ሲና ዘ ሙሴ
” የሚበላውን እና የሚለብሰውን ያጣ ደኻ ፣ የተወለደበትን አገር የሚወድበትን ምክንያት ያጣልና የአገሩ መንግሥት ቢበረታ ወይም ቢጠፋ ግድ የለውም ። …”
የነጋድራስ ገ/ህይወት ባይከዳኝ ዘላለማዊ መልዕክት እንሆ !
የሚበላውን እና የሚለብሰውን ያጣ ደኻ ፣ የተወለደበትን አገር የሚወድበትን ምክንያት ያጣልና የአገሩ መንግሥት ቢበረታ ወይም ቢጠፋ ግድ የለውም ። ስለ ሁም መንግሥት የሚጠቀምበት የአገሩ ሀብት በጥቂት ሰዎች እጅ ሲሰበሰብ አይደለም ። የአገሩን ሀብት በመላው ህዝቡ ሲከፋፈለው ነው እንጂ ። የሀብታምች አኗኗር እና የሠራተኛው ደኻ አኗኗር አይነቱ እንበለ መጠን የሚራራቅበት አገር መንግሥቱ ከጥፋት አፋፍ እንደደረሰ ያስረዳል ። የኢትዮጵያን ህዝብም ሁኔታ ብንመለከት እንደዚህ ያለ ጥፋት እንዳይደርስ ያስፈራል ።
በአንድ ፊት ነግደው የሚያድሩት የውጪ አገር ሰውች እና ለህዝቡ አንዳች ጥቅም ሳይሰሩ ድካሙን እየቀሙ አንዳንድ ሹማሙት ደኅና ደኅና ቤት እየሰሩ እያጌጡ የተመቸ ኑሮ ሲኖሩ እናያለን ። በአንድ ፊትም የዕለት ምግብና የአንድ ዓመት ልብስ እናገኛለን ሲሉ ብዙሺ ድኾች ወባና ችጋር ፈጅቷቸው ከድሬዋ አንስቶ እሥከ አዲስ አበባ ድረስ ከምድር ባቡር ጎን ለጎን አልፈው ፣ አልፈው ተቀብረዋል ። ግማሾቹም የተቀበሩበት መቃብር ጠሊቅ ሥላልሆነ ዱሮ አጥንታቸው ወጥቶ ከምድር ባቡር መንገድ ግራ ና ቀኝ ተበታትኗል ።
ደግሞም ይኽን ያህል ሩቅ መንገድ መሄድ አያስፈልገንም ነገሩ ፣ በየከተማው ውሥጥ ይገለፃልና ። ያማረ የግንብ ቤትና ትንንሽ ጎዦ አጠገብ ለአጠገብ ተሠርተው እናያለን ። ባንዱ ቤት ውሥጥ ትልቁ ጌታ ህዝቡ ደክሞ ያፈራውን ገንዘብ ሲያባክን በጎዦው ውስጥ የሚኖረው ደሃ የሚበላው ፣ የሚለብሰው ና የሚያበራው አጥቶ በረኻብና በብርድ ተጨብጦ በኩበት ጪስ እና በእድፍ ውስጥ ይጨማለቃል ። በአንዱ ቤት ጌትነቱ እየበዛ ሲሄድ በአንዱቤት ድህነቱ እየሰፋ ይሄዳል ። የጎዦውን እና የአዲሱን ግንብ ቁመት ብናስተያይ በአገራችን ደሃ ና ጌታ እንዴት እየተራራቁ እንደሄዱ ይገልጹልናል ። ይኽ ግን ለመንግሥት ክፉ ምልክት ነው ። ይኽም ክፉ ነገር እየሰፋ እንዳይሄድ መንግሥት ህዝቡን በሥራ እንዲያሠለጥን ያስፈልገዋል ። ህዝቡ በሥራ ከሠለጠነ ዘንድ ጌታና ደሃ እንደገና ይቃረባሉ ። በምክርና በኃይልም ተደጋግፈው የመንግሥታቸውን መሠረት ያጠናክራሉ ። ብርና ወረቅም ረዳቶች የለውጥ መሣሪያዎች የሚሆኑት በዚያን ጊዜ ነው ። ( መንግሥትና የህዝብ አሥተዳደር ተፃፈ በነጋድራስ ገ/ህይወት ባይከዳኝ ገፅ 119 እና 120 ) የብዕረኛው መልዕክትለም” በቃላት መጫወትን እንመርጣለን ? “ጉርጥ አደፈጠ ወይም ዘለለ ያው ጉርጥ ነው ። ”
ኦነግ ሸኔ ኦነግ ነው ። የአማራ ሸኔ የተባለው የአማራ ፋኖ መሆን ግን አይችልም ። በግልፅ በአደባባይ ሰው የሚያርደውን የሤጣን ስብስብ ቡድን ሥም ለአማራ መሥጠት በእውነቱ ሥርኤት የሌለው ሐጢያት ነው ። ጠቅላዩ በቅርብ ሰዎቻቸው አሉባልታ ብዙን ጊዜ ካልተሸወዱ በሥተቀር ይኽንን ተራ ሥህተት አይሳሳቱም ለማለት የሚያሥችል ጥርጣሬ ግን አለኝ ። ሙሉ ንግግራቸውን ያዳመጣችሁ እንደሆነ ኮንፊውዝድ የሆኑ ይመሥላል ።
በእርግጥ በግል ጠቅላዩ ያላቸው ሁለት እግር ነው ። እናም በአንድ ጊዜ ሁለት ዛፍ ላይ መውጣት አይችሉም ። ነገር ግን ሺ ዛፍ ላይ የሚወጡ የደህንነት ሰራተኞች አላቸው ። እውነቱን ከእነሱ ቢሰሙ ይኽን መሠል ከእውነት የተጣረሰ ንግግር አይናገሩም ነበር ።
በእርግጥ ቅድሚያ የሚሰጠውን የሠንግሥት ሥራ ትቶ ነገ ሠላም ከሌለ ወደ ሚፈራርስ ፕሮጀክት ላይ ማተኮር ህፃንነት ነው ። ህፃናት በብልጭ ነገር እንደሚታለሊ ይታወቃል ። ዋናው እና ትልቁ ችግር መቀመጫ ላይ የተሳካ እሾህ ነው ። እርሱን ሳይነቅሉ የ20 እና የ40 ቢሎን ለሠገንባት መነሳት ትርፉ ለቻይና ሀብታሞች ና በቋንቋ ለተቧደኑ ሌቦች ነው ።
ጥቅላዩ አሥተዋይ እና ከሥልጣን ሥግብግብነት የፀዳ አእምሮ ያላቸው መሆኑንን የምናረጋግጥበት 11 ኛው ሰዓት ላይ ደርሰናል ። ከአጠገባቸው ያሉትን የቋተቧዳኞች ፣ ወንዜኘዎችን እየሰሙ ከሄዱ ግን በቅርቡ ብልፅግና ተረት ይሆናል ። ኢትዮጵያ ግን በድል ትቀጥላለች ። …
ዘረኝነት ያበዱ ሰዎች በቅርቡ ይጠፋሉ ። የደሃው ህዝብ ትዕግሥት ተሟጧል ። ሰው መሆናቸውን የካዱ ሰዎችን ተሸክሞ አመታትን አይጓዝም። የሥልጣን አረቄ ጭንቅላታው ላይ ወጥቶ በሥካር ህዝብን የሚያሥተዳድሩ ሰዎችን ይዤ ህዝብን እንደ ህዝብ ፈቃድ ሊያሥተዳድር የቻለ መንግሥት እንደሌለም ሳይረፍድባቸው ከታሪክ ይማሩ ።
የሥልጣን አረቄ ናላቸውን ባዞረው ጨካኝ እና ግፈኜ ፣ በለሥልጣናት ላይ ፣ የፈጣሪ ቁጣ በየቤተሰባቸው ላይ ጭምር ቁጣውን መውረዱ አይቀርም ። እሥከዛሬም የቤተሰቦቻቸው እና የኃይማኖት ሰዎች የዘወትር የልብ ፀሎት እንዲሁም የልጆቻቸው ፀሎት ጠብቋቸው ( ጠቅላይ ማኒሥቴሩንም ጨምሮ ) ይኸው አገር እየመሩ ነው ።
ዛሬ እና አሁን ግን ጠቅላዩ አውቀውም ሆነ ሳያውቁ ፤ ወደው ይሁን ተገደው ፤ ግልፅ ባልሆነልን ሁኔታ የተወሰነ Conspiracy እያስተዋልንባቸው ነው ። የሚያነሱት ምሳሌ እና ምሣሌያዊ አነጋገር ከአምክንዮ ውጪ የሆነ ፣ ሣይንሣዊ እና ፖለቲካዊ ጭብጥም የሌለው የህፃን ማባበያ የመሠለ ሆ፣ ግራ አጋቢ ሆኖብናል ።
አሁን ማን የእያንዳንዱ ግለሰብ ፣ የእምነት ፣ የባህል ( ቋንቋንም ይጨምራል ) አይከበር አለ ? እንዴ ! በትልልቅ የኢትዮጵያ ከተሞች ( መቀሌም ከወያኔ ጥጋብ በፊት እኮ ከመላው ኢትዮጵያ በእንጀራ አሥገዳጅነት የመጡ ሰዎች ፣ አንድ ባህል ያላቸውን ያህል ተከባብረው ፣ ተፋቅረው ፣ አንድ ላይ መዕድ ቆርሰው ሲኖሩ እኮ ነው የምናየው ። ህዝብ እኮ አልተለያየም ።
ዛሬ የወጣቶቹ መፋቀር የሚያሥቀና ነው ። ፖለቲከኞች ግን በአጥር ውሥጥ ሥላሉ የህዝቡን ፍቅር አያሥተውሉም ። እታች በቀበሌ ደረጃ ካሉት አመራሮችም ጋር ሆዳሙ እና መድረሻ ቢሱ እንጂ የየከተሞቹ ኗሪዎች ተሰብስበው አያውቁም ። በወያኔ ጊዜም ይኸው ነበር ።… እናም ይህንን እውነት አብይ ካላወቅህ እንደ ጉተማ ቡዳህ አንድ ቀን መናኛ ልብስ ለብሰህ ፣ እራሥህን ለውጠህ ከቤተመንግሥትህ ከአንድ ታማኝ ወታደር ጋ ውጣና የህዝቡን እውነት ተረዳ ። እንደጉተማ ቡዳህ ቤተመንግሥት በቃኝ ። እንደማትል ግን እ ነዘባለሁ ። ሆኖም ወቅታዊውን እውነት እና የፖለቲካውን ሸፍጥ በቅጡ ታውቃለህ ። …
ውድ ጠቅላይ ሚኒስትራችን ፤ የወያኔ ህገ መንግሥት የፌደራል እና የክልልን አወቃቀር ከቋንቋ አኳያ እኮ ነው ፤ የሚያየው ። እንዲሁም እያንዳንዱ ክልል እንደ አንድ ሉአላዊ አገር ህገ መንግሥታዊ መብቴ ነው ፣ ብሎ ቋንቋውን እና የቋንቋውን የጎሣ አባል ብቻ በክልሉ እንደ ዜጋ ሌላውን ጎሣ ና የማህበረሰብ ክፍል መጤ አድርጎ ነው የሚቆጥረው። ዜጎች በዚህ ህገመንግሥት እሥከተመሩ ድረስ ፣ መላዋ ኢትዮጵያ አገራቸው በተግባር አገራቸው እንዴት መሆን ትችላለች ?
ምድር ላይ ያለው የዛሬው ዕውነት
ዛሬ ሰዎች በፖለቲካ አሥተሣሠባቸው ፣ ” ለምን ለእኔ ቋንቋ አልወገንክም ? ለምን ሰው ነኝ በማለት ከዜጎች እውነት ጋር አበርክ ? …ከሰዎች ማህበራዊ ህይወት እና ኑሮ ጋርወገንክ ? ዜጎች ሰው እንጂ መግባቢያ ቋንቋ አይደሉም በማለት በሚዲያ ተሟገትክ ? “ እየተባሉ እየታሰሩ ያሉት በወያኔያዊው አሥተሣሠብ የተቃኙ የፖሊሥ ሹመኞችና የህግ ሰዎች በብልፅግና (…) ውሥጥ ሥላሉ ነው ። ይኽ ቆሞ ቀር አሥተሣሠብ ነው ። አሥተሣሠቡሞ የመነጨው ፖለቲካው ካሥገኘው ጥቅም አንፃር ነው ። ፖለቲካው ዛሬም ፣ ኦህዴዳዊ ፣ ብአዴንናዊ እና የደቡብ ህዝቦች ነው። ከፖርቲነት የተቀነሰው ህውሃት ብቻ ነው ።
ከዚህ እውነት አንፃር ፣ ብልፅግና ፖርቲ አዲስ አይደለም ። በጥገናዊ ለውጥ ሰበብ ፣ የመወሰን ሥልጣን የሌላቸውን አጋር የነበሩትን ክልሎች ፣ በጥደፊያ አባል አድርጎ የአገሪቱን የአምሥት ዓመት ሥልጣን የያዘ ጠንካራ መሠረት የሌለው በአድር ባይ ካድሬዎች የተሞላ ቁጥር 2 ኢህአዴግ ነው ፤ ብልፅግና ተብሎ በድራማዊ መንገድ የተፈጠረው ። ይኽ የነቶሎ ቶሎ ቤት አሠራርን የሚያመለክት ፤ ዘመናዊነትን ያልተከተለ የፖርቲ አደረጃጀት መንገድ የዛሬው ጦስ ጥንቡሣሥ አዋላጅ ነው ። …
አብይ መራሹ መንግሥት በድንገት ቢንኮታኮት ድንገት ሥልጣን ለያዘው ባለጠመንጃ የሚያሸረግዱ ናቸው የብልፅግና አባላት ። አብዛኞቹ ሆድ እንጂ መርህ የላቸውም ። የፖርቲውን ራዕይ ፣ ዓላማና ግብ ፈፅሞ የማያውቁ ፣ ቢያውቁም በተግባር የተለያዩ ናቸው ። ለኃይለኛው ለመሰለፍ አይናቸውን የማያሹ ፤ ኮሽ ሲል ወደ ውጪ ለመፈርጠጥ ሻንጣ የሚሸክፉ ቦቅባቆች ናቸው ። ዕድሜ ለኢትዮጵያ ልጅ ፣ ለመከላከያ ና ለፋኖ ይበሉ ። ከሞት አፋፍ ነው የመለሣቸው ። ዛሬም ከነዚህ ገሚሶቹ ፣ በሱስ የተበከሉ ህሊና ቢሶች ናቸው ። ቁጥራቸው የትየለሌ የሆነ ህሊና ቢስ ፣ የበሰበሱ አባላትን ይዞ በሥመ ብልፅግና አገርን ወደ ብልፅግና መውሰድ እንዴት ይቻላል ?
ደግሞስ ፣ ህገ መንግሥቱ የፌደራል እና የክልልን አወቃቀር ከቋንቋ አኳያ እያየ እንዴት አሥተማማኝ ሰላም በአገር ሊመጣ ይችላል ? ዛሬ እና አሁን ፣ እያንዳንዱ ክልል እንደ አንድ ሉአላዊ አገር ህገ መንግሥት ብሎ ቋንቋውን እና የቋንቋውን የጎሣ አባል ብቻ በክልሉ እንደ ዜጋ ሌላውን ጎሣ ና የማህበረሰብ ክፍል መጤ አድርጎ ነው የሚመለከተው ። ዜጎች በዚህ ከፋፋይ የአፖርታይድ ህገመንግሥት እሥከተመሩ ጊዜ ድረስ ፣ መላዋ ኢትዮጵያ አገራቸው አትሆንም ።
አንድ ኦሮሞ ትግራይ ሄዶ ኑሮውን መመሥረት ፤ ቤተሰብ እና ሀብት ማፍራት ቢችልና እርሱ ዕድሜ ጠግቦ ቢሞት ና የልጅ ልጆቹ በመቀሌ የቱንም ያህል ቢበዙ በትግራይ ህገ ንግሥት መሰረት የመምረጥ እንጂ የመመረጥ መብት አይኖራቸውም ። በተገላቢጦሽ ትግሬውም ኦሮምኛን አርሲ በመወለዱ አቀላጥፎ ቢናገርም በትግሬነቱ ምክንያት ” ጨፌ ” ወይም ምክር ቤት ለመግባት አይችልም ። በተቀሩትም ክልልች እንዲሁ ነው ። …
እንዲህ አይነቱ ኢ ፍትሐዊ ህገ መንግሥት በመላው ዓለም የለም ። የዓለም የፊደረሽን ሥርዓት ፣” ፌደረሽኖች ፣በማዕከላዊው መንግስት የማይተገበሩ ፣ ውሥጣዊ የአሥተዳደር ስልጣኖች ይጠበቁላቸዋል ። ከዚህ አንፃር ፣ ክልሎች በተወሰነ መልኩ ሉዓላዊ ናቸው ። ነገር ግን ፌዴሬሽኑ የነፃ ክልሎች ጥምረት ብቻ አይደለም። የፌደራሉ ክልሎች የውጭ ፖሊሲን በተመለከተ ስልጣን የላቸውም ። የጦር ኃይል ሊመሠረቱ አይችሉም ። የፀጥታ አሥከባሪ ተቋም ቢኖራቸውም የሚቀጠሩት ከህዝቡ ውሥጥ ያለአድሎ መሆን ይኖረበታል ። በከተሞች የሚኖሩ ዜጎች በዜግነታቸው እንጂ በቋንቋቸው እየተመዘኑ እየተለዩ ፣ ፖሊሥ እና ወታደር መሆን የለባቸውም ። ” ቢልም ፤ ዛሬ በኢትዮጵያ ፣
ፖሊሥ ብቻ ሣይሆን መምህራን ፣ ኃኪሞች ፣ የሂሣብ ሠራተኞች ፣ ወዘተ ። በየክልሎቹ በቋንቋ መሥፈርት እየተቀጠሩ እንጂ ዜጎች በሰብዓዊ እና ተፈጥሯዊ መብታቸው ታይተው የኢትዮጵያን ገበታ በጋራ ተቋዳሽ አልተደረጉም ። የህ ከባድ የሰብዓዊ መብት ጥሰት ብቻ ሳይሆን የአፖርታይድ ሥርዓት ነው ። ( እንዴት ለአፍሪካዊያን ነፃነት ፣ አፖርታይድን ለመገርሰሰ ግንባር ቀደም ተፋላሚ የሆነች ፣ በባርነት ያልተገዛች አገር ዛሬ መንግሥቷ የአፖርታይድን አገዛዝ በየክልሉ ሁሉ እንዲተገበር እንዴት ያደርጋል ? ከዚህ በከፋ መልኩ ደግሞ ህሊናቸውን ለነዋይ በሸጡ ፣ በጥቂት የህወሓት አባላት ጠብ አጫሪነት እርስ በራሣችን ተገዳድለን ሥናበቃ ፣ ትላንት ነፃ እንዲወጡ በታገልንላቸው ውንድም የአፍሪካ አገራት መሪ ልጆች ሥንሸመገል ማፈር ነበረብን ።ተዋርደናል ። ወያኔዎች ከከፍታችን አውርደውናል ። የቁሥ እንጂ የሰው ፍቅር ሥለሌላቸው ኢትዮጵያን ክደዋል ። ታላቅነታቸውን በሆዳቸው ለውጠዋል ። የኢትዮጵያን እድገት በ15 እና 20 ዓመት ወደኋላ ጎትተዋል ። ኢኮኖሚዋ እንዲኮታኮት አድርገዋል ። )
ይኽ ዜጎችን በቋንቋ የማበላለጥ ከእምነት የሚያጣላ ( ከፈጣሪ የሚያርቅ ) ሥርዓት ሂትለራዊ እና ሞሶሎኒያዊ ነው ። በዚህ ሥርዓት ከቀጠልን ኢትዮጵያን አጥፍተን 17 አገር የማንሆንበት አንዳች መንገድ አይኖርም ።
እንበልና የአማራ ክልል ዘርን መሠረት በማድረግ አማርኛ የሚናገሩ ሆኖም ከኦሮሞ ማህበረሰብ የተገኙ ባለሙያዎች ሁሉ ሥራቸውን ለቀው ወደ ክልላቸው ይሂዱ ቢል ፣ የሚ ጠረውን ትርምሥ አስባችሁታል ? አገርን ወደ መበታተን የሚያመራ አይደለምን ?
ኦሮሚያ በተሰኘው ክልል አመራሮች የኽ አገርን የማፍረስ ድርጊት በህቡ እየተከወነ ነው ። ይሄ ድርጊት ” አሳፋሪ ነው ። ” ብለን የምናልፈው አይደለም ። ” እጅግ አሥፈሪ እና ደም አፈሳሽ ነው ። ” ሥለሚሆን ከወዲሁ ልንገታው ወይም ልንቀለብሰው በጀግንነት መነሳት አለብን ። ቅኝ ገዢው ሞሶሎኒ እንኳ በአምሥት ዓመት ቆይታው የዛሬውን አይነት አሥጠሊ የከፋፍለህ ግዛ እና የዘረፋ መንገድ አልተከተለም ።
ከሞሶሊኒ የባሰ የዘረኝነት እና የዘረፋ መንገድን በመከተል ፣ በአማርኛ እያወሩ አማርኛን መጥላት ፤ በበኩሌ በታሪክ ተፅፎ ፣ የፋሺሥቱ ኢጣሊያ ሥራ ነው ተብሎ አላነበብኩም ። የዛሬው የዘር ፖለቲካ የጤነኝነት ነው አልልም ። የቁሥ ሠቀቀን እና የሥግብግብነት ነው ። ” ሌላው ዜጋ አራት እግሩን ይብላ እኔ እና መሰሎቼ ግን በጥጋብ ሰማይን በእርግጫ እያልን እሥከህልፈታችን እንኑር ። ” የማለት የጅል አሥተሣሠብ የወለደው የህሊና ቢሶች የውድቀት መንገድም ነው ።
ሰው ህሊና ቢሥ ሲሆን የሤጣን ቁራኛ ይሆናል ። እንደዚህ ያለው ሰው ተሰባስቦ ፖርቲ ከመሠረተና መንግሥት ከሆነ ደግሞ ፣ አዲዮስ ! … እጅግ ዘግናኝ ተግባራትን ከመፈፀም ወደ ኋላ አይልም ። ምክንያቱም እርሱ ባለመማሩ ዕውቀት ሥለሌለው በዙሪያው የሚያሰልፋቸው በዕወቀት ዕጦት ማመዛዘን የማይችሉ ሰዎችን እና በተለያዩ ጎጂ ሱሶች የተዘፈቁ ግለሰቦችን በመሆኑ ፣ ቆሜለታለሁ ለሚለው ህዝብ እልቂት ነው ጠብ የሚልለት ።
( ዕውቀት ማለት ባችለር ፣ ማሥተርሥ ፣ እና ፒኤች ዲ በአንድ የዕውቀት ዘርፍ ማገኘት ማለት አይደለም ። ዕውቀት ከዚህ ባሻገር ነው ። ሰው ራሱን ፣ ማንነቱን ፣ ተፈጥሮውን ሰብዓዊ መብቱን በቅጡ የሚገነዘብበት እና አምሳያውንም እንደእራሱ የሚያይበትን አመዛዛኝ ህሊና መጎናፀፊያ መሣሪያ ነው ። አብዛኛዎችን በጎ ዕውቀቶች ሰው ከህይወት ዩኒቨርስቲ ደረጃ በደረጃ ይቀስማል ። ጎጂዎችንም እንዲሁ ።
ሰው ልጅ በዓለም ላይ ሲኖር በጎ ና መጥፎ ትምህርቶችን በተለያየ መንገድ በመማሩ አዋቂ አይሰኝም ። አዋቂ ሰው ሰው መሆኑንን በቅጡ የተገነዘበ እና ለእርሱ የሚያሥፈልገው መልካም ነገር ሁሉ ለአምሳያው ያሥፈልገዋል ብሎ ከልቡ የሚያምን ነው ። … ሰው የሚባለውም ይኽ ሰው ነው ።)
ትላንት ከ80 ዓመት በፊት ነጋድራስ ገ ህይወት ባይከዳኝ ሰው የሚመራበትን መንገድ ከኢኮኖሚና ከአሥተዳደር አንፃር መፃፋቸውን ከላይ ገልጫለሁ ። ይኽንን ሥለመንግሥትና ህዝብ አሥተዳደር የፃፉትን መፅሐፍ እንኳ አንብበው ጠቃሚ ፍሬዎቹን የለቀሙ ግለሰቦች በመንግሥት ሥልጣን ላይ በብዛት ይቅርና በጥቂቱ እንኳን የሉም ። በአማካሪነት ደረጃ ግን አንድ ሁለት አሉ ።
ወያኔ እንደ ዕቃ፣ዕቃ ጫወታ “ፖርቲ” እና ” ዴድ “በማድረግ ሥልጣን ሥለሰጠቻቸው ራሳቸውን እንደ አዋቂ እና እና እንደ መኮንንት ቆጥረው የወጡበትን ማህበረሰብ ቁልቁል ማየት የጀመሩ ግን መሃት ናቸው ። …