March 13, 2019
2 mins read

በኢትዮጵያ የፖለቲካ ምህዳሩ ሙሉ ለሙሉ መዘጋቱን አቶ አንዳርጋቸው ጽጌ ገለጹ

andargachew 101

አቶ አንዳርጋቸው ጽጌ በተለይ ለDW በሰጡት ቃለ ምልልስ ዶክተር አብይ ስልጣን እንደያዙ የፖለቲካ ምህዳሩ መስፋት ቢጀምርም በየክልሉ ያሉ የኢህአዴግ አባላት ከቀደመው ሥርዓት በከፋ መልኩ ሙሉ ለሙሉ የፖለቲካ ምህዳሩን እንደዘጉት ይፋ አድርገዋል::የዜግነት ፖለቲካ አራማጅ ድርጅቶችን በጠላትነት ፈርጀው እንቅስቃሴያቸውን ገድበዋል ሲሉም ተናግረዋል።

የኢትዮጵያ መንግሥት ካለው ጉልበት በላይ በፌደራሊዝም ሥርዓት ስም የራሳቸውን የደህንነት መዋቅር ወታደራዊ ኃይል እና በዘር ላይ የተመሰረተ ሚድያ ያደራጁ የክልል አስተዳደሮች በዴሞክራሲ ሥርዓት ግንባታው ላይ ትልቅ ማነቆ መፍጠራቸውን የአርበኞች ግንቦት 7 ከፍተኛ አመራር አስታወቁ:: የድርጅቱ ዋና ጸሃፊ አቶ አንዳርጋቸው ጽጌ በተለይ ለ DW በሰጡት ቃለ ምልልስ ዶክተር አብይ ስልጣን እንደያዙ የፖለቲካ ምህዳሩ መስፋት ቢጀምርም በየክልሉ የሚገኙ የኢህአዴግ አባላት ከቀደመው ሥርዓት በከፋ መልኩ ሙሉ ለሙሉ የፖለቲካ ምህዳሩን እንደዘጉት ይፋ አድርገዋል:: እነዚህ አባላት የዜግነት ፖለቲካ አራማጅ ድርጅቶችን በጠላትነት ፈርጀው እንቅስቃሴያቸውን ገድበዋል ሲሉም ተናግረዋል። በዚህ የተነሳም የሕብረተሰቡም ሆነ የአገሪቱ ህልውና በአሁኑ ወቅት ከመቼውም ጊዜ በላይ ከፍተኛ አደጋ እና ስጋት ውስጥ ወድቋልም ብለዋል:: ዝርዝሩን እንዳልካቸው ፈቃደ አጠናቅሮታል::

እንዳልካቸው ፈቃደ

ኂሩት መለሰ

እሸቴ በቀለ

DW

2 Comments

  1. wow Anbesaw Andargachew you hit the nail on the head and you make my day. semi joro kale Ethiopian ena hezbuwan madaginaw gize ahun new !tebarek. Ethiopian Egzer yetebkat !

  2. ይህ የመነጋገሪያ ሃሳብ ለሁላችንም እንዲሆን ሼር ቢዲረግ ጠቃሚ ይመስለኛል፤
    ለሁሉም ነገር የፈጣሪያችን መልካም ፈቃድ ይሁንልን፥ ዓሜን

    #በብሄር ብሎም #በሃይማኖት ስም ለፖለቲካ መደራጀት በህገመንግስቱ መከልከል አለበት ሲሉ የኢትዮጵያውያን አሜሪካውያንሲቪክ ካውንስል ሰብሳቢ ዲ #ዮሴፍ_ተፈሪ ተናገሩ። ይህን የተናገሩት #በ123ኛው በኮሎራዶ የአደዋ በአል አከባበር ላይ ነው። ሀገራችን መስቀለኛ መንገድ ላይ ነች በዘርና በሃይማኖት መደራጀት ሃፂያት ነው ሲሉ መልክታቸውን ለመላው የኢትዮጵያ ህዝብ አስተላልፈዋል።

Comments are closed.

Kimant i
Previous Story

በሰሜን አሜሪካ ከምንገኝ የቅማንት ተወላጆች የተሰጠ መግለጫ

Next Story

በአንድ ሀገር፣መንግሥት ዜጎች በህግ የሰጡትን ሥልጣን (ጉልበት ወይም ተመጣጣኝ ኃይል ) በአግባቡ ካልተጠቀመ አናርኪዚም እየተንሰራፋ ይሄዳል

Latest from Blog

አስቸኳይ ህዝባዊ ጥሪ

July 24, 2024 ዓለማቀፍ ትብብር ለኢትዮጵያዊያን መብት Global alliance for the Rights of Ethiopians (GARE) በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ገዜ ጎፋ ወረዳ ኬንቾ ሳቻ ጎዝዲ ቀበሌ በደረሰው የመሬት መንሸራተት የብዙ ወገኖቻችንን ህይዎት ማለፉን
Go toTop