December 25, 2020
11 mins read

ኢትዮጵያዪ፤ ምነው እመብረሃን የስደት አገርሽን ተውሻት

 

ኢትዮጵያዪ

              ምነው እመብረሃን የስደት አገርሽን ተውሻት

              ዝም አልሻት እረሳሻት።

  • ኢትዮጵያየ ምነው ልጆችሽ ጨከኑብሽ

ለወዳጅ ጥላት ሊሰጡሽ አሰፍስፈው አሴሩብሽ።

ሰላምሽን ጠልተው ገፉት

ወተትሽን ንጠው ድፉት

ሥልጣን ሰጥተሻቸውም ሊጠሩሽ ጠሉሽ

በጎሳ ተከፋፍለው እርስ በእርሳቸው ተባሉልሽ

በአጎረስኩ ተነከስኩ ሆኑብሽ።

ግና አይዞሽ አሁንም ቢሆን ልጅ አለሽ

ብትገፊውም አርቀሽ

ነፍገሽም ቢሆን ሰስተሽ

ከማዕድሽ መቋደስ ባይችልም

ምን አረግሽልኝ ብሎ አይጠይቅም

ውርደትና መደፈርሽን አይፈልግም

ተነካሽ ሲሎት አይወድም።

  • ያለችውን ውድ ሕይወቱን ሊሰጥሽ

ውርድ ለሰማይ ለምድር ብሎ፣

ይዘምትልሻል ነፍጡን ያነሳል ሞቱን መርጦ

ከጠላት ሊታደግሽ ወድ ሕይወቱን ከፍሎ። 

            ምነው እመብረሃን የስደት አገርሽን ተውሻት

            በጎሳ ከፋፍለዋታል ሊአፈርሷት

           ዝም አልሻት አትርሻት።

 

  • እንዲህ አዝግመሽ ዘመናትን ያስቆጥረሽው

የአበው አባቶቻችን ጸሎትና ቡራኬ ቢደርሰን ነው።

ውሽትን ጠልተው ስርቆትን ተጠይፈው

በኢትዮጵያዊነታቸው ጥግ ዘልቀው ሁሉንም አካተው

መድሎን ኮንነው በማተባችው  ጸንተው

በአንች አማላጅነትና በልጅሽ አዳኝነት ተማምነው።

እንዲህ ነበር እኮ ያቆዮአት

3ሽህ ዘመን ያስቆጠሯት።

ግን እኮ እማማየ!! የአንችነትሽን ዲካ አሻራ

ታሪካዊነትሽን የሚአስጠራ

ከአገራት በፊት ቀደምትነት ያሰጠሽን

የዕምነት ሥረአትሽን  ባህልና ወግሽን

የአንችነት መገለጫዎች እኒያ እኒያ ትውፊታዊ ቅርሶችሽን

ቃል የዕምነት ዕዳ ሆኖበት አስጠብቆ ያቆየሽን

ለአንች ብለው የሞቱልሽን ድሮም ሆነ ዛሬ መች ፈለግሻቸው መች ከፈልሻቸው

አገር ባቀኑ ዕምነት ባጸኑ መታረድ  ሆነ እንጅ ትርፋቸው?

                          ክፍል ሁለት

  • አልሰሜን ግባ በለው አሉ

እንዴት እንዴት እንዲህ አልከኝ

መቸ አውከኝ ማንነቴን የት አይህኝ

አገር ማለት ምጥቅትና ስፋቱን መቸ አውቀህው

አቅል ገዝተህ ምኑስ ገብቶህ መቸ ኖርከው ።

እንጅማ የዓለም አገራት ታላቅ ነን ከሚሉት ቀደም ብየ

         እታወቅ ነበር መንግሥት መስርቸ ሥረአት ጥየ

አውሮፓዎች ከእኔ በኋላ አገር ሁነው ሥልጣኔውን ቢአፋጥኑት

ከነሱ ተምረህ እንድ ጃፓን ቻይና መሽቀዳደም ሲገባህ

ጭራሽ አውቀህ ሙተህ ከዚያም ከዚያ በቃረምካት

አገርህን የብሔርስብ አስር ቤት ናት አልካት ።

ይህን እውቀት ብልህ

ከኢትዮጵያዊነት አሰባሳቢ ማንነትህ ወጥተህ

አንዲት ሰበዝ ብቻ መዘህ ቋንቋን መለኪያ አድርገህ

እንዲህ ነኝ ማለትህ

እውነት ይህ ብቻ  ሆኖ ነው የአንተ መገለጫ ማንነትህ?

አናማ  የወረደ ማንነት ፈለጋ ስትዳክር

የሳለፍከው ጊዜ ቢቆጠር

ለአገርና ለሕዝብ የሚጠቅም ስንት ቁም ነገር ትሠራበት ነበር።

  • አየ ኢትዮጵያየ!! ይህ ሁሉ ምን ያደርጋል የሚወዱሽ ልጆችሽ

በሕይወታቸው ተወራርደው የታደጉሽ

አሁንም  እኮ  እስር ሆነ የተረፋቸው

መሳደድ ሆነ ዕጣ ፈንታቸው።

አንዳንዶቹም እንግልቱን ተቋቁመው ሞትን ቢአሸንፉት

ከሃዲና ባንዳዎች ናቸው ሥልጣኑን የሚይዙት

ዋሸው እንዴ ኢትዮጵያየ አስቲ ንገሪኝ በእኔ ሙት!!!አልኳት

ምነው ወላዲት አምላክ ምልጃሽን ነፈግሻት

              የሰደት አገርሽን ዘነጋሻት ዝም አልሻት።

  • ይኽውና ሦስት አሥር አመታት አለፈን

በጎሳ ነገድ ተከፋፍለን ከተቧደን።

እርስ በእርሳችን እንዳንስማማ ተደርገን

የአንድ እናት ልጆች ሁነን አንዳላደግን

መደማመጥና መግባባት ተስኖን

አገር የሚአፈርስ  ሕግ አርቅቀን

ሆን ተብሎ እንደ ጠላት እንድንተያይ ከተደረገን።

እንዳይሻሻል በጎጤኞች እንቢተኝነት

በተረኞች እየተስፈራራን በመንጋ እየተዳኘን

አገር አልባ እኮ ሊአደርጉን ነው።

የዘር መጋኛ ተጠናውቶን ተጣግቶን

ክፍ አንዳላልን ወርደን ዘቅጠን

መወያየትና  መግባባት እኮ ተሳነን።

እኮ እረ እኛንስ ምን አስነኩን? ምን ተሻለን???

እመብረሃን ምነው ዝም አልሽን

              ባዝን እኮ በዘር ልክፍት ጠመደውን

እረ እባክሽ ተለመኝን ከልጅሽ ከወዳጅሽ አማልጅን ።

  • ቀደመ አባቶቻችን ያስተማሩን

የምንታወቅበት ፍረሃ አግዚአብሔር ዕምነታችን

የወደቀ አንጀራ እንኳ ስናይ ጡሩን ፈርተን

ከመሬት ላይ አንስተን

ወደ ላይ ወደ ፈጣሪ አንጋጠን ስሙን ጠርተን

ይቅር እንዲለን ተማጽነን እንጎርሰ ነበር እፍ እፍ ብለን።

የአሳደገነውን ከበት ለመባረክ እጃችን አልጨክን ቢለን

እናስባርክ ነበር ከጎረቤት ሰው ጠርተን።

ሰውን በመንጋ ማጥቃትም የፈሪነት እንጅ የወንድነት ሙያ አልነበረም

ጠላት መሬት ሙጥኝ ካለም ጠያፍና ነውር ነው አይገደልም።

ይኽ ይኽ ሁሉ የጅግንነት ትውፊቱ ተረስቶ

አገር ለማዘመን የከፈለው መስዋአትነት ተሰርዞ ጠፍቶ

ሥልጣኑ  መንበሩ ላይ ባንዳው ተተክቶ

በእነ እንቶ ፈንቶ ፍርድ አማራው ታረደ ተበላ

ግፉ ጥግ ደረሰ  ቂም አርግዟል ሞልቶ።

ዋ !! ቤ ን ሻ ን ጉ ል የ ደ ም  ም ድ ር

የሚበላ እህል ሳይጎድል

ምነው የአማራ ስጋ አማረው ቤንሻጉል።

ታናሽና ታላቅ እያለ የውስጥ ዕቃ ያማረው

“የቀየ ሰው ደም” የጠማው

ቤንሻንጉልን ምን ነክቶት ነው ?

ለመሆኑ ቤንሻንጉልን እንዲህ ያጀገነው

ማን አይዞህ ቢለው ነው

ማን የልብ ልብ ቢሰጠው ነው??

እኛ ስናውቅ መተክል የጎጃም የአማራ ምድር  ነበር

አሁን ግን ጉምዝ፣ ወይጦውና ሽናሻው መዥንገር ሆነና ባላአገር

በቀስት በጎራዴ አማራው እየተለየ ይታረድና ይመተር ጀመር።

 

  • ኢትዮጵያዪን ባሉ የአገር አቅኒ ልጆች የነስሜ አይጠሬ

የእኒያ የእነ አጅሬ የነሞት አይፈሬ

ውጣልን ይሉታል ከአገር ከደንበሬ።

ወያኔም ከሄደ ጉድ እየስማን ነው ትናትና ዛሬ

ይታረዳል አሉ ከቤት ከደጃፉ እንደሰንጋ በሬ።

ፍትሕ ተጓድሎበት ያም ያም ይገድለዋል

የአማረው ደም  ይጮሃል !!! የአማራው ደም ይጮሃል!!

ምነው እመብረሃን ዝም አልሻት

ቅድስት ሀገራችንን እንዳያፈርሷት

አባክሽ ከእንደነዚህ ያለ ብልሃስቦች ታደጊያት ።

  • መታሰቢያነቱ፤ በቤንሻንጉል ጎምዝ/ በመተከል፣ በኦሮሚያና በማይካድራ በአማራነታቸው ምክንያት ለታረዱና ለተጨፈጨፉ አማሮች ይሁንልኝ።

ኦ!!  ማ  ይ  ካ  ድ  ራ፤

  • የቅድስት አገር የኢትዮጵያ የአንድ እናት ልጆች መሆናችንን እረስተው

ደደቢት ላይ ከለከፋቸው ጋኔን ተጣብቀው

ሃይማኖታቸውን ክደው

ለፍቅረ ነዋይ ተገዝተው

ኢትዮጵያን አጨቀዩአት በደም ስክረው ዋጀተው።

ድሮ እንዲያ ትግራይን አጥግብልን ብለን ተማለደን እንልህ የነበር

በወያኔ እንዳየነው

እንዳለፈው 30 ዓመት መች እንደዚህ እንዲሆን ነው ።

አሁን ደግሞ ከ27ዓመት ወዲህ የተለየ የተለየ ጥጋብ ሆነ

ትንግርት ያለው ድግስ  ጠላና ጠጅ ተጣለ

በእያይነቱ ብልት በብልት ተደለደለ

አማራ አማረን ያስባለ

  • ማይካድራ ላይ ጉድ ተባለ ጉድ ያስባለ!!
  • መታሰቢያነቱ ማይካድራ ላይ በማንነታቸው ምክንያት በግፍ ለተጨፈጨፉ አማሮች ይሁንልኝ።

Leave a Reply

Your email address will not be published.

Go toTop