March 20, 2019
19 mins read

አትዮጵያን ለማፍረስ  እንደ አኔስቴዥያ  እያገለገሉ የሚገኙ አበይት ነገሮች!   (እያሱ ወልደ-ነጎድጓድ)

በሕክምና ስራ  ህሙማንን ለማከም በተደጋጋሚ ጥቅም ላይ ከሚውሉ መድኃኒቶች መካከል  አንዱ አኔስቴዥያ ነው፡፡ አኔስቴዥያ የአንድን ታካሚ ሰው  የማስታወሽ ችሎታ ለተወሰኑ ደቂቃዎች/ሰዓታት እንዳይሰራ በማድረግ(ሰመመን ውስጥ እንዲገባ በማድረግ) ሐኪሞች  አላስፈላጊ ነው የሚሉትን የታካሚውን የሰውነት አካል ተካሚው ሳይሰማ (ሳይሰቃይ) ለማስወገድ የሚጠቀሙበት አደንዛዥ መድሃኒት ነው፡፡ አንድ በዚህ ሂደት እግሩ የተቆረጠ ታካሚ እግሩ መቆረጡን የሚያውቀው እግሩ ከተቆረጠ ከደቂቃዎች በኋላ ነው፡፡

 

ከዚህ ዘንፃር በአሁኑ ወቅት ኢትዮጵያ ሀገራችንን ለማፍረስ ጸረ-ኢትዮጵያ ኃይሎች በሚያካሂዱት የባንዳነት ተግባር እንደ አኔስቴዥያ ሁነው በማገልገል ላይ የሚገኙ ነገሮች  ምን ምን ናቸው? የሚለውን ጥያቄ ማንሳት ሀገርን ከውድቀት ለመታደግ  ወሳኝ  ሚና አለው፡፡

ሀ፡ የኦነግና ህወሓት ህገመንግስትና የዘር ፌደራሊዝም

የኢትዮጵያ ህገ-መንግስት መጠራት ያለበት  በፈጣሪዎቹ ስም ‘’የህወሓትና የኦነግ ህገመንግስት’’ ተብሎ ነው፡፡ ኢትዮጵያ የሚለው ገላጭ ቃል ከህገ-መንግስቱ ፌት የገባው ኢትዮጵያውያንን ለማደንዘዝና ኢትዮጵያውያን  የኦነግና የህወሓትን ህግ መንግስት ጠባቂ ለማድረግ  ያለመ ሴራ ነው፡፡

ይህን አግላይ የህወሓትና የኦነግ ህገ-መንግስት መሠረት በማድረግ ህወሓት ላለፉት ሩብ ክፍለ ዘመን ኢትዮጵያውያንን ሲገድል፣በጉልበት የሌላውን ዕርስት ሲነጥቅ፣ህዝብ ሲያፈናቅል፣ፍጹም ኢሰባዊነት በጎደለው መንገድ የኢትዮጵያውያንን ጥፍር ሲነቅል፤ እግር ሲቆርጥና የሀገሪቱን አንጡራ ሀብት ያለምንም ርህራሄ በመዝረፍ ኢትዮጵያ በአጽሟ ብቻ እንድትቆም ያደረገ በሰው አምሳል የተፈጠሩ የአውሬዎች ስብስብ ድርጅት ነው፡፡ ህገ-መንግሰቱ ደግሞ ለህወሓትና ኦነግ እንደ በግ ለምድ የሚገለገሉበት ጸረ-አትዮጵያ ህገ-መንግስት ስመሆኑ በአሁኑ ወቅት ኢትዮጵያ ያለችበተ ነበራዊ ሁኔታ ብቻ በቂ ማስረጃ ነው፡፡

የህወሓትና የኦነግ ህገ-መንግስት የሌሎች ኢትዮጵያውያንን እርስት በመንጠቅ ለህወሓትና ለኦነግ ያስረከበ በመሆኑ ሁለቱ ድርጅቶች  ህገ-መንግስታቸውን እንደ አይናቸው ብሌን ይቆጥሩታል፡፡ ለዚህም ነው ህወሓትም ሆነ ኦነግ/ኦዴፓ  በአሁኑ ወቅት በተደጋጋሚ ህገ-መንግስቱ ይከበር፤ በህገ መንግስቱ አንደራደርም የሚል መፈክርና መግለጫ የሚያወጡት፡፡

 

ሁለቱ ጸረ-አትዮጵያ ድረጅቶች የዘር ፌደራሊዝሙና ህገ-መንግስቱ ኢትዮጰያውያንን ከቀያቸው እያፈናቀል፣ በህግ ሽፋን የከተማ ቤቶችች እያፈረሰ፣ ህዝባችንን ለርሀብና ለሞት እየዳረገ፣ ኢትዮጵያን በየቀኑ ወደ አዘቅት ውስጥ እድትገባ እያደረገ በተግባር  እየተመለከትን ህገ-መንግስቱና የዘር-ፌደራዝሙ የብሄረ -በሄረሰቦች ዋስትና ነው እያሉ የፌዙብናል፡፡

በእጅጉ የሚገርምው ደግሞ በአሁኑ ወቅት ሀገሪቱን እየመራሁ ነው የሚለው  ጠቅላይ ሚኒስትር  ዶ/ር አቢይ ህገ-መንግስቱ የአማራ ህዝብ ስለጠየቀ ብቻ አይሻሻልም በማለት ለአማራ ህዝብ ያለውን ኦነጋዊ  አስተሳሰብ  በአደባባይ ማንጸባረቁ ነው፡፡ የጠቅላይ ሚኒስትሩ  ትልቁ ጥያቄ መሆን የነበረበት ህገ-መንግስቱ የሁሉንም ህዝብ ፍላጎት ያካተተ ነው ወይስ አይደለም? የሚለው ነበር፤ ከዚያም ከፍ ሲል በህገ መንግስቱ ላይ ጥያቄ ያነሳው ህዝብ ከጠቅላላው የኢትዮጵያ ህዝብ ስንት ፕርሰንቱ ነው የሚለው የችግሩን አሳሳቢነት ለመረዳት ይጠቅም ነበር፡፡

የአማራ ህዝብ ህወሓትን በነፍጥ በመፋለም ተስፋ ቆርጦ ወደ መቀሌ እንዲሸመጥጥ ያደረገና አቢይ ወደ ስልጣን እንዲመጣ ቁልፍ ሚና የተጫወተ ህዝብ ነው፡፡ ይሕ ህዝብ  ለሩብ ክፈለ ዘመን ከፌደራል መንግስቱ ተገልሎ የኖረ ቢሆንም  አሁን ተራው የእኔ ነው ሳይል በኢትዮጵያዊነቱ ላየ ብቻ  በማተኮር ዶ/ር አቢይ በኦዴፓ/ኦነግ ፕሮፓጋንዳ የተመረዘ መሆኑን  እያወቀ  ኢትዮጵያዊነትን ስላቀነቀነ  ብቻ ከኦሮሞ  በበለጠ ሙሉ  ድጋፉን  የሰጠ ህዝብ ነው፡፡ የጠቅላይ ሚ/ሩ ምላሽ ግን ብር ላበድር ጠጠር እንደሚባለው ሆኖ አረፈ፡፡

በጥቅሉ  አፍቃሪ ኢትዮጵያውያን ህገ -መንግስቱንና  የፌደራሊዝሙን ስርዓት  አግዝፈውና አይነኬ አድርገው እንዲመለከቱ በማድረግ የህገ-መንግስቱና የዘር ፌደራሊዝም ብቸኛ ተጠቃሚዎች(ህወሓትና ኦነግ)  ኢትዮጵያን በማፍረሱ ሂደት ላይ ከአፍቃሪ ኢትዮጵያውያን እንቅፋት እንዳይገጥማቸው  እንደ አኔስቴዥያ  የሚጠቀሙበት ጸረ-ኢትዮጵያ  ህገ-መንግስት ነው፡፡

 

ለ. የይስሙላ ተቃዎሚወች አፍዝ አደንግዝ ፡ በኢትዮጵያ ለሩብ ክፍለ ዘመን ይሕ የሰው በላ ስርአት ጠንክሮ እንዲቆይ ካደረጉት ምክንያቶች አንዱ የይስሙላ ተቃዋሚ ፓርቲዎች መኖር ነው፡፡ አብዛኛዎቹ በገዥው ፓርቲ የተቋቋሙና ለመንግስት ጆሮ ሆነው የኖሩ፤ ብዙ ህዝብ ያስጨረሱ ናቸው፡፡በይስሙላ ፓርቲዎች ስም ኢህአዴግ የፖለቲካ ምህዳሩ ሰፊ ነው የሚል ፕሮፓጋንዳ ለውጭ ሀገራት  በማሰራጨት በአንድ በኩል ብድር የማግኘት እድሉን ከፍ በማድረግ በሀገሩቱ ስም የተበደረውን ብድር ለግል ጥቅም በማዋል ኢትዮጵያ በእዳ እንድትዘፈቅ አድርጓል፡፡ በሌላ በኩል  ብዙ የይስሙላ ፓርቲዎች መኖር የዲሞክራሲ መኖር ነው ብለው የውጭ ሀገሮች እንዲገነዘቡ በማድረግ በኢትዮጵያ ነግሶ የኖረውን ግፍ እንዳያወግዙ አድርጓል፡፡ በተመሳሳይ ሁኔታ አፍቃሪ ኢትዮጵያውያን የይስሙላ ፓርቲዎች ለውጥ ሊያመጡ ይችላሉ ብለው እንዲያምኑ በማድረግ በሀገራቸው ላይ የተጋረጠውን የመፈረካከስ አደጋ  በፍጥነት እንዳያያዩና ሀገርን የመታደግ እንቅስቃሴ እንዳያደርጉ ትልቅ አስተዋጾ አድርገዋል፡፡ ስለዚህ አሁንም ከ100 በላይ የሚሆኑ  ተቃዋሚ ፓርቲዎች  ሀገር ከውድቀት ለመታደግና እውነትን ለመጋፈጥ ወኔ የሌላቸው አብዛኛዎቹም የመንግስት ፍላጎትን ለማሳካት የተሰለፉ አነስቴዥያዎች ናቸው፡፡ ስለዚህ አፍቃሪ ኢትዮጵያውያን ከነዚህ አደንዛዥና አስመሳይ የፖለቲካ ፓርቲዎች በመውጣት ኢትዮጵያን ለመታደግ በተግባር ላይ የተመሰረተ እንቅስቃሴ ልናደርግ ይገባል፡፡ ኦነግና ህወሓት ሀገሪቱን ለማፍረስ ቀን ተሌት እየሰሩ  ለመሆኑ አስረጅ አያስፈልግም፡፡

 

ሐ. የኦሮሞ ዴሞክራቲክ ፓርቲ (ኦዴፓ) አደንዛዥ ስልቶች፡

የህወሓትን ፈላጭ ቆራጭነት ለማስወገድ በተደረገው ትግል አብዛኛው የኢትዮጵያ ብሄር ቤሄረሰቦች ከፍተኛ አስተዋጾ አድርገዋል፡፡ በተለይም በአማራና በኦሮሚያ ክልሎች ወጣቶች ያካሄዱት እልህ አስጨራሽ ትግል ከፍተኛው ነው፡፡ በአማራ ክልል ፋኖው ከማንም በላይ በነፍጥ በመታገዝ  የህወሓትን  ሰራዊት ያርበደበደ ኃይል ነው፡፡ ህወሓት በውጊያ ላይ የተገደሉ ወታደሮቹን እሬሳ በልመና  ለቀብር ይቀበል እንደነበር በወቅቱ የተሰራጩ መረጃዎችን ማስታወስ በቂ ነው፡፡

ይሁን እንጅ የኦዴፓና አዴፓ መሪዎች የወጣቱ  ትግል መሪ አልባ መሆኑን በመገንዘብ ከህወሓት አሽከርነት  በመውጣት የለውጡን ኃይል ተቀላቀሉ፤ የለውጡም መሪዎች  መሆን ቻሉ፡፡

በዚህ የለውጥ ሂደት ኦዴፓ ሁለት ግቦችን ይዞ ተንቀሳቅሷል፡- አንደኛው የኦሮሞ ወጣቶችን እንቅስቃሴ መምራት ሲሆን ሁለተኛው ግን  የሀገሪቱን ስልጣን ለመቆጣጠር እንዲረዳውና ከህወሓት የሚሰነዘረውን ብትር ለመመከት  ከአዴፓ ጋር ጊዚያዊ ትብብር መመሥረት ነበር፡፡

ነገር ግን ኦዴፓ ከአዴፓ አንድ መሰረታዊ ችግር እንዳለ ተገነዘበ ፤እርሱም አዴፓ በአማራ ህዝብ ዘንድ ተቀባይነቱ ውስን መሆኑ፡፡ ስለዚህ ይህን የአዴፓ ውስንነት በማስወገድ የአማራንና አዴፓን ተቀባይነት ለማግኘት ዘዴ ማፈላለግ ነበረበት፡፡ በዚህም ጊዜ የወሰደ ጥናት አድርጎ የነደፈው ስልት አማራን ማታለል የሚቻለው በኢትዮጵዊነት ጉዳይ ላይ ለተወሰኑ ወራት  ስናተኩር ነው የሚል ነበር፡፡ በዚህ መሠረት አቶ ለማ መገርሳና ዶ/ር አቢይ የስራ ክፍፍል አደረጉ፡፡ አቶ  ለማ ኢትዮጵያ ‘’ሱስ’’ ነች በማላት አማራን ብቻ ሳይሆን መላው አፍቃሪ ኢትዮጵያውያንን ድጋፍ አገኘ፡፡ ዶ/ር አቢይ ደግሞ ከአሜሪካኖች በተቀዳ ሀገርና ፈጣሪን የማያያዝ ስልት ተጠቅሞ  ‘’ፈጣሪ ኢትዮጵያን ይባርክ ; ስንኖር ኢትዮጵያዊ ስንሞት ኢትዮጵያ’’ በሚሉ በባለሙያ የተጠኑ ሀሳቦች ሁሉንም ኢትዮጵያውያን በሚባል ደረጃ ከጎናቸው አሰልፉ፡፡ ህዝቡ ቆም ብሎ የቆየ ተግባራቸውን እንዳያጤን  በማድረግ በስሜት እንዲጋልብ አደረጉ፡፡ምሁራን  ነኝ የሚሉ ሳይቀር በስሜት ውስጥ ገብተው ለግለሰቦቹ መለኮታዊ ፍቃድ ያላቸው በማስመሰል እነረሱ  ተሸውደው ሌላውን ኢትዮጵያዊ ሂደቱን በአንክሮ እንዳያዩ የራሳቸውን  አሉታዊ አስተዋጾ አድርገዋል፡፡

 

ነገር ግን ለረጅም ዘመን የቆየና ስር የሰደደ ጸረ-ኢትዮጵያዊ አስተሳሰብ በመፈክር ስለማይቀር አቶ ለማ መገርሳ አንድ አመት ሳይሞላቸው ከኢትዮጵያዊነት ሱስ ሙሉ ሙሉ ወጥተው በኦሮሞነት ሱስ ውስጥ ወደቁ፤ የኦሮሞንም ህዝብ በሌላው ኢትዮጵያ ህዝብ  እንደ ስጋት እንዲታይ አደረጉ፡፡ እርሳቸውም በኢትዮጵያውያን  ከወጡበት የክብር ማማ ተነስተው ወደ ውርደት ጋጣ ወረዱ፡፡ ምስጋና ይገባውና ለፈጣሪ  በአጭር ጊዜ  ድብቅ አጀንዳቸው ተጋልጠ እንጅ ለብዙ ኢትዮጵያውያን እንደ አኔስቴዥያ ሁነው ነው የቆዩት፡፡

ጠቅላይ  ሚኒስትር ዶ/ር አቢይ ምንም እንኳ የሀገሪቱ  ጠቅላይ ሚኒስትር ቢሆኑም የአቶ ለማ መገርሳን ሀሳቦችና ድርጊቶች ከመጋራት አልፈው እቅድ ያወጡ ናቸው ቢባል ማጋነን አይሆንም፡፡ አንዱ በሌላው ሳንባ ነው የሚተነፍሱት፡፡ ልዩነቱ አቶ ለማ መገርሳ ስሜቱ ቶሎ ፈንቅሎት ስለወጣና ስለተጋለጠ እንጅ ከአቶ ለማ ይልቅ አደገኛው ጠቅላይ ሚኒስትሩ  እንደሚሆን በሂደት እናየዋል፡፡ እስከአሁነም የወሰዱት እረምጃ በዘረኝነት ላይ የተመሠረተ፣ ኦዴፓን በማንገስ ሌሎችን በባርነት እንዲኖሩ የሚያደርጉ ስራዎች ናቸው፡፡ ድርጊታቸውን በመረጃ ለማስደገፍ ከተፈለገ በመከላከያ ሰራዊት ውስጥ ያካሄዱት ሪፎርም ስልጣኑን ከህወሓት ወደ ኦዴፓ አሸጋግረዋል፤ በአዲስ አበባ ዙሪያ እየተፈጸሙ ለሚገኙ ግፎች( የአሸዋ ሜዳ ግፍ፤ የለገጣፎ መፈናቀል፤ የአዲስ አበባ ህዝብ ስብጥር የመቀየር እኩይ ተግባር) አልሰማሁም በማለት በህዝብ አፊዘዋል፤ ወሳኝ የፌደራል ስልጣኖችን በሙሉ በሚባል መልኩ ለኦዴፓ አስረክበዋል፤ አብሮት የታገለውን አዴፓ አንድ አመት ሳይሞላ ክደዋል፤በሀገሪቱ በኦነግ/ኦዴፓ የሚፈጸመውን ግፍ በዝምታ ተመልክተዋል እየተመለከቱ ነው፤የኢትዮጵያ ንግድ ባንኮች በኦነግ ሲዘረፉ ምንም አይነት እርምጃ አልወሰዱም፡፡ እየሰሩት ያለውን  ሀገር አፍርስ ስህተት ኢትዮጵያውያን እንዳይቃወሟቸው  መገምገም ያለብኝ በተርም ነው እኔ ግን ገና አንድ አመቴ ነው በማለት በኢትዮጵያውያን  አሹፈዋል ፡፡

በአጠቃላይ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር አቢይ በመድረክ ላይ ፍቅርና ሰላምን በመስበክና ኢትዮጵያውያንን በማደንዘዝ ኢትዮጵያውያን እያዩ ሀገራቸው እንድትፈረስ እያደረጉ ነው፡፡ ስለሆነም  ኢትዮጵያውያን ሀገራችንን ከውድቀት ለመታደግ  ከአደንዛዦች እንጠንቀቅ፤ሀገራችንን ከውድቀት ለመታደግ  አሁኑኑ እየተናበብን እንቀሳቀስ፡፡

 

ኢትዮጵያ በክፉ ቀን ልጆቿ ይህን ክፉ ዘመን በድል ትሻገራለች!

Go toTop