የአረና ትግራይ ስትራቴጂውን እና አማራጭ ፖሊሲውን ለመቀሌ ሕዝብ አስተዋወቀ

ዓረና ትግራይ ዛሬ እሁድ 17/06/2011 ዓ/ም በትግራይ ከመቀሌ ሕዝብ ጋር ተወያየ:: በስብሰባው አረና አማራጭ ፖሊውንና ስትራተጂውናን ለሕዝብ ያስተዋወቀ ሲሆን በሃገሪቱ ወቅታዊ ፖለቲካዊ ሁኔታ ከሕዝቡ ጋር ተወያይቷል:: ስብሰባው የተሳካ እንደነበር የድርጅቱ አመራር አቶ አምዶም ገብረሥላሴ ገልጸዋል::

https://www.youtube.com/watch?v=ZdkEBlHGPDA&t=1s

ተጨማሪ ያንብቡ:  Sport: የባርሴሎናው ቴክኒሻን ኢኔሽታ ውለታውን እየመለሰ ነው

1 Comment

  1. እንኳን ደስ አላችሁ
    ይህ ቀላል ስኬት አይደለም፡፡ ፓርቲው እንኳን በነጻነት ስብሰባ ሊያካሂድ ይቅርና አባላቱ ሻይ ቤት ቁጭ ብለው ማውራት አይችሉም ነበር፡፡ ወያኔ ሲስራችሁና ሲያሳድዳችሁ እንደነበር በተለያዩ መድረኮች ስትገልጹልን ነበር፡፡ ወዶ ሳይሆን በህዝብ አስገዳጅነት ወያኔ በመቀሌ ጭምር ይህን መሰል መድረክ እንዲከፈት መፍቀዱ ዲሞክራሲያዊነቱን እረጋገጥልን ሳይሆን በግዱ ያደረገው፣ እምቢ ቢል ምን ሊደርስበት ስለሚያውቅ ነው፡፡ አሁን ከተግራይ አደረጃጀት ውጭ ያሉ ፓርቲዎች መቀሌ መጥተው እራሳቸውን ሲያስተዋውቁ መስማት እንሻለን፡፡ የዚህ ጊዜ ጥቂት የሚመጡ ሰዎች በወያኔ አደረጃጀት በኩል ጥያቄ፣ ስድብ፣ ዛቻ፣ ማጣጣል እንደሚደርስባቸው ይሆናል ብለን ብናስብ ተሳስተን ይሆን፣
    ለማንኛውም የህወሃትን ሴራ ከአረና በላይ አናውቅምና ይህቺን ደቃቅ ቀዳዳ ፈቅዶ ጠልፎ ወደቀድሞው እንዳያስገባችሁና አሽከር እንዳያደርጋችሁ መጠንቀቅ ያስፈልጋል፡፡ የጋራ ሃሳብ ለማስመሰል ህገ-መንግስቱ ጠጥሷል፣ የትግራይ ህዝብ ተፈናቅሏል፣ ወልቃይትና ራያን ሊወስዱብን ነው፣ የድንበር ኮሚሽኑ ያነጣጠረው ትግራይ ላይ ነው በሚል ሴራ 27 አመት ሲጨፈጭፍ፣ ሲያስር፣ ሲገድል የነበረ ቡድን ዛሬ ቢሸብባችሁ ከሰማችሁት ድሮም እንትን ቢሸፍት የሚለው ተረት ግጥማችሁ ይሆናል፡፡

Comments are closed.

Share