አዴፓ በአዲስ አበባ የባለቤትነት ጉዳይ ላይ ጠንካራ አቋም እንዳለው አስታወቀ

የአማራ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ (አዴፓ) አዲስ አበባ የነዋሪዎቿ እንድትሆን እና አግላይ አመለካከቶች እንዲወገዱ በትኩረት እንደሚሠራ አስታወቀ:: ድርጅቱ በአዲስ አበባ ከሚገኙ የአዴፓ አመራሮች ጋር ከተወያየ በኋላ ዉይይቱን የመሩት የአዴፓ ማዕከላዊ ኮሚቴ ጽሕፈት ቤት ኃላፊ አቶ ምግባሩ ከበደ እንደገለጹት አዲስ አበባ የነዋሪዎቿ እና የኢትዮጵያ መዲና እንጅ የማንም አይደለችም፡፡

https://youtu.be/9_PNwyW18Qg

አዲስ አበባን የነዋሪዎቿ መዲና እንዳትሆን አጀንዳውን የሚያራግቡት ለዉጡን የማይደግፉ ኃይሎች የሚጠነስሱት የፖለቲካ ሤራ መሆኑን ነው ያሉት አቶ ምግባሩ ፡ ‹‹ችግር የሚፈጥሩ ግለሰቦች ወይም አመራሮች ካሉም በማጣራት እና ከሚመለከተዉ አካል ጋር በመሆን ጉዳዩ ይፈታል:: በአዲስ አበባ ባለቤትነት ጉዳይ አቋማችን ጠንካራ ነው›› ብለዋል፡፡

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ምክትል ከንቲባ እና የንግድና ኢንዱስትሪ ቢሮ ኃላፊ ኢንጅነር እንዳወቅ አብቴ በበኩላቸዉ ‹‹አዲስ አበባ የራሷ መዋቀር እና አስተዳደር ያላት የኢትዮጵያ እና የአፍሪካ ከተማ እንጅ የማንም አይደለችም::” ብለዋል;; በዚህ ጉዳይ ላይ ችግር ካለም በዉይይት እንደሚፈታና ችግር ፈጣሪዎችም ተናግረዋል:: በአዲስ አበባ የሚኖሩ የአዴፓ አመራሮችም አዲስ አበባ የሚኖረዉ የአማራ ሕዝብ መብትና ጥቅም እንዲከበር ጠንክረዉ እንደሚሠሩ በመግለጫቸው ላይ ተናግረዋል::
በሌላ በኩል አዴፓ በዛሬው ዕለት በአራዳ ክፍለ ከተማ ከአባሎቹ ጋር አድርጓል::
ይህ በ እንዲህ እንዳለ የሕወሓት 44ኛ ዓመት የምሰረታ በአል በአዲስ አበባ የተለያዩ ክፍለ ከተማዎች ተከብረዋል:: በአራዳ ክፍለ ከተማ እና በአቃቂ ቃሊቲ የሚኖሩ የድርጅቱ ደጋፊዎች እና አባላት የመለስ ዜናዊን ምስል ይዘው ወጥተዋል::

ተጨማሪ ያንብቡ:  ለነጭ ፈረስ አትሁን - ድምፃዊ አቡሽ ዘለቀ እያለቀሰ ያስተላለፈው መልዕክት -ጦቢያ

2 Comments

  1. በታሪክ ኣጋጣሚ፣ ትናንት ኣባቶቻችሁ ኢትዮጵያ ነጻነቱዋን ጠብቃ ፣ ልጥቁር ህዝብ የነጻነት ኣርማ እንዳረጉዋት ሁሉ ፣ዛሬ በእናንተ ጫንቃ ላይ ኢትዮጵያን እንደ ሀገር የማስቀጠል ሀላፊነት ተጥሎኣል።
    ንቁ፣ ተደራጁ ፣ ኣደራጁ !!
    እግዛብሄር እትዮጵያን ይጠብቅ !!

  2. አዲስ አበባ የብሔረሰብ ይሁን ከተባለ የአማራ ናት። ምክናያት ከተፈለ ሺ ምክናያት መዘርዘር ይቻላል።

Comments are closed.

Share