ያሳማ ዋና ፍላጎት ተጨማልቆ ማጨማለቅ ስለሆነ፣ ካሳማ ጋር በጭራሽ አትታገል፡፡
(Never wrestle with a pig. You both get dirty and the pig likes it. George Bernard Shaw)
“የኤርምያስ ለገሰና የመሳይ መኮንን መንገዶች፤ ቀጣዩ የኤርምያስ እሥሥታዊ እርምጃ” በሚል ርዕስ ከሳምንት በፊት (April 13, 2023) በጦመርኩት ጦማር ላይ የሚከተሉትን ሁለት አንቀጾች ጽፌ ነበር፡፡
- “አቶ ኤርምያስ ኢትዮ360ን የለቀቀው ኢትዮ360ን አዳክሞ የማጥፋት ልዩ ተልእኮ አንገቦ ነው፡፡ ተልእኮውን ከከፍተኛ ገንዘብ ጋር የሰጠው ደግሞ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ወደ ዋሽንግተን ዲሲ መለስ ቀለስ የሚለው አቶ ታከለ ኡማ ነው፡፡ አቶ ኤርምያስ ኢትዮ360ን አዳክሞ ለማጥፋት ያሰበው ደግሞ ጭራቅ አሕመድ አማራን አዳከሞ ለማጥፋት እየተጠቀመበት ባለው ዘዴ ነው፡፡ ዘዴው ደግሞ የሚከተለው ነው፡፡”
- “አቶ ኤርምያስ አቶ ታከለ ኡማ የሰጠውን ገንዝብ በመጠቀም በሁሉም ረገዶች የተሟላ፣ ደረጃውን የጠበቀ፣ ቆንጆ እስቱዲዮ በቅርብ ጊዜ ይከፍታል፡፡ የሚዲያውን ሥራ ማስኬጃ ደግሞ የጭራቅ አሕመድ መንግስት በየጊዜው ፈሰስ ያደርግለታል፡፡ ከዚያም የኢትዮጵያዊነት አቀንቃኞች ነን የሚሉትን አማራ ጠሎች (ልደቱ አያሌው፣ ታምራት ላይኔ፣ ያሬድ ጥበቡ፣ ቴድሮስ ፀጋየ ወዘተ. ) በተደጋጋሚ እየጋበዘ በማር የተለወሰ መርዝ ላማራ ሕዝብ በየዕለቱ ይመግባል፡፡ ይሄን የሚያደርገው ግን የኢትዮ360 ታዳሚወችን ወደሱ በመሳብ ኢትዮ360ን ለማዳከም ሲል ብቻ ነው፡፡ እንዳሰበው ኢትዮ360ን ካዳከመ ደግሞ ግቡን ስለመታና ተልእኮውን ስለጨረሰ እውነትኛ ማነነቱን ገሃድ አውጥቶ ፀራማራነቱን በግለፅ ያውጃል፡፡ ጭራቅ አሕመድ አማራን አዳክሚያለሁ ብሎ በማሰቡ አሁን ላይ ፀራማራነቱ በግልፅ እንደተናገረ፣ ኤርምያስም ኢትዮ360ን ማዳከም ከቻለ ጊዜው ሲደርስ ኦነጋዊነቱን በግልፅ ይናገራል፡፡”
እነሆ፣ የኔ ጦማር በተጦመረ በነገታው አቶ ኤርምያስ ባፍቃሪ ወያኔ ሚዲያ ላይ ቀርቦ “ያማራ ከባዱ ቀወስና የመንግሥት አቋም” በሚል ርዕስ ካቶ ልደቱ አያሌው ጋር ተወያይቷል፡፡ ልበ በሉ፣ አቶ ኤርምያስ ኢትዮ360ን የለቀቀው “አማራ፣ አማራ አትበሉኝ” ብሎ ነበር፡፡ ከኢትዮ360 በለቀቀ ማግስት ግን አትበሉኝ ያለውን ማለት ጀመረ፡፡
አቶ ልደቱ ደግሞ ሲታሰር አማራነቱን የሚያጎላ ሲፈታ ወደ ወያኔና ወደ ኦነግ የሚሮጥ፣ የወያኔንና የኦነግን ጽንፈኞች እያወደሰ ያማራ ሕልውና ታጋዮችን የሚወቅስ፣ ትግሬነትንና ኦሮሞነትን እያገነነ አማራነትን የሚኮንን፣ ያማራ የሕልውና ትግል በተቀጣጠለ ቁጥር ትግሉን አቅጣጫ ለማስቀየር ሲል ብቻ ምንም ፋይዳ የሌላቸውን “አማራጭ ሐሳቦች” ይዞ ካደፈጠበት ብቅ የሚል፣ ኢትዮጵያዊነትን በመውደድ ሰበብ አማራነትን የሚጠላ፣ ባንደበቱ ለመናገር ፈሪ ቢሆንም በምግባሩ ግን የለየለት ፀራማራ የሆነ አሳሳች ግለሰብ ነው፡፡ በወያኔና በኦነግ የታሰረውና የሚታሰረው ደግሞ ያማራን ሕዝብ ለማታለል ሲል ካሳሪወቹ ጋር እየተመሳጠረ ባይሆን እንጅ ቢሆን አያስገርምም፡፡
ስለዚህም አቶ ኤርምያስና አቶ ልደቱ ባፍቃሪ ወያኔ ሚዲያ ላይ ቀርበው ያለ ልማዳቸው የአማራን ጉዳይ ነጥለው የተወያዩት ያማራ ጉዳይ አሳስቧቸው ሳይሆን፣ ከኢትዮ360 ጋር ርዕስ ለመሻማትና የኢትዮ360 ታዳሚወችን ልብ ለማሸፈት ሲሉ ብቻ ነው፡፡
አቶ ኤርምያስ ኢትዮ360ን ለማፍረስ በተሰጠው ልዩ ተልእኮ መሠረት አቶ ታከለ ኡማ በሰጠው ገንዘብ ይከፍታል ያልኩትን ሚዲያ ትናንትና (April 19, 2023) ከፍቷል፡፡ ልብ በሉ፣ አቶ ኤርምያስ ሚዲያውን የከፈተው ከኢትዮ360 ራሱን ካገለለ ሳምንት ባልሞላ ጊዜ ውስጥ ነው፡፡ ይህ የሚመሰክረው ደግሞ አቶ ኤርምያስ ኢትዮ360 ስለቅ በሐዘን ነው ያለው ውሸቱን እንደሆነ ነው፡፡ አለልክ መዋሸትና አለቅጥ ማጋነን ደግሞ አቶ ኤርምያስ ከወያኔ የወረሰው መቸም የማይለቀው ባሕሪው ነው፣ የወያኔ ጉዲፈቻ ነውና፡፡ ውሸቱን ባይሆንማ ስሜቱን ለማዳመጥና “ሐዘኑን” ለመወጣት ቢያንስ፣ ቢያንስ የወር ያህል የጽሞና ጊዜ ባስፈለገው ነበር፡፡ ያማራ የሕልውና ትግል በፍጥነት እየተቀጣጠለ ስለሆነ ግን፣ ኦነግና ወያኔ ጊዜ የላቸውም፡፡ ጊዜ ስለሌላቸው ደግሞ ላቶ ኤርምያስ ጊዜ ሊሰጡት አይችሉም፡፡ ዋና ጠላታችን የሆነውን ኢትዮ360ን ለማፍረስ የሰጠንህን ተልዕኮ ባስቸኳይ ጀምር የሚል ቀጭን ትእዛዝ ስለሰጡት፣ ሳምንት እንኳን ሳያርፍ ባስቸኳይ ጀምሯል፡፡
አቶ ኤርምያስ ትናንት ለከፈተው ሚዲያ ሥራ ማስኬጃ ጭንቀት የለበትም፣ በየጊዜው ፈሰስ ይደረግለታልና፡፡ ስለዚህም አቶ ኤርምያስ ኢትዮ360ን ቢቻል ጨርሶ ለመግደል፣ ባይቻል ደግሞ አለቅጥ ለማዳከም የተሰጠውን ተልዕኮ ለማሳካት የሚያስፈልገው፣ የሱ ሚድያ ብዙ ተከታይ እንዳለው በማሳየት፣ የኢትዮ360 ታዳሚወችን ቢቻል ጨርሶ ባይቻል ደግሞ አብዛኞቹን ወደሱ መሳብ ነው፡፡ ስለዚህም ዐዲስ የተከፈተውን ያቶ ኤርምያስን ሚዲያ በነቂስ ሰብስከራይብ (subscribe) እንዲያደርጉና አያሌ ተከታዮች ያሉት እንዲያስመስሉ፣ ኦነጎችና ወያኔወች ዲጂታል ሠራዊታቸውን በቅርቡ ያሰማራሉ ወይም ደግሞ ትናንትናውኑ (የኤርምያስ ሚዲያ በተከፈተበት ዕለት) አሰማርተዋል፡፡ ስለዚህም ያቶ ኤርምያስ ሚዲያ ሰብስክራይበሮች (subscribers) ቁጥር ባጭር ጊዜ ውስጥ ቢያድግና ቢመነደግ፣ የኦነግና የወያኔ የማጭበርበር አካል መሆኑን አገር ወዳድ ጦቢያውያን በተለይም ደግሞ ያማራ ሕዝብ አውቆ፣ እኛም አውቀናል ጉድጓድ ምሰናል ማለት አለበት፡፡
ያቶ ኤርምያስን ሚዲያ (ባጠቃላይ ደግሞ ኦነጋዊ እና ወያናዊ ሚዲያወችን) በማናቸውም መንገድ (በማየት፣ አስተያየት በመስጠት፣ ላይክ እና/ወይም ሰብስክራይብ በማደረግ ወዘተ.) የሚደግፍ አማራ፣ የወገኖቹን ማረጃ ሜንጫ፣ መግደያ ጠመንጃ ለመግዛት ገንዝብ እንዳዋጣ ሊያውቅ ይገባል፡፡ በቀጥታም ባይሆን በተጓዳኝ ወንጀል የፈጸመ (guilty by association) የወንጀለኞች ግብራበር ወንጀለኛ እንደሆነ መረዳት አለበት፡፡ የነዚህ ፀራማራ ሚዲያወች ዋና ዓላማ አማራውን በማር የተለወሰ መርዝ በየዕለቱ እየመገቡ በየዕለቱ መግደል መሆኑን መርሳት የለበትም፡፡ ባንድ ወቀት አቶ ኤርምያስ በውጭ አገር የባልደራስ ተወካይ ስለነበር፣ የአማራ ሕዝበ በማንነቱ ሊጨፈጨፍ እንደሆነ አስቀድሞ ባስጠነቀቀው በአስክንድር ነጋ ላይ ይህ ሁሉ መከራ የደረሰበት አንዱ ምክኒያት አሁን ላይ ገልፅ ሊሆንለት ይገባል፡፡
በመጨረሻም ምክር ቢጤ ለኢትዮ360ወች፡፡ በርናርድ ሻው (George Bernard Shaw) እንዳለው፣ ያሳማ ዋና ፍላጎት ተጨማልቆ ማጨማለቅ ስለሆነ፣ ካሳማ ጋር መታገል በጭራሽ አያስፈልግም፡፡ ስለዚህም አቶ ኤርምያስ ስለናንተም ሆነ ስለዝግጅታችሁ ያለውን ቢልም ንቃችሁ ተውት እንጅ መልስ እንዳትሰጡት፡፡ ካቶ ኤርምያስ ጋር አትካራ አትግጠሙ፡፡ ያቶ ኤርምያስ አንዱ ተልእኮ ሙሉ ትኩረታችሁን በጭራቅ አሕመድ ላይ እንዳታደርጉ መሆኑን አትዘንጉ፡፡ የጭራቁ እንጅ ያሳማው ጉዳይ አያስጨንቃችሁ፡፡ አሳማው የቆመው በጭራቁ ላይ ስለሆነ፣ ጭራቁ ጨርቅ ሲደረግ ያሳማው አረንቋ ስለሚደርቅ፣ ተጨማልቆ ማጨማለቁን ሳይወድ በግዱ ያቆማል፡፡
መስፍን አረጋ