March 14, 2023
23 mins read

የሽግግር ፍትህን ለማሰብ የሚቻለው ከትናንቱ ዛሬ የተሻለ በጎነት ሲኖር ነው (ገለታው ዘለቀ)

አንድ ሃገር ከነበረበት ከፍተኛ ቀውስ ወጥቶ ትንሽ ፋታ ሲያገኝና ወደፊት መመልከት ሲጀምር ባለፉት ጊዚያት የተፈጠረውን በደል ስርየት ለመስጠት፣ የቆሰለውን ለማከም፣ የተጎዳውን ለመካስ፣ ሲል የሽግግር ፍትህ ጥያቄ ያነሳል። በሌላ በኩል የሃገሪቱን መጻኢ እድል ለማሳመር የተሻለ ፍኖተ ካርታ በማዛጋጀት የነገውን የሃገሪቱን ህይወት ለማበጀት እንዲችል የሽግግር መንግስት አቁሞ ይሰራል። እንግዲህ የሽግግር  ጊዜ ሲባል በአንድ በኩል ያለፈውን ጊዜ ቁስልና አስከ ዛሬ ድረስ ሲንከባለል የመጣውን ችግር በብሄራዊ የሽግግር ፍትህ  የሚበየንበት ጊዜ ሲሆን፣ በሌላ በኩል የሃገሪቱን መጻኢ አድል ለማሳመር ጥሩ ፍኖተ ካርታ አበጅቶ በምክክር የሚለወጡትን ለውጦች በምክክር እንዲሻሻሉ በማድረግና በሚያድግ ዴሞክራሲ የሚፈቱትን ችግሮች ደግሞ ፓርቲዎች በምርጫ እየተወዳደሩ እንዲፈቱት በማድረግ ሽግግር ማምጣት ሲሆን፣ ከዚያም ደግሞ ትልቅ የምርጫ ድግስ ደግሶ በምርጫ ያሸነፈውን ፓርቲ የእርሻውን እርፍ አስጨብጦ ሃገርን በዴሞክራሲ ጎዳና ላይ ማስጀመር ማለት ነው ሽግግር ማለት።

በኢትዮጵያ ሁኔታ ስለብሄራዊ የሽግግር ፍትህና ስለሃገራዊ ምክክር ጉዳይ ለማሰብ ዛሬ ላይ ያለንበትን ሁኔታ ስናይ ተገቢነት ያለው ጥያቄ ነው ወይ? የሚለው ጉዳይ ዋና የፖለቲካ ጥያቄ ሆኗል። እንደ ኣንድ የሃገሪቱን ፖለቲካ ሁኔታ በቅርበት እንደሚከታተል ሰው እኔ እንደ ዜጋ ዛሬ ላይ ያለውን የፖለቲካ አቋሜን ለወገኖቼ ለማካፈል ነው የዛሬው አነሳሴ……………

ዛሬ ላይ ሆነን ስናይ የኢትዮጵያ ሽግግር ሙሉ በሙሉ መክሸፉን እናያለን። ሽግግር ሲባል  የሚይዛቸው ጉዳዮች አንደኛ የሚሻገሩ ጉዳዮቻችን ሁለተኛ የሽግግር ፍኖተ ካርታ፣ ሶስተኛ አሻጋሪ ሃይልና አራተኛ የጊዜ ሰሌዳ  ዋና ዋና ጉዳዮች ናቸው። ከነዚህ ውስጥ አሻጋሪው ወይም የሽግግሩ መሳሪያ (Instrument) ሙሉ በሙሉ ከሽፏል። ይህ ችግር በግልጽ ይታያል። ከመነሻውም ሃገራችን ወደ ለውጥ ውስጥ ስትገባ የሽግግር መንግስት ጥያቄን የዘለለችው ሲሆን ከገዢው ፓርቲ ተሰንጥቆ የመጣን ሃይል ኣሻጋሪ መሳሪያ ነህ ተብሎ ሜዳውም ያው ፈረሱም ያው መባሉ ትልቅ ሃገራዊ ስህተት ነበር። ይህ እርምጃ አያሌ ስጋቶችን (risks) የያዘ ውሳኔ ነበር።  ዶክተር አብይ ይመሩት የነበር ሃይል ሃገሪቱ ላሉባት የጠጋገቡ ቱባ ቱባ ጥያቄዎች የማይመጥንና ሲበዛ ቀጭን የሆነ ሃይል ስለነበረ ይህንን ሽግግር ሊመራ የሚችል መሳሪያ እንዳልነበር ቀድሞም መገመት ይቻል ነበር። ይህ ሃይል ማእከላዊውን ስልጣን ከያዘ በኋላ በወቅቱ የፖለቲካ ማሻሻያዎችን መውሰድ ሳይችል ቀርቶ የመጨረሻውን ዛሬ ተዝለፍልፎ ሲንገዳገድ ከመታየቱም በላይ አንድ ቀን ስልጣን ላይ ውሎ ባደረ ቁጥር ችግሮችን መፍታቱ ቀርቶ ሌሎች አዳዲስ ችግሮችን በከፍተኛ ፍጥነት እያመረተ የሚገኝ አደገኛ ሃይል ሆኗል።

ለአንዳንዶች ጊዜ የወሰደ ነገር ቢሆንም ዛሬ ላይ ግን  ይህ ዶክተር አብይ አህመድ የሚመራው መንግስት የሃገሪቱን ሽግግር ለመምራት መክሸፉን በግልጽ ማየት የሚቻልበት ደረጃ ላይ ስለተደረሰ የሽግግር ጥያቄ ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመር እንዲመጣ አድርጓል። ዶክተር አብይ አጠቃላይ የሽግግር ክሽፈትን ከማምጣቱም በላይ በሃገሪቱ ችግሮች ላይ ተጨማሪ አበሳዎችን እየጨመረ በመሆኑ ሃገሪቱ ሌላ የሽግግር ጥያቄ እንድታነሳ ሌላ አዲስ የትግል ምዕራፍ ላይ ወስዶ የጣለበት ጊዜ ላይ መሆናችንን በግልጽ እያየን ነው።

ገዢው ፓርቲ ገና ከመነሻው፣ ለውጦችን በቅደም ተከተል መምራት አቅቶት እንደቆየ በግልጽ ይታይ ነበር። የራሱን የፓርቲውን ውህደት ስንመለከት ምንም ዓይነት የህገ መንግስት ማሻሻያ ሳያደርግ የፖለቲካ ውህደት ፈጽሚያለሁ፣ ብልጽግና ተብያለሁ ሲል አንዳንድ የዋሆችን ያስደሰተ ቢሆንም ነገር ግን የዜግነት ፖለቲካን ማስተናገድ በማይችል ህገ መንግስትና የፌደራል ስርዓት ላይ ይህንን ውህደት ማስቀደም ለከፍተኛ መዋቅራዊ ግጭት እንደሚዳርግ የታወቀ ነበር። ነገር ግን በግብታዊነትና በስሜት ብልጽግና ውህደት ፈጸምኩ ባለ ማግስት የየክሉ ብልጽግና ፓርቲ ተፈጥሮ ከቀደመው በሰፋ መልኩ ልዩነቶች እየጠለፉ ይጥሉት ጀመር። መንግስት በጠዋቱ ወደ ህገ መንግስት ማሻሻያ ገብቶ ፖለቲካውን ወደ ዜግነት ፖለቲካ ሳያዞር የዜግነት ፖለቲካ ውስጥ ገባሁ ማለቱና ውህደትን ሊሸከም በማይችል ውቅር ላይ ራሱን መጣዱ ከፍተኛ ፖለቲካዊ ቀውስና ትኩሳት አምጥቶበታል። ከዚህ በተጨመሪ የጠራ ፍኖተ ካርታ ሳይኖረው ሽግግርን ልምራ ማለቱ ከፍተኛ ብሄራዊ ቅራኔን በማምጣቱ ይህ ስልጣን ላይ ያለ ግራ የተጋባ ሃይል ዛሬ ላይ በይፋ ከሽፏል። ክሽፈቱ እየሰፋ ሲሄድ ሁለት ግዙፍ የሆኑ ችግሮች ላይ ሃገሪቱን ጥሎብናል። አነዚህ ጉዳዮች፦

1ኛ የፖለቲካ ሽብር (Political disorder)

2ኛ ማህበራዊ ሽብር (Social disorder) ናቸው።

መንግስት የሃገሪቱን ወፍራም ለውጦች ሰፋ ባለና በብዙ ተቋማት በታገዘ የሽግግር ሃይል የሃገሪቱን ሽግግር ጥያቄ ለመፍታት ባለመጣሩ ቀስ እያለ የፖለቲካ ሽብር (Political disorder) ውስጥ ገብቶ ቆይቷል። በሶሻል ሳይንስ ውስጥ የፖለቲካ ሽብር ማለት የመንግስት የፖለቲካ ቁጥጥር ማነስ፣ በተለይም ማእከላዊ መንግስት የፖለቲካ ቁጥጥሩ ሲላላ ወይም ፖለቲካው ከቁጥጥሩ ውጭ ሲሆን፣ ከዚህ የተነሳ ከፍተኛ የፖለቲካ ክፍፍል (faction ሲፈጠር) የሚያታይ ከባድ ችግር ነው። የኢትዮጵያ ፌደራል መንግስት ከጊዜ ወደ ጊዜ የፖለቲካ ቁጥጥሩ እየሳሳ ሲሄድ በራሱ በገዢው ፓርቲ መሃል ሰፊ የሆነ የፖለቲካ ልዩነት ወይም (ፋክሽን) እየፈጠረ መጥቷል። ለምሳሌ በአማራ ብልጽግና እና በኦሮሞ ብልጽግና፣ በሌሎች ብልጽግና ፓርቲዎች መካከል ከፍተኛ የፖለቲካ አለመናበብ መፈጠሩ ሃገሪቱን ወደ ፖለቲካ ሽብር ወይም (political disorder) ውስጥ መግባቷን የሚያሳይ ግዙፍ ምልክት ነው። በሰሜን በኩል ከህወሃት ጋር የነበረው ጦርነትም አንድ የፖለቲካ ክሽፈት ማሳያ ሲሆን አጠቃላይ ብልጽግና ሃገሪቱን ሊያሻግር የማይችል ሃይል መሆኑን አሳይቷል። ብልጽግና አሁንም በየጊዜው ስለሽግግር ሲያወራ ቢታይም ነገር ግን በተግባር ይህ ፓርቲ የሚራመደው እርምጃ ሁሉ በተቃራኒው ሆኖ ሃገሪቱን ተጨማሪ ችግሮች እያስፈለፈላት ይገኛል። የሚከፋው ነገር ብልጽግና የተባለው ፓርቲ አሻጋሪ መሳሪያ ለመሆን ሳይችል ቀርቶ ሲከሽፍ ይህ ክሽፈት የሚንጸባረቀው የፖለቲካ አለመናበብና ሽብር ብቻ ሳይሆን የዚህ የፖለቲካ ቁጥጥር ማጣት ዳፋው ለማህበራዊ ሽብር መትረፉ ነው።  ሽግግር የከሸፈበት ሃገር ሁለተኛው አደገኛ ችግር ማህበራዊ ሽብር ወይም (social disorder) ለሚባለው ችግር መዳረጉ ነው። ማህበራዊ ሽብር (social disorder) ማለት በሶሻል  ሳይንስ በማህበራዊ ተቋማት ውስጥ የሚፈጠር ውስጣዊና ውጪያዊ  ሽብሮች ናቸው። ማህበራዊ ተቋማት ከምንላቸው ውስጥ በዋናነት ብሄርንና የሃይማኖት ተቋማትን  ይመለከታል። ባለፉት ጊዚያት ሃገራችን ኢትዮጵያ በደረሰባት የፖለቲካ ክሽፈት ችግር ሳቢያ ከፍተኛ የሆነ የማህበራዊ ተቋማት ግጭትና ሽብር ውስጥ ገብታለች። በተለይ ብሄር ማህበራዊ ተቋም ሲሆን ኢትዮጵያ ውስጥ የፖለቲካ መሳሪያ በመሆኑ ፖለቲካው ሲከሽፍ ወዲያውኑ ከፍተኛ ችግር ሆኖ የሚወጣው የብሄር ግጭት አንደሆነ ይታወቃል። በመሆኑም ባለፉት አራትና አምስት አመታት ከፍተኛ የሆነ መፈናቀል፣ የብሄር ግጭት፣ አርስ በርስ መጫረስ የታየው አሻጋሪው ሃይል ሲከሽፍ የተፈጠረ የማህበራዊ ሽብር (social violence and social disorder) ውጤት እንደሆነ እኛ ኢትዮጵያውያን በጥብቅ ማስተዋል አለብን። በሁለተኛ ደረጃ ካሉት ማህበራዊ ተቋማት መካከል የሃይማኖት ተቋም አንዱ ሲሆን የፖለቲካው ክሽፈት ወደ ማህበራዊ ሽብር  ሲዛመት የሃይማኖት ተቋማትን እያመሰ፣ የሃይማኖት አባቶችን ግራ እያጋባ፣የሃይማኖት ተከታዮችን እያስለቀሰ ይገኛል። ይህ ችግር የአሻጋሪ ሃይል መውደቅና የሽግግር ክሽፈትን ተከትሎ የሚመጣ ማህበራዊ ቀውስ ነው። ለምሳሌ የኢትዮጵያ ኦርቶዶስክ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን በታሪኳ ሁሉ ገጥሟት የማያውቀውን ችግር እያስተናገደች ያለችበት ምስጢር ይሄ ነው። ችግሩ ሲንኖዶሱን ለመክፈል የተወረወረ ፍላጻ ሆኖ ይታያል። ተቋሚቱን እንደ ተቋም ለመምታት የተቋሚቱን ራስ ለመምታት የሞከረ ክፉ ጦር የተሰነዘረው የፖለቲካ ክሽፈቱ ዋሻ ውስጥ የተደበቀ የሽግግር ክሽፈት ዳፋ መሆኑን ማየት ተገቢ ነው። ቀደም ሲል የኢትዮጵያን የእስልምና ተቋም እንዲሁ ሲያምስ የቆየ ሲሆን አስከ አሁንም ይህንን ተቋም እንዳይረጋጋ አድርጎት ይታያል። በኢትዮጵያ የፕሮቴስታንት ሃይማኖቶች መካከል ከፍተኛ ችግር አለ። እንደ ሙሉ ወንጌልና መካነ እየሱስ ያሉ አብያተ ክርስቲያናት በውስጥ የአሰራርና የብሄር ችግር እየታመሱ ነው። በአጠቃላይ ማህበራዊ ተቋማት ሁሉ የዚህ የፖለቲካው ክሽፈት ዳፋ መከራ እያሳያቸው ያለ ሲሆን ሃገሪቱ በአስቸኳይ ሃገራዊ የሽግግር መንግስት ጥያቄ አንስታ የሽግግር መንግስት በማቋቋም ፖለቲካዊ ቁጥጥር (order) መስተካከል አለበት።

እኛ ኢትዮጵያውያን የሰሉ ጥያቄዎችን ማንሳት አለብን። በዚህ ሰዓት ከፍ ሲል እንደጠቀስኩት አንድ ሃገር ሽግግር ውስጥ ሳትገባ እንዴት ነው የሽግግር ፍትህ አጀንዳ ላይ የምትወያየው? የሽግግር ፍትህ ጥያቄ የሚነሳው እኮ ሃገር ሰከን ብሎ ትንፋሽ ትንፋሽ  ሲያገኝ የሚያስበው ጉዳይ ነው። ከትናንቱ የባሰ የፖለቲካና የማህበራዊ ቀውስ ውስጥ ያለች ሃገር እንዴት ነው፣ ኑ…. ስለ ሽግግር ፍትህ እንምከር የምትለው? ኢትዮጵያውያን ይህንን ጥያቄ በጥብቅ መጠየቅ አለብን። ዶክተር አብይ ወደ ስልጣን ከመምጣታቸው በፊት እስከ አሁን ድረስ እየደረሰ ያለውን መፈናቀል፣ ግጭት፣ ዘር ማጥፋት አስተናግደን የማናውቅ ሰዎች በዚሁ በዶክተር አብይ ዘመን ስለአለፈው በደል እናውራ ለማለት እንችላለን ወይ? ይህ ጥያቄ መሰረታዊ ጥያቄ ነውና ኢትዮጵያውያን ይህንን ጥያቄ ማንሳት አለባቸው። ቀደም ሲል ይህ የዶክተር አብይ ቡድን የሃገሪቱን ሽግግር ለመምራት ይቀጥናል ስለዚህ የሽግግር መንግስት ይቋቋም ሲባል ለአንዳንዶች ያልተዋጠላቸው ምን አልባት ይህ ሃይል በገለልተኛ ተቋማት ከታገዘ ልንሻገር እንችላለን ከሚል ተስፋ ነበር። ነገር ግን ዶክተር አብይ ወደ ስልጣን ከመጣ በኋላ የማንነት አስተዳደርና ወሰን ኮሚሽን፣ የብሄራዊ እርቅ ኮሚሽንና ሌሎችም ተቋማትን እየገነባ ሲያፈርሳቸው ታይቷል። ከመነሻው ተቋማቱን ሲገናባ እንዳይሆን እንዳይሆን አድርጎ ይገነባል ከዚያም ድንገት ያፈርሳቸዋል። እነዚህ ጉዳዮች በከፍተኛ ሁኔታ አንድ የሽግግር ክሽፈትን የሚያሳዩ ምልክቶች ነበሩ።

 

ጎበዝ አሁን ያለንብተ ምእራፍ የተለየ ምእራፍ ነው። አሁን ያለነው ስለ ሽግግር ፍት ህና ዲያሎግ የምናስብበት ሰዓት ሳይሆን ሃገሪቱ በፍጥነት የሽግግር አካል ፈጥራ በዚህ ኣሻጋሪ ሃይል አማካኝነት ገለልተኛ የሆኑ የምክክር ኮሚሽንና ገለልተኛ የሆነ የእርቀሰላም ኮሚሽን መገንባት የሚያስፈልግባት ሰዓት ላይ ናት። የሚቋቋመው የሽግ ግር ሃይል ከነዚህ ኮሚሽኖች በተጨማሪ የህገ መንግስት አርቃቂ ኮሚሽን ገንብቶ መዋቅራዊ ለውጥ ለማምጣት መስራትን ይጠይቃል። ይህ ሲሆን የፖለቲካ ኦርደር ወደ ቦታው ይመለስና ማህበራዊ ኦርደር ይሻሻላል። ይህ ሳይሆን ቀርቶ ውለን ባደርን ቁጥር የፖለቲካ ኦርደር መጥፋት ችግር እየሰፋ ሄዶና የለሂቁ ክፍፍል እየሰፋ ሄዶ ማእከላዊ መንግስትን ሊያፈርሰው ይችላል። ከዚህ በከፋ ሁኔታ ደግሞ ማህበራዊ ተቋማት በተለይ በብሄር ላይና በሃይማኖት ላይ የተነሳው የስርዓት ሽብር ወደ ከፋ ችግር እያደገ ሃገራችንን ከዚህም ለከፋ ችግር አሳልፎ ይሰጥብናል። በመሆኑም የኢትዮጵያ ለሂቃን፣ የሃይማኖት መሪዎች፣ ወጣቶችና ምሁራን ሁሉ ችግሩን ተረድታችሁ ሃገሪቱ የሽግግር መንግስት እንድትመሰርትና የፖለቲካ ኦርደር እንዲታከም የበኩላችሁን የሽግግር ጥያቄ ልታሱሙ የሚገባችሁ ወሳኝ ምእራፍ ላይ ነን። ነገሮችን ዝም ብሎ ከዳር ሆኖ ማየት ተገቢ አይደለም። የኢትዮጵያ ወዳጅ የሆነችውን አሜሪካንን ጨምሮ ሌሎች ወዳጅ ሃገራትና የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የሃገራችንን የአሻጋሪ ሃይል ክሽፈት በመረዳት በዚህ ሰዓት ስልጣን ላይ ያለውን መንግስት የሽግግር ፍትህ አምጣ፣ ሰላምና መረጋጋት አምጣ፣ ማህበራዊ ተቋማትን ጠብቅ ወዘተ የሚለውን ምክር ትተው ሃገሪቱ ሁሉን ኣሳታፊ የሆነ የሽግግር መንግስት እንድትፈጥርና የፖለቲካ ኦርደር አንዲመለስ እንዲያደርጉ ሁላችንም የዲፕሎማሲ ትግላችን መሪ ሃሳብ ልናደርገው ይገባል።

 

እንግዲህ በዚህ ክፉ ጊዜ በተለይ ማህበራዊ ተቋማት፣ የችግራችሁን ምንጭ በመረዳትና ችግሩ የፖለቲካ ኦርደር መበላሸት፣ የአሻጋሪ ሃይል ክሽፈት የፈጠረው ዳፋ መሆኑን በመገንዘብ ህዝባችሁን ማንቃትና ለሽግግር አንዲታገል ማድረግ ይጠበቅባችኋል። አንድ ሃገር ውስጥ የፖለቲካ ኦርደር ሲጠፋና ይህ ችግር ዳፋው ለማህበራዊ ተቋማት ሲተርፍ በዚያ ሃገር የማይታመኑ ዜናዎች መስማት የሚጠበቅ ነው። ዛሬ የሰማነውን የሚዘገንን ዜና አዳምጠን ሳንጨርስ ነገ ሌላ አስደንጋጭ ዜና የምንሰማው የፖለቲካ ክሽፈት ውስጥ ስለገባን ነው። በዚህ ጊዜ አዳዲስ አጀንዳዎች በየቀኑ መምጣታቸው አይቀርም። ችግር በችግር ላይ ይደራረባል። ዜና በዜና ላይ ይደራረባል። የሃይማኖት አባቶች፣ ህዝቡ በአጠቃላይ ግራ መጋባት ውስጥ ይገባሉ። ከዚህ በፊት ሰምተን የማናውቀውን ጭካኔ እንሰማለን፣ አድረን ደግሞ ዛሬ ምን ይመጣ ይሆን? እያልን እንቆዝማለን። ይህ ሁሉ የችግሮች መደራረብና መዘበራረቅ ምንጩ የፖሊቲካ ኦርደር በሃገራችን ከቁጥጥር ስለወጣ ነው። ስለዚህ ወገኖቼ በኢትዮጵያ ውስጥ በአስቸኳይ የሽግግር መንግስት ይቋቋም ዘንድ ሁላችን በአጭር ታጥቀን እንታገል። ሃገራችን ተስፋ አላት ። በአለም ላይ ሽግግር ሲከሽፍ ሊሆን የሚችል ነገር ነው አሁን እኛ ላይ እየሆነ ያለው። ስለዚህ ሳንደናገጥ በርጋታ የሽግግር ጥያቄ እናንሳ። እግዚአብሄር ሃገራችንን ይባርክ ይጠብቅ።

 

[email protected]

Leave a Reply

Your email address will not be published.

Latest from Blog

ከሃይለገብርኤል   አያሌው የኦቦ ሲራጅና የወይዘሮ ፉንታዬ ልጅ ጃዋር መሃመድ ትላንትን ዛሬንና ነጋችንን ሊያሳይ የሚችል መጽሃፍ አዘጋጅቶልናል:: በእውነቱ መጽሃፉ ሊነበብ በሚችል የሃሳብ ፍሰት ተቀንብቦ በአነጋጋሪነቱ ቀጥሏል:: ጃዋርን እና የቄሮን ትውልድ በቅጡ ለመረዳት መጽሃፉ ማንበብ

የጃዋር የፖለቲካ ጅዋጅዌ! “ድመት መንኩሳ አመሏን አትረሳ’’

ጥር 2 ቀን 2017 ዓ/ም   January 10, 2025  በኢትዮጵያዊነታችሁ፡ በኦርቶዶክሳዊ እምነታችሁ፡ በአማራነታችሁ፡ በአማረኛተናጋሪነታችሁ፡ በተሰነዘረባችሁ ብትር፡ ቤተ ሰብ፡ ወዳጅ ዘመዶቻችሁን ያጣችሁ: ልጆቻችሁን የቀበራችሁ፡ አካልችሁን ያጣችሁ፡ የተሰነዘረውን ብትር በመከላከል ላይ ያላችሁ፡ያለፈቃዳችሁ በመንግሥት ተጽእኖ ወደመግደልና

በኢትዮጵያዊነታችሁ፡ በኦርቶዶክሳዊ እምነታችሁ፡ በአማራነታችሁ፡ በአማረኛ ተናጋሪነታችሁ፡ በተሰነዘረባችሁ ብትር፡

January 10, 2025
መኮንን ሻውል ወልደጊዮርጊስ ¹⁵ የምድርም ነገሥታትና መኳንንት ሻለቃዎችም ባለ ጠጋዎችም ኃይለኛዎችም ባሪያዎችም ጌቶችም ሁሉ በዋሾችና በተራራዎች ዓለቶች ተሰወሩ ፥ ¹⁶ ተራራዎችንና   በላያችን ውደቁ በዙፋንም ከተቀመጠው ፊት ከበጉም ቍጣ ሰውሩን ፤ ¹⁷ ታላቁ የቁጣው ቀን  መጥቶአልና ፥ ማንስ ሊቆም ይችላል ? አሉአቸው ። ራእይ 6 ፤  15_17 ይኽ የመጽሐፍ ቅዱስ ቃል ። የኢየሱስን ልደት ሰናከብር የየሐንስ ራእይን ማንበብ ጠቃሚ ይመስለኛል ። ምክንያቱም በመጨረሻው ዘመን

ከኢየሱስ የፍርድ ቀን በፊት በህሊናችን ውስጥ ፍቅርን ለማንገስ እንጣር 

የምጣኔ ሀብታዊ ፍጥ፣ የፖለቲካ፣ የእውነትና የሰብአዊ መብት ታጋይ፣ የአመኑበትን ነገር ለመናገር እንደ ፖለቲከኛ በቃላት ሳያሽሞነሙኑ ቀጥታ የሚናገሩት የሀገሬ ኢትዮጵያ ታላቅ ሰው ነበሩ “ዘር ቆጠራውን ተዉት፤ የአባቶቻችሁን ሀገር ኢትዮጵያን አክብሩ!”  አቶ ቡልቻ ደመቅሳ

ሀገር ወዳዱ አቶ ቡልቻ ደመቅሳ ከዚህ አለም በሞት ተለዩ

January 6, 2025
ግን ይህ ሁሉ ወጣት የት ገባ? ግን ይህ ሁሉ ወጣት የት ገባ? ዛሬ፣ 2025 ዓ/ም ላይ ብንገኝም በዝንጋታ ገመድ ወደ ሞት እየተጎተትን እንደሆነ አናውቅም። (ሁል ጊዜ የሚሞተው የገነዝነው ይመስለናል። ) “ገብርዬ ነበረ

ግን ይህ ሁሉ ወጣት የት ገባ?

January 3, 2025
Go toTop