ምትክ የለሽ አገራችን ኢትዮጵያ በታሪክ ከላሹና በአገር አፍራሹ አብይ አህመድ እጅጉን ተመሰቃቅላለች፡፡ አገሪቱ ኢዚህ ጭቦኛ ሰው እጅ መውደቋ ተረግማለች ያሰኛታል፡፡ ይህ ከጫፍ እስከጫፍ በህዝብ ተመርጫለሁ እያለ የሚያጭበረብረው አረመኔው አብይ አህመድ ቦቅቧቃ ጨፍጫፊና ጨካኝ ሰው ነው፡፡ ጭካኔ የፈሪ መገለጫ ሲሆን ሩህሩነት ግን የጀግና መገለጫ ነው፡፡ አብይ መርህ የለሽ ሰው ነው፡፡ ክሰው በታች የሆነ ሰው ነው፡፡ኢትዮጵያን አንቆ ይዟታል፡፡ ጠፍንጎ ይዟታል፡፡ አራችን ከተረኝነትና ከዘረኝነት ውጭ ምንም የማያውቅና የማስተዳደር ችሎታም ሆነ ክህሎት የሌለውን ሰው ጥሎባታል፡፡
ሰውየው ከዚህች ድሀ አገር የህዝብን ገንዘብ (ብር እንዳይመስላችሁ ዶላር ነው) እንደፈለገው እየመዘበረ ሚስቱን ይዞ ከአገር አገር ከመንሸርሸርና ሲመለስም በቴሌቪዥን እየቀረበ በውሸት ከመቀደድ ሌላ ለህዝቡም ለአገሪቱም አንድም እርባና ያለው ነገር አልሰራም፡፡ በበታችነት ስሜት የታላላቆቹን ነገስታት ቤተ መንግስትን አፍርሶ ሙዘይም አድርጓል፡፡የአልበገሬነት ምልክታችን የሆነውን የአንበሳን አርማ በወፍ ቀይሯል፡፤ ማንም ምንም አላለውም፡፡ በውሸት ይምላል ይገዘታል፡፤በተግባር ግን ህዝቡንና አገሪቱን ሊቀብር ጉድጓድ ሲምስ ይውላል፡፡ ጉድጓድ ሲምስም ያድራል፡፡ አማካሪወቹም በተረኝነት የታበዩት፣ አክራሪ የኦሮሙማ አቀንቃኞችናቸው፡፡ የስብስቡ አባላት አስተሳሰባቸው ለብዙ አመታት ባለበት የቆመና የቆዘመ የተላና የነቀዘ አስተሳሰብ ያላቸው የኦሮሙማ አቀንቃና ልክፍተኛ መንደርተኞች ናቸው፡፡ ህዝቡ የእነዚህንም መንደርተኞችና የራሱን የአብይንም ማንነት ጠንቅቆ ተረድቶታል፡፡
የድምር የኦሮሙማ እሳቤ ዉጤትእንደሚያሳየው አብይ አህመድ ከይሲ ከይሲውን የሚሰራው የታሪክ ዱካን ለማጥፋት ነው፡፤ በየእለቱ በሚነገረው የብልጽግና የቴሌቪዥን የዜና ሰአታት ላይ የእርሱ ምስል ያልቀረበበት ጊዜ በጣም ዉሱን ነው፡፡
በነገራችን ላይ ስንቶቻችን ነን በኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን ላይ አብይ ጫና ለማድረግ በሞከረበት በዚያች ሳምንት ውስጥ አንድም ቀን የቴሌቪዥን ዜና በኢንተርኔት አለመጫኑን የምናውቅ?? አብይ በትእዛዝ ይህንን ያስደረገው ለምን እንደሆነ መገመት ትችላላችሁ፡፡ ከህዝቡ የሚጎርፉትን የተቃውሞ አስተያየቶች ለሌሎች እንዳይደርሱ አስተያየቶቹን ለማፈን ነው፡፡ይህ የተለመደ የዲክታተሮች አሰራር ነው፡፡ ያን ሳምንት ለአብይ አጎብዳጅ በሆኑት የአማራ ክልል መሪወችም በኩል በአብይ አህመድ ትእዛዝ በአማራ ቴሌቪዥንም ላይ ይሄው ተፈጽሟል፡፡
በአብይ አህመድ አገዛዝ (አገዛዝና አመራር ስለሚለያዩ አመራር አላልኩም) ሰላም ሊመጣ አይችልም፡፡ አገዛዙ ሰላም እንዲመጣ አይፈልግማ!! አብይ ህዝቡን መግዛት የሚፈልገው ህዝቡን ከህዝብ በማጋጬት፣ ህዝብን በፍርሀት ውስጥ በማስመጥ እንደሆነ በሚገባ ያምናል፡፡ ይህንኑም እርካብና መንበር በሚለው መጽሀፉ ላይ አስፍሮታል፡፡ በእርሱ ጊዜ አገሪቱ ግድያ በግድያ፣ ስዴት በስዴት ሆናለች፡፤ ይህም ነውረኛ አሰራር በኦሮሙማ (የኦሮሞ የበላይነት እሳቤ) የአገዛዙ ስልትና ዘዴ ተደርጎ ተወስዷል፡፡
ሁልጊዜ ግጭት መጥመቅ፣ ሁልጊዜ ‘ሁሉም የእኔ ነው’ በሚል የኬኛ እሳቤ የህዝብን ገንዘብ መዝረፍ፣ መሬት መዝረፍ፣የንጹሀንን ህይወት መቅጠፍና አሁንም መልሶ መላልሶ ያገኘውን ሁሉ መዝረፍ፣ ሁልጊዜ መዋሸት፣ ሁልጊዜ ከእውነታው በተቃራኒ ሆኖ መገኘት፣ ጤፍ በሚቆላ ምላሱ ህዝብን ማታለል፣ ህዝብን ማስለቀስና ማሳዘን፣ ባንኮችን እያዘረፉ፣ ንጹሀንን እያስገደሉ ሬሳወችን በዘር መቁጠር … ወዘተ ሆኗል የውሬው አብይ አህመድ ስራ!!!
ከአብይ አህመድ እጅግ አሳፋሪና ነውረኛ ስራወች ውስጥ ምኑ ተነስቶ ምኑ ይቀራል?
ጥቂት በድሀው ገንዘብ የተገዙ ሆዳሞች ”ታላቁ መሪያችን” የሚሉት አብይ አህመድ አላማው ኢትዮጵያዊነትን ነቃቅሎ በመጣል ኦርማዊነትን መትከል ነው፡፤ኦሮሚያን እንደአገር መፍጠር ነው፡፤ ይህ ነው የአብይ አህመድ ኦሮሙማ አላማና ኢላማ፡፡ ኢትዮጵያ ይህንን ሰው የጣለባት የማን እርግማን እንደሆነ ባይታወቅም ጉዳዩ ግን የመረገም ዉጤት እንደሆነ አለማመን ይከብዳል፡፡
አውሬው አብይ አህመድ የሰራቸው እጅግ አሳፋሪ ድርጊቶች ለታሪክና ለፍርድ ተሰድረው ተይዘዋል፡፡ ከነዚሁ መሀከል ለዛሬው ርእሳችን ይጠቅመን ዘንድ ሰውየው ባለፉት ሁለት ወራት ውስጥ ብቻ ሚስቱን አስከትሎ ያደረጋቸውን የውጭ አገሮች ሽርሽሮች ለይተን እንመልከትና ጀዝባው አህመድ አሊ ምን ያህል ዋልጌ ሰው እንደሆነ ግንዛቤ እንውሰድ፡፡
ባለፉት ሁለት ወራቶች ውስጥ ብቻ አብይ አህመድ ሚስቱን እያስከተለ በኳታር ፣ ፈረንሳይ፣ ኢጣልያ፣ ማልታ፣ እንደገና ኳታር ሶማሊያ ፣ ሱዳን ፣ የተባበሩት አረብ ኢምሬትስ፣ ፣ግብጽና ፣በአሜሪካ – ዋሽንግተን ዲሲ ጉብኝት አድርጓል፡፤ ተንሸራሽሯል፡፡ ይህ ወራዳ ሰው በሁለት ወራት በአስር አገሮች ውስጥ ያደረገውን ይህንን አይነት ሽርሽር መለስ ዜናዊ በ27 አመታት ውስጥ ወይንም መንግስቱ ሀይለማርያም በአስራ ሰባት አመታት አገዛዛቸው ውስጥ አላደረጉትም፡፡
ድርጊቱ እጅግ አሳፋሪና እብሪት የተሞላበት ነው፡፡ ማን አለብኝነት ነው፡፡ አብይ አህመድ በስልጣን ላይ ሆኖ ለሰራው ለእያንዷንዱ ግፍና ዝርፊያ ግዲያና ጭፍጨፋ ሙሉ በሙሉ ተጠያቂ ስለሆነ ዋጋ ይከፍልባቸዋል፡፡ ድምጻቸውንና መልካቸውን ሲያይ ጭራውን የሚቆላላቸውና በሰራቸው ወንጀሎች እንዳይጠየቅ እንድሚያደርጉለት ቃል የገቡለት በጣት የሚቆጠሩት ሀያላን አገራቱም ሆኑ በስምምነት ስም ዛሬ በጋብቻ ተጣምረው በጫጉላ ሽርሽር ላይ ያሉት የወያኔ ቡድን ሁለቱም በወንጀል የተጨመላለቀውን አብይ አህመድን ከህዝብ ፍርድ አያድኑትም፡፤ በጭራሽ አያድኑትም፡፡
በዝቅተኛ ባለሙያወች አማካይነት ሊወከሉ ይገባቸው የነበሩ ስብሰባወችም ላይ የአገር መሪ ተብየው ራሱ አብይ አህመድ ከነሚስቱ እየሄደ የአገሪቱን የተመናመነ የውጭ ምንዛሬ በሽርሽር መዝብሯል፡፡አባክኗል፡፡አላግባብ እንዲወድም አድርጓል፡፡
ይህ የህዝብ ገንዘብ ዝርፊያና ውድመት በአገር ውስጥ በብር የሚደረገውን አያካትትም፡፡ በዶላር የተከናወነውን ብቻ ነው የሚያካትተው፡፡ በአገር ውስጥ እርሱ ራሱ በግሉና ሚስቱም ራሷ የህዝቡን ገንዘብ ለህዝብ በማይጠቅሙ የይስሙላ ድርጊቶችን እየመረጡ ገንዘቡን ራሳቸው ሰርተው እንዳፈሩት በማስመሰል በየግላቸው በልዩ ልዩ ምክንያቶች የአገርን ሀብትና ገንዘብ እየዋኙበት ነው፡፡ የራሳቸው ሰርተው ያፈሩት ገንዘብ አለመሆኑን እያወቁ እነዚህ ጅቦች ያለልክ ናኝተውበታል፡፡
ዱሮስ ባልና ሚስት ከአንድ ባህር ይቀዳል ይባል የለ??
አብይ አህመድ በአገር መሪነቱ እንዲሁም ወ/ሮ ዝናሽ ታያቸው የመሪ ሚስት በመሆኗ ከተለያዩ ምንጮች ከውስጥም ከውጭም ገንዘብ ሊያገኙ ይችላሉ፡፤ ያንን ገንዘብ ያገኙት ግን በኢትዮጵያ ውስጥ ባላቸው የመሪነት ቦታ በአገር ዲፕሎማሲና የጥቅም ግንኙነት እሳቤና ደረጃ እንጅ ከዚያ ወርዶ ለአብይ አህመድ ወይንም ለዝናሽ ታያቸው ማለትም አብይና ዝናሽ ታያቸው በመሆናቸው ያገኙት ገንዘብ አይደለም፡፡ በዚህ አድራጎታቸው ሁለቱም ትክክል እንዳልሆኑ አያውቁም አይባልም፡፡ጉዳዩ እኛን ማን ደፍሮ ይጠይቀናል ነው፡፡ነገሩ እብሪት ነው፡፤
ከውጭ አገራትም ሆነ ከአገር ውስጥ ሁለቱም በአገሪቱ ውስጥ ባላቸው የስልጣን ቦታ ምክንያት የሚገኝ ገንዘብ በአገሪቱ የገንዘብ ሚኒስቴር በኩል ተመዝግቦና በኦዲተር ተጣርቶ በብሄራዊ ባንክ በኩል ማለፍ ሲገባው ይህ አልተደረገም፡፡ የትም አገር ህጉና አሰራሩ ይህንን የተከተለ ነው፡፡ በኢትዮጵያ ውስጥ ግን ይህ አይታሰብም፡፡ይህ የሁለቱ ድርጊት ዘረፋ ነው፡፤ ሌብነት ነው፡፡ ያስጠይቃል፡፡ ህግ ፊት ያስቀርባል፡፡ ያስቀጣልም፡፡
በአሁኑ ሰአት ፓርላማውም ሆነ ህግ አውጭው በራሱ በአብይ አህመድ ቁጥጥር ስር ነው ያለው፡፤ ባንኩም ታንኩም እንደዚሁ በአንድ ሰው ቁጥጥር ስር ነው ያለው፡፡ የምን ህግ፣ የምን ነውር፣ የምን ነግ በእኔ?? እነርሱ ይህንን አያውቁትም!!!
የኢትዮጵያ ሰራዊት የአገር ሰራዊት እንጅ የአብይ አህመድ ሰራዊት አይደለም፡፡ የፓርቲም ሰራዊት አይደለም፡፡ በተጓዳኝም አብይ እንደፈለገ የሚጋልባቸው ብዙ አደረጃጀቶች አሉ፡፡ ምሳሌ የአገሪቱ ህግ አውጭውና ህግ ተርጓሚው ክፍል፡፡ ይህ ህግ አውጭ የአገር ህግ አውጭ ነው፡፤ ይህ ህግ ተርጓሚም የኢትዮጵያ ህጎች ተርጓሚ መስሪያ ቤትና አደረጃጀት ነው፡፡ በአሁኗ ኢትዮጵያ ውስጥ ግን ሁሉም ተጥሷል፡፡ ሁሉም የኬኛወች ነው፡፤ የኬኛወቹ መሪ ደግሞ አብይ አህመድ አሊ ነው፡፡
በአውሬው አብይ አህመድ ስር ባሉት እንደ ግመሬው ሽመልስ አብዲሳና እንደ ቀበሮዋ አዳነች አበቤ …. ወዘተ አማካይነት የሚካሄዱት ዘረፋወች ቁጥሩ አይታወቅም፡፡ ህዝቡ ግን እየመዘገበ ይዞታል፡፡ በጠራራ ጸሀይ ከተዘረፉት 16 ባንኮች ጀምሮ ባለፉት አራት አመት ተኩል በኦሮሙማ ጅቦች አማካይነት የተዘረፈው የህዝብ ንብረትና የገንዘብ መጠን የት የለሌ ነው፡፡ ተቆጥሮም አያልቅ፡፡
በከተማ ላይ ከተማ መመስረት፣ህዝብን በማፈናቀል የኦሮሙማ የጫካ ቤተመንግስት መመስረት፣ የአገሪቱን የኢኮኖሚ አውታሮች አስላፎ መስጠት ህዝቡን በጥቁር ገበያ ፍዳውን ማብላት ..ወዘተ..።ወዘተ ስንቱ የኬኛውች ጉድና ጉድጓድ ተዘርዝሮ ያልቃል፡፤
የኦርሙማ ቁንጮ መሪወች የቻሉትን ዘርፈው ሲያበቁ ቀሪውን የዘረፋ ትእይንት የዘረፋው ተጠቃሚወች ለሆኑ ለዘመዶቻቸው፣ ለጥቅም ተካፋዮቻቸውና የኬኛ አቀንቃኝ ለሆኑ የተወሰኑ የህብረተስብ ክፍል አሳልፈው ሰጥተውታል፡፤ በህዝቡ ህይወትና ምስቅልቅል ኑሮ ላይ የጠገበው የኦሮሙማ ዘራፊ ለአፍታ ጋብ ሲል የተራበው የኦሮሙማ ዘራፊ ከስር ይተካል; ፡፡ዘረፋው የአብይ አህመድ አሽከሮች የሆኑትን ሆዳም የአማራ ትርፍ አንጀቶችንም ይጨምራል፡፡
ባለፉት ጥቂት አመታት የሰውየውን አስተሳሰብና ከእውቀት የጸዳ መሆን የሚገልጹ ብዙ ገጠመኞችን ታዝበናል፡፡ አይተናል; ሰምተናል፡፡በመጀመሪያ ደረጃ አብይ ምሁር ለመምሰልና አዋቂ መስሎ ለመታየት የሚያደርጋቸው እየተነሱ የመፈጥፈጥ ትርኢቶቹ ከአስቂኝነታቸው ባሻገር የሰውየውን በበታችነት ስሜት ውስጥ ወድቆ እየተሰቃየ መሆኑን ቁልጭ አድርገው ያሳያሉ፡፡
ነገሩ ትግራይን/መቀሌን በሻሻ አድርገናታልት ከሚለው ይጀምርና እስከ ሚታፊዚክስ ቲዮሪና ትንተና ይደርሳል፡፡
ከእውቀት የጸዳው አብይ አህመድ እንደወትሮው ሁሉ ከሰራቸው ነዉሮቹ ውስጥ አንዱን ክፍል ማለትም እኔን ይበልጥ ፈገግ ያደረገኝን ላካፍላችሁ፡፡ባለፈው ሳምንት ወጣቶችን ሰብስቦ ስለሜታ ፊዝክስ፣ ስለ አማኑኤል ካንት፣ ስለ ግራና ቀኝ የአእምሮ ክፍሎች፣ የማይገናኘውን እያገናኘ ምሁርነቱና አንባቢነቱን ለመደስኮር የቻለውን ያህል እየቀብጣጠረ ሊያቀረሽ ሞክሯል፡፤ በመሰረቱ ይህ የሚመነጨው ከትንሽነት ስሜት ነው፡፤ ከበታችነት ስሜት ነው፡፤ የበታችነትና የትንሽነት ስሜቶች ደግሞ በራሳቸው በሽታወች ናቸው፡፡ስለዚህ ሰውየው በበታችነት በሽታ ተይዞ በመሰቃየት ላይ ነው፡፡
አብይ አህመድ በታሪክ ከሚታወቁት ድክታተሮችና ፋሽሽቶች ይበልጥ ፋሽሽትና ይበልጥ ድክታተር ሆኗል፡ ከሂትለርም በሉት ከሙሶሎኒ በድርጊቶቹ ከሁሉም ታሪክ ከሚያውቃቸው ድክታተሮች ይበልጣል፡፡ ቢያንስ ቢያንስ ሂትለርም ሆነ ሙሶሎኒ አገሮቻቸውንና ህዝቦቻቸውን በእኩል አይን ይወዱ ነበር፡፡ፋሽሽቶችና ዲክታተሮች ከመሆናቸው ውጭ በየአገሮቻቸው ዜጎቻቸውን በዘር ለይተው ብሄርን ከብሄር፣ ጎሳን ከጎሳ አላገዳደሉም፡፡ የአንዱ ዘር ሌላውን ገድሎ ዘቅዝቆ ለሚሰቅለው ቡድን ድጋፍ አልሰጡም፡፤ ሴት ተማሪወችን በዘራቸው መርጠው በመለየት አሳፍነው ዱካቸውን አላስጠፉም፡፡ እርጉዞችን አሳርደው ሽሎቻቸውን ከሆዳቸው አስወጥተው ለሟች እናቶች አላስታቀፉም፡፡ ሂትለርም ሆነ ሙሶሎኒ ይብዛም ይነስም በየአገሮቻቸው ላይ ከየአገሮቻቸው ጠላቶች ጋር አላሴሩም፡፡
የእኛው ጉድ ግን በኢትዮጵያና ሱዳን መካከል 250 ኪሎ ሜትር በሚረዝመው ድንበር ላይ የሱዳን ጦር ወደ ኢትዮጵያ መሬት 50 ኪሎ ሜትር ዘልቆ ገብቶ ኢትዮጵያን እንድወርር አድርጓል፡፡ወረራውንም ፈቅዷል፡፡ አሁንም እነዚያ የኢትዮጵያ መሬቶች በሱዳን እንደተወረሩ ናቸው፡፤ ለምን ቢባል ምስጢሩ ግልጽ ነው፡፡ይህም በሱዳን የተወረሩት ቦታውችና መሬቶቹ በአማራ ክልል ውስጥ ናቸው፡፤ የአማራ ርስቶች ናቸው፡፡አማራ ደግሞ አብይ አህመድ አብዝቶ የሚፈራውና የሚጠላው ጨርሶ እንዲጠፋም የሚፈልገው ዘር ነው፡፡ የአማራን ዘር ጥፋት ለማፋጠንም አጥብቆ እየሰራ ነው፡፡
የአብይ አህመድ ነውሮችና የቂልም በሉትየብልጠት ድብቅና በማር የተለወሱ ሴራወቹ አገርን እየጎዱ ነው፡፤ መቆም አለባቸው፡፡ይህ ይሆን ዘንድ አብይ አህመድና የኦሮሙማ መንጋ መወገድ አለበት፡፡ አማራ ሲታረድ ሌሎች በተለይ ደቡቡ ቆሞ ያይ ነበር፡፡ አሁን አብይ አህመድ በገሀድ ደቡቡን ከፋፍሎ ለመሰልቀጥ የሚያደርገውን ሴራና ተንኮል ማየቱ ሰውየው ለማንም የማይመለስ መሆኑን ማረጋገጫ ነው፡፡ በተለያዩ የደቡብ ብሄር ብሄረሰቦች ላይ አሁን ኦሮሙማ እንደዘንዶ እየተጠመጠመባቸው ነው፡፤
ሀያሉ አማራ ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ በደረሰበት ግፍና መከራ እንደብረት ጠንክሮ ወጥቷል፡፡ ግንባሩ አይታጠፍም፡፡ ነጻነቱን ለማስመለስ ለየተኛውም አይነት መስዋእትነት ዝግጁ ነው፡፡ ኦሮሙማንም ሆነ የወያኔ ርዝራዦችን ቢጣመሩም ባይጣመሩም ሁለቱንም ጸረ አማራና ጸረ ኢትዮጵያ ስብስቦች ጠንክሮ በመታገል ያለጥርጥር ያሸንፋቸዋል፡፡
አማራው ያለልክ መገፋት፣ በጽኑ መበደል፣ እንደ ከብት መታረድና በራሱ አገር መስደድ እጣ ፈንታው ስለሆነ ያለጥርጥር አማራው በየጎበዝ አለቃው በፋኖ ዙሪያ በአማራ ህዝባዊ ሀይልነት ተደራጅቶ አንድ ሆኖና በአማራነቱ ኮርቶም ጠንክሮም በመቆም ያሸንፋቸዋል፡፡ እንደ ሽህ አመታት ታሪኩ ሁሉ በነፍኛጠነቱ እንደሚኮራና እንደሚተማመንም ለአለም መልሶ ያረጋግጣል፡፡
አማራው ለሌሎችም የኦሮሙማ ኢላማ የሆኑ የደቡብ ኢትዮጵያ ብሄር ብሄረሰቦች አርእያ ሊሆንና የትግላቸውም አጋር ሊሆናቸው የትግል ጉዞውን ጀምሯል፡፡ነገሩ ተረኞቹ በጥጋብ ታውረውና በእብሪት ተነፋፍተው እንደሚያሾፉት አይደለም፡፡ኢትዮጵያ ለኦሮሙማ ሳይሆን አሁንም እጆቹዋን ወደ እግዚአብሄር ትዘረጋለች፡
በልጆቿ አንዲነትና ብርቱ ትግልም መልሳ ጠንካራና ነጻ አገር ትሆናለች፡፡ ህዝቡ ሌላ አማራጭ የሌለውን ሁሉም ኢትዮጵያዊ ተከባብሮ በእኩልነትና በነጻነት የሚኖርባት አንዲትና ትክክለኛ ፌደራላዝም የሰፈነባት ኢትዮጵያን እውን ያደርጋል፡፡ ነጻነቷንም አስከብሮ ለቀጣዩ ትውልድ ያስተላልፋል፡
እኔም ፋኖ ነኝ፡፡ ድል ለፋኖ!!!