በአሜሪካ አሌክሳንድሪያ ቨርጂኒያ ውስጥ ነዋሪ የሆኑት አቶ መርጊያ ንጉሴ ፍርድ ቤት ቀርበው ጥፋተኛ ተባሉ

በአሜሪካ አሌክሳንድሪያ ቨርጂኒያ ውስጥ ነዋሪ የሆኑት አቶ መርጊያ ንጉሴ ትንናት ፍርድ ቤት ቀርበው ጥፋተኛ ተባሉ፡፡

https://youtu.be/9_PNwyW18Qg

የ58 አመቱ አቶ መርጊያ ጥፋተኛ የተባሉት በማጭበርበር የአሜሪካ ዜግነት አግኝተዋል በሚል ነው፡፡ በዛሬው እለት የተሰየመው ፍርድ ቤቱ እንደገለፀው አቶ መርጊያ በቀይ ሽብር ወቅት ተጠርጣሪ እስረኞችን ደብድበዋል፣ ገርፈዋል፣ አሰቃይተዋል፡፡ ይህ ድርጊት የተፈፀመባቸው ግለሰቦችም ለዘላቂ ጉዳት ተጋልጠው ይገኛሉ፡፡

 

ይሁንና በ1999 እ.ኤ.አ ወደ አሜሪካ በገቡበት ወቅት ለኢምግሬሽን ሰራተኞች ሙሉ በሙሉ ውሸት የሆነ ታሪክ ተናግረው የስደተኝነት ፈቃድ ማግኘታቸውንና በ2008 ደግሞ የአሜሪካ ዜግነት እንደተሰጣቸው ፍርድ ቤቱ አስታውቋል፡፡ የአሜሪካ ዜግነት ለማግኘት ቃለመጠይቅ በተደረገላቸው ወቅት ማንንም ሰው በፖለቲካ አመለካከቱ ምክንያት እንዳላሰቃዩ ተናገረው የነበረ ቢሆንም ለፍርድ ቤቱ ግን ያንን ያሉት በሀሰት እንደነበር አምነዋል፡፡ በአሜሪካ ህግ መሰረት በሀሰት መግለጫ ዜግነት ማግኘት ክልክል በመሆኑም የጥፋተኝነት ውሳኔ እንደተላለፈባው ፍርድ ቤቱ አስረድቷል፡፡ የአሜሪካ ረዳት ጠቅላይ አቃቤ ህግ ቤንዝኮወውስኪ እንደተናገሩት ከባድ የሰብአዊ መብት ጥሰት ፈፅመው ራሳቸውን ደብቀው አሜሪካ ለሚኖሩ ሰዎች ምንም ምህረት የሌለ ሲሆን ሌሎች እንደ መርጊያ አይነቶችም ታድነው ለፍርድ ይቀርባሉ፡፡ አቶ መርጊያ የፊታችን ሜይ 17 ቀን ፍርድ እንደሚሰጣቸው ለመረዳት ችለናል፡፡

ተጨማሪ ያንብቡ:  የጠበቆች ማህበር በአርቲስት ግሩም ኤርሚያስ ላይ የወንጀል ክስ መመስረታቸው ተሰማ
Share