April 16, 2023
16 mins read

የቹ ግዛት ዝንጀሮዎችና አዲስ አበባ — ፊልጶስ

oromo 2 1 1

ቅንድቤን ትላለች

————————–

ወይ አዲስ አበባ !——- የአፍሪካ መዲና፤

ወይ አዲስ አበባ !——-

የ’ኛ ሰው ከተማ – —

የዘመን ጉማጉግ—-የሀገር ገመና፤

በቁሟ  ግጠዋት- እርቃን -ገላ ቀርቷት

ህብርነቷ ጠፍቶ- በቁሟ ቀብረዋት፤

ምላሷን ቆርጠውት – አፏን ለጉመዋት

ለከንፈሯ ”ክልል” -”ሶስላ” ቀበተዋት

አልሞት ባይ -ተጋዳይ፣ አለሁኝ ለማለት፤—–

ኩሏን ተኳኩላ፣ ሙሾ እያወርደች

እንባዋን ጨርሳ፣ በልቧ እያነባች፤

በረገፈ ጥርሷ ፣ በድዷ እየሄደች

ዓይኗን አውጥተውት – ቅንድቤን ትላለች።—–

 

አዲስ አበባ በዚህ ከቀጠለች እንኳን የአፍሪካ፤ የኢትዮጵያ  ዋና ከተማ መሆኖ ተረት ሊሆን እየተቃረበ ነው።  ”አዲስ አበባ የኢትዮጵያዊነት ማሰሪያ ውል ናት!” የሚለው እውነታ፤ የኢትዮጵያዊያን የመከራ ቋት ወደሚለው ተቀይሯል።

በባለተረኞቹ ገዥዎቻችን ዘነድ የአዲስ አበባ ህዝብ ‘የአዲስ አበባ ህዝብ አይደለም ። መጤ ነው። ኗሪ ነው። ዜግነት የለውም። ማንኛውም የመኖር ሆነ የመስራት መቱ የሚወሰነው በተረኞቹ የኦነጋዊ ብልጽግና ገዥዎቻችን በጎ ፈቃድ ብቻ ነው። መጤ  መብት የለውም፤ መጤ ማለት ውጣ ሲባል የሚወጣ፣ ግባ ሲባል የሚገባ፤ የገነበው ቤት በላዩ ላይ የሚፈርስበት፣ በላቡ የሰበሰበው ኃብትና ንብረት የሚወረስበትና የሚዘረፍበት ፤ልጆቹ የገዥዎችን ቋንቋ ካልተማሩ (ቋንቋ መማር በግዳጅ  ወይም የሌለውን ቋንቋ ለማጥፋት እሰክ ካለሆነ ድረስ ጥቅም እንጅ ጉዳት የለውም።) በቀር  ከትምህርት ቤት የሚባረሩበት፤  በአጠቃላይ  ከሰው በታች ከሞቱት በላይ ”የአፓርታይድ” አገዛዝ  ውስጥ  ከወደቀ ዓመታትን አስቆጥሯል።

ግን እንዴት? የአዲስ አበባ ህዝብ ለዘመናት ተሳስሮና ተጋምዶ የኖረ፤  በኢትዮጵያ የፓለቲካ ትግል ውስጥ  ከአዲስ አበባ ዮኒቨርስቲ  ጀምሮ የአምበሳውን ድርሻ   የሚይዝ፣   በአንደነት በመታገል  ለሌሎች ከተሞችና አካባቢዎች  አርያ የነበረው ህዝብ፤ እንዴት ዛሬ  ኢትዮጵያዊነቱ ተገፎ፣ ማንነቱ ተዋርዶና ተንቆ፤  ልጆቹን በጅብ ሳይቀር  እያስበላ ለመኖር ፈቀደ?

እንዴት ሃይማኖቱንና አገራዊ የድል ቀኑን ማክበር እንኳን ተከለከል? እንዴት ሰንደቅ ኣላማውን እንኳን በመሰለው መልክ መጠቀም የሚያስገድለው ሆነ? እንዴት ከአገራችን ህዝብ ሁሉ ለዘመናዊነት  ለስልጣኔና መብቱን ለማስከበር ቅርብና ችሎታው ያለው በሚልዮን የሚቆጠር ህዝብ ፤ ከሌላ አካባቢ በመጡ ገዥዎች እንደ እቃ እየቆጠሩና እያንቋሸሹ ፤ በኑሮ ውድነት አይጠበሱ ሲገዙት አሜን ብሎ ተቀበለ??መልሱ ብዙ መመራመር የሚያስፈልገው አይመስለኝም ፤ ሶስት ምክንያቶች አሉ፤

1ኛውስለ አልተደራጀ

2ኛው / ስለ አልተደራጀ

3ኛውስለ አልተደራጀ

 

ታዲያ ዛሬ አዲስ አበቤ  በዚህ በሰለጠነ ዘመን ድህነትን አንደ ጫማው -ተጫምቶ፣ ግፍን እንደ ዕለት ጉርሱ -ጎርሶ፣ ዘረኝነትን እንደ ዓመት ልብሱ ለብሶ እያስተናገደና በየቀኑ እየሞተ፤ ገዥዎቻችንም የኢትዮጵያዊነትና የአንድነት ተምሳሌት የሆነውን ህዝብ ጎሰኝንትንና መንደርተኝነትን ሲገቱትና በአሸናፊነት ሲመጻደቁበት፤  የግፍ ጽዋው ሞልቶ መፍሰሱ ፤ ”ዩሊዝ ” የተባለ   የቻናዊያን  የጥንት ተረት ገላጭ ምሳሌ ነው።–

”—-በታላቋ ቻይና ቹ የምትባል ግዛት አለች። በዚች ቹ በተባለች  ግዛት ውስጥ ዞንግ የተባለ ሰው የብዙ መንጋ ዝንጀሮዎችን  ባለቤት ነበር። ዞንግ ሃብት ያካበተውና የሚተዳደረው ዝንጆሮዎቹን ወደ ጫካ በማሰማራት፤ እነሱ ለቃቅመው በሚያቀርቡለት ፍራፍሬና አትክልት ነበር። ስለዚህም በአካባቢው ሰው ” የዝንጆሮዎቹ ጌታ” ለመባል በቃ። በየቀኑ ማለዳ ላይ ዝንጀሮዎቹን ግቢ ውስጥ ይሰበስባቸውና ትዕዛዝ ይሰጣቸዋል። ፈርጣማውንና አለሁ  አለሁ ባዩን  ዝንጀሮ መርጦ በሌሎቹ ላይ  ስልጣን ይሰጠዋል። ፈርጣማዋ ዝንጀሮ ሌሎቹን በመምራት ወደ ጫካ ሄደው ፍራፍሬና አትክልት ለቅመው እንዲያመጡና እያንዳንዱ ዝንጀሮ ከሰበሰበ ላይ ከአሥር አንዱን እጅ ለጌታ ዞንግ መስጠት እንዳለባቸው ህጉ ያዛል። ህጉም ይፍርጸማል። ህጉን መፈጸም  የማይችል ዝንጀሮ ግን አይቀጡ ቅጣት ይቀጣል። ሁሉም ዝንጀሮዎች ኑሯችውን የሚገፋትበገባርነት፣  በስቃይና በግርፋት ነበር። ይሁን እንጅ እንዳቸውም የተቃውሞ ወይም የህግ ይሻሻልልን ድምጽ አሰምተው አያቁም።  ሁሉም በፍርሃት ቆፈን የተያዙ ነበሩ።

ሁሉም ዝንጀሮዎች ኑሮ ምሯቸው የሚያደርጉት በጠፋባቸው ሰዓት  አንድ ቀነ ከሁሉም ያነሰው ትንሹ ዝንጀሮ፤ ለመሆኑ ፍራፍሬዎችንና አትክልቶቹን የተከለው ጌታ  ንግ ነውን? ” በማለት ሁሉም ዝንጀሮዎች በተሰበሰቡበት ጠየቃቸው ።

”ዞንግ አልተከላቸውም ፤ በተፈጥሮ የበቀሉና ያደጉ ናቸው።” አሉት።

”ካለ ዞንግ ፈቃድ ፍራፍሬዊችንና አትክልቶችን መውሰድ እንችልምን?” ሲል በድጋሜ ትንሹ ዝንጀሮ ጠየቃቸው።

ሁሉም ዝንጀሮዎች ተያዩና ” አዎ !—- እንችላለን።” በማለት መለሱለት።

ትንሹ ዝንጀሮ ግን ጥያቄውን በመቀጠል ”ታዲያ ለምንድነው በጌታ ዞንግ እጅ ላይ የወደቅነውና እሱን የምናገለግልው፤ ብሎም የሚያሰቃየን—?” በማለት ንግግሩን ሊቀጥል ሲል ሁሉም ዝንጀሮዎች ሚስጢሩ ተገለጸላቸው፤  ከተኙበት የዘመናት እንቅልፍ ባነኑ።

‘በዕለቱ ማታ ዝንጀሮዎቹ ተመካከሩ ፤ ስለሚወስዱት እርምጃም እቅድ አወጡ። እናም  በእቅዳቸው መሰረት  ጌታ ዞንግ እንቅልፍ ሲወስደው የታጎሩበትን በረት ሰባበ። ግቢውንም በሙሉ አፈራረሱ። የጌታ ዞንግ ንብረት የነበረውንና ለዘመናት ያከማቸውን፤ በእነሱ የሰበሰቡትን ፍራፍሬና አትክልት በሙሉ  ጠራርገው በመውሰድ የሚችሉትን ያህል በመያዝ ወደ ገደላቸው ሄደው ገቡ።  ከዚያም በኋላ አልተመለሱም፤ እነሱም በሰላምና በደስታ መኖር ጀምሩ። ጌታ ዞንግም በድህነት ኖሮ-በድህነት ሞተ።’–‘

የዘመኑ ገዥዎች የአዲስ እበባን ሃብት፣  የአዲስ አበባ መሬት ፤ በአጠቃላይ ሳርቅጠሉ ሳይቀር ”ፊንፊኔ ኬኛ ” አሉት ።  ዞንግ   ለዝንጀሮዎእቹ የፈቀደላቸውን ”ከአስር እንድ እጅ”  እንኳን አልተፈቀደላቸውም። ህዝብም እንደ ዞንግ ዝንጀሮዎች ”የአፓርታይደን” ኑሮ ተቀብሎና ህብትና ንብርተቱን እያሰረከበ ፤  በፍርሃትና በሞት ጥላ ውስጥ ግዜውን ይገፋል።  የራሱ ሃብትና ንብረት እየዘረፋ በህዝብ መሃከል ቅራኔና ጥላቻ ለመስፋፋት ”ከዘመናት በፊት ለተበደለው ወገንናቸው”  አከፋፈሉት ፤ ተከፋፈሉት። በአሁን ሰዓት በመቶ ሺዎች የሚቆጥሩ ዜጎች ቤት አልባ መሆናቸው ስላለበቃ፤  የሚያሰጠጋቸውም እንድይኖር ተረኞቹ ህግ አውጥተዋል። ህዝብ  የመንቀል ተግባሩም   ተጧጥUፏል።  የአዲስ አበባ ህዝብ  ከ’ርስቱ እንዲነቀል ወንጀል ሆኖ የተቆጠረበት ደግሞ ኢትዮጵያዊነቱ ነው።  ገጣሚው እንዳለው፤

በሕልም ተበድለው  በውን ተበቀሉ

ግራር ይተክላሉ ሰው እየነቀሉ።

በኦሮሞኛ እንድ እባባል አለ፤ ” ዳገቱን መውጣት ካቃተህ በቁልቁለቱ ተንደርደር።” ይላል።  የጠ/ ሚ አብይ አህመድ አገዛዝ   የሁላችንም  መዳኛ የሆነውንና ይሰብክ  የነበረው  ኢትዮጵያዊነት  ዳገት ሆኖበት፤  ቁልቁለቱን እየተደረደር ነው። ከዳገት ወድቆ በቁልቁለት የሚንደረደር ድግሞ ያገኘውን ሁሉ ማፈረርሱና  ማውደሙ ግልጽ ነው።

እንግዲህ የአዲስ አበባ ብሎም የኢትዮጵያ ህዝብ- ከዚህ የበለጠ ስቃይና መከራ አለወይ? ብሎ መጠየቁ ተገቢ ነው። እንደ ቹ ግዛት ዝንጀሮዎች’፤”ለመሆኑ አዲስ አበባ የማናት? ብለን ራሳችን እንጠይቅ። በላቡና በጥረቱ ያፈራውን የራሱን ሃብት ዘርፈውና   በ ሺ ዎችን አፈናቅለው፤ በዓል በመጣ ቁጥር ” መዕድ መጋራት ”እያሉ  ሲመጽደቁና የአዞ እምባ ሲያንቡ፤ ለመሆኑ ”መዕዱ የማነው?” ብለን እንጠይቅ ።   ርስ-በርስ ባለመተማመንና በፍርሃት የተዋጠን ይመስላል። ፍርሃት ደግሞ ውርደትንና ውድቀትን እንጅ ነጻነትንና መከበረን  አያወጣም።

ፈሪዎች ሳይሞቱ፣ ሲሞቱ ሲኖሩ መልሰው መላልሰው ጀግና ግን፣ የሞቱን  የሞተለታ  ነው  ጣዕሙን  የሚቀምሰው።  (ሼክስፒር/ ትርጉም ተገኘ በቀለ)  የተባለ ያለ ምክንያት አይደልም።

ለቅሶና በዋይታ ወይም የፊስ ቡክና የዩቲዮብ ጫጫታ  ቤታችን ካላያችን ላይ ከመፍረስ፤ ልጆቻንና አዛውቶች መጥጊያ ከማጣት፣ እምቦቀቅላ በጅብ ከመበላት አላዳነም።  ትላንትም ሆነ ዛሬ  ነገም ያለው እውነታ ፤  በየቦታው እንደ አቅማችንና እንደ ችሎታችን ተደራጅተን፣ መሪና ተመሪ በመሆን፤ ታግለን በመታገልና የሚያስፈልገውን መሰዋአትነት ከከፈል ብቻ ነው፤  አዲስ አበባን እስከ ማንነትቷ ልንታደግታና መብታችን ልናስከብር የምንችለው። የትግልን አስፈላጊነት ደግሞ ወርሃ  ሚያዝያ  ተምሳሌትነት አለው። ዓምላካችን ከርስቶስ ከሰይጣን ጋር ታግሎ  ያሸነፈበትና ሰይጣንን ወደ ጥልቁ የወረውረበት ነው።

ከዘመኑ የጎሰኝነትና የመንደርተኝነት  የነቀርሳ በሽታ ራሳችን አጽድተን፤  ተደራጅተንና አደራጅተን ከታገልን፤

የሁላችን አዲስ አበባ፣ ሁሉም ዜጎቿ ልዕልነዋ በተከበረ ኢትዮጵያ፣  በፍትህ፣ በእኩልነትና በባለቤትነት የምንኖርበት የ’ጋራችን ሀገር፣ በጋራ ኃላፊነት  እንገነባለን።  ምክን\ ያቱም  እውነትና  ኢትዮጵያዊነት ከኛ ጋር ነውና። ምክንያቱም  የኋላ-ኋላ ኢትዮጵያና ኢትዮጵያዊነት አሸናፊ ነውና።

 

ኢትዮጵያ ለዘላለም ትኖራለች!!

———-//——-ፊልጶስ

ሚያዚያ/ 2015

e-mail: [email protected]

Leave a Reply

Your email address will not be published.

Latest from Blog

ከሃይለገብርኤል   አያሌው የኦቦ ሲራጅና የወይዘሮ ፉንታዬ ልጅ ጃዋር መሃመድ ትላንትን ዛሬንና ነጋችንን ሊያሳይ የሚችል መጽሃፍ አዘጋጅቶልናል:: በእውነቱ መጽሃፉ ሊነበብ በሚችል የሃሳብ ፍሰት ተቀንብቦ በአነጋጋሪነቱ ቀጥሏል:: ጃዋርን እና የቄሮን ትውልድ በቅጡ ለመረዳት መጽሃፉ ማንበብ

የጃዋር የፖለቲካ ጅዋጅዌ! “ድመት መንኩሳ አመሏን አትረሳ’’

ጥር 2 ቀን 2017 ዓ/ም   January 10, 2025  በኢትዮጵያዊነታችሁ፡ በኦርቶዶክሳዊ እምነታችሁ፡ በአማራነታችሁ፡ በአማረኛተናጋሪነታችሁ፡ በተሰነዘረባችሁ ብትር፡ ቤተ ሰብ፡ ወዳጅ ዘመዶቻችሁን ያጣችሁ: ልጆቻችሁን የቀበራችሁ፡ አካልችሁን ያጣችሁ፡ የተሰነዘረውን ብትር በመከላከል ላይ ያላችሁ፡ያለፈቃዳችሁ በመንግሥት ተጽእኖ ወደመግደልና

በኢትዮጵያዊነታችሁ፡ በኦርቶዶክሳዊ እምነታችሁ፡ በአማራነታችሁ፡ በአማረኛ ተናጋሪነታችሁ፡ በተሰነዘረባችሁ ብትር፡

January 10, 2025
መኮንን ሻውል ወልደጊዮርጊስ ¹⁵ የምድርም ነገሥታትና መኳንንት ሻለቃዎችም ባለ ጠጋዎችም ኃይለኛዎችም ባሪያዎችም ጌቶችም ሁሉ በዋሾችና በተራራዎች ዓለቶች ተሰወሩ ፥ ¹⁶ ተራራዎችንና   በላያችን ውደቁ በዙፋንም ከተቀመጠው ፊት ከበጉም ቍጣ ሰውሩን ፤ ¹⁷ ታላቁ የቁጣው ቀን  መጥቶአልና ፥ ማንስ ሊቆም ይችላል ? አሉአቸው ። ራእይ 6 ፤  15_17 ይኽ የመጽሐፍ ቅዱስ ቃል ። የኢየሱስን ልደት ሰናከብር የየሐንስ ራእይን ማንበብ ጠቃሚ ይመስለኛል ። ምክንያቱም በመጨረሻው ዘመን

ከኢየሱስ የፍርድ ቀን በፊት በህሊናችን ውስጥ ፍቅርን ለማንገስ እንጣር 

የምጣኔ ሀብታዊ ፍጥ፣ የፖለቲካ፣ የእውነትና የሰብአዊ መብት ታጋይ፣ የአመኑበትን ነገር ለመናገር እንደ ፖለቲከኛ በቃላት ሳያሽሞነሙኑ ቀጥታ የሚናገሩት የሀገሬ ኢትዮጵያ ታላቅ ሰው ነበሩ “ዘር ቆጠራውን ተዉት፤ የአባቶቻችሁን ሀገር ኢትዮጵያን አክብሩ!”  አቶ ቡልቻ ደመቅሳ

ሀገር ወዳዱ አቶ ቡልቻ ደመቅሳ ከዚህ አለም በሞት ተለዩ

January 6, 2025
ግን ይህ ሁሉ ወጣት የት ገባ? ግን ይህ ሁሉ ወጣት የት ገባ? ዛሬ፣ 2025 ዓ/ም ላይ ብንገኝም በዝንጋታ ገመድ ወደ ሞት እየተጎተትን እንደሆነ አናውቅም። (ሁል ጊዜ የሚሞተው የገነዝነው ይመስለናል። ) “ገብርዬ ነበረ

ግን ይህ ሁሉ ወጣት የት ገባ?

January 3, 2025
Go toTop