ማለቂያ የሌለው ጉዳችን – አንዱዓለም ተፈራ

ማክሰኞ፣ ሐምሌ ፴ ቀን ፳፻፲፩ ዓመተ ምህረት

የኛ፣ የዐማራዎች፣ የራሳችን ያለመሰባሰብና ባንድ ላይ ያለመቆም ችግር፤ ለሌሎች መጫወቻ እንድንሆን አደረገን። ዐማራው ለኢትዮጵያ ለሀገሩ ያደረገውን አስተዋፅዖ መዘርዘሩ ትርጉም የለውም! ለራሱ ያደረገው ነውና! አሁንም ቢሆን ዐማራው ከኢትዮጵያ ሌላ ሀገር የለውም። እንኳንስ ቀደምቶቻችን፤ እኛም አሁን ያለነው ልጆቻቸው፤ ኢትዮጵያዊ ነኝ ብለን ለሀገራችን ሙሉ ለሙሉ ሕይወታችን ሠጥተን ታግለናል፣ ተሰውተናል፣ ለወደፊቱም ይሄ ይቀጥላል። ሌሎች እኛና እነሱ እያሉ፤ አንዱን ከፍ ሌላውን ዝቅ ሊያደርጉ ይችላሉ። ያ፤ ራሳቸውን ማሳነስና ሌሎች ብሎ ከፋፍሎ፤ ከሌሎች ጋር ለመወዳደር መሞከር፤ የራሳቸው ችግር ነው። ክፋቱ ላለፉት ሃያ ሰባት ዓመታት የትግሬዎቹ ነፃ አውጪ ግንባር ሀገር ሲገዛ፤ ሀገሪቱን በጁ ጨብጦ፤ ነገር ግን በጠባብ ወገንተኝነቱ ተጠምዶ፤ እንደ ኢትዮጵያዊ ሳይሆን፤ እንደ ትግሬነቱ ብቻ ሌሎችን ኢትዮጵያዊያንን መግዛት ስለያዘ፤ በሀገራችን የዘራው የመከፋፈል መርዝ፤ አሁን ቅርሻቱ ሀገራችንን በክሏታል። እናም በተለይ በዐማራው ላይ የተደረገውን በደል አስመልክቶ፤ በኢትዮጵያዊነቴ ተሰምቶኝ፣ በዐማራነቴ ፤ “በኢትዮጵያዊነት መታገል ነው መልሱ!” የሚሉ አሉ። ይሁንላቸው። ለኔ ደግሞ፤ ዐማራውን ከጥፋት ማዳን የአሁን ግዴታዬ ነው ብያለሁ።

እናም የራሳችንን ጉዳይ እኛው ራሳችን እንጂ፤ ሌላ ወገን እንዲፈታልን መጠበቁ ከየዋህነት አልፎ ጅልነት ነው። የኛ አለመተባበርና ተስማምቶ ባንድ አለመሰለፍ፤ አሁን በወገናችን ላይ ሌሎች በየተራ እንዲረባረቡብን መንገድ ከፍቷል። ዛሬ ደግሞ የሰማሁት ሌላ ዘርፍ ጨምሮበታል። ፋሲል ደሞዝ ያጎቴ ልጅ፤ ወንድሜ ነው። ሰሞኑን በሱ ስም የተለቀቀ ዘፈን አለ። ከመንገድ ወጥተው ይሄንን ተንኮል እንደሠሩ ሳስብ፤ በዐማራው ላይ እየተደረገ ያለው የተቀነባበረ የመከፋፈል ዘመቻ ምን ያህል ሥር እንዳለው ተረዳሁ። አዎ! ሁሌም ቢሆን የራስ ቁስል ያንገበግባል። የሱን ቅንጣቢ ድምጽ ጨምረውበታል። አብላጫው ግን የሱ ድምጽ እንዳልሆነ አብዛኛዎቻችሁ ታውቁታላችሁ። ከደረሰብን የመሪዎቻችን ሕይወታቸውን ማጣት አልፎ፤ እኛ ርስ በርሳችን በጠበበ ጎጠኝነት እንድንከፋፈል፣ ለነሱ እንድንመች፤ አንዳችን ከሌላችን እንድንጋጭ፣ ከቁስላችን ላይ ስንጥር ሰነቀሩብን።

ተጨማሪ ያንብቡ:  "ወላሂ ሁለተኛ አማራ አልሆንም!"

ፋሲል የተዋጣለት የባሕላዊ ሙዚቃ ጉምቱ ተጠሪ ከመሆኑም በላይ፤ ለወገኑ ተቆርቁሮ ከፈተኛ ግፍና በደል ደርሶበታል። በዛብኝ ስይል ለወገኑ ቁሞ፤ በሚያውቀው ሙያው የሚችለውን ከማድረግ አላረፈም። አሁን በዚህ መሰሪ ቅንብራቸው፤ ፋሲልን ረግጠው በላዩ ላይ ቆመው መጠቀሚያ አድርገው፤ ዐማራውን ለማጥቃት ተነስተዋል። ፋሲል በሕግ መሠረት ማስኬድ ያለበትን ያደርጋል። ይህ መሰሪ ተንኮል ግን፤ ሁላችንን ሊያስቆጣን ይገባል። እያንዳንዳችን የሕግ ባለሙያ፣ የዜና ማዕከል፣ የትንታኔ ባለቤት፣ የሀገር ፖለቲካ አዋቂ፣ ሕግ አውጪ፣ ዳኛና ፖሊስ በሆንበት የድረገጽ፣ የዜና መድረኮችና ባጠቃላይ በሕዋው መድረክ ዓለም፤ ንጉሥ ሆነናል። ስነ ሥርዓት፣ መከባበር፣ ትክክለኛ ካልሆነ ነገር መታቀብ፣ ከብልግናና ከስድብ መራቅ፣ የሚሉትን “የኅብረተሰባችን ዕሴቶች!”፤ ገደል ተጥለዋል። እኔን ብቻ ስሙኝ በሚል አደናቋሪ ትርክት ማዋከቡ ሙያ ሆኗል። በመሐል ቤት፤ ሃያ ሰባት ዓመታት ሀገሪቱን ለማፍረስ የሚችለውን ያደርግ የነበረው የትግሬዎቹ ነፃ አውጪ ግንባር፤ ዛሬ አጋዥ አግኝቶ፤ አሁንም ሀገራችንን በመከፋፈል ማጥቃቱን ይዟል።

በፋሲል ደሞዝ ስም የተለቀቀው ዘፈን ግን፤ ዐማራው ላይ ያተኮረ ነው። በርግጥ እስካሁንም፤ “ዐማራውን በማጥቃት ኢትዮጵያን ማጥፋት!” በሚል መመሪያ፤ ዐማራውን በዐማራነቱ ማጥቃቱ የገዥው ክፍል መመሪያ ነበር። ይህን የጻፍኩት፤ ዘፈኑን አቀነባብሮ የበተነውን አካል ተው ለማለት አይደለም። ሌሎች የሚሠሩትን ያውቃሉ። እኔ፤ ዐማራዎች ምን እያደረግን ነው? ብዬ ልጠይቅ ነው።

በርግጥ ኢትዮጵያዊነታችን የሚያጠያይቅ አይደለም። ከሌሎች ጋር በኢትዮጵያዊነታችን የሀገር ባለቤትነታችን አያጠያይቅም። ተነጥለን በዐማራነታችን ስንጠቃ ግን፤ በዐማራነታችን መከላከል ይገባናል። እኔ ካገሬ የወጣሁት በኢትዮጵያዊነቴ ነው። ያን ማንም ሊነጥቀኝ አይችልም። ለኢትዮጵያዊነቴ አልታገልም። ኢትዮጵያዊ ነኝ። አሁን በዐማራነቴ ነው ጥቃቱ እየደረሰ ያለው። በመሠረቱ ማንም ኢትዮጵያዊ በዐማራነቴ ለሚደርስብኝ ጥቃት፤ አብሮ” ኢትዮጵያዊ ጥቃት ደረሰበት!” ብሎ ሊረዳኝ በተገባ ነበር። ከሌሎች የበለጠ ኃላፊነት ስላለብኝ፤ ግንባር ቀደም በመሆን በዐማራነቴ ልከላከል የሚገባኝ እኔው ነኝ። ይሄ ግዴታዬ ነው። እከሌ እንዲህ ስላለ ወይንም ስላላለ ሳይሆን፤ ጥቃት ስለደረሰብኝ መከላከሉ ግዴታዬ ነው። ትናንት አኙዋኩ ሲበደል ጮኼያለሁ። ኦጋዴኑ ሲበደል ጮኼያለሁ። ኦሮሞው ሲታሰር ጮኼያለሁ። በኢትዮጵያዊነቴ ብቻ ለሌሎች ኢትዮጵያዊያን ጮኼያለሁ። አልፎ ተርፎ ለኢትዮጵያዊያን ነፃነት በትግሬዎች ነፃ አውጪ ግንባር ከባድ የጥይት ጉዳት ደርሶብኛል። አሁንም ቢሆን ለኢትዮጵያዊያን ነፃነት፤ ትግሬ ወይንም ኦሮሞ፣ ኦጋዴኒ ወይንም አኝዋክ ብዬ አልመርጥም፤ ለሁሉም እቆማለሁ። ነገር ግን፤ በዐማራነቴ፤ ዐማራው አሁን ያዘመመበት አደጋ፤ ከሁሉም በላይ አሳስቦኛል። ይሄን አደጋ ተገንዝበን፤ ዐማራዎች፤ ኢትዮጵያዊነታችንን ለማንምና ለምንም ነገር መደራደሪያ ሳናደርግ፤ ባንድ ተሰባስበን ለወገናችን መድረስ አለብን። ነገ ለቁጭት የሚያደርስ የምቾት ጊዜ የለንም። ከበራችን ሞፈር እየተቆረጠ ነው። እኛው እየተመቸናቸው ነው። ወደሌሎቹ ሳይሆን ወደራሳችን እንመልከት።

ተጨማሪ ያንብቡ:  ውድ ወንድሞችና እህቶች - ሙሉጌታ በትረ ገብረማሪያም

4 Comments

  1. The anti-Amhara political ideology started with the launching of the Marxist thesis of Walelign Mekonen in the late 1960s. This thesis highlights among others the oppression of the what it calls the nations and nations by the Amhara mation. It clearly demonizes the Amharas as the oppressors of the others in Ethiopia. The disciples of this Stalinist teaching are the EPLF,TPLF,EPRP and OLF all of which waged direct and indirect anti-Amhara campaigns. The EPRP was able to garner widespread among the Amhara elites and students. But the party was under the leadership of the Tigrean elites and incited violence that led to the deaths of tens of thousands of Amharas in the whole country. The Tigream elites whether they are in the TPLF or EPRP, they hated the Amharas and used their own evil ways to destroy the Amharas.

  2. I just heard the news – Hibir Radio – that Fasil Demoz has released a music (even with 3-4 seconds of voice) in honor of Asamenew and Ambachew et al. The news added that the song is called “Asamenew Tsige”. Well, I do not have to tell you my first reaction.
    Now you are telling us that some one else used Fasil’s name – confusing!
    Why can’t Fasil himself come out in the open with a disclaimer? Why was it necessary for the alleged singer to impostor Fasil (He can use his own name)?
    Zehabesha is duty bound to further look into the matter and inform its followers.
    Hmmmm……..

    • KEDIR,

      YOU ADMITTED THAT YOU WERE SURPRISED BY THE TITLE OF THE NEW SONG “ASAMINEW TISGIE”. WHY? THERE ARE MILLIONS OF AMHARAS, INCLUDING ME, WHO BELIEVE IN WHAT WAS SAID IN THE SONG. GENERAL ASAMINEW TSIGIE IS A MARTYR AND A HERO. HE CORRECTLY TOLD US THAT WE WERE SURROUNDED BY ENEMY FORCES IN ALL DIRECTIONS AND PREDICTED WHAT WOULD HAPPEN TO THE AMHARA PEOPLE IF WE DO NOT UNDERSTAND THE CONDITION ON THE GROUND AND PREPARE OURSELVES ACCORDINGLY. NOW, WITHIN A FEW DAYS OF HIS DEATH, THE OLFITES AND TPLFITES ARE JOINING HANDS TO ATTACK US AND TO CLAIM WOLLO AND DISINTEGRATE THE AMHARA KILIL. HOWEVER, THERE ARE MILLIONS OF ASAMINEW TISGIES AMONG US AND THINGS WILL BE QUITE DIFFERENT FROM WHAT OUR ENEMIES ARE EXPECTING. WHAT IS SURPRISING IS THAT THESE ALL ARE HAPPENING WITH THE KNOWLEDGE OF MR AHMED THE TRAITOR WHO IS BUSY JAILING AMHARAS.

      RIP MY HERO GENERAL ASAMINEW TISGIE

  3. ዘመኑ ጠፋብኝ ግን ጉዳዪ እንዲህ ነው። 707 የኢት. አየር መንገድ ከማድሪድ ስፔን ተነስቶ ወደ አቴንስ በመብረር ላይ ነው። ሳይታወቅ ጠላፊዎች ከተሳፋሪዎቹ ጋር ተጭነዋል። በዘመኑ በአሁኑ ብ/ጄ ተስፋዬ ሃ/ማሪያም ቀዳሚነት የሰለጠነ ጠለፋ አምካኝ ቡድን ከተሳፋሪው ጋር ተሰባጥሮ ተቀምጧል። ጠላፊዎቹ የተነገራቸው “አማራ መልክ ያላቸውና ጠንከር ጠንከር ያሉ ወንዶች” በጸረ ጠላፊነት አውሮጵላኑ ውስጥ እንደሚኖሩ ተነግሯቸዋል። ተነስተውም አውሮፕላኑ መጠለፉንና ሁሉም ትዕዛዝ ከእነርሱ ብቻ እንዲቀበል ያሳውቃሉ። ከዚያም የታጠቁ ሰዎችን ለማወቅ ፍተሻ ይጀምራሉ። ግን አልሆነም። ከጠላፊዎቹ አንዱ አንዷ አስተናጋጅ ላይ መሳሪያ ደግኖ ወደ አብራሪው ክፍል ለመግባት ሲቃጣ ከመቀመጫው በፍጥነት ተፈንጥሮ በመነሳት በታጠቀው ድምጽ አልባ መሳሪያ ይዘርረዋል። ሌሎች የደህንነት አባሎችም ቀሪዎችን ወደ እማይቀርበት ዓለም ይሽኟቸዋል።

    ሊባኖስ (በወያኔ ዘመን) – አንድ የወያኔን መከራ ሸሽቶ በዚያው ሃገር የተሰወረ ወገናችን መኖሩን የወያኔ የስደተኛ የስለላ መረብ ደርሶበታል። ታዲያ ሴት ልጅ አዘጋጅተው በእርሷ ፍቅር በማሳበብ ወጥመድ ውስጥ ሊያስገቡት ሌት ተቀን ይኳትናሉ። ልጅ ግን አያሌ ሃበሳ የቆጠረ በመሆኑ የሴት ፍቅር ሳይሆን ሁሌ የሚወዘውዘው የሃገሩ ሁኔታ ነበር። አልሆን ያላቸው ወያኔዎች የሥራ ማመልከቻ ፎርም መሙላት እንዲረዳት ሌላ እሱ ጋር የምትቀራረብ ሴት አዘጋጅተው መመሪያ ይሰጧታል። እቤቱ ስትሄድ ፍላሽ ድራይቭ፤ ፎቶ፤ ጽሁፍ ሌላም ነገር ሰርቀሽ ይዘሽ ነይ ይሏታል። እሷም ሳይሆንላት ተመልሳ ትመጣለች።
    ኤርትራ – ጦር ግንባር – በደርግ ጊዜ በዚህ ስፍራ እልክ አስጨራሽ እና ጭካኔ የተሞላበት ፍልሚያ ስለመደረጉ ለቋሚ ግልጽ ነው። በሊቀመንበሩ እቡይ አመራርና በጦሩ መሪዎች በነበረ ሽኩቻ ውድቀቱ ያለቅጥ የቀረበው ደርግ በየጎራው በሻቢያ ጦር እየተደመሰሰ ነበር። በዚህ ጊዜ ወደ 100 የሚጠጉ የጦር አባሎች ለሻቢያ እጃቸውን ይሰጣሉ። አማሮች ናችሁ ይላል የሻቢያው የብርጌድ መሪ? ዝምታ ይበዛል። መልስ የለም ከተማራኪዎች። ከደርግ የተማረከ ታንክ አስነስቶ 100 ውን ሰው ደፍጥጦ ይገላቸዋል። የነጻነት ዋዜማ ይሉሃል ይሄ ነው። አረመኔነት።
    ጎንደር – ወያኔ በድል አድራጊነት ገብቶ መንግሥት ነው ተብለናል። በዚህም በዚያም የሚራወጡት የወያኔ ቡችላዎች ብቻ ናቸው። ያሻቸውን ይገላሉ፤ ያስራሉ፤ ሲላቸው ይደበድባሉ ካልሆነም ከሻቢያ ጋር በመተባበር አሳልፈው ይሰጣሉ። ይህ በዚህ እንዳለ ለከተማይቱ የኤሌክትሪክ ብርሃን አመንጪ አንድ ትልቅ ጄኔሬተር ነቅለን ትግራይ እንወስዳለን ብለው ሃተፍ ተፍ ይላሉ። ደግሞም ይችላሉ። ችለዋልም። አይሆንም ያሉ ጥቂት ሰዎች በሽማግሌ ልመና ዝም እንዲሉ ይደረጋል። ወያኔ ቂም ቆጥሮ እነዚያን ሰዎች አንድ ባንድ አጠፋቸው። ታዲያ ይህን ሁሉ ምን አስባለህ ይል ይሆናል አንባቢ። ትንሽ ታገሱ ልጨርስ ነው።
    የአማራው ህዝብ ጠላት ወያኔ ብቻ አይደለም። ሻቢያ በአማራ ህዝብ ላይ ያለው ጥላቻ እስከ ወዲያኛው ዓለም ነው። ወያኔን ያሰለጠነ ያስታጠቀ እሱ ነው። አሁንም በሻቢያ ውስጥ ያሉ ሁሉ ይህ በሽታ አለቀቃቸውም። ችግሩ አማራው ኢትዮጵያ ኢትዮጵያ ሲል እነርሱ ከስር ስሩ ተንኮል እየሸረቡ ግልጽ እና ሰውር በሆነ መንገድ እዕላፍ የሃገሪቱ ልጆችን በንጉሱ ጊዜ፤ በደርግ ወቅትና እነርሱም የከተማ አለቆች ከሆኑ በህዋላ እንዲመነጠሩ አድርገዋል። አሁን ደግሞ አክራሪ ኦሮሞዎች ጭራሹን ከመሬታችን ውጡልን በማለት ለመከራና ለሰቆቃ ሰውን እየዳረጉ ይገኛሉ። ይህም ሻቢያ አስመራን ከተቆጣጠረ በህዋላ ካደረገው ወንጀል ጋር ይመሳሰላል። ወታደሩን፤ ሲቪሉን ቦዘኔውን ሰራተኛውን ኤርትራዊ ደም የላችሁም በማለት ሰብስቦ ሂድ ያቺ ናት አገራችሁ ከእኛ ጋር መኖር አትችሉም ብሎ በበረሃ የገፈተራቸው ስንቶች በውሃ ጥም እንዳለቁ የተረፉ ይናገራሉ። ያው ፓለቲካ ሸርሙጣ ስለሆነ ወያኔ ከሻቢያ ጋር ተፋልሞ ለዘመናት በኢትዮጵያ ውስጥ የኖሩትን ደማቹሁ ኤርትራዊ ነው በማለት ለገመና ዳርጓቸዋል። ወያኔ የአማራ ህዝብ ጠላት ነው። አማራው በራሱ አስቦ፤ ታጥቆና ተደራጅቶ፤ የሌላውን ወገናችን መብት ጠብቆ የራሱን መከላከል እስካልቻለ ድረስ መጠቃቱ አይቀሬ ነው። ለዚህ ደግሞ አንድ መሆን አስፈላጊ ነው። ይህ በፈጠራ የተዘራ የሙዚቃ ቅንብርም የአማራን ህዝብ ለመከፋፈል፤ ለማጋደል፤ ጭራሹን የበላይነት ለመያዝ ከሚጥሩ ሃይሎች የተንኮል ከረጢት አንድ ጠብታ ብቻ ናት። የማይፈነቅሉት ድንጋይ፤ የማይምሱት ጉድጓድ፤ የማይቀምሙት መርዝ የለም። መቼ ይሆን የምንነቃው? መቸ ይሆን የሞተ ሁሉ ተፈጥሮ እንደ ቀማን አምነን መቀበልን የምናቆመው? የወያኔ መርዛማነት ባህር ተሻጋሪ ነው። በሃገርም በውጭም ትላንትም ዛሬም ከሻቢያ የአየር መንገድ ጠለፋ ጀምሮ በከተማ ውስጥ የማያቋርጥ ሴራ ከመስራት በጭራሽ አያቆሙም። የተካኑበት በሽር ፓለቲካ ብቻ ነው። የወያኔና የሻቢያ መሪዎችና አባሎች በህይወት እስካሉ ድረስ አማራውን ከማጥቃት አይቆጠቡም። አሁን ደግሞ ጊዜው የሰጠው የኦሮሞ አክራሪ ቡድን በይፋ እየተባበራቸው ነው። አይ ሃገሬ እንዲህ ትሆኝ?

Comments are closed.

Share