን ይህ ሁሉ ወጣት የት ገባ? ግን ይህ ሁሉ ወጣት የት ገባ? ዛሬ፣ 2025 ዓ/ም ላይ ብንገኝም በዝንጋታ ገመድ ወደ ሞት እየተጎተትን እንደሆነ አናውቅም። (ሁል ጊዜ የሚሞተው የገነዝነው ይመስለናል። ) “ገብርዬ ነበረ

ግን ይህ ሁሉ ወጣት የት ገባ?

January 3, 2025
Go toTop