September 1, 2019
7 mins read

ኢትዬጵያኖች አዲሱ አመትን በጸሎት እንዲቀበሉ ተጠየቀ (በታምሩ ገዳ)

pray

ኢትዬጵያኖች መጪው አዲሱ የ ዘመን መለወጫ በዓል ዋዜማን እንደ እየ እምነታቸው ሰለአገራቸው እና ስለሕዝባቸው ከልብ በመነጨ ብሔራዊ የጸሎት ቀን እንዲይደርጉበት ጥሪ ቀረበ።

የኢትዬጵያ የሀይማኖትተቋማት ካውንስል( Inter-Religous Council of Ethiopia , IRCE)ተብሎ የሚታወቀው ጉባኤ በሳምንቱ ማብቂያ አርብ እለት የጠሩት ጋዜጣዊ መግለጫን የጠቀሰው መንግስታዊው የመረጃ ተቋም ፣ኤዜአ እንደገለጸው ከሆነ በአገሪቱ ውስጥ የተከሰተውን ብሔር ተኮር ግጭቴችን እና ያስከተለው አሉታዊ ተጽእኖዎችን ከግንዛቤ ውስጥ በ መክተት ያለ ውንጀላቸው ለተገፉት፣ህይወታቸው ለተቀጠፈው፣ንብረታቸው ለወደመው፣ለተፈናቀሉት እንዲሁም ስለ መጻኢው የአገሪቱ እና የህዝቦቿ እጣፈንታ ፈጣሪ እንዲታደግ በኢትዬጵያ ጉዳይ ያገባናል የሚሉ ወገኖች በሙሉ እንደ እየእምነታቸው በመጪው ጷጉሜ 1/2011ዓም(መስከረም 6, 2019እኤአ) የብሔራዊ የጸሎት ቀን እንዲሆን ወስነዋል።

የብሔራዊ የጸሎት ቀን አስፈላጊነቱን በተመለከተ የሐይማኖት አባቶቹ ሲገልጹ”አዲሱን አመትን በሰላም፣በፍቅር፣ ከተቃርኖ በጸዳ እና አንዱ ወገን ለሌላኛው ወገኑ የሚያስብበት ድባብ በመፍጠር ለመቀበል አገር አቀፍ የጸሎት ቀን ማድረጉ ወቅታዊ እና አስፈላጊ ሆኖ አግኝተነዋል “ብለዋል።
በማንኛውም ማሕበረሰብ ውስጥ ልዩነቶች መኖራቸው የነበረ እና የሚኖር መሆኑን የጠቆሙት የሐይማኖት ተቋማቱ ተወካዬች”ኢትዬጵያኖች በተቀረው የአለም ማህበረሰብ ዘንድ ልዩ የሚያደርገን በልዩነት ውስጥ አንድነትን የማጎልበት ባሕላችንን ዛሬም ልናዳብረው እና ልናጠብቀው ግድ ይለናል” በማለት የኢትዬጵያዊነት መግለጫን አጽኖት በመስጠት ስለሰው ልጅ ስብእና፣ ስለህግ የበላይነት እና ስለእኩልነት ቅድሚያ ስፍራ በመስጠት ከፊታችን የተደቀነውን የስጋት ደመናን ለመግፈፍ የመንግስት ሐላፊዎች፣ወጣቶች፣የሚዲያ ተቋማት ፣ጎልምሶች ፣አዛውንቶች እና ሁሉም የማህበረሰብ ክፍል የበኩሉን ሐላፊነትን እንዲወጣ ጥሪ አቅርበዋል።
ምንም እንኳን ኢትዩጵያ እና ህዝቦች ከተደቀነባቸው አስፈሪው የተቃርኖ ማእበል ለመታደግ ሁኔታው ያሳሰባቸው እና የሚመለከታቸው የሐይማኖት ተወካዮች መጪው የጷጉሜ 1 በጸሎት እና በምልጃ እናሳልፈው በማለት ቢያውጁም አንዳንድ አገራት ህዝባቸው ወደ ፈጣሪ ፊቱን እንዲያ ዞር በአመት አንድ ቀን ብሔራዊ የጸሎት ቀን ይሁን በማለት አውጀዋል።

ለምሳሌ ያህል አሜሪካኖች እኤአ ከ1952 ጀምሮ በወረሃ ግንቦት/ሜይ በእለት ሐሙስ የብሔራዊ የጸሎት ቀን አድርገው ይቆጥሩታል። በዚህ እለት ሁሉም አሜሪካዊ ዜጋ ስለአገሩ ፣ስለወገኑ እና ስለ አለም ሰላም እንዲጸልይ መሪዎች ይበረታታሉ። የአሜሪካኖችን የእርስ በርስ ጦርነት እና የባሪያ ፍንገላን በህግ ያስቆሙት ፕ/ት አብርሃም ሊንከንም ቢሆኑ እኤአ ሚያዚያ/አፕሪል 30 1863 የብሔራዊ የጾም እና የጸሎት እለት እንዲሆን በፊርማቸው አጽድቀው እንደ ነበር መዛግብቶች ይገልጻሉ።

በኢትዬጵያ ውስጥም ቢሆን የኮ/ል መንግስቱ ኃ/ማርያም አስተዳደር ወድቆ በምትኩ ኢሕአዲግ ስልጣኑን ሊቆጣጠር በተቃረበበት በግንቦት 1983ዓም “በአገሪቱ ውስጥ የማያባራ የእርስ በርስ ጦርነት እና የደም መፍሰስ ሊከሰት ይችላል” የሚል ስጋት ያደረባቸው ኢትዬጵያኖች ዘር፣ሀይማኖት፣ጾታ እና እድሜ ሳይለዩ ወደ እየ እምነት ተቋማቱ በመሄድ መሪር እንባቸውን ያነቡበት እና አገሪቱም ቢሆን ያለማእከላዊ መንግስት ቁጥጥር ፣ እንድም ኮሽታ ሳይሰማ ለሳምንታት በሰላም የጸናችበት ያ አስገራሚ እና ታሪካዊ ወቅት ለብዙዎች የቅርብ ጊዜ ትዝታችን ነው።

የኢትዬጵያ የሐይማኖት ተቋማት ጉባኤ እኤአ 2010 የኢትዬጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤ/ን፣የኢትዬጵያ እስልምና ጉዳዬች ከፍተኛ ም/ቤት ፣የኢትዬጵያ ካቶሊካዊት ቤ/ን፣የኢትዬጵያ ኤቫንጀሊካን ቤ/ን፣የኢትዬጵያ አድቬንቲስት ቤ/ን፣የኢትዬጵያ ኢቫጀሊካል መካነየሱስ ቤ/ን እና የኢትዬጵያ ቃለህይወት ቤ/ን ተወካዬች በጋራ ስምምነት እና ራዕይ ያቋቋሙት ተቋም ሲሆን ኢትዬጵያኖች በተለይ ወጣቱ ክፍል የግብረገብ ትምህርትን እንዲያገኝ አገር ተረካቢ እና ጤናማ ማህብረሰብን በመፍጠር ረገድ ከመደበኛው የትምህርት አሰጣጥ ስርአት በተጨማሪ ከፍተኛ አውንታዊ ሚና ሊጫወቱ እንደሚችሉ ብዙዎች ይገምታሉ ።

(በታምሩ ገዳ)

Previous Story

ማን ቢስምሽ ታሞጠሙጫለሽ? ፖለቲከኞችና እበላ ባይ ተከታዮች ማን መረጣችሁና ነገር የምታምሱ፤ታሪክ የምታረክሱ፤ ሕዝብ የምታናክሱ ሀገር የምታፈርሱ? ኧረ በፈጠራችሁ ወደ ቀልባችሁ ተመለሱ!

Issa vs Afar 1024x682
Next Story

የኢሳን (የሶማሌ ጎሳ) ውለታ ፣ አማራ እንዳይረሳ!! –  (ናኦድ አፍራሳ)

Latest from Blog

አስቸኳይ ህዝባዊ ጥሪ

July 24, 2024 ዓለማቀፍ ትብብር ለኢትዮጵያዊያን መብት Global alliance for the Rights of Ethiopians (GARE) በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ገዜ ጎፋ ወረዳ ኬንቾ ሳቻ ጎዝዲ ቀበሌ በደረሰው የመሬት መንሸራተት የብዙ ወገኖቻችንን ህይዎት ማለፉን
Go toTop