አዳማ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ የመማር ማስተማር ሂደቱ..

በአዳማ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ የመማር ማስተማር ሂደቱ ዘንድሮ ለሁለተኛ ጊዜ መቋረጡንና ላለፉት ዘጠኝ ቀናትም በግልጽ ባልታወቀ ምክንያት ተማሪዎች ወደክፍል አለመግባታቸውን ዩኒቨርሲቲው ገለጸ፡፡

https://www.youtube.com/watch?v=I4V8VygwOuk&t=204s

የዩኒቨርሲቲው ማኔጅመንት በሁለት ቀናት ውስጥ በሚደርሰው ውሳኔ መሰረትም ችግሩን ለይቶ ተገቢውን እርምጃ ለመውሰድና ተማሪዎችም ትምህርታቸውን እንዲቀጥሉ የሚደረግበት ሂደት እንደሚፈጠርም አስታውቋል፡፡

በአዳማ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ትምህርት የተቋረጠው በቅርቡ በዩኒቨርሲቲው ሦስት ልጆች ባልታወቀ ሁኔታ ሕይወታቸው አልፎ በመገኘቱ ምክንያት እንደሆነ ዘ-ሐበሻ ከዚህ ቀደም ዘግቦ ነበር::

ተጨማሪ ያንብቡ:  ሸንጎ በሲያትል ዋሽንግተን የተሳካ ህዝባዊ ስብሰባ አካሄደ
Share