“…የዐብይ ሽመልስ ጉዳይ አስፈጻሚዎቹ ዐማራውን ከመገደላቸው በፊት በመጀመሪያ እንዲህ አቆራኝተው ያስሯቸዋል። ከዚያ …ከዚያማ ምን ይጠየቃል…?
• በማግስቱ ደመቀ መኮንን ብቅ ይልና “…በአሸባሪዎቹ ላይ ጠንካራ እርምጃ እንወስዳለን። የተጎጂ ቤተሰቦችንም መልሰን እናቋቁማለን” ብሎ ይለጥፋል። ዐቢይ አሕመድም ሃዘን ቀንሱና ተነሥተን ችግኝ እንትከል ይላል። ከዚያ ቸማራው ትንሽ ዋይ ዋይ ዋይ ይላል። ተመልሶ ድምጹ ይጠፋል። ገዳዮቹ ግድያቸውን ይቀጥላሉ…
“…አብረን እንበድ…!!
በምዕራብ ወለጋ በሸኔ የተገደሉ ሰዎች ቁጥር 1 ሺሕ 600 ደርሷል።
በኦሮሚያ ክልል ምዕራብ ወለጋ ጊምቢ ወረዳ ቶሌ ቀበሌ ራሱን የኦሮሞ ነጻነት ጦር/ሠራዊት ብሎ በሚጠራው ሸኔ የተገደሉ ሰዎች ከ1 ሺሕ 600 መሻገሩን የዐይን እማኞች ገለጹ።
በጥቃቱ የሞቱ ሰዎችን አስከሬን በመሰብሰብ ላይ የተሰማሩና ለደኅንነታቸው ሲባል ሥማቸው እንዲጠቀስ ያልፈለጉ ዐይን እማኞች ለአዲስ ማለዳ እንደገለጹት፣ ታጣቂዎች በፈጸሙት ጥቃት ከ1 ሺሕ 600 በላይ ሰዎች እንደተገደሉ እና 900 የሚሆኑ ሰዎችን ሬሳ ቆጥረን ቀብረናል ብለዋል።
አዲስ ማለዳ
————————————————————–
በወለጋው የዘር ጭፍጨፋ የአብይ አህመድ አስተዳደር እጁ እንዳለበት ለማስረገጥ ካልሆነ በቀር የ Tagesse Chaffo Dullo ፓርላማ በግልፅ አሸባሪ ብሎ የፈረጀውን “ኦነግ ሼኔን” (aka ኦህዴድ-ኦነግ) በሰላማዊ ሰልፍ ማውገዝ በፌደራል ፖሊሲ የጭካኔ ዱላ የሚያስወግር አልነበረም።
የአዲስአበባ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች በሰላማዊ ሰልፍ የወለጋውን የኦሮሙማ የሽብር ፖለቲካ ሰለባዎችን በማሰብ ጭፍጨፋውን ማውገዛቸው የሚያሸልም ተግባር ካልሆነ በቀር የሚያስደበድብ አይደለም! አብይ አህመድ ቁልቁለቱን በፍጥነት እየነዳ ነው።
You better come to your sense before it is too late