በአማራ ክልል ማዕከላዊ ጎንደር ዞን ጭልጋ ወረዳ አንዳንድ ቀበሌዎች በተቀሰቀሰ ግጭት የሰዉ ህይወት መጥፋቱንና ንብረት መውደሙ ተሰማ::
https://www.youtube.com/watch?v=QY21a9JgtmU&t=58s
በተለይ ጭልጋ ወረዳ በ”አማኑኤል ቀን ወጣ’ ቀበሌ አማኑኤል በተባለ ቦታ እና በሌሎችም አጎራባች ቀበሌዎች በቅማንት ኮሚቴ ስም የታጠቁ ሀይሎች በርካታ ቤቶችን ማቃጠላቸው ተሰመቷል:: ቡድኑ በተመሳሳይ በአይምባ ሰቀልት አካባቢም በንፁሀን ላይ በፈፀመው ቃጠሎ የብዙዎች ሀብት የወደመ ሲሆን በርካታ ሰዎች ቤት ንብረታቸውን ጥለው ተሰደዋል::
የዞኑ ፖሊስ መምሪያ ሀላፊ ኮማንደር እንየዉ ዘዉዴ በግጭቱ የጠፋዉን የሰዉ ህይወትና ንብረት ልክ ግን ለመናገር ባይደርፍሩም ግጭቱ አሁንም ድረስ አለመብረዱን ኮማንደሩ አረጋግጠዋል::
በዚህ አካባቢ በተነሳው ከፍተኛ ግጭት የመተማ ከተማን ከጎንደርና ከባህርዳር የሚያገናኘዉ መንገድ በመዘጋቱ ነዳጅ የጫኑ ቦቴዎች ሳይቀሩ መቆማቸውን የአካባቢው ኔዋሪዎች ይናገራሉ::
በሌላ በኩል ቤደምቢያ ወረዳ ከፍተኛ በቅማንትና አማራ በሚል በተከፋፈሉ ወገኖች ግጭት መኖሩ ታውቋል:: በዚህም ግጭት በሰው ሕይዎትና በንብረት ላይ ጉዳት መድረሱን ምንጮች የገለጹ ሲሆን የአማራ ክልል የመንግሥት ኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች ጽሕፈት ቤት ጉዳዩን አስመልክቶ መግለጫ ሰጥቷል፡፡
የመንግሥት ኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች ጽሕፈት ቤት ዋና ዳይሬክተሩ አቶ አሰማኸኝ አስረስ በደምቢያ ወረዳ እየተስተዋለ ባለው አለመረጋጋት በሰው ሕይዎትና በንብረት ላይ ጉዳት ደርሷል ይህንንም የአማራ ክልል መንግሥት ያወግዛል ብለዋል:: “ግጭቱ ሁለቱንም ሕዝቦች የማይወክል መሆኑ በተጨባጭ ማሥረጃ ተረጋግጧል:: ከጉዳዩ ጋር ቀጥተኛ ግንኙነት አላቸው በሚል የተያዙ ተጠርጣሪዎች አሉ;; የእሥር ማዘዣ የወጣባቸውአሉም” ያሉት አቶ አሰማኸኝ ግጭቱ ዳግም ያገረሸበት ምክንያት አካባቢውን ለማረጋጋት ተሰማርቶ የነበረው 24ኛ ክፍለ ጦር ወጥቶ 33ኛ ክፍለ ጦር ለግዳጅ ሊገባ እያለ ጥር 24/2011 ዓ.ም መንግሥት ‹‹የተደራጁ ቡድኖች›› ያላቸው አካላት በጸጥታ አካላት ላይ ጥቃት በማድረሳቸው ነው፡፡
ራሱን የቅማንት ኮሚቴ ነኝ ዕያለ የሚጠራው ቡድን አብዛኞቹ ቅማንቶች አለመሆናቸውና በ እነርሱ ስም የሚዋጋው ሕወሓት መሆኑ በተደጋጋሚ ሲነገር ቆይቷል:: ሕወሓት ጎንደርን ለ27 ዓመታት በኢኮኖሚው አድቅቋታል አሁን ደግሞ በጦርነትና እርስ በ እርስ ግጭት ሊያጠፋት ቆርጦ ተነስቷል የሚሉ አስተያየት ሰጪዎች በርካታ ናቸው::