እግዚአብሔር ሙቷል። – መ/ር አበባው አሰፋ

በፍሬድሪክ ኒቼ ዘመን በሀልወተ እግዚአብሔር ዙርያ መቅበዝበዞች ጨምረው ነበር። በዚህ ሁሉ መቅበዝበዝ መሀል አንድ አማራጭ ዜና ከወደ ጀርመን ተሰማ። ነውጠኛው ፍሬድሪክ ኒቼ ታላቁን የምስራች ነገረን እግዚአብሔር ሙቷል፣ሰው ነጻ ውጥቷል። ኒቼ እግዚአብሔርን ሬሳ የቀበሩ የመቃብር ቆፋሪዎችን ድምጽ አልሰማችሁምን ይለናል። እግዚአብሔርን ማን ገደለው ብንለው እናንትም እኔም ገድለነዋል አለን ድሮም ምናባዊ እንደነበር ለማስረዳት።

አማልዕክት ምናባዊ ድርሰቶች ከሆኑ ለምን ይታመንባቸዋል? አማኞች በሚያመልኩባቸውና እምነታቸውን በሚገልፅባቸው ቤተ እምነቶች ከሚከውኑት፣ ከሚፅፏቸው ፅህፎችና ከሚያራምዳቸው አቋሞች በመነሳት ለምን እንደሚያምኑ ማወቅ ይችላል፡፡ በአንድ አምላክም ይመኑ በብዙ የሶሾሎጅና የሳይኮሎጅ ሙህራን ከሚያስቀምጧቸው ምክንያቶች የሚወጣ አይመስለኝም፡፡ እምነት ነክ ምክንያቶቹ ሀይማኖትን ለማስቀጠል ሚናቸው እጅግ ከፍተኛ ቢሆንም እውነተኝነታቸው ግን ጥያቄ ውስጥ ነው፡፡ አማኞች እግዚአብሔር አለ ካሉ ማስረዳት አለባቸው፡፡ መናፍቃንና ካሂዲዎች ለሚሉን ለእኛ ለማሳየትና ማሳመን ይጠበቅባቸዋል፡፡ ኢ-አማኞች አስቸጋሪ ባህሪያችን አማልዕክትን በተመለከተ ካላየን አናምንም፡፡ እኔን ጨምሮ እግዚአብሔር በቢ.ቢ.ሲ፣ በሲ.ኤን.ኤን፣ በኢ.ቢ.ሲ፣ በፋና፣ በኢሳት፣ በአልጀዚራ፣ በኒዮርክ ታይምስ፣ ወይም በማንኛውም መገናኛ ብዙሃን መግለጫ እንዲሰጥ እንፈልጋለን፡፡ ለብዙ አማኞች ይህ ፍላጎት ሞኝነት ይመስላቸዋል። በፅሁፎቻቸውና በሰብከቶቻቸው የሚወርፉን ከምንም አንቆጥራቸውም የምንፈልገው የሰማዩን አለቃ ንጉሱን ብቻ ነው፡፡ ጋሻ ጃግሬዎቹ ሰልችተውናል፡፡ ጉዳያችን ከንጉሱ ጋር እንጅ ከኮልኮሌዎቹ ጋር አይደለም፡፡ ጉዳያችን ከሁሉ ጌታ ጋር እንጅ ከእስራኤል አምላክ፣ ከግሪክ አማልዕክት፣ ከግብፅ ጣኦታት፣ ከአረቢያው መልዕክተኛና ከየዘመናቱ መናፍስት ጋር አይደለም፡፡

እኛ የምንፈልገውን እንከን የለሽ ፈጣሪ ፈልገን አጣነው፡፡ ያጣነው ስለተሰወረ አይደለም ስለሌለ እንጅ፡፡ አምላክ ከሚያምኑት ይልቅ ለማያምኑት ቅርብ ነው ይፈልጉታልና፡፡ ችግሩ የሚያምኑት የአመኑትን ሲፈጥሩት ያለመኑት ግን ገና ይፈልጉታል፡፡ የሰው ስልጣኔ ከተጀመረ ጀምሮ ፈለግነው አልተገኘም ለምን አሁንም መልሱ ስሌለለ እንጂ ድብብቆሽ የሚጫወት ህፃን ሆኖ አይደለም፡፡ ላለመኖሩ ማስረጃ የሚፈልግ ካለ እና ከእውነት ጋር ለመኖር ለቆረጠ 48 ማስረጃወችን አቀርባለሁ። ዝርዝሩን <<ይድረስ እግዚአብሔር ልጆች>> ከተሰኘው መጽሃፌ ታገኙታላችሁ። በዚህ ጋዜጣ እና በሌሎች ፍቃደኛ በሆኑ መጽሄቶችም ማስረጃወቹን አብራራለሁ። አላማየ ታላቁን ሴራ ማጋለጥ ነው።  በዘመነ መንግድ ለሚሞግተኝ ለሚፈልግ ስልክ ቁጥሬን ከመጽሃፉ ይውሰድ ወይም abebawacc3368@gmail.com ላይ ይጻፍልኝ።

ተጨማሪ ያንብቡ:  የግብዝነት ፖለቲካ ክፉ ልክፍት  (ጠገናው ጎሹ)

ክፍል አንድ፣ ሰው ለምን ተጠራጣሪ እና ኢ-አመኝ ይሆናል?

  1. ሀይማኖት ለመንፈሳዊት እንቅፋት ነው።
  2. አሁን ካሉት ብዙ ሐይማኖቶች መካከል እውነተኛው የቱ ነው?
  3. የእግዚአብሔር ዝምታ (God’s Silence)
  4. አማልዕክት ምናባዊ (Imaginary) ናቸው።
  5. የተዛባ ማስረጃ (Wrong Evidence)
  6. Science (the magic of reality) explains almost everything
  7. በአጽናፈ ዓለም ውስጥ የእኛ ኢምንት ቦታ
  8. የዝግመተ ለውጥ እውነታ
  9. የሀይማኖት አብዮተኞች ታሪክና ትምህርቶቻቸው
  10.  የክፍተት አምላክ (God of the gap) ውድቀት
  11.  አጉል ምኞትና የሀብት ብክነት
  12.  የጸሎት ዋጋ
  13.  አታላይ እና አስመሳይ የሃይማኖት መስራቾች፣ መሪዎችና ሰባኪዎች
  14.  ሀማኖቶች የሚፍጥሩት ችግር
  15.  God Is Not Great, but Christopher Hitchens
  16.  ብዛኞቹ ሳይንቲስቶች አምላክ የለሾች መሆናቸው
  17.  በቅዱሳን መፅሃፍት የተተረከው እግዚአብሔር ኢ-ሰብአዊ ነው
  18.  ሀይማኖትዊ አስተሳሰቦች አርጅተዋል
  19.  God is Dead, Now Zen is the Only Living Truth
  20.  እግዚአብሔር ቅዠት ነው (God is Delusion)
  21.  Bierf Answers to the Big Questions
  22.  The stars died so that you could be here today.
  23.  የሰውን ልጅ ተፈጥሮ ያላገናዘቡ፣ ሀይል የተቀላቀለባቸውና ፍትህ የጎደላቸው ትዕዛዛትና ስብከቶች
  24.  ኢ-አማኞች ያዳበሩት ሰላማዊ የአኗኗር ዘይቤ

ክፍል ሁለት፣ አማኞች በእግዚአብሔር ለማመን ለሚያቀርቧቸው ምክንያቶች መልስ

  1.  የእግዚአብሔር መኖር በተለያየ መልኩ ተግልጧል – ትክክል አይደለም
  2.  የእግዚአብሔርን መኖር ታሪክ ይመሰክራል- ትክክል አይደለም
  3.  የሕይወትን ውስብስብነት በሳይንስ ሊገልጽ አይችልም- ትክክል አይደለም
  4.  የእግዚአብሔር መኖር በቅዱሳን መፅሀፍት ተገልጧል – ትክክል አይደለም
  5.  ሰዎች የሚሰጡት ምስክርነት የእግዚአብሔር መኖር ያረጋግጣል              – ትክክል አይደለም
  6.  ያልተጠበቁ ክስተቶች እና ተአምራት የእግዚአብሔር መኖር ያረጋግጣሉ- ትክክል አይደለም
  7.  ግብረ-ገብነት የሚመነጨው ከእግዚአብሔር ነው እናም ግብረግብነት ስላለ እግዚአብሔር አለ          – ትክክል አይደለም
  8.  አምላክ ባይኖር ኖሮ በአምላክ ማመን ባልተስፋፋ ነበር – ትክክል አይደለም
  9.  እግዚአብሔር በመኖሩ ለጸሎት መልስ ይሰጣል             – ትክክል አይደለም
  10.  ከአምላክ ጋር ግልአዊ ግንኙነት እንዳለኝ ይሰማኛል      – ትክክል አይደለም
  11.  በእግዚአብሔር ማመን የተሻለ ነው፣የእኔ ማመንም ማንንም አይጎዳም – ትክክል አይደለም
  12.  የእግዚአብሔርን ባህሪ መተንተን አንችልም – ትክክል አይደለም
  13.  አምላክ ላለመኖሩ ማስረጃ የለም – ትክክል አይደለም
  14.  እግዚአብሔር ከለለ ሁሉም ነገር ከየት መጣ? – ትክክል አይደለም
  15.  እግዚአብሔር ረድቶኛል፣ ፈውሶኛል፣ አድኖኞል፣ ጠብቆኛል፣ ጸሎቴን ሰምቶኛል ወ.ዘ.ተ – ትክክል አይደለም
  16.  እግዚአብሔር ፍቅር ነው – ትክክል አይደለም
  17.  ሳይንስና ፍልስፍና አምላክ መኖሩን ያረጋግጣሉ- ትክክል አይደለም
  18.  በአምላክ ማመን ለህይወት ትርጉም ያስገኛል ካለሱ ሕይወት ትርጉም የለሽ ይሆናል            – ትክክል አይደለም
  19.  በጣም ብዙ ቅዱሳን ሰዎች ለእግዚአብሔር እና ለሀይመኖታቸው ሞተዋል             – ትክክል አይደለም
  20.  እምነት የለሽነት ከሃይማኖት በላይ ብዙ ሰዎችን አስገድሏል፣ መጥፎና ሰይጣን አምላኪነት ነው       – ትክክል አይደለም
  21.  የኢየሱስ ክርስቶስ መገለጥ- ትክክል አይደለም
  22.  የእግዚአብሔር እርዳታ በሚፈልጉበት ጊዜ አማኝ ትሆናላችሁ   – ትክክል አይደለም
  23. ብዙ ታዋቂ ሳይንቲስቶች፣ አክተሮች፣ እስፖርተኞ፣ ዶክተሮች ወ.ዘ.ተ በእግዚአብሔር ያምናሉ            – ትክክል አይደለም
  24.  ሀገር የምትመሰረተው፣ የምትጠበቀው በፈጣሪ ነው ኢትዮጵያ እንደማሳያ           – ትክክል አይደለም
ተጨማሪ ያንብቡ:  የአዲስ አበባ ዋና ከተማ እና የወልቃይት ደንበር የኢትዮጵያ እና የቀጠናው የወደፊት የህልውና መሠረት ናቸው

ከሐዋርያው ቅዱስ አርዮስ (መ/ር አበባው አሰፋ)

4 Comments

  1. ‘God’ is a multi-Billion dollar business, man! ስንቱን ቄስ፣ ገበዝ፣ ጳጳስ፣ ሼክ፣ ነቢይ ነኝ ባይ፣ ስንቱን የሃይማኖት መጻህፍት አሳታሚና ሻጭ ልታከስር፣ ስንቱን ቤተ ሃይማኖት ባዶ ልታደርግ፣ ኧረ ስንቱን ለማኝ መለመኛ ልታሳጣ! ኧል ስንቱ ዳዊትን ከመድገም፣ ቁርዐን ከመቅራት፣ ቶራ ከማነብነብ ይልቅ ጊዜና እውቀቱን ወደፍሬያማ ትምህርት እና ፈጠራ ፊቱን ብያዞር፣ ነቢይ ነኝ ባይ ኪስ አዉላቂ፣ እኔ እስክበላ አይናችሁን ጨፍኑና ጸልዩ ባይ ሁሉ ምን ልሆን??
    ድሃውስ ለሰማያዊው ህይወት ተስፋ ባይኖረው ምድራዊውን ኩነኔ እንዴት ይቻለው? Religion is the doping stuff for the poor, የተባለውስ ሊቀር? ኧረ ስንቱ??

  2. መዝሙረ ዳዊት
    14፥1
    ሰነፍ በልቡ፦ አምላክ የለም ይላል። በሥራቸው ረከሱ፥ ጐስቈሉ፤ በጎ ነገርን የሚሠራ የለም።

    53፥1
    ሰነፍ በልቡ፦ አምላክ የለም ይላል። ረከሱ በበደላቸውም ጐሰቈሉ፤ በጎ ነገርን የሚያደርጋት የለም።

Comments are closed.

Share