ሰላቢ ሁላ!!!
“””””””””””””””
ሳይማሩ፣የተማሩ
ባጋጣሚ፣የከበሩ
ከእውቀት ጥበብ የተፋቱ
ግርድፍ ሽርክት፣ግንፍል ጥሬ
ተፈጭተው፣ተሰልቀው!
ተወቅጠው፣ተደልዘው!
በቅጡ እንኳን ያላሙ
ትንሽ ትልቅ፣ልጅ አዋቂ
ፍጥረተ ሰብእ፣ያማረሩ
አብለው፣ቀጥፈው ሀገር መሩ::
ድንቄም ብልጽግና?
<…የልማት ጎዳና
የዃሊት ገስግሶ፣ስለ ፊት ሚያውራ
ፍልጥ ድንጋይ፣ሰገጤ ሁላ
ገሪባ ዝባዝንኬ፣ግተት ዝተት
ጅላጅል ማሞ ቂሎ፣የመንደር ጅላንፎ
ሰላም ነው ባይ፣ያገር ክብር ገፎ
የወይን! ግልባጭ፣በሸፍጥና ሴራ
ለባለሀገር ሞት፣መንፈሱ ማይራራ
የምስኪኑን ሌማት፣አዋዩን ያጠፋ!
እንደ መተተኛ፣ልክ እንደ ሰላቢ!
አፈር ድሜ ያበላ፣ያገር ኢኮኖሚ::
~***°•***°•***~
ለቀሽም አስመሳይ
ያገር ሾተላይና ሰንኮፎች
መዘከርያ
,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,, ,,,,,,,,,,,,,,,,
መጋቢት ፫/፳፻፲፬ ዓ.ም
March 12/2022
ቅዳሜ )03:19 ምሽት(ሚኪ.ላ/አ.አ
©ያመጌዕ