ጎንደር እየደማች ነው

በጎንደር ከተማ አዘዞ አካባቢ ትናንት ከምሽቱ 5 ሰአት ላይ ሕወሓት የሚመራው የቅማንት ኮሚቴ ስር በተደራጁ ኃይሎች ባስነሱት  ከፍተኛ  የ እሳት ቃጠሎ 20 የከብቶች ማድለቢያና የወተት ላሞች ማርቢያ የነበሩ ቤቶች ሙሉ በሙሉ የወደሙ ሲሆን 51 ከብቶችም ጉዳት ደርሶባቸው መሞታቸው ታወቀ::

https://www.youtube.com/watch?v=PfVYx0Ma0Rs&t=440s

በማዕከላዊ ጎንደር ነዋሪ የሆኑ የዓይን  እማኞች እንደተናገሩት ትናንት ምሽት በጎንደር ከተማ አስተዳደር አዘዞ አካባቢ ልዩ ሥሙ ግራር ሰፈር በሚባል ቦታ በእንስሳት ማድለቢያ ላይ ይህ በሕወሓት የሚመራው የቅማንት ኮሚቴ ባስነሳው እሳት 60 የሚደርሱ የደለቡ ከብቶች ተቃጥለዋል፤ በጣት የሚቆጠሩ ከብቶችን ብቻ በሕዝቡ ጥረት ማትረፍ ተችሏል፡፡

የአይን ምሥክሮቹ እሳቱን ለመቆጣጠር የአካባቢው ነዋሪና የጎንደር ከተማ አስተዳደር ጥረት ቢያደረጉም መቆጣጠር የተቻለው በዳግማዊ ቴዎድሮስ አየር ማረፊያ የእሳት አደጋ መከላከያ ተሽከርካሪና ሠራተኞች እገዛ ነው:: ምናልባትም የቴዎድሮስ አየር ማረእፊያ የእሳት አደጋ መከላከያ በፍጥነት ባይደርስ ኖሮ አደጋው ከዚህም በላይ የከፋ ይሆን ነበር::

ሌሊቱን  ሙሉ በአዘዞ አካባቢ ተኩስ እንደነበር የአካባቢው ነዋሪዎች ገልጸው ንብረቱ የወደመባቸው በብድር ገንዘብ ተደራጅተው በከብት ማድለብ የተሠማሩ ወጣቶችን ንብሬት ነው ተብሏል::

በጎንደር ከተማ አስተዳደር የ5ኛ ፖሊስ ጣቢያ የወንጀል ምርመራ ባለሙያ ምክትል ሳጅን ሙሐመድ ሰይድ  በጉዳዩ ላይ ተጠይቀው “ምሽት 5፡00 አካባቢ እሳት ቃጠሎው መነሳቱን አስታውሰው በማድለቢያና እንስሳት እርባታ ድርጅት ላይ በደረሰ ቃጠሎ 51 የቁም ከብቶች መሞታቸውን  አረጋግጠናል:: ቃጠሎው በደረሰበት አካባቢ የእንስሳት መኖ መኖሩ ለቃጠሎው መባባስ አስተዋጽኦ አድርጓል” ያሉት  ምክትል ሳጅን ሙሐመድ ‹‹የአደጋውን መንስኤ ለማወቅ የምርመራ ሂደቱ እንደቀጠለ ነው፤ በአካባቢው ለእሳት መነሳት ምክንያት የሚሆን ተፈጥሯዊ ምክንያት አልነበረም:: ድርጊቱን የፈጸሙ አካላትን በተመለከተ መረጃ መስጠት የሚፈልግ ሁሉ ለፖሊስ ጣቢያው ጥቆማ መስጠት ይቻላል:: ወደፊት ውጤት ላይ ስንደርስ ለሕዝብ እናሳውቃለን›› ብለዋል፡፡

ተጨማሪ ያንብቡ:  የተደበቀው የህወሓት ማንነት ከደደቢት እስከ ቤተ መንግስት (ክፍል 8) - በአየር ኃይል በህወሓታዊያን ብቻ የተያዙ ከፍተኛ የአዛዥነት ቦታዎች

በጎንደር ያለው ሁኔታ እጅግ እየተባባሰ ሄዷል:: በአሁኑ ወቅት በዚህ ግጭት የተነሳ  39 ሺህ ያህል ሰው ከማዕከላዊ ጎንደር መፈናቀሉ  ተገልጿል:: የሕወሓት ቡድን ባስነሳው ግጭቶች የተነሳም በአጠቃላይ  በክልሉ 80 ሺህ ተፈናቃይ እንደሚገኝ መረጃዎች ይጠቁማሉ::

ከመተማ ወደ ወደ አዲስ አበባ የሚያመጡ መንገዶች እዚያው መተማ ላይ በመዘጋታቸው የነዳጅ ጫኝ ቦቴዎች ለቀናት መቆማቸውን የሚገልጹት ምንጮች ይህ በዚህ ከቀጠለ በሃገሪቱ የነዳጅ እጥረት ሊያስከትል እንደሚችል ተሰግቷል::  እንዲሁም ይህ ዜና እስከተጠናቀረበት ጊዜ ድረስ ከጎንደር ወደ አርማጭኾ የሚወስደው ምስራቅ ደንቢያ በሕወሓት የሚታዘዘው የቅማንት ኮሚቴ ቡድን ቁጥራቸው ያልታወቀ ሰዎችን አፍነው በመውሰዳቸው የተነሳ ትንስፖርት ቆሟል:: ውጥረት ነግሷል ያሉት የዜና ምንጮቻችን የጎንደር ጉዳይ አሳሳቢ ሆኗል ብለዋል::

Yh be endif endive

አጀንዳ ሰጭና ተቀባይ በመሆን ወንድማማች ህዝቦችን ለማጋጨትና ጎንደርን የጦርነት ቀጠና ለማድረግ እየሰሩ ያሉ ኃይሎች ከድርጊታቸው ሊቆጠቡ እንደሚገባ የአማራ ክልል አሳሰበ:: የክልሉ የመንግስት ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ጽ/ቤት ኃላፊ ዋና ዳይሬክተር አቶ አሰማኸኝ አስረስ በጉዳዩ ዙሪያ ዛሬ መግለጫ ሰጥተዋል፡፡ በመግለጫቸውም ጥር 24/2011 ዓ /ም የመከላከያ ሰራዊት 24ኛ ክፍለ ጦር ለቆ በ33ኛ ክፍለጦር ለመተካት እንቅስቃሴ በመጀመረበት ወቅት ግጭት መቀስቀሱን ያስታወቁት አቶ አሰማኸኝ እስካሁን በአካባቢው በተፈጠረው ግጭት ከ39000 በላይ ዜጎች ተፈናቅለዋል፡፡

አጀንዳ ሰጭና ተቀባይ በመሆን ወንድማማች ህዝቦችን ለማጋጨትና ጎንደርን የጦርነት ቀጠና ለማድረግ እየሰሩ ያሉ አካላት ከድርጊታቸው ሊቆጠቡ ይገባል ብለዋል፡፡

በአሁኑ ሰዓት ከጎንደር አርማጭሆ የትራንስፖርት አገልግሎት ሙሉ በሙሉ ተቋርጧል፤ ሁለት ሰዎችም በተደራጁ የጥፋት ሃይሎች ታፍነው ተወስደዋል ያሉት ዋና ዳይሬክተሩ የጥፋት ሃይሎች ከህብረተሰቡ ጋር ተቀላቅለው ያሉ በመሆናቸው ህዝቡ ጥፋተኞችን ለመንግስት አጋልጦ በመስጠት አስፈላጊውን ድጋፍ እንዲያደርግ ጠይቀዋል፡፡

ተጨማሪ ያንብቡ:  ኢህአዴግ በግዳጅ ገንዘብ አምጡ በማለት ነጋዴውን እያናደደ ነው

በሌላ ዜና ዛሬ ጠዋት ከንደር ወደ ሳንጃ ለመስታወት ስራ እየሄደ ያለን የ18 ዓመት ወጣት ይኸው በሕወሓት የሚታዘዘው ቡድን  ግንድ መጣያ ላይ በጥይት እንደገደለው የአካባቢው ነዋሪዎች ገለጹ:: አማኑኤል ባንተ የሚባለው ይኸው ወጣት ለሥራ ከቤቱ ወጥቶ በሚሄድበት ወቅት ግንባሩ ላይ በጥይት መተው እንደገደሉት ነው የሰማነው::

1 Comment

  1. እውነትም ጎንደር የአጋነንት አገር መድማት አለባት :: ነገር ለሰሪው እሾህ ላጣሪው ነው ምሳሌው በጎረቤት ጭስ ስታጨሱ በቤታቹ ነበልባል አመጣቹ ገና ምኑ አይታቹ ነው ምድረ የአህያ ዘር::

Comments are closed.

Share