April 4, 2023
5 mins read

የአብይ የጎርጎራው ጉዞ ሽፋን ናት – መሳይ መኮነን

Gorgora ጎርጎራ 1 3
#image_title

ዓላማው የኦሮሚያ ብልጽግናን የእውር ድንብር ሽምጥ ግልቢያ አሜን ብላችሁ ተቀበሉ ዓይነት መዳረሻው የሆነ ጥብቅ ውይይት ለማድረግ ነው። ሰውዬው የበሰበሰ ዝናብ አይፈራም ውስጥ ዘው ብሎ ገብተው እየተንቦራጨቁ ነው። በመላው ኦሮሚያ ሰልፍ አስወጥተው እሳቸው ባህር ዳር ላይ ”እንግዲህ በኦሮሞ ዓይን ከመጣችሁ ጫፌን መንካት ትችላላችሁ። እኔ ተነካሁ ማለት ይህ የምታዩት ማዕበል ፋሲል ቤተመንግስት ለመድረስ 24 ሰዓት አይፈጅበትም” የምትል ፍርሃት ወለድ ማስፈራሪያ ለማሰማት ተዘጋጅተዋል። እያበቃ ያለው ሳምንት የሰውዬውን እውነተኛ ቀለም ከምን ጊዜውም በላይ ፍንትው አድርጎ አውጥቷል። ጭምብላቸው ወልቆ የተደበቀው ማንነታቸው ዕርቃኑን አደባባይ ላይ ተሰጥቷል። በተለይ ”እኛ ኦሮሞዎች ኢትዮጵያን አናፈርስም። ማፍረስ ከፈለግን ደግሞ የሚያቆመን ሃይል የለም” የሚል ንግግር በፓርላማ ካሰሙ በኋላ አንደኛውን በስብሰናል፡ ዶፍ በሆነ ዝናብ ውስጥም መራመድ እንችላለን እያሉ ናቸው።

እነጌታቸው ረዳ ያልተቀደሰው ጋብቻ ላይ ከታደሙና ጫጉላ ሽርሽሯንም ከአቶ ሽመልስ ጋር ካሳለፉ በኋላ ወደ መቀሌ ተመለሰዋል። በዚህ ሳምንት የሁለት ዓመቷን በጀት ከድጎማዋ ጋር ይልፋሉ ተብሎ ይጠበቃል። ጠ/ሚሩ ባህርዳር ላይ የአማራ አመራሮችን በስብሰባ ሲጠምዱ የእሳቸው የነፍስ አጋር፡ የሚስጢራዊ ፕሮጀክቶች ተባባሪ አዘጋጅ የሆኑት አቶ ሽመልስ አብዲሳ ደግሞ ከህወሀት ጋር የተጀመረውን ልዩ ግንኙነት መልክ በማስያዝ ላይ እረፍት አጥተው ሰንብተዋል። የባህርዳሩም ሆነ የአዲስ አበባው የሁለቱ የኦሮሚያ ብልጽግና መሪዎች ዓላማ ከዚህ በፊት እንደነበረው ኮንቪንስ ወይም ኮንፊውዝ አይደለም። ዓይን ያወጣ የበላይነት ጥማችንን ከዳር ለማድረስ በጀመርነው ጎዳና ላይ እንቅፋት አትሁኑብን የሚል ግብና ተልዕኮ ያለው ነው። እንቅፋት ከሆናችሁ ሀገሪቱን ”ዝናብ ያበላሸው ሰርግ” እናስመስላታለን የምትልም ማስፈራሪያ ታክሎበታል።

ጠ/ሚሩ ጓዛቸውን ጠቅልለው የጎሳ ፖሊቲካ ውስጥ ከገቡ ሰነባብተዋል። ሰሞኑን ‘ምን ታመጣላችሁ’ ብለው በአደባባይ ስለማን እስከቀራኒዮ ድረስ እንደሚዋደቁ በግልጽ ነግረውናል። ከዚህ በኋላ እሳቸውን የኢትዮጵያ ዋስና ጠበቃ አድርጎ የሚያምን ሰው ካለ ጤንነቱን በጊዜ ይፈትሽ። የነገውን ሰልፍ ሲያስጠሩ ዓላማው ግልጽ ነው። እኔ የምሞትለትና ለእኔ የሚሞትልኝ ብሄር አለኝ ነው መልዕክቱ። በበቀደሙ የፓርላማ ውሏአቸው ‘ስልጣን ልቀቅ’ ተባልኩኝ ብለው በንዴት ጦፈው፡ እጅግ አሳፋሪ የሆነ የፊዚክስ (እሳቸው የማቲማቲክስ ቢሉትም’) ቲዮሪ አንስተው ፡የብሄር ካርድ በመምዘዝ ሲጫወቱ ቀጣዩ አካሄዳቸው ምን ሊሆን እንደሚችል መገመት አይከብድም ነበር።

ሰውዬው አሁን ፍጥነት ላይ ናቸው። ፍሬን የበጠሰ መኪና ሆነዋል። በግንድም፡ በድንጋይም፡ ብቻ በሆነ ሃይል ማስቆም ካልተቻለ በዚህ ፍጥነታቸው የሚያደርሱት ጉዳት በቀላሉ የሚቀለበስ ላይሆን ይችላል። ችኩልነት + ሴራ + ጥራዝ ነጠቅ እውቀት + ዘረኝነት + የአቅም ማነስ + ስልጣን ተደማምረው ተነስተዋል። ፊት ለፊት ያገኘውን ሁሉ እየጠረማመሰ ነው። ገደሉ ሩቅ አይደለም። ፍሬን የበጠሰው መኪና ግስጋሴው ወደዚያው ነው። በቶሎ የምናስቆመው እንዴት ነው? የሚለው አብዝቶ የሚያስጨንቀን፡ የጊዜው አንገብጋቢ ጉዳይ ነው።

 

Gorgora (ጎርጎራ)|Amhara Region (አማራ)|City Gallery

https://www.skyscrapercity.com/threads/gorgora-%E1%8C%8E%E1%88%AD%E1%8C%8E%E1%88%AB-amhara-region-%E1%8A%A0%E1%88%9B%E1%88%AB-city-gallery.1075467/

2 Comments

  1. መፍትሄው ጊዜ ሳይባክን የተበተነውና ያልተደራጀውን ኢትዮጵያዊነት መሰብሰብ ብቻ ነው:: ይህ ሀይል ቢሰበሰብ ትልቅ የማይገፋ ተራራ ይሆናል:: ከጎሳ የፀዳ ኢትዮጵያዊነት በሁሉም ክልል እጅግ ብዙ ህዝብ አለ:: አልተቆጠረም: አባት ወያኔ ልጅ ብልፅግና ከጎሳና ዘር ፖለቲካ ብዙም አንጠብቅ

  2. ጥሩ አማካሪ ጥሩ ተላላኪ ተሿሚዎች እና ሹመቶችን እየታዘብን ነው ! ግን ጠቅላይ ሚኒስትሩ ደግመው ደጋግመው ከዚህ አደገኛ የተባነበት የተሰለቸ የፖለቲካ ቁማር ጨዋታ ወጥተው ጥሩ የሀገር መሪ ቢሆኑ ብለን እንጠይቃለን !! ዘመነ ስልጣናቸው በደም የተጨማለቀ ሰላም የጠፋበት : የኢትዮጵያ ራስ ምታት የዜጎች ተስፋ እና እምነት የራቀው መሆኑ ግልፅ እየሆነ መጥቷል !! ስለዚህም ….

Leave a Reply

Your email address will not be published.

ረ/ፕሮፌሰር ሲሳይ አውግቼው በምሽት 4:00 ላይ ከመኖሪያ ቤቱ ለጥያቄ ትፈለጋለህ ተብሎ ተወስዷል። እስካሁን ያለበት ስፍራ አልታወቀም!
Previous Story

የአማራ ሕዝብ ከዘረኛው አገዛዝ ጥቃት ለመዳን ፕላን ቢ አለው?

Getachew and maferiaw Abiy 2 1 1
Next Story

“ከዚህ በኋላ ልዩ ኃይል የሚባል ነገር አታስቡት!” ዐቢይ | የአማራ ልዩ ኃይልን ለማፍረስ የኦህዴድ እና የትህነግ ሰዎች ለምን ወሰኑ?

Latest from Blog

“መነሻችን እዚህ መዳረሻችን እዚያ” የሚለው የዲያስፖራ ከንቱ አታካራ! – ክፍል ሁለት

በላይነህ አባተ (abatebelai@yahoo.com) በአንዳንድ ስብሰባዎችና የሕዝብ መገናኛ መድረኮች የሚታየው የአንዳንድ ዲያስፖራዎች  “መነሻችን እዚህ መዳረሻችን እዚያ” የበከተ ከንቱ አታካራ በልጅነታችን ወላጆቻችን ትምህርት እንዲሆነን ይተርኩልን የነበረውን ከጫጉላ ወጥተው ጎጆ ለመመስረት የታከቱ ሁለት ያልበሰሉ ባልና ሚስትን ታሪክ

መነሻችን አማራ መድረሻችን አማራ እና ወያኔያዊ መሠረቱ

የማይወጣ እንጀራ ከምጣዱ ያስታውቃል። የዛሬን አያድርገውና የትግሬ ልሂቆች “ትግራይ የጦቢያ መሠረት ናት ።  ጦቢያ ያለ ትግራይ፣ ትግራይ ያለ ጦቢያ ሊታሰቡ አይችሉም” በማለት ጦቢያዊ ከኛ ወዲያ ላሳር እያሉ አለቅጥ ይመጻደቁ፣ ይኩራሩ፣ ይታበዩ ነበር። ወያኔ

አቶ ታዲዮስ ታንቱ በተከሰሱባቸው ወንጀሎች ጥፋተኛ ተባሉ

ለአመታት በእረስር ላይ የሚገኙት  አቶ ታዲዮስ ታንቱ በተከሰሱባቸው የጥላቻ ንግግር ማሰራጨት እና የዕርስ በዕርስ ግጭት መቀስቀስ ወንጀሎች ጥፋተኛ መባላቸው ታውቋል፡፡ አቶ ታዲዮስ ታንቱ በተከሰሱበት ክሶች በዛሬ ቀጠሮ የጥፋተኝነት ፍርድ የሰጠው የፌደራል ከፍተኛ

ከ”ችርቻሮ” ድል አልፎ ለመሄድ የአንድነት አስፈላጊነት – ግርማ ካሳ

በአሁኑ ጊዜ ሁለት የፋኖ አሰላለፎች አሉ:: መኖር ያልነበረበት:: አንከር ሜዲያ ከሁለቱም አሰላለፎች፣ ሁለት ፋኖ መሪዎች ጋር ቃለ ምልልስ አድርጋለች፡፡ ሁለቱን አደመጥኩ፡፡ በሰማሁት ነገር ተደስቻለሁ:: ትልቅ ተስፋ እንድሰንቅም አድርጎኛል:: የአማራ ህዝባዊ ድርጅት የፖለቲካ
Go toTop