ትግራይን መገንጠል ያስፈልጋል? – ማሕበር ኢትዮጵያውያን ተጋሩ

በኣሁኑ ጊዜ በኢትዮጵያ ውስጥ ከኣካባቢ ኣሰተዳደር ጥያቄ ያለፈ የመገንጠል ጥያቄ ዓላማ ለመተግበር የሚታገል ቡድን የለም። ይህም የኢትዮጵያ ህዝብ የኣንድነት መንፈስ ስለሚያመለክት ተገቢ ትኩረት ሊሰጠውና ሊዳብር ይገባዋል። ከዚህ ኣንጻር ሲታይ ኢትዮጵያ በመበታተን ኣፋፍ ላይ የምትገኝ የሚያስመስል ከእውነት የራቀ ቅስቀሳ ቦታ ሊኖረው ኣይገባም።

በትግራይ ውስጥም የመገንጠል ዓላማ ይዞ የሚታገል ቡድን ባይኖርም ደብረፅዮን (ዶ/ር) በትግራይ ህዝብ የመገንጠል ዝንባሌ እንደተከሰተ ገልፀዋል። ገለጻው ልክ መሆኑን በተጨባጭ ለማሳየት ሁለት ቅድመ ሁኔታዎች ያስፈልጋሉ። በኣንድ በኩል የህዝብን ፍላጎት ለማወቅ የሚያስችል ህዝቡን የመጠየቅ ድርጊት (ሰርቨይ) እና ድርጊቱን የሚፈጽም ሞያዊ ተቋም፡ በሌላ በኩል ደግሞ የህዝብ ነጻነት ያስፈልጋሉ። ትግራይ ውስጥ ሰላም ሊያስከብር፣ ሲፈልግም የወጣቶች መንጋ ሊያሰማራ የሚችል የክልል መንግስት

ኣለ የተጠቀሱት ሁለት ቅድመ ሁኔታዎች ግን የሉም። ስለዚህ የትግራይ ህዝብ ነ ነት ተሰምቶት በመንግስት የማይፈለግ ፍላጎቱን ሊገልጽ ኣይችልም።

የተጠቀሱት ቅድመ ሁኔታዎች ባይሙዋሉም የተወሰኑ የትግራይ ምሁራን የኢትዮጵያ ኣንድነት ኣስፈላጊነትን ማጣጣል ጀምረዋል። ይህ የመገንጠል ዝንባሌ በጥቂት የህወሓት መስራቾች የተጀመረ ነው። ምሁራን ፍላጎታቸውን የማስራጨት ኣቅም ስላላችው ዝንባሌው ክህወሓት ጋር ይሁን ካለ ህወሓት ሊቀጥል ስለሚችል በቀላሉ የሚታይ ኣይደለም።

በዚህ መሰረት የመገንጠል ዝንባሌው ምንጭና ምክንያቶች ማወቅ ያስፈልጋል። በ68 በተጻፈው የህወሓት ማኒፌስቶ ትግራይን መገንጠል እንደ ዓላማ ተገልጾ ነበር፣ የማኒፌስቶው መገንጠልን የሚመለከተው ይዘት የጥቂት ሰዎች ፍላጎት እንጂ የድርጅቱ ኣባሎች የተስማሙበት ስላልነበረና ተቀባይነት ስላልነበረው በትጥቅ ትግሉ ጊዜ እንደ ኣጀንዳ ተነስቶ ኣያውቅም። ሆኖም የመገንጠል ዓላማ ያነገቡ ሰዎችም ማንነታችው በድርጅቱ ኣባሎች ሳይታወቅና ከስልጣን ሳይወርዱ ቀጥለዋል።

ተጨማሪ ያንብቡ:  ሙሉ ፓርላማው ታፈነ | የጠቅላዩ ቅርብ ሰው ተሰደዱ | ፕሬዘዳንቱ ተከሰሱ

ህወሓት መንግስታዊ ስልጣን ከያዘ በ ላም የመገንጠል ዓላማ የጻፉ ሰዎች በይፋ የመገንጠል ፍላጎታቸውን ባይገልጹም ሌሎች ሰዎች ታሪክን ለታሪክነቱ ሳይሆን ለፖለቲካዊ የጥላቻ ቅስቀሳ እንዲሰራጭ ምቹ ሁኔታ በመፍጠራችው በትግራይ ህዝብ ባልተለምደ ሁኔታ መገንጠል የተወሰኑ ምሁራን ኣጀንዳ ሆነዋል። የመገንጠል ኣጀንዳው እየጎላ የመጣው የህወሓት ኣመራር በኢትዮጵያ ደረጃ የበላይነቱን ካጣ ወዲህ ቢሆንም ህወሓት በኢትዮጵያ ደረጃ የነበረውን ስልጣን ለማስመለስ የሚያደርገው ቅስቀሳ እንደሆነ ማየቱ ትክክል ኣይመስልም፤ ምክንያቱም የበላይነቱ በትግራይ ህዝብ ላይ ያስከተለው ችግር የትግራይ መሰረቱን እንደሚያሳጣው ያውቃል።

የመገንጠል ቅስቀሳውን የሚያቀጣጥሉት ዋና ምክንያቶች በትግራይ ተወላጆች ላይ የሚፈጸሙ ጥቃቶችና ህዝቡን የመደምሰስ ይፋዊ ኣረመኔዊ ቅስቀሳዎች ናቸው። የትግራይ ተወላጆች ከሌሎች ክልሎች፡ በተለይ ከኣማራ ክልል መፈናቀላቸው፣ መገደላቸው፣ ከትግራይ ጋር የሚያገናኘው መንገድ መዘጋቱ፣ በመንገድ ላይ የሚፈጸሙት ዝርፊያዎች ወዘተ.. በተራውና ባላጠፋ ህዝብ ላይ የሚደርሱ ችግሮች ስለሆኑ የመራራቅ ስሜት ፈጥርዋል፣ ድርጊቶቹ ህወሓትን የሚያጥናክሩ እንጂ የሚያዳክሙ ኣይደሉም።

ኢትዮጵያ ታሪካዊት ኣገር ናት፣ ህዝ  ም በብዙ መንገድ የተሳሰረና የተቀላቀለ ነው። ኢትዮጵያ የጥቁር ህዝቦች የነጻነት ተምሳሌት

የሆነችው በህዝ ህብረት ነው። የህዝባችን ብዛት የጋራ ገበያ ሲሆን የኣገራችን ስፋት የልዩ ልዩ ሃብት ምንጭ ነው። ፌደራል ስርዓቱ ኣብዛኞቹ የተደራጁ፣ መንግስታዊ ስልጣን የያዙ የብሄሮች ምሁራን ስለሚደግፉት በኣጭር ጊዜ የሚነቃነቅ ኣይደለም፣ በቋንቋ ላይ የተመሰርቱ ክፍለ ሃገሮች መኖራቸው ምሁራን ከተስማሙበት የመጣላት ምክንያት መሆን የለበትም። መገንጠል

ለማንም ኣይጠቅምም ኣያስፈልግም።

ህዝባችን የረዥም ዘመናት ስርዓትን የማክበር ልምድ ስላለው መንግስት ከፈለገ በቀላሉ ስርዓትን፣ የህግ የበላይነትንና ሰላምን ማስከበር ይችላል፣ ማስከበርም ኣለበት።

ተጨማሪ ያንብቡ:  የመንግስት ሰራዊት ከአማራ ክልል እየወጣ ነው፥ ደብረማርቆስ በድሮን ጥቃት ተፈጸመባት

ሰውን ማክበርና ህግን ማከበር ይደጋገፋሉ፣ ኣንድነታችን ይጠነክራል።

ሓምሌ 2011

 

 

5 Comments

    • Tigray existed as a proud and prosperous ancient country before it was annexed by the Ethiopian empire. The Ethiopian empire used the Tigraian civilization,history and culture to survive and be known in the world. The Tigraians also repulsed all the colonial powers that came to colonize the empire. The empire should have been colonized without the valor and military power of the Tigrains. The Tigraians are the first people in Africa to defeat the Italian colonial powers in the major battles.

  1. Tigaru people like Meles Zenawi while others donot like Meles Zenawi.Just for this reason we Tigaru chose to say BYE BYE!! We might change our minds if we see the Meles Zenawi’s billboards put back in every regions across Ethiopia otherwise we are out of this draining union.

  2. “የመገንጠል ቅስቀሳውን የሚያቀጣጥሉት ዋና ምክንያቶች በትግራይ ተወላጆች ላይ የሚፈጸሙ ጥቃቶችና ህዝቡን የመደምሰስ ይፋዊ ኣረመኔዊ ቅስቀሳዎች ናቸው” በለው! የውስልትና ፓለቲካ ሁለገብነት የለውም። ለዘመናት በህዝባችን ላይ ሰቆቃ ያደረስ ቡድን አሁን የትግራይ ህዝብ ተበደለ ብሎ ማላዘን ተንጋሎ መትፋት ነው። ማን ነበር በአርባ ጉጉ ህጻናት፤ አሮጊቶችና ሌሎች በቆንጨራ ሲገደሉ ቆሞ ያየውና ያስገደለው? ወያኔ አይደለም? ማን ነበር ፕ/አስራትን በሥጋ ማመላለሻ መኪና ወደፍርድ ቤት ያጓጉዝ የነበረው ኢ-ሰበአዊው ድርጅት፤ ማን ነበር አዲስ አበባ ውስጥ ነጋዴዎች ያጠራቀሙትን ቡና የሰረቀው? ማን ነበር የጋምቤላውን ፍጂት እንዲፈጸም መመሪያ የሰጡት አቶ መለስ ናቸው ብሎ ለመናገር ስነድ ይዞ እያለ ከሚበላው ምግብ ላይ መርዝ በመጨመር ወደ መቃብር ያወረደው? ማን ነበር በባህርዳር በአልሞ ተኳሾች ሰዎችን እንደ ቅጠል ያረገፈው? በመሰረቱ በትግራይ ተወላጆች ላይ ከሌላው የሃገሪቱ ክፍል ሰቆቃ የተለየ የደረሰባቸው ነገር የለም። እውነት ነው በወያኔ ተደግፈው ከበርቴ የሆኑትን አሁንም ቢሆን ሰው አይፈልጋቸውም። ግን ሃገር ወዳዱና ሃይማኖቱን ጠባቂው የትግራይ ህዝብ ወያኔ የሚነግድበት ዋሻ እንጂ ነጻነቱን አላገኘም። ወያኔ ሃገርን የሸጠ፤ ለዘመናት አብሮ የኖርን ህዝብ እርስ በርሱ እንዲባላ ያደረገ እኩይ ድርጅት ነው። እስቲ በቅርቡ በእነ ዶ/ር አረጋዊ ላይ የሆነውን ልብ ብሎ ሰው ያስብ? እኔ በነገሩ ከመገረሜ የተነሳ ዶ/ር አረጋዊ በእውነት መቀሌ ነው ወይስ ሰሜን ኮሪያ ነበር የሄደው ብዪ እንዳስብ ተገድጃለሁ። የነጻነት መለኪያው ለወያኔ የሰው ስቃይና ሰቆቃ ነው። በመሰረቱ የትግራይ ህዝብ መገንጠል ከፈለገ ያው እንደ ጎረቤት ኤርትራ ሲኖሩ ልጥቅ ሲለዮ ምንጥቅ ስለሆነ ይመቻቹሁ እንላለን። ይህ አይነቱ እብደት ግን ህዝባችንንን ማቆሚያ ወደሌለው የሰላም እጦት ይከታል እንጂ ሻቢይ ይለፍ እንደነበረው አፍሪቃዊቱን ታይላንድ አይፈጥርም። የቀድሞዋ ዮጎዝላቪያ ዛሬ ያለችበትን ማየት ታላቅ ትምህርት ይሰጣልና። ከጅምሩ ግን ወያኔ ጠባብ ድርጅት ስለሆነ የሚያስበውና የሚተነፍሰው እዚያው በረሃ እያለ በተገጠመለት ጭንቅላትና ሳንባ ነው። ጊዜ የማይሽረው ጥላቻ የተሞላ ስብዕና! በምዕራብ አውሮፓና በአረብ ሃግሮች እንዲሁም በሰሜን አሜሪካ ባጠቃላይ በአለም ላይ የተበተኑት የሻቢያና የወያኔ ጭፍን ደጋፊዎች ሰውን ያስፈራራሉ፤ ይደባደባሉ፤ የውሸት ወሬ ያናፍሳሉ፤ ጥቆማ ይሰጣሉ፤ ይቀበላሉ በድምሩ የራሳቸውን ምድር አጋይተው በመጠለያነት የሚኖሩበትን ህዝብና ሃገር ሰላም ይነሳሉ። ሲራመዱ፤ ሲተኙ፤ ሲበሉና ሲጠጡ የሚተነፍሱት ይህን ሽምድምድ ፓለቲካ በመሆኑ ለራሳቸውም ሆነ ላስጠለላቸው ሃገር አይጠቅሙም። ትግራይ ከኢትዮጵያ እንድትገነጠል የሚሹ የዚህ የፓለቲካ ውዥንብር ፈጣሪዎችና መሪዎች ብቻ ናቸው። የትግራይ ህዝብ ምርጫ ቢሰጠው ወያኔን አንድ ቀን ስልጣን ላይ አያቆየውም። መገንጠል የሚያመጣውን ያለፈ ሰቆቃ መረዳት ለሚሻ Freedom at Midnight by Larry Collins and Dominique Lapierre And/Or The Night Diary by Veera Hiranandani ማንበቡ የመገንጠልን ሰቆቃ አጉልቶ ያሳያል። ግን በራስ ፓለቲካ ለሰከሩ እውነት አትታያቸውምና ያው በዘርና በቋንቋችን ዙሪያ ተሰልፈን አካኪ ዘራፍ እንዳልን ብርሃንን ሳናይ ተጠርተን ወደ ማንመለሰማበት አለም እናሸልባለን። አይ ፓለቲካ…በአፍንጫዬ ይውጣ!!

Comments are closed.

Share