March 1, 2023
31 mins read

 ዝ ክ ረ   ዓ   ደ   ዋ  ! – መኮንን ሻውል  ወልደጊዮርጊስ

334476376 616109283712666 256688385386527955 n 1 2” ዓደዋ ኢትዮጵያዊነት ማለት ነው ፤ ኢትዮጵያዊነት ማለት ደግሞ ሰው መሆን ነው _ ሰው የጠፋ ዕለት ። አፍሪካዊያን ስለዚህ ነው በኢትዮጵያ ድል የሚኮሩት ። ኢትዮጵያዊን የአፍሪካውያን የኩራት ምንጭ ሆነናል በዓደዋ ።”

ስለ ዓደዋ የሚያወሳውን ፅሑፌን የምጀምረው በድንቁ ሰላያችን  በአውዓሎም ሐረጎት ነው ። ይህ በትግራይ በኢንጥጮ የተወለደው አንድ ህኖ ሳለ ፣ የሺዎችን የጀግንነት ሥራ የሰራ  ኢትዮጵያዊ ጀግናችን የታወቀ   ሲራራ ነጋዴ ነበር  ። ” በመላው  ዓደዋ  እና በትግራይ ከተሞች ሁሉ እየተዘዋወረ ሸቀጥ የሚያቀርብ ።  ወጣት ብልህ  ና ቀልጣፋ ነጋዴ … ። ለኢጣሊያን መንግሥት እንዲያገለግል  በመረጃ አቅራቢነትም በድብቅ  ተቀጥሮ የሚሰራ ጮሌ ሰላይ ። ከአደዋ ጦርነት በፊትም ፈቃድ ተሰጥቶት በኢጣሊያኖች  ጦር ሰፈር ሁሉ እንደልቡ  የሚዘዋወር ታማኝ …።

የአደዋ ጦርነት ሊነሳ ሲል ግን  ልቡ ወደ ኢትዮጵያ መሆኑንን  ያሳየ ጀግና መሆኑንን በስለላ ጥበቡ ያስመሰከረ ።  ” ሥለዚህ መንፈሰ ብርቱ እና እጅግ ጠንካራ ሰው ፣ በመፃፍ  ጀግኖቻችንን እና ተጋድሏዋቸውን ″ ሀ ″ ብዬ  መዘከር እጀምራለሁ ።

እርሱ ና  በላታ ገብረ እግዚአብሔር ጊላይ በኢጣሊያ ትዕቢት እጅግ የሚናደዱ ፤ ደማቸው ውስጥ ኢትዮጵያዊነት የገነነ  ነበር ። በኢጣሊያ ቅኝ አገዛዝ ሥር ኤርትራ በመውደቋ በዛ አካባቢ በወቅቱ ጉልበታም ለሆነው ለቅኝ ገዢው  ኢጣሊያን መስለው ቢያድሩም ፣ ልባቸው ከአገራቸው ጋር ነበረ ።

የዓድዋን ድልን ስኬት ዕውን ካደረጉት ጀግኖች አንዱ ወደሆነው ወደ  አውዓሎም ሐረጓት ነገሬን ለመልሰው ። …

331622857 666103708650173 309605985106260073 n 1 1
እ ኔ : ሴ ት : ነ ኝ ፤ ጦ ር ነ ት : አ ል ወ ድ ም : : ሆ ኖ ም : ኢ ት ዮ ጵ ያ ን : የ ኢ ጣ ሊ ያ : ጥ ገ ኛ : የ ሚ ያ ደ ር ግ : ው ል : ከ መ ቀ በ ል : ጦ ር ነ ት ን : እ መ ር ጣ ለ ሁ : :
እ ቴ ጌ : ጣ ይ ቱ : ብ ጡ ል : ኃ / ማ ር ያ ም
[ ብ ር ሃ ን : ዘ : ኢ ት ዮ ጵ ያ ]
ሰላዩ አውዓሎም  የምኒልክን ጦር እንቅሥቃሴ  በመሰለል  ለኢጣሊያን ጦር እንዲያቀብል  ሥምሪት ተሰጥቷት ነበር ። አውዓሎም ግን በምሥጢር ፤ ከራስ መንገሻ ስዩም ጋር በመገናኘት ና ዕቅዱን በመናገር ከንጉሥ ምኒልክ ጋር ለመገናኘት ና የኢጣሊን ወራሪ ጦር  በተሳሳተ መረጃ በቀላሉ  ድል ማድረግ እንዴት እንደሚቻል ከብላታ ገብረእግዛብሔር ጊላይ  ጋር መከረ ።

በዚህ ሃሳብ መሠረትም  ከራሥ መንገሻ ሥዩም ዘንድ በድብቅ እንዲገናኝ ብላታ ረዱት ።  አፄ ምኒልክ እና እቴጌ ጣይቱ ዘንድም  ራሥ መንገሻ  አቀረቡት። የስለላ  ሥራውንም ተመሳስሎ ለኢትዮጵያ መሥራት ጀመረ ። በምሥጢር የሁለት ወገን ታማኝ ሰላይ ሆነ ። ታማኝነቱ ለኢትዮጵያ መሆኑንን በሚከተለው የሥለላ ዕቅድ አረጋገጠ ።

“ራሥ መንገሻም ከአፄ ምኒልክ እና ከእቴጌ ጣይቱ ጋር አውዓሎምን አስተዋወቁት ።ለኢትዮጵያ መሰለል ዠመረ ። የጦርነቱ ጊዜ ሲቀርብ የኢጣሊያንን ዕቅድ ለማሳከር በአፄ ምኒልክ በኩል ፣ አንድ ዘዴ ተዘይዶ በአውዓሎም አማካይነት ለጄኔራል ባራትይሪ  እንዲደርስ ተደረገ ። ሐሰተኛ መረጃውም እንደሚከተለው ነው ። ‘ የካቲት 21/1988 ዓ/ም ማሪያም ስለሚከበር ሰራዊቲ ሁሉ አክሱም ፅዮን ማሪያምን ለመሳለም አደዋን ለቆ ይሄዳል ።በማግሥቱም ሰንበት ነው ። እሁድ ፣ የካቲት 23/1988 ዓ/ም  ጊዮርጊስ ነው ። እናም መኳንንቱ እስከ አጃቢዎቻቸው ወደጊዮርጊስ ቤተ ክርስቲያን በመሄድ የታብቱን ንግስ ያከብራሉ ። ሠራዊቱም ቀለብ ፍለጋ ወደየመንደሩ ይሰማራል  ። ይህ አጋጣሚ ንጉሱን ካከማቹት የጦር መሳሪያ ጋር ለመማረክ ይመቻል ። እናም ጀነራል ባራቲዬሪ በዚህ ቀን ፣ ኢትዮጵያዊያን  ጦርነቱን ሳያስቡት ፣ ሳይዘጋጁበት ቢጀምር በቀላሉ ድል ያደርጋል ።  ‘ የሚል የተሳሳተ መረጃ ለኢጣሊያ ጦር መሪ ለጄኔራል ባራቲዬሪ አቀረበ ።

ይህን የተሳሳተ መረጃ ሳይሸራርፍ ለኢጣሊያኑ የጦር አዛዥ ለማቅረብ ፣ አውዓሎም ከእቴጌ ጣይቱ ጋር መኳንንቱ ባሉበት በጋራ መዕድ በመብላት ቃለ ምህላ ፈፅሞ እንደነበረ አንባቢ ሆይ ተገንዘብ ።

በገባው ቃለ ምህላ መሠረትም አንዳችም ጥርጣሪን በማይጭር መልኩ ለጀነራል ባራቴዬሪ አቀረበ ። ጀነራሉም አመነው ። ምክንያቱም የንጉሱ ድንኳንም ሆነ የወታደሩ ሠፈር ድንኳኖች በሙሉ ተነቅለው የአደዋ ጦር ሰፈር ባዶ እንዲመሥል ተደርጓልና !

ይህን ሲመለከት ጀነራል በራቲዬሪ የአውዓሎም መረጃ እጅግ አስተማማኝ አገኘው ። ወዲያው ለሠራዊቱ ትዕዛዝ አስተላለፈ ። የካቲት 22/1988 ዓ/ም ቅዳሜ ማታ የኢጣሊያ ጦር ከአምባ ሠዋሪያ ( ምነጉዳ ) ምሽጉ እየተግተለተለ ወጣ ። ሚኒሊክን ከጥቂት አጃቢዎቺ ጋር  ብቻውን አገኘዋለሁ በሚል ጥዲፊያም ወደ ሚኒልክ የጦር ሥፍራ ገሰገሰ ።

ወደ ጦር ሰፈሩ ሊነጋጋ ሲል በ11 ሰዓት ወደ አደዋ የሚኒልክ ጦር ሰፈር እንደተቃረበ ፣ የእሩምታ ተኩስ ከፈተ ። ምሽግ ሰርቶ አድፍጦ የጠበቀው  የምኒልክ ጦር አፀፋውን መለሰ ። ሊነጋጋ ሲል የካቲትት 22/1988 ዓ/ም የተጀመረው ፍልሚያም እስከ የካቲት 23/1988 ዓ/ም ዘልቆ ማታ 12 ሰዓት ላይ በኢትዮጵያውያን ድል አድራጊነት ተቋጨ ።

ከድሉ በኋላ አውሎም እና ጓደኞቹ ከኢትዮጵያ ጦር ጋር ተቀላቀሉ። ይኽንን ያየ አንድ የኢጣሊያን መኮንን ” አውዓሎም ! አውዓሎም ! ” ሲል ተጣራ ። አውዓሎምም ” ዘወአልከዩ አያውዕለኒ ” ብሎ መለሰለት ።

ከድል በኋላ በምኒልክ  የባሻነት እና የእንትጮ አሥተዳዳሪነት ማዕረግ ተሰጠው ። እንደሜ ጠግቧም ሞተ ። የእርሱ የልጅ ፣ ልጆች ግን ከ40 ዓመት በኋላ በ1928 ዓ/ም የኢጣሊያ ፋሺስት መንግሥት ኢትዮጵያን በአውሮፕላን በሚርከፈከፍ  በመርዝ ጋዝ ጭምር ታግዞ በዳቢሎሳዊ ድርጊት ወረራ አድርጎ ለአምሥት አመት በኃይል ሲገዛ የአውዓሎምን ዘር እያደነ መግደሉ በታሪክ ተመዝግቧል ።

ለአደዋ ድል የአንድ ሠራዊትን ያህል ትልቅ ሚና የተጫወተውን ጀግናችንን ባሻ አውሎም ሐረጎትን ሳስታውስ በፅሑፌ መግቢያ ምሥል ላይ ያሉትን ግንባር ቀደም ተፋላሚዎችን ሚናም አግዝፎ ለማሳየት ይኼ ጀግናችን በእጅጉ ይረዳል ብዬ በማሰብ ነው ። የፅሑፉን ሐሳብ ከ ” ጣይቱ ብጡል ” ከተሰኘ ከቀኛዝማች ታደሠ ዘወልዴ መፅሐፍ ማግኘቴንም እጠቅሳለሁ ።

ዓደዋ ለእኛ ኢትዮጵያውያን ብቻ ሳይሆን ለመላው ጥቁር ህዝብ የኩራቱ ምንጭ ነው ። በማንኛውም መልኩ ፣  የሰው እኩልነትንም ያረጋገጠ ፤ ፀረ ባርነት እንቅስቃሴን በመላው ዓለም ያፋፋመ ፣ ነጭ ከጥቁር የሚያንስበት ተፈጥሯዊም ሆነ ዓለማዊ ሁኔታ እንደሌለ  ያሥመሰከረ የጭቆና ቀንበር የተጫናቸው የጥቁር ህዝቦች ሁሉ  ድል ነው ።

ዛሬም እነ አፈወርቅ ገ/ኢየሱስ ፣ጳውሎስ ኞኞ እና ተክለፃድቅ መኩሪያ የፃፉትን የታሪክ ማሥታወሻ ደጋግመን በማስታወስ አንገታችንን ቀና አድርገን እንድንሄድ ያደረጉንን ጀግኖች አባቶቻችንን እንዘክራለን ። ክብር ለዓደዋ ሰማዕታት አባቶቻችን እንላለን ። የአኩሪ ታሪኳን ለማጥፋት በፍርፋሪ የተደለለን ባንዳ ሁሉ ዓላማህ ፣ በመቃብራችን ላይ ካልሆነ  ፈፅሞ አይሳካም ብለን እናስጠነቅቀዋለን ።

ታሪክን ካላወቅህ አንብብ ። እውነተኛ መሪዎች አንባቢዎች ናቸው ። ጊዜውን አመቻችቶ  ዘወትር  የማያነብ መሪ ፣ በወጉ ሊመራ አይችልምና ! እንሆ ካነበብኩት ከታሪክ ጥቂቱን ልጋብዝህ ።

ጳውሎስ ኞኞ

ጳውሎስ ኞኞ ‹‹አጤ ምኒልክ›› ብሎ ባሳተመው (1984 ዓ.ም.)

ካፒቴን ሞልቴዶ በጻፈው ደግሞ ‹‹. . . ከአራተኛው ባታሊዮን አንድ የሸሸ የኢጣሊያ ወታደር ወደ ካምፓችን ሲሮጥ መጣ፡፡ ካለሁበት በራፍ ላይ ሲደርስም ወደቀ፡፡ የእኛ ጦር ደጀን ነበር፡፡ በአረብኛ ቋንቋም ነገሩ ምንድን ነው? ምን ሆንክ? አልኩት፡፡ አለቁ፣ ሞቱ አለኝ፡፡ የወታደሩ ጠርቡሽ (ባርኔጣው) ካጠገቡ ወድቋል፡፡ ጠርቡሹን አቧራና ላብ በክሎታል፡፡ ኮቱ የመድፈኞች ኮት መሆኑን ባውቅም ምልክት ያለበት የኮቱ እጅጌ ተገንጥሎ ስለሌለ ከየትኛው መድፈኛ ክፍል እንደሆነ ላውቅ አልቻልኩም፡፡ በዚያ ክንዱ ላይም ክፉኛ ስለቆሰለ ደሙ በብዛት ይወርዳል፡፡ ዙርያውን ከብበን በጥያቄ አጣደፍነው፡፡ አንጌራ፣ ማንፍሬዲኒ፣ ቶዜሊ፣ አስካላ እያለ ይቃዣል፡፡

 

‹‹ምንድነው የምትለው! አልኩት

‹‹ሰላም መቶ አለቃ፡፡ አበሾች ደርሰዋል እዚህ ናቸው፡፡ የአራተኛው ወታደር ሁሉ አለቀ፡፡ ሁሉም ሞቱ፡፡ ማጆር ቶዚሊ ሞተ፡፡ አንጊራ ሞተ፡፡ ማንፍሬዲኒ ሞተ፡፡ ሁሉም፣ ሁሉም ሞቱ አለኝ፡፡

‹‹ንገረን እንዴት ሞቱ? አልኩት፡፡

‹‹ዛሬ ጧት፡፡ አበሾቹ ብዙ ነበሩ፡፡ ግማሹ ያህል ሞተ፡፡ ሌሎቹ ግን መጡብን፡፡ መድፍ ይተኮሳል፡፡ ጥይት ይተኮሳል፡፡ አበሾቹ ግን መጡብን፡፡ ኦህ ስንትና ስንት መሰሉህ፡፡

 

‹‹በማን ውስጥ ነበርክ? አልኩት፡፡

‹‹ማንፍሬዲኒ ውስጥ፡፡

‹‹አይተሃል እሱን?

‹‹አዎን አይቼዋለሁ፣ ሞቷል፡፡

‹‹አስካላንስ አይተኸዋል?

‹‹አዎን አይቼዋለሁ፣ ሞቷል (አስካላ ግን ቆስሎ ተማርኳል) ሁሉንም አይቻለሁ፡፡ ሁሉም ሞተዋል፡፡ ታመልጡ እንደሆነ እናንተም አምልጡ፡፡ አበሾቹ ከኋላዬ ናቸው፡፡ ጥፉ አለን የኢጣሊያ ሶማሌ ላንድ ወታደር. . . .››

አፈወርቅ ገ/የሱስ

አፈወርቅ ገብረ የሱስ ደግሞ ‹‹ዳግማዊ አጤ ምኒልክ›› በሚባለው መጽሐፋቸው ‹‹. . . ወታደሩ ሌሊቱን ሙሉ በጀርባው ከባድ ኮረጆውን፣ በጫንቃው ጠመንጃውን፣ በቀኝ ጎኑ የጥይት ከረጢቱን ተግራ ጎኑ የውሃ ታኒካውን ተሸክሞ የገረረ ከባድ ጫማውን እስከ ጉልበቱ አጥልቆ ደልቀፍቀፍ እያለ በዚያ ጭንጫ፣ በዚያ አቀበትና ቁልቁለት ያ ሁሉ ፈረንጅ፣ ያ ሁሉ ጎበዝ፣ ያ ሁሉ ወጣት ልጅ ባገሩ እንዲያ ሲያምርበት በሰው አገር ላሊበላ ሳሚ መስሎ ኮርፈፍ፣ ኮርፈፍ ሲል. . . ሲማስን ሲደክም ሲንደላቀፍ አድሮ . . . ሲነጋጋ አባ ገሪማ ደረሰና መድፉን ጠመደ፡፡ ጦርነት ተጀመረ፡፡ ከዚያማ ወዲያ ምን ያነጋግራል፡፡ ኢትዮጵያዊው. . . አደጋ እንደተጣለበት ባየ ጊዜ የቸኮለ በሌጣው፣ ያልቸኮለ በኮርቻው እየተሰካ እየፎከረ እየተንደቀደቀ ገባበት፡፡ የቀረው ግን ገና እንቅልፉን አላሳብ ተኝቶ ነበር፡፡ የኢጣሊያ መድፍ ነው በማለዳ የቀሰቀሰው፡፡ የሸዋ ፈረሰኛ፣ የጎጃም እግረኛ፣ የትግሬ ነፍጠኛ፣ ያማራ ስልተኛ ከቦ ያናፋው፣ ይቆላው ያንደገድገው ጀመር፡፡ ከእንዝርት የቀለለ የጁዬ፣ ተነብር የፈጠነ በጌምድሬ፣ [ሐሞተ ቆራጡ] ትግሬ. . ፈጀው፤ ሰጣው፤ ዘለሰው፡፡ ወደኋላ ቀርቶ የነበረው ሁሉ ነገሩን ሳያውቅ ወደ ጦርነት ሲጓዝ ነበር፡፡ ነገር ግን የጄኔራል ባራቲየሪን መሸሽና የጦሩን መፈታት ባየ ጊዜ ያ ሁሉ ወደኋላ የነበረ ኢጣሊያ መድፈኛ እየጣለ፤ በመድፉ ሥፍራ እሱ እየተተካ በአጋሰሱ ሳይተኮስ እስከ ጥይቱ እስከ መንኮራኮሩ ወድቆ ቀርቶ ተያዘ፡፡ . . .›› ብለዋል፡፡

 

የታሪክ ጸሐፊው ተክለ ጻድቅ መኩርያ ” ዓፄ ምኒልክ እና የኢትዮጵያ አንድነት ። ” በሚል መፀሐፋቸው ሥሐ ባሻ አውዓሎም እንደፃፉት ።

የዓድዋ ጦርነት ሲነሣ ሁሌም የሚወሱት ባሻዬ አውዓሎም ሐረጎት ናቸው፡፡ በስለላ ሙያቸው ተጠቅመው የኢጣሊያን የጦር እቅድ በማሳከር አኩሪ ተግባር አከናውነዋል፡፡ የታሪክ ጸሐፊው ተክለ ጻድቅ መኩርያ እንደጻፉት ለዓድዋው ድል ዋና መድን የሆነው የስለላ ሥራ ነው፡፡

‹‹የዓድዋ ሥላሴን ጠላት አረከሰው

ገበየሁ በሞቴ ግባና ቀድሰው›› የተባለላቸው ፊታውራሪ ገበየሁ፣

‹‹ገበየሁ ቢሞት ተተካ ባልቻ

መድፍ አገለባባጭ ብቻ ለብቻ›› የተባለላቸው ደጃዝማች ባልቻ፣

‹‹ክፉ አረም በቀለ በምጥዋ ቆላ

አሁን ሳይበረክት አርመው አሉላ፡፡

አሉላ አነጣጥረህ ቶሎ አወራርዳቸው›› የተባለላቸው ራስ አሉላ አባ ነጋና ሌሎች ጀግኖች የጋለ አርበኝነትና የላቀ ጀግንንነት ተደምሮበት ቢሆንም  ፣ በግልፅ ና በጨበጣ ውጌያ ለመፋለም   ዕድሉ የተገኘው  ፣ ከምሽግ አልወጣም ብሎ ያስቸገረው የኢጣሊያ ጦር በባሻይ አውዓሎም ሐረጎት ሐሰተኛ ምሥጢር አቅራቢነት እና  እና በብላታ ገብረ እግዚአብሔር ጊላ ማርያም  ዕቅድ ተታሎ ከምሽጉ በመውጣቱ ነው፡፡

የእንትጮው ተወላጅ ባሻ አውዓአሎምን በስለላ እንደምን አገራቸውን እንዳገለገሉ ያገራችን ሽማግሌዎች ከሚያውቁት ጋር ካርሎ አናራቶሬ የሚባለው ኢጣሊያዊ እንደዚህ ሲል ጽፏል፡፡

‹‹ባሻ አውአሎም የሚባለው ከሰላዮቻችን አንዱ ነበር፡፡ እርሱም ለጠላታችንም ሰላይ ነው፡፡ ከዓድዋ ጦርነት ከብዙ ቀን በፊት በራስ መንገሻ አቅራቢነት ከዐፄ ምኒልክ በተገናኘ ጊዜ ጠንክሮ እንዲሠራ አደራ ተቀብሎ ተሰናበተ፡፡ ራስ መንገሻ እንደነገሩትም አውዓሎም ወደ ዠኔራል ባራቲዬሪ መጥተው፤ ‹‹የኢትዮጵያ ጦር ስንቅ አልቆበታል፡፡ ብዙም ወታደሮች ሞተዋል፤ የቀሩትም ታመዋል፡፡ ስለዚህ በዓድዋም ከመቀመጥ ወደኋላም ከመመለስ ወደፊት ወደ ቅኚው አገር መረብን ተሻግረው አልፈው ስንቅ ሊፈልጉ ነው፡፡ አለዚያም ደግሞ በየካቲት 23 ቀን ንጉሡ እንደ ፊተኛው አሳቡ ወደኋላ ለመመለስ ነው ብሎ ተናገረ፡፡›› አቶ ተክለ ጻዲቅ እንደጻፉት ከዚህም ወሬ የስንቁ ማለቅ፣ የበሽታው መግባትና ወደኋላ ለመመለስ መታሰቡ እውነት ነው፡፡ ወደፊት ወደ ኤርትራ ሊገቡ አስበዋል ያለው ግን አሰቱ ነው፡፡ ባራቲዬሪ ለመዋጋት የቆረጠው በተለይ በነዚህ ወሬዎች ተመሥርቶ ይመስላል፡፡

ባሻ አውአሎም በ22 ሰዓት (ከሌሊቱ በ10 ሰዓት) የተደረገውን የእኛን ሰልፍ በተመለከተ ጊዜ የኢጣሊያኖች ጦር መጣ ብሎ እንዲነግር አንድ ወጣት ላከ፡፡ ምኒልክ ግን ሌሊት አገር ለመፈተሽ የወጡ ወታደሮች ይሆናሉ እንጂ ጣሊያኖች ውጊያ ቆርጠው የሚወጡ አይመስሉኝም ሲሉ መጠርጠራቸውን ገልጸው ቢሆንም በጥንቃቄ መጠባበቅ ነው የሚል ትዕዛዝ ለራስ መንገሻ ላኩባቸው፡፡ ይህም ሰላይ ከዤኔራል ባራቲዬሪ ጋር ሆኖ ወደፊት ተጉዞ እኩለ ሌሊትም ራዓዩ ተራራ ሲደርስ ከእኛ ጦር ውስጥ አምልጦ የቱሪቶ ባታዩ ከመድረሱ በፊት ወደ ራስ መንገሻ ሰፈር ደረሰና በጊዜው ለራስ አሉላ፣ ለራስ መንገሻ፣ ለዋግሹም ጓንጉል ነገረ፡፡ ለነዚህም ራሶች፣ ራስ ወሌና ራስ መኰንን ደረሱላቸውና ሁሉም በአንድነት ግንባር ቀደሙና የኢጣልያ ጦር መታኮስ ሲጀምር ለመዋጋት ተዘጋጁ፡፡

ከድል በኋላ የተደረገ አቀባበል

( ዛሬ የኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት ይህንን በማስታወስ ይሆንን የድል በዓል በበላይነት እኔ እየመራው በደማቅ ሁኔታ  አብረን እናከብራለን ያለን ። እንዲህ ከሆነ እሰየው ! በርታልን ! ጀግናችን  !! ከጎንነህ ነን ! እንለዋለን ። )

 

አዲስ አበባ ከድል በኋላ ፣ ዓፄ ምኒልክ ከነሠራዊታቸው ፣ ምረኮኞችን ይዘው ሲገቡ ፣  በሊቀ መኳስ አባተና በጭፍሮቻቸው ትጋት ቀደም ብለው አዲስ አበባ ደርሰው በደንብ ተጠምደው የሚጠባበቁት መድፎች የደስታ ድምፃቸውን አሰሙ፡፡ በተረፈ ምንም ተጽፎ ባናገኘው ከመናገሻ ከተማ ውጭ ከሰባት ወራት በላይ በዘመቻ ያሳለፉት ንጉሠ ነገሥት ከነጦራቸው የድል አድራጊነትን ግርማ ተጎናጽፈው ከከተማው ሲገቡ ወንዱ በሆታ፣ ሴቱ በእልልታ፣ በታላቅ የደስታ ግርግር እንደተቀበሉዋቸው የታወቀ ነው፡፡ ጸሐፌ ትእዛዝ ገብረ ሥላሴ የቤተ ክህነቱን አቀባበል ሲያመለክቱ በዚህ ታላቅ አገባብ ላይ የከተማውን ሕዝብ የሞቀ አቀባበል አልዘረዘሩትም፡፡

 

በካህናቱ በኩል የተደረገውን አቀባበል ግን የእንጦጦ ማርያምና የራጉኤል፣ የሥላሴና የዑራኤል እንደዚሁም የጊዮርጊስ ካህናት ልብሰ ተክኗቸውን እየለበሱ ቀደም ብለው በሰፊው ጃንሜዳ ተሰብስበው ይጠብቁ ስለነበር፣ ‹‹ወምድርኒ ትገብር ፋሲካ ተሐጺባ በደመ ኢጣልያ››-መሬቷ በኢጣሊያ ደም ታጥባ ፋሲካ (ደስታ) አደረገች፡፡ የሚለውን ጠቅሰው በንጉሠ ነገሥቱ ፊት አሸበሸቡ ሲሉ አመልክተዋል፡፡

ከድሉ በኋላ ምን ተባለ ?

ከድሉ በኋላ በአዲስ አበባና ሮም ስለነበረው ልዩ ክሥተት አቶ ተክለ ጻድቅ መኩሪያ ከጻፉት ውስጥ የሚከተሉት ይገኙበታል::

 

አዲስ አበባ – ፈረንሣዊው የዓድዋ አርበኛ

የካቲት 23 ቀን ከማለዳ ጀምሮ እስከ እኩለ ሌሊት በቆየው በዚህ ጦርነት የሞቱት ብዙዎች መሆናቸው ግልጽ ነው፡፡ በንጉሥ ተክለ ሃይማኖት፣ በየራሶቹና በየደጃዝማቾቹ ውስጥ ሆኖ ዘምቶ የሞተውና የቆሰለው ብዙ መሆኑ ሲታወቅ ከሰነድ ጥፋት የተነሳ ስማቸውን በዚህ የታሪክ መጽሐፍ ላይ ለማንሣት አለመቻሉ ያሳዝናል፡፡

ከዚህ ጋር ደግሞ ካፒቴን ክሎሼት የሚባል የፈረንሳይ ተወላጅ በበጅሮንድ ባልቻ ውስጥ ሆኖ በመድፍ ኢጣልያኖችን በመውጋት ኢትዮጵያን የዓድዋለት ማገልገሉን ልናስታውስ ይገባል፡፡ እርሱም በፈረንሣይ ጦር ሠራዊት ውስጥ በመድፈኛ ክፍል ሳለ ላፄ ምኒልክ ገብቶ በጦር ትምህርትና በሌላውም በብዙ ወታደር ነክ ጉዳይ ሲመክርና ሲያገለግል የቆየ ነው፡፡ በጦርነቱ ዋዜማ ዓመቱን ሁሉ ወታደሩን የጠመንጃና የመድፍ አተኳኮስ ሲያስተምር የነበረ ይባላል፡፡ በኋላም ጦርነቱን ለመካፈል አልጋውን ከሚጠብቁት ከራስ ዳርጌ ተሰናብቶ ከአዲስ አበባ ወደ ጦሩ ግንባር መጥቶ የካቲት 22 ቀን ደረሰ፡፡ በማግሥቱ ሲዋጋ ውሎ ከድሉ በኋላ በተራው እንደ አንድ ኢትዮጵያዊ መኰንን ባፄ ምኒልክ ፊት ሲፎክር የተማረኩት ኢጣልያኖች አይተውታል፡፡

ጄዎቫኒ ቴዶኒ የሚባለው ምርኮኛ የጦር መኰንን በጻፈው ውስጥ ስለ ካፒቴን ክሎሼት እንደዚህ ይላል፡፡ ‹‹. . .በ6 ሰዓት በንጉሡ ድንኳን ፊት እኛ እስረኞቹ ስናልፍ ከንጉሠ ነገሥቱ ድንኳን በራፍ ላይ እግሩን አጣምሮ የተቀመጠ ጠጉሩ ወርቅማ (ብሎንድ) እኛን በንቀት እያየ የሚስቅ ነጭ አየሁ፡፡ ብሏል፡፡

ሮም – ‹‹ክሪስፒ ይውደቅ፤ ምኒልክ ሕያው ይሁን››

ከሁሉም ከተሞች ግርግሩ የነበረው በዋናው ከተማ በሮም ነበር፡፡ በዚያም ወጣቶቹ በጩኸት ትእይንት በሚያደርጉበት ጊዜ ኦዲስካልኬ የሚባለው መስፍን በትሪቶኒ አውራ ጎዳና በጋሪ ተቀምጦ ሲያልፍ አግኝተው በፊቱ ላይ ጭቃ እየረጩ ከበቡት፡፡ ወዲያውም ‹‹ምኒልክ ሕያው ይሁን›› በል እያሉ አስፈራሩት፡፡ ጠቅላይ ሚኒስትር ክሪስፒንም አወገዙት፡፡ እርሱም ‹‹ኢጣልያዊ ስለሆንኩ ኢጣልያ ሕያው ትሁን እላለሁ እንጂ ምኒልክ ሕያው ይሁን አልልም›› እያለ ሲጨቃጨቅ በመካከሉ የንጉሡ ዘበኞች (ካራቢኒያዎች) ደርሰው በግድ አስጥለውት በጋሪው ለማምለጥ ቻለ፡፡ በዚሁ ጊዜ የመሸነፉ መዋረድ አንሶ እዳር ቆሞ የሚመለከተውን በጣም ያስገረመውና ያነደደው፤ ‹‹ክሪስፒ ይውደቅ ምኒልክ ሕያው ይሁን›› የሚለው ጩኸት በወጣቶቹ ዘንድ መሰማት ነው ።

የአደዋን የጀግንነት ፍልሚያ የመሩት ዋና ፣ ዋና ኢትዮጵያዊያን ፣ የሚከተሉት ናቸው ።

_እምዬ ምኒልክ ወይም ዓፄ ምንሊክ ንጉሣችን ፤ እቴጌ ጣይቱ  ፣ አሥተዋይ ና አርቆ አሳቢ ንግሥታችን ።

_ራሥ መንገሻ ዮሐንስ

_ራሥ ሚካኤል ዓሊ ( በኋላ ንጉሥ ሚካኤል )

_ራሥ ወሌ ብጡል

_ራሥ አባተ ቧ ያለው

_ደጃዝማች ባልቻ ሳፎ

በኢጣሊያ በኩል ደግሞ ጦሩን በዋናነት የመሩት

_ጀነራል ባራቴዬሪ

_ጀነራል ደቦርሜዳ

_ጀነራል አሪሞንዲ

_ጀነራል ማቲዎስ

 

ዓደዋን ዘላለማዊ ባለታሪክ ለማድረግ ፣ በአደዋ ከተማ ታላቅ አፍሪካዊ ዩኒቨርስቲ እና የጦር አካዳሚ መገንባት አለበት እላለሁ ። አደዋ ሌለኛዋ የጥቁር ህዝቦች መነሀርያ ሆና የልጅ ልጆቻችን ማየት ይኖርባቸዋል እላለሁ ። በፅሑፌ ማሳረጊያ ።

Leave a Reply

Your email address will not be published.

Latest from Blog

ከሃይለገብርኤል   አያሌው የኦቦ ሲራጅና የወይዘሮ ፉንታዬ ልጅ ጃዋር መሃመድ ትላንትን ዛሬንና ነጋችንን ሊያሳይ የሚችል መጽሃፍ አዘጋጅቶልናል:: በእውነቱ መጽሃፉ ሊነበብ በሚችል የሃሳብ ፍሰት ተቀንብቦ በአነጋጋሪነቱ ቀጥሏል:: ጃዋርን እና የቄሮን ትውልድ በቅጡ ለመረዳት መጽሃፉ ማንበብ

የጃዋር የፖለቲካ ጅዋጅዌ! “ድመት መንኩሳ አመሏን አትረሳ’’

ጥር 2 ቀን 2017 ዓ/ም   January 10, 2025  በኢትዮጵያዊነታችሁ፡ በኦርቶዶክሳዊ እምነታችሁ፡ በአማራነታችሁ፡ በአማረኛተናጋሪነታችሁ፡ በተሰነዘረባችሁ ብትር፡ ቤተ ሰብ፡ ወዳጅ ዘመዶቻችሁን ያጣችሁ: ልጆቻችሁን የቀበራችሁ፡ አካልችሁን ያጣችሁ፡ የተሰነዘረውን ብትር በመከላከል ላይ ያላችሁ፡ያለፈቃዳችሁ በመንግሥት ተጽእኖ ወደመግደልና

በኢትዮጵያዊነታችሁ፡ በኦርቶዶክሳዊ እምነታችሁ፡ በአማራነታችሁ፡ በአማረኛ ተናጋሪነታችሁ፡ በተሰነዘረባችሁ ብትር፡

January 10, 2025
መኮንን ሻውል ወልደጊዮርጊስ ¹⁵ የምድርም ነገሥታትና መኳንንት ሻለቃዎችም ባለ ጠጋዎችም ኃይለኛዎችም ባሪያዎችም ጌቶችም ሁሉ በዋሾችና በተራራዎች ዓለቶች ተሰወሩ ፥ ¹⁶ ተራራዎችንና   በላያችን ውደቁ በዙፋንም ከተቀመጠው ፊት ከበጉም ቍጣ ሰውሩን ፤ ¹⁷ ታላቁ የቁጣው ቀን  መጥቶአልና ፥ ማንስ ሊቆም ይችላል ? አሉአቸው ። ራእይ 6 ፤  15_17 ይኽ የመጽሐፍ ቅዱስ ቃል ። የኢየሱስን ልደት ሰናከብር የየሐንስ ራእይን ማንበብ ጠቃሚ ይመስለኛል ። ምክንያቱም በመጨረሻው ዘመን

ከኢየሱስ የፍርድ ቀን በፊት በህሊናችን ውስጥ ፍቅርን ለማንገስ እንጣር 

የምጣኔ ሀብታዊ ፍጥ፣ የፖለቲካ፣ የእውነትና የሰብአዊ መብት ታጋይ፣ የአመኑበትን ነገር ለመናገር እንደ ፖለቲከኛ በቃላት ሳያሽሞነሙኑ ቀጥታ የሚናገሩት የሀገሬ ኢትዮጵያ ታላቅ ሰው ነበሩ “ዘር ቆጠራውን ተዉት፤ የአባቶቻችሁን ሀገር ኢትዮጵያን አክብሩ!”  አቶ ቡልቻ ደመቅሳ

ሀገር ወዳዱ አቶ ቡልቻ ደመቅሳ ከዚህ አለም በሞት ተለዩ

January 6, 2025
ግን ይህ ሁሉ ወጣት የት ገባ? ግን ይህ ሁሉ ወጣት የት ገባ? ዛሬ፣ 2025 ዓ/ም ላይ ብንገኝም በዝንጋታ ገመድ ወደ ሞት እየተጎተትን እንደሆነ አናውቅም። (ሁል ጊዜ የሚሞተው የገነዝነው ይመስለናል። ) “ገብርዬ ነበረ

ግን ይህ ሁሉ ወጣት የት ገባ?

January 3, 2025
Go toTop