ግልፅ ደብዳቤ ለክቡር ዶ/ር ዓብይ ኣሕመድ የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር – መርስዔ ኪዳን

October 12, 2019

መርስዔ ኪዳን
ከሜኔሶታ ሃገረ ኣሜሪካ

በቅድሚያ በታሪክ ከፍተኛ የሆነው የኖቤል የሰላም ሽልማት ተሸላሚ በመሆንዎ እንኳን ደስ ኣለዎ ለማለት እወዳለሁ። የኖርዌይ የኖቤል ኮሚቴ እርስዎ በኢትዮጵያና በጎረቤቶቿ ሰላም ለማስፈን ባደረጉት ጥረት እንዲሁም በኢትዮጵያ ውስጥ የፖለቲካ ለውጥ እንዲመጣ በተለይ ደግሞ ያለምንም ቅድመ ሁኔታ ከኤርትራ መንግስት ጋራ ያደረጉትን የእርቅ ተነሳሽነት ጠቅሶ ለእነዚህ ስራዎችዎ እውቅና በመስጠት የኣመቱ የሰላም የኖቤል ተሸላሚ መሆንዎን በድረገፁ ኣስታውቋል።

የኣገራችን መሪ ለዚህ ከፍተኛ ሽልማት እና እውቅና መብቃት ሁላችንን ሊያስደስተን የተገባ ሆኖ ሳለ ኣንዳንድ ኢትዮጵያውያን ወገኖችዎ ግን የደስታው ተቋዳሽ እንዳንሆን የሚያደርጉን እርስዎንም በተሰጠዎት የኣለማቀፍ እውቅና ልክ እንዳናከብርዎ የሚያደርጉን ነገሩች ኣሉ። ይህ የተሸለሙት ሽልማት እንደነ ማህተመ ጋንዲ ያሉ ታላላቅ ሰዎች የተሸለሙት ሽልማት ነው። እኛም እንደነዚህ ታላላቅ ሰዎች እንዲሆኑ ምኞታችን ነው። የነኚህ ታላላቅ ሰዎች ኣንዱ መለኪያ ለሰብኣዊነት ያላቸው ከፍተኛ እይታ እና ከጊዜያዊ ነዋያዊና የስልጣን ጥቅም ይልቅ ዘላቂ የሆነ ለሰው ልጅ የሚበጅ እሳቤ ያላቸው መሆናቸው ነው። በዚህም ምክኒያት ከቂመኝነትና ከበቀልኝነት የፀዱ ናቸው።

ክቡርነትዎም በዚህ በተሰጠዎ ኣለማቀፍ እውቅና ደረጃ ራስዎን ከፍ ኣድርገው ሁላችንንም ኢትዮጵያውያንን የደስታው ተካፋይ ሊያደርጉ የሚችሉበት እድል ኣለ። ኣብዛኞቻችን የትግራይ ብሄር ተወላጆች እርስዎ ስልጣን ላይ ከመጡ ወዲህ በሺዎች የሚቆጠሩ የትግራይ ብሄር ተወላጆች እስር ቤት በመግባታቸው ለውጡ ለኛ ሳይሆን እኛ ላይ እንደመጣ እንድንቆጥረው ተገደናል። በተለይም እንደቀድሞ የስራ ባልደረባዎ እንደነ ኮሎኔል ቢኒያም ተወልደ ያሉ ወጣት ምሁራን እንዲሁም ወታደራዊ መሪዎች እንዲሁም ነጋዴዎች በእርስዎ ትእዛዝ መታሰራቸው እጅግ ኣሳዝኖናል። በዚህም መሰረት በመላው ኣለም የምንገኝ የትግራይ ብሄር ተወላጆች ‘ወፍሪ ሓርነት’ በሚል መሪ ቃል እስረኞቻችን እንዲፈቱ ትግል ለመጀመር በመዘጋጀት ላይ እንገኛለን። ኣለም ኣቀፍ የሜዲያ ተቋማትና፣ የሰብኣዊ መብት ተቋማትን ለማስተባበርም ስራው እየተጀመረ ነው። ከነዚህ ተግባራት ኣንዱ ራሱ የኖቤል ኮሚቴው ላይ ጫና ማሳደርንም ሊያጠቃልል ይችላል።

የኖርዌይ የኖቤል ኮሚቴ እውቅናውን ሊሰጥዎት ከተነሳባቸው ምክኒያቶች ኣንዱ በሺዎች የሚቆጠሩ እስረኞችን መፍታትዎ እንደሆነ በመግለጫው ጠቅሷል።  ታዲያ እርስዎም ይህን ከፍተኛ የስብእና መለኪያ የሆነ እውቅናና ሽልማት በሚመጥን መልኩ ራስዎን ከጊዜያዊ እልህና በቀለኛነት በማፅዳት ወደስልጣን ሲመጡ የገቡልንን የይቅርታና የፍቅር ቃላት ወደተግባር እንዲለውጡ እማፀንዎታለሁ። ዛሬ በፖለቲካ ለውጡ ምክኒያት እስር ቤት የሚገኙ የትግራይም ሆነ የሌላ ብሄር ተወላጅ ኢትዮጵያውያንን በምህረት ከእስር ቢለቅቁ ለዚህ ሽልማት ያበቃዎትና በመላ ኢትዮጵያውያን ላይ ተስፋ የጫሩት የይቅርታና የፍቅር ቃላትዎን ተግባራዊ ማድረግዎን ያሳያል። የተሰጠዎት የሰላም የኖቤል እውቅና ተገቢ መሆኑን ያረጋግጣል። ስለሆነም ኣንዳችን ከምንሸነፍ በእርስዎ ይቅርታ ኣድራጊነት ሁላችንም እናሸንፍ። የትግራይንም ሆነ የሌሎች ብሄሮች የፖለቲከኛ እስረኞች ይፍቱ!

በመጨረሻም መልእክቴን በደንብ በሚገልፁት በቴዎድሮስ ካሳሁን ስንኞች እቋጫለሁ።

ለለውጥ ያጎፈረው ዙፋን ላይ ሲወጣ
እንደ አምናው ባለቀን ያምናውን ከቀጣ
አዲስ ንጉሥ እንጂ ለውጥ መቼ መጣ
ይቅር በለውና የበደለን ወቅሰህ
ምህረት አስተምረን
አንድ አድርገን መልሰህ

 

በድጋሜ እንኳን ደስ ያለዎ!

መርስዔ ኪዳን

ከሜኔሶታ ሃገረ ኣሜሪካ

mersea.kidan@gmail.com

2 Comments

  1. መለስ ዜናዊ የኦሮሞን እጅና እግር ሲቆርጥ፥ ዐይናቸዉን ሲያጠፋ፥ ሴቶቹን ሲያስደፍርና ወንዶቹን ሲያኮላሽ፥ ንብረታቸዉን በትግሬ መንጋ ሲያዘርፍና መቀሌን ንዉ ዮርክ አስመስሎ ሲገነባ ተዉ አታድርግ ሰዉን አትበድል ብለህ ጽፈህለታል ወይ?

  2. 27 አመታት እንደጦር ትፈሩት የነበረውንና ስታሳድዱት የነበረውን የቴዲ አፍሮን ሙዚቃ ማዜም ጀመራችሁ?
    አይ እናንተ፡ምን አይነት ፍጥረት ትሆኑ?

Comments are closed.

Previous Story

 ለቤት ቀጋ ለውጭ አልጋ – አገሬ አዲስ   

103641871 1855312385
Next Story

ከሁለት ቀናት በኋላ ህወሓት ኢትዮጵያን ለማፍረስ ይወስናል! – ስዩም ተሾመ

Latest from Blog

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤ/ክ የውጪ ግንኙነት የቤተክርስቲያኒቱን የሺሕ ዘመናት ታሪክ እና እሤቶቿን የሚመጥን መሆን ይኖርባታል!!

በተረፈ ወርቁ (ዲ/ን) (ለሪፖርተር ጋዜጣ እንደጻፈው) እንደመንደርደሪያ ለዛሬው የግል ትዝብቴንና ታሪክን ላዛነቀው ጽሑፌ መነሻ የሆነኝ- ባሳለፍነው ሳምንት በአፍሪካ ኅብረት ኔልሰን ማንዴላ የመሰብሰቢያ አዳራሽ ለአንድ ቀን የተካሄደው፤ ‹‹የአፍሪካ  መንፈሳዊ ቀን/The African Spiritual

የአበባው ታደሰ እና የአረጋ ከበደ ፍርጠጣ | ስለአማራ ክልል ከነዋሪዎች የተሰማው | አበባው ጉ’ድ ሆነ – “አበባውን ሳትይዙ እንዳትመጡ”|“በባህርዳር ተከበናል፣ ከፍተኛ አዛዦች ተመተዋል” | “ፋኖ መንግ’ስት ሆኗል” ጄ/ሉ |

የአበባው ታደሰ እና የአረጋ ከበደ ፍርጠጣ አበባው ጉ’ድ ሆነ – “አበባውን ሳትይዙ እንዳትመጡ”|“በባህርዳር ተከበናል፣ ከፍተኛ አዛዦች ተመተዋል”| “እጅ ከመስጠት ውጭ አማራጭ አይኖረንም” ፊ/ማ “ፋኖ መንግ’ስት ሆኗል” ጄ/ሉ |
Go toTop