March 22, 2023
16 mins read

የአብይ አህመድ የመደመር ትውልድ የመጽሐፍ ምረቃ እና ያደረጋቸው አፍራሽ ንግግሮች –  በሽፈራው ዘውዴ

አፍራሽ ገቢር አንድ፡- ስልጣን አልለቅቅም

ዩትዩብ ላይ የምፈልጋቸውን ቪድዮችን ስፈልግ ድንገት ማስታወቂያውን አየሁትና ይህ ሰውዬ ደግሞ ምንድን ብሎ ነው የሚሰከስከው ብዬ አለፍ አለፍ አድርጌ ተመለከትኩት፡፡ በንግግሮቹ እጅግ አፍራሽ ነገሮችን አዳመጥኩ፡፡ እናም እንደ ሁልገዜው ዝምብየው ላልፈው ነበር፡፡ እንዲህ እየቀለደ እስከ መቼ ነው የሚኖረው? በሀገር እና በሕዝብ ላይ እንዲህ እያፌዘ እና ይህን ሁሉ ጥፋት እና በደል እያደረሰ እስከ መቼ ነው የሚቀጥለው? እንደተለመደው ይሰክሳል (He sucks! He sacks!) ቪድዮውን ሙሉውን ለመመልከት ትግዕስቱም ጊዜውም አልነበረኝም፡፡ ይሁን እንጂ አለፍ አለፍ አድርጌ ሳዳምጠው የሰማኋቸውን አፍራሽ ነገሮች ላጋራችሁ፡፡ ምናልባት ወደፊት ለሕዝባዊ የጋራ መግባባት እና መነሳሳት እና የሰውየውን ክፋት ለማጋለጥ ስል ወደፊት ሙሉን ቪድዮውን ላዳምጠው እችላለሁ፡፡ እናም መስመር በመስመር እየተከተልኩ ክፋቱን ተንኮሉን ሴራውን የውስጥ ፍላጎቱን ላጋልጠው እችላለሁ፡፡

አብይ እንዲህ ይጀምራል፡- “የሽግግር መንግስት የሚሉ አሉ….ገና ሶስት ዓመት ይቀረኛል…..እግረ መንገዴን ይህ እንደማይሳካ ላረጋግጥላችሁ እወዳለሁ፡፡”

ሰዎች በ45 ቀን ስልጣናቸውን በሚለቁበት ዓለም ይህ ሁሉ ግፍ እና በደል አረመኔያዊ ጭካኔ ያለማቋረጥ ለአምስት ዓመታት በመላ ሀገራችን እየተፈፀመ ስልጣኔን አልለቅቅም ቁርጣችሁን እወቁት ማለት ምን ማለት ነው? በፖለቲካዊ፣ በኢኮኖሚያዊ እና በማህበራዊ በሁሉም ዘርፎች ሀገሪቱ እጅግ ከፍተኛ ቀውስ ውስጥ ገብታ ሳለ የአስተዳደሩ ኢ-ውጤታማነት ተረጋግጦ ሳለ ስልጣን አልለቅቅም ማለት ምን አይነት አምባገነንነት እና ምን አይነት የስልጣን ጥም ነው? ይህ ሁሉ ድንፋታ እና ፉከራስ ምን ይሉታል? ከዚህ ንግግሩ የተዳሁት ነገር ቢኖር አብይ ከሶስት ዓመት በኋላም ስልጣን እንደማይለቅ ነው፡፡ በማጭበርበርም ይሁን በጉልበት ጦርነት ገጥሞም ቢሆን በስልጣን ላይ መቀጠል እንደሚፈልግ ግልፅ አድርጓል፡፡ ይህንንም ያረጋገጠው በዛቻ እና በማስፈራሪያ ጭምር ነው፡፡

“ኮንትራት አለኝ” መለስም ይለው የነበረ ነገር ነው፡፡ የአፍሪካ አምባገነን መሪዎች ምርጫን እንደ ሕጋዊ በስልጣን መቆያ መንገድ ያደርጉታል—ሕዝባዊ ጥቅሞች ሳይሰጡ—ወንጀል እና በደል እየፈፀሙ፡፡ ምርጫን እያጭበረበርክ እያለፍክ በየጊዜው “የታደሰ ውል አለኝ” ማለት በአፍሪካ የተለመደ ግን የተሳሳተ አስተሳሰብ እና አካሄድ ነው፡፡ ሕዝባዊ አቅም ስለጠፋ እንጂ የማይሆን ተግባር ከሰራህ ወይም ኃላፊነትህን ካልተወጣህ በአንድ ቀንም ቢሆን ከስልጣን ትባረራለህ፡፡ የኛው ጉድ ግን ይህ ሁሉ ጥፋት እና በደል ከደረሰም በኋላ ገና ሶስት ዓመት ይቀረኛል ከዚያ በኋላም ይለናል፡፡

ወያኔ በመላ ሀገሪቱ ንጹሃንን ሲያስገድል፤ ከተሞችን ሲያወድም፤ ሕዝባዊ ሰላምን ሲያውክ፤ ምስራቁ የሀገሪቱ ክፍል እንዲገነጠል በትብብር ሲሰራ፤ ከፍተኛ ወታደራዊ ዝግጅት ሲያደርግ…. ይህ ድርጅት አንድ ነገር ይባል ብለን ብንጮኽ እያጃጃለን ዝም አለን፡፡ ይልቁንም ለሴራው በደሉን ሁሉ ወያኔ ላይ እየደፈደፈ ኃላፊነቱን ባለመወጣት ምናልባትም በመተባበር ለአቤቱታችን ሁሉ ለጥያቄያችን ሁሉ ጆሮ ዳባ ልበስ አለን፡፡ ወያኔ እርምጃ እንደሚወስድ እየታወቀ ሕጋዊ ኃላፊነቱን ባለመወጣት በአንድ ቀን ብቻ አስር ሺህ የኢትዮጵያ መከላክያ አባላት ኢትዮጵያዊያን እንዲያልቁ አደረገ፡፡ ይህም አልበቃው ብሎ ሁለት ሶስት ጊዜም የኢትዮጵያ ሰራዊት መሰዋዕት ከፍሎ ከያዘው ቦታ “ውጡ” እያለ ከፍተኛ ጥቃት እንዲደርስበት አደረገ፡፡ ሀገር እና ሕዝብ እንዲወድም አደረገ፡፡ ወያኔ ሊሸነፍ እና ሊደመሰስ ሲመስለው ጦሩን ያስወጣል፡፡ አሁንም በብዙ መሰዋትነት ከያዘው ቦታ÷ ከስምምነቱ ውጭ÷ መከላክያው ትግራይን ለሕወሓት አስረክቦ ባዶ እጁን እንዲወጣ አድርጓል፡፡ እናም የኢትዮጵያ መከላክያ የሚጠቃበትን ቀን እየቆጠረ ነው፡፡ ያዋረድህን አለቃ እንድትጠፋ ያደረገህን አለቃ ትቀይራለህ ወይስ ውድመትህን ትቀጥላለህ? ይህን የምታደርገው ሕዝቡን ለመታደግ ብቻ ሳይሆን ራስህንም ለመታደግ ነው፡፡

ሰውዬው ቴሌቭዥን ላይ ወጥቶ እኔ ከስልጣን የምለቅ ከሆነ በመቶ ሺህዎች የሚቆጠሩ ሰዎች በአንድ ቀን ይገደላሉ አለን፡፡ ይኼኔ ደፈር ብለን ከቤተ መንግስት አውጥተን አማኑኤል ልናስገባው ሲገባን ዝም ስንለው የልብ ልብ ተሰምቶት በየጊዜው በመቶዎች የሚቆጠሩ አማራዎችን በወለጋ ያስገድላል፡፡ ይህ ሰው ነው ስለ መደመር ስለ አንድነት የሚያወራን፡፡ የስልጣን ፍርሃቱን እና ስጋቱን የአማራውን ሊህቅ “ወደ እኔ ብትመጣ” በማለት በፍርሃት ተሸብቦ እንዲቀመጥ ንፁሃንን ያለ ርህራኄ ያስገድላል፤ ያፈናቅላል፡፡ ባያውቀው ነው እንጂ ወደ ስልጣን ያመጣው የደገፈው አማራው ነበር ምክንያቱም ሀገሩ ተመልሳ ታላቅ እንድትሆን ስለሚፈልግ ሁሉም ኢትዮጵያዊያን በእኩልነት እና በሰላም የሚኖሩባት ሀገር እንድትኖር ስለሚፈልግ፡፡ እርሱ ግን የሚናገረው እና በውስጡ የሚያምነው ሊያደርገው የፈለገው የተለየ ስለነበር አማራውን ማጥቃት እና ማዳከምን ያዘ፡፡ አብዛኛው የኢትዮጵያ ሕዝብ ኢትዮጵያን እንድሚፈልግ አሳይቷል፡፡ ሀገሩን ያዋረደበት በብሔር ከፋፍሎ ያባላው የነበረው የኢህአዴግ አገዛዝ እንዳንገሸገሸው ማረጋገጫ ሰጥቷል፡፡ ጠንካራ ሕዝባዊ አንድነት እና ጠንካራ ሕዝባዊ መንግስት እንደሚፈልግ አሳይቷል፡፡ ነጻነት፣ እኩልነት፣ ፍትህ፣ ዴሜክራሲ እና ልማት እንደሚፈልግ አሳይቷል፡፡ ተኩላው ግን ጥያቄያችንን አውርዶ አውርዶ ታች አድርሶታል፡፡

አብይ የወያኔ ዲቃላ ነው፡፡ የወያኔ ማደጎ ነው፡፡ በወያኔ እጅ እና ትምህርት ያደገ ሰው ነው፡፡ ብዙ ተስፋ ልንጥልበት አይገባም ነበር፡፡ ከዘረፈን፣ በሀገራችን ባይተዋር ካደረገን፣ ሀገራችንን ካዋረደ፣ ብሔራዊ ጥቅሞቿን ለባዕዳን አሳልፎ ከሰጠ፣ መልዕክቶቿን ከነቀፈ፣ ታሪኮቿን ካዋረደ፣ ተቋሞቿን ካወደመ፣ ሕዝቧን ካደኽየ የፓርቲ ስብስብ ላይ እምነታችንን መጣል አልነበረብንም፡፡ አብይ የሚፈልገው ልክ እንዳሳዳጊዎቹ ማድረግ ነው፡፡ መለስ እና ፓርቲው ይለን እንደነበረ አንዴ “ኮንትራት ተሰጥቶኛል” ሌላኛ ጊዜ “ሜዳውም ፈረሱም ያው” ከቻልክ በጦርነት ገጥመህ ስልጣኔን ውሰድ አብይ የደገመውም ያደረገውም ይኼንኑ እና ያንኑ ነው፡፡ በዚህ የመጽሐፍ ምረቃ ላይ በሌሎች መድረኮችም በፓርላማም ጭምር የነገረን ስልጣን እንደማይለቅ ነው፡፡ ችለነው ታግሰነው እንድንኖር እያለማመደን (Condition) እያደረገን ነው፡፡

አብይ ፓስተር ነው፡፡ ፓስተር የነበረ ሰው ነው፡፡ አብዛኞች የኢትዮጵያ ፓስተሮች ውሸታሞች፣ አታላዮች፣ ጥቅመኞች፣ የሃይማኖተኝት ባህሪ የሌላቸው፣ የሀገራቸውን ፍላጎት ለባዕዳን ሀገሮች አሳልፈው የሚሰጡ በሀገራቸው ላይ የሚዶሉቱ ሰዎች ናቸው፡፡ የምዕመኖቻቸውን አእምሮ በስልት በማጠብ የማይሆኑ ተግባራትን እንዲያደርጉ የሚያስገድዷቸው ናቸው፡፡ ከሰውነት ሳይቀር ሲያዋርዷቸው አይተናል? ምን ቢያደርጋቸው ነው ብለን ተደንቀን እናውቃለን? ኢትዮጵያዊያንን እንዲህ መቀለጃ ያድርጉን ብለን ተቆርቁረን እናውቃለን፡፡ ብዙ ፓስተሮች በሃይማኖት ስም በእግዚአብሔር ስም ሰዎችን ሲያጃጅሉ እና ወንጀሎችን ሲፈፅሙ አስተውለናል፡፡ አብይ በፖለቲካው መድረክ የደገመው ይሄንን ነው፡፡ በዚህ ንግግሩ የተረዳሁት ከላይ ከላይ የማታላዩን የማስመሰያውን ለእውነተኛ ደጋፊዎቹ እና ተከታዮቹ አብረውት ለሚሰሩት ደግሞ እውነተኛ ውስጣዊ መልዕክቱን ያስተላለፈበት ነው፡፡ በሃይማኖት ቦታዎች ሕዝቡን ሲያሳብድ ሲያታልል እንደነበረው በዚያ ስለለካን ባገኘው ልምድ መላ ኢትዮጵያዊያንን እያታለለ እና እያጃጃለ እንደሚኖር እንደሚቀጥል እርግጠኛ ሆኗል፡፡ ሁሌም እንዲህ አላለሁ፡-ፓስተሮች ውሸታሞች እና አታላዮች ናቸው፡፡ ፓስተሮች መጨረሻ ደረጃ ላይ ሲደርሱ አብይን ይሆናሉ፡፡ በቃ የሆነው ያ ነው፡፡ እናም በቃህ ለማለት ጊዜው አሁን ነው፡፡

በሃይል አውሮፓን አንድ አደረጋለሁ ብሎ የተነሳው እና በታሪክ እጅግ የጦር ሊቅ ነው የሚባለው ናፖሊዮን ቦናፓርቴ እንዲህ ይላል፡-

“ድርጊቶች አይዋሹም፡፡ የሚናገረውን ሳይሆን የሚያደርገውን እመን፡፡”

“ፍርቶ ሳለ የድፍረት ነገርን ሊናገር ይችላል፡፡ ሊሸሽ እየተዘጋጀ ሊያጠቃህ እንደሆነ ሊናገር ይችላል፡፡ እየጠላህ እንደሚወድህ ሊናገር ይችላል፡፡ ድርጊቶችን አስተውል፡፡ ድርጊቶች አይዋሹም፡፡”

ይህ ሁሉ ጥፋት እና በደል እየደረሰ አብይ ስልጣን አልለቅቅም ከዚህ የተለየ ስርዓት እንዲመጣ አልፈቅድም ማለቱ ትክክል ነው? ይህ ጤናማ አእምሮ እና ለራሱ ክብር ካለው ሰው አይጠበቅም

አብይ ዕድል ፈንታ እንዲኖረው ከፈለገ ስልጣኑን በቆራጥነት በሰላማዊ መንገድ ያስተላልፍ፡፡ አለበለዚያ ተጠያቂነት እና ክፉ አመሟት መሞት ሩቅ አይሆንም፡፡

በቀጣይ “ሰን ዙን እያጠና ፀጋዬ ገብረ መድኅንን የማያውቅ” ብሎ ስለተናገረው “እኛ ኦሮሞዎች በጦርነት አንቻልም” መልዕክት በዚህ “የመደመር” በሚለው በተግባር ግን ሀገር አፍራሽ ስለሆነው ጉዞው እና ስለሚያስከትለው መዘዝ እና ይህ ድንፋታ ጊዜው እንዳለፈበት በጥቂቱ እንወያይበታለን

                           “ትግሉ ይቀጥላል”

                             “ሀገራችንን በእጆቻችን እንገነባለን”

 

 

 

Leave a Reply

Your email address will not be published.

Latest from Blog

ከሃይለገብርኤል   አያሌው የኦቦ ሲራጅና የወይዘሮ ፉንታዬ ልጅ ጃዋር መሃመድ ትላንትን ዛሬንና ነጋችንን ሊያሳይ የሚችል መጽሃፍ አዘጋጅቶልናል:: በእውነቱ መጽሃፉ ሊነበብ በሚችል የሃሳብ ፍሰት ተቀንብቦ በአነጋጋሪነቱ ቀጥሏል:: ጃዋርን እና የቄሮን ትውልድ በቅጡ ለመረዳት መጽሃፉ ማንበብ

የጃዋር የፖለቲካ ጅዋጅዌ! “ድመት መንኩሳ አመሏን አትረሳ’’

ጥር 2 ቀን 2017 ዓ/ም   January 10, 2025  በኢትዮጵያዊነታችሁ፡ በኦርቶዶክሳዊ እምነታችሁ፡ በአማራነታችሁ፡ በአማረኛተናጋሪነታችሁ፡ በተሰነዘረባችሁ ብትር፡ ቤተ ሰብ፡ ወዳጅ ዘመዶቻችሁን ያጣችሁ: ልጆቻችሁን የቀበራችሁ፡ አካልችሁን ያጣችሁ፡ የተሰነዘረውን ብትር በመከላከል ላይ ያላችሁ፡ያለፈቃዳችሁ በመንግሥት ተጽእኖ ወደመግደልና

በኢትዮጵያዊነታችሁ፡ በኦርቶዶክሳዊ እምነታችሁ፡ በአማራነታችሁ፡ በአማረኛ ተናጋሪነታችሁ፡ በተሰነዘረባችሁ ብትር፡

January 10, 2025
መኮንን ሻውል ወልደጊዮርጊስ ¹⁵ የምድርም ነገሥታትና መኳንንት ሻለቃዎችም ባለ ጠጋዎችም ኃይለኛዎችም ባሪያዎችም ጌቶችም ሁሉ በዋሾችና በተራራዎች ዓለቶች ተሰወሩ ፥ ¹⁶ ተራራዎችንና   በላያችን ውደቁ በዙፋንም ከተቀመጠው ፊት ከበጉም ቍጣ ሰውሩን ፤ ¹⁷ ታላቁ የቁጣው ቀን  መጥቶአልና ፥ ማንስ ሊቆም ይችላል ? አሉአቸው ። ራእይ 6 ፤  15_17 ይኽ የመጽሐፍ ቅዱስ ቃል ። የኢየሱስን ልደት ሰናከብር የየሐንስ ራእይን ማንበብ ጠቃሚ ይመስለኛል ። ምክንያቱም በመጨረሻው ዘመን

ከኢየሱስ የፍርድ ቀን በፊት በህሊናችን ውስጥ ፍቅርን ለማንገስ እንጣር 

የምጣኔ ሀብታዊ ፍጥ፣ የፖለቲካ፣ የእውነትና የሰብአዊ መብት ታጋይ፣ የአመኑበትን ነገር ለመናገር እንደ ፖለቲከኛ በቃላት ሳያሽሞነሙኑ ቀጥታ የሚናገሩት የሀገሬ ኢትዮጵያ ታላቅ ሰው ነበሩ “ዘር ቆጠራውን ተዉት፤ የአባቶቻችሁን ሀገር ኢትዮጵያን አክብሩ!”  አቶ ቡልቻ ደመቅሳ

ሀገር ወዳዱ አቶ ቡልቻ ደመቅሳ ከዚህ አለም በሞት ተለዩ

January 6, 2025
ግን ይህ ሁሉ ወጣት የት ገባ? ግን ይህ ሁሉ ወጣት የት ገባ? ዛሬ፣ 2025 ዓ/ም ላይ ብንገኝም በዝንጋታ ገመድ ወደ ሞት እየተጎተትን እንደሆነ አናውቅም። (ሁል ጊዜ የሚሞተው የገነዝነው ይመስለናል። ) “ገብርዬ ነበረ

ግን ይህ ሁሉ ወጣት የት ገባ?

January 3, 2025
Go toTop